የዞን ሰጠኝ አምደኞች ተሸለሙ

Zone_9 bloggers
ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «CPJ-በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ» ኢትዮጵያዉያኑን የዞን ዘጠኝ አምደ-መረብ አምደኞች «ብሎገርስ» ሸለመ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ወንጀል ከሷቸዉ ታስረዉ የነበሩትና አሁንም እንደታሰሩ ያሉት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ባልደረቦችን የሸለመዉ ለፕሬስ ነፃነት በመታገላቸዉ ነዉ። በሲፒጄ ዘገባ መሠረት አምደኞቹ የታሰሩና የተከሰሱት መንግሥትን የሚተች ዘገባ በማቅረባቸዉ ነዉ። ስለ ሽልማቱ የዋሽግተኑን ወኪላችን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ አነጋግሬዉ ነበር። listen