የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቀረቡ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ትላንት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ The National Endowment For Democracy የተባለው ዓለምአቀፍ የጥናት ተቋም ባመቻቸላቸው መድረክ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

 

ዶክተር ነጋሦ ባቀረቡት በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ያተኮሩት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር “ሕገ-መንግሥቱ የሁሉንም ብሄረሰቦች ፍላጎት ማንፀባረቅ ያስፈልገዋል” በሚለው ላይ ነው።

 

በኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት ስለሚካሄደው ምርጫ፥ በሀገሪቱ ስለታየው የረዝም ጊዜ መረጋጋትና ልማትም በጽሁፋቸው ዳሰዋል።

 

ሰሎሞን ክፍሌ በስፍራው ነበር። ተከታዩን አዘጋጅቷል።