ሊቆም የሚገባው ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የተጠናወተው ፖለቲካ ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
Minilik Salsawi መልካም እና ጽኑ ታጋዮች እንደተጠበቁ ሆነው በስለናል የትግል ልምድ አለን ከሚሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እዚህ ግቡ የማይባሉ ገደል ማሚቱዎች ድረስ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቦርቅቀው ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከኛ በላይ ላሳር የሚሉ እንጭጭ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጥቂቶች ሰፊዉን ሜዳ በተግባር ኣልባ ፕሮፓጋንዳ ብቻ አጣበዉት ሌላው እጁን አጣጥፎ ሲያይ መመልከትም ግርምትን ይፈጥራል::የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰከረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህን ያህል ተተራምሷል ለማለት ግን አያስደፍርም::የሕዝብ ማንዴት ያሌላቸው ፖለቲከኞች ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አሊያም በሕዝብ የተቀቡ አድርገው ሲያቀርቡም የፖለቲካ እብደቶች እየገነኑ ይመጣሉ::በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካ ጥላቻ ምቀኝነት ግለኝነት ቅናት የመሳሰሉት ለውጡ በእንብርክክ እያስኬዱ የሚገኙ ሲሆን ሂደቶን ሁሉ ባለህበት እርገጥ ሆነዋል:: እንደኔ እምነት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የጎሳ እና ከፋፋይ ፖለቲካ የሚከተለ እንደ ሕወሓት ያሉ ድርጅቶች ያነገቡት አርማ ነው::
በየሄድንበት በጎራ ተከፍሎ ጥላቻ ሲሰበክ በያረፍንበት ለለውጥ ሰራን የሚሉ ሰዎች ግለሰቦችን አሊያም የፖለቲካ መሪዎችን በጥቅሉ የለውጥ ሃይሎችን ሲያብጠለጥሉ ማየት ያማል::ይህ በግለሰብ ደረጃ ተንከባሉ የፖለቲካ ሰዎችን አሊያም የለውጥ ሃይሎችን መዘርጠጥ ይሁን ማብጠልጠል የወረደ ፖለቲካ ነው::ያዉም ክፉ የፖለቲካ ሃሜት::ተሽሎ የተገኘ የዳበረ ሃሳብ ባልቤት የሆነ የፖለቲካ ሰው ከተገኘ የደጋፊዎቹን ያህል የፖለቲካ ምቀኞቹም ይበረክቱበታል::በፖለቲካው አለም ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እየተቻለ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ግን የፖለቲካ ሰዎችን ማብጠልጠል ከተቻለ ማስመታት ካልተቻለ በወረደ ቋንቋ ስማቸውን ማጠልሸት ስራ ሆኖ ተይዟል::አለም ከዘር ከሃይማኖት ከቀለም እና የተለያዩ ልዩነቶች ተገላግሎ በአንድነት ስር ለመጠለል በሚያደርገው የቴክኖሎጂ እድገት ሩጫ ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን በጎሳ ታጥሮ በግፍ ተከቦ እርስ በእርሱ ሲጠባጠብ ይስተዋላል::
ከገዢው ፓርቲ ጀምሮ የለውጥ ሃይል ነን እስከሚሉ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የክፋት የጥላቻ የምቀኝነት የቅናት እና ግለኝነት ፖለቲካ ሲያራምዱ በገሃድ እናያለን::ድርጅቶቻችንን ደግፈን ለሕዝብ እየሰራን ነን ከሚሉ እስከ ድርጅታቸው እስከከዱ ሰዎች ድረስ በምቀኝነት እና ቅናት ተሞልተው የፖለቲካ ሰዎችን ሲያብጠለጥሉ ሲሰድቡ የለውጥ ሃይሎችን ሲያንቋሽሹ ውለው ያድራሉ::ይህ ደግሞ አውቀናል ተምረናል ከሚሉ ጀምሮ እስከ ገደል ማሚቱዎቻቸው ድረስ እየታዘብናቸው ነው::ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት ምንም እውቀት ከሌለው የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ከድርጅቶች እንከሚታከከው ድረስ ፖለቲካውን/የለውጥ ትግሉን ሳያውቁት በተላላኪነት ብቻ ጥልአሸት ሲቀቡት ይስተዋላል::
የአንድ ድርጅት አባላት የሆኑ ወጥ ካድሬዎች ለኢትዮጵያ እነሱ ብቻ የተፈጠሩ አድርግ ሲያዩ ሌላውን እንደ እንጀራ ልጅ አድርገው ሲገፉ ማየት ያማል::ይህ ብቻ አይደለም ስህተታቸውን ስትነግራቸው የሚያብጠለጥሉ ካለስም ስም ሰጥተው ጥላሸት የሚቀቡ በገዢ መደብ በርካቶች ቢሆኑም በለውጥ ሃይሉም ውስጥ ተሰግስገው እያፏጩ ይገኛል::አሁን አሁን ደሞ የለውጥ ሃይል ነን በሚሉ ከሃዲዎች እና የገደል ማሚቱኦች እንዲሁም ስሜት እና ፕሮፓጋንዳ በተደበላለቀባቸው ሰዎች ላይ የፖለቲካ ክፋት ምቀኝነት እና ቅናት ብሶ ተገኝቷል ይህ ደግሞ ለለውጥ በሚድረገው ሂደት ላይ ችግር እና አለመተማመን ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው::ጊዜው የለውጥ ነው:;ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል እስካልን ድረስ የሕወሓት የፖለቲካ ውጤቶች የሆኑት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የተጠናወተው ፖለቲካ ሊቆም ይገባል:: #ምንሊክሳልሳዊ
ይህን የፈጠረው የጎሣ ፌድራሊዝም መርህ ነው።
ስለምን እንደምታወራ ግልፅ አይደለም ። ምንድነው እንዲህ አይነት የዞረበት ፅሁፍ ማቅረብ ? ራስህ የፃፍከውን እንኳን የተረዳሀው አትመስልም
::በፖለቲካው
አለም ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እየተቻለ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ግን
የፖለቲካ ሰዎችን ማብጠልጠል ከተቻለ ማስመታት ካልተቻለ በወረደ
ቋንቋ ስማቸውን ማጠልሸት ስራ ሆኖ ተይዟል::
Minilik
ante yemitfelgewen bicha endinastegaba tifelgaleh ?
hulum yerasu aquwan alew eko!!!
and ye Hager mere aquwanmun enji Dr prof mehonu le and Hizb min yrteqnewal ?
bemeseretu le Hager meqorqor yegid Botelekegna mehon alebin ???
hulum hasabub yemestet mebt alew !!!
degm0s man min serana new miqegninetu ??
be propaganda Hager aygenebam !!!
be,propaganda Hager netsa atwetam !!
serto megnegnet new ! man beman yeqenal? min teserana ?
4 kilo egbat filmeya kalhone !yetesera sera yelem !!!
Kenant eko new zeregnenet kefat mekegnet yetemarnew ahun kenante beletn lolol kikiki minilik salsawi yeoromo yetgray yedebub yesumalew bedagmawi minilik yefesese yentsuhan dem zarem lebekel yechohal!!!!antedemo salsawi dem afsash nah?
Are u trying to preach about unity and diversity while you have a supporters of the genocide of the evel minilik who couse the blood shade of the innocent Oromo tigray somalia south nation …welayta….by appointing your self as a 3rd minilik to continue the blood shade.the shaded blood still crying for justices and revenge….
Are u trying to preach about unity and diversity while you are a supporter of the genocide committed by minilik who couse the blood shade of the innocent Oromo tigray somalia south nation …welayta….by appointing your self as a 3rd minilik to continue the blood shade.the shaded blood still crying for justices and revenge…
gonder@
be Ethiopia tarik ,,ende weyane Dem yafesese ale ?
enante Tut teqorete aluchu
Bilit qorto yemechefir manew ?
rasehen eweq !!
Sarah…