ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ መሆኑን ገለጸ::

• ‹‹ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነውን ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን››

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር – ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መስከረም 27/2008 ዓ.ም በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው ‹‹ረሃቡ የገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት ነው!›› በሚል በሰጠው መግለጫ ‹‹ገዥው ፓርቲ ችግር ቢከሰት እንኳ በአደጋ ጊዜ ለዜጎች የሚበቃ እርዳታ አቀርባለሁ ሲል የነበረ ቢሆንም ለወገኖቻችን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡›› ሲል ወቅሷል፡፡ ‹‹ለዜጎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዳይደርሱላቸው የተፈጠረው ረሃብ የራሱ የፖሊሲ ውድቀት መሆኑን የሚያውቀው ስርዓቱ የዜጎቻችን ስቃይና መከራ ሲሸፋፍን እንደቆየና ከአቅሙ በላይ ሲሆን ችግሩ እንደተከሰተ ቢገልፅም ለዜጎች ተገቢውን እርዳታ በሚያስገኝ መልኩ እርምጃ እየወሰደ አይደለም›› ብሏል መግለጫው፡፡ ለተከሰተው የረሃብ አደጋ ተገቢው ትኩረት መነፈጉም ገዥው ፓርቲ እመራዋለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ ቢስነቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ረሃቡ፣ ርዛቱ፣ ድህነቱ፣ ስደቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ የኑሮ ውድነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎችን በብርቱ እየተፈታተኑ በሚገኝበት ወቅት ገዥው ፓርቲና በስሩ ያሉ ድርጅቶች ተመሰረትንበት የሚሉትን ጊዜ ለወራት በቅንጦት በማክበር በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ጉሮሮ ነጥቆ ድግስ ሲደግስና አሸሸ ገዳሜ ሲል በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡›› ብሏል፡፡ ለተከሰተው ረሃብ ኢህአዴግ ለይስሙላ ቆሜለታለሁ የሚለውን አርሶ አደርና አርብቶ አደርን ህይወት ለማሻሻል የረባ ስራ እንዳልሰራ አረጋግጧል ያለው መግለጫው ግብርናው ኢኮኖሚውን ይመራል ቢልም እስካሁን ግን በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የረሃብ ሰለባ እንደሆነ መቀጠሉን ገልፆአል፡፡ መሬት የመንግስት ነው በሚል ሽፋን አርሶ አደሩን ከቀየው እያፈናቀለ ለስርዓቱና ደጋፊዎችና ለባዕዳን መሬትን እየሸጠ አርሶ አደሩን ለረሃብ ተጋላጭ አድርጎታል ሲልም ለርሃቡ ምክንያት የኢህአዴግን የፖሊሱ ውድቀት እንደሆነ ገልፆአል፡፡

ገዥው ፓርቲ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ችግሩ ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያስረዳ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ በረሃብ ለተጠቁት ዜጎች መፍትሄ እንዲፈለግም ጠይቋል፡፡ ስርዓቱ ደካማና ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ የገለፀው ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያውያንና የዓለም ማህረሰብ ማህበረሰቡ ከተጎጅዎቹ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያውያን መከራ የመነጨው ከገዥው ፓርቲ የተሳሳተ ፖሊሲ፣ የአፈፃፀም ብቃት ችግርና ለኢትዮጵያውያንም ባለው ግድ የለሽነት በመሆኑ ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነ ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን›› ሲልም ለህዝብ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ፓርቲው ረሃቡ በተከሰተባቸው አካባቢዎች መረጃ በማሰባሰብና በማጣራት ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ገልፆል፡፡

3 Comments on “ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ መሆኑን ገለጸ::”

  1. Please people have feed up of your stinky
    politics. we learned how g7 killed the peoples
    sprit for struggle by being sell out Mercenaries for the
    most notorious , dictator and # one enemy of Ethiopia Isayas
    Afeworki. After collecting millions of Dollars from the
    poor diaspora now their handful members have melted away.

  2. እውነት ነው!!!
    **********************************************
    ገበሬው በመልካሙ ግዜ ለተቀማጭ እና ፍጆታ ብሎ በግዳጅ አውጥቶ
    የሸጠለትን እህል እንኳን በልመና ማግኘት አቅቶታል ይህ ነው ብድሩ? የገዛ
    እህሉን በፖርላማ ፀድቆ በካቻምናው በልግ እንዲሸጥበት ተደርጓል እሥቲ ታዘቡ
    የአደጋ ዝግጁነትና ተጠሪ ብሎ ሢያንባርቁ ኤክሥቴሽን መርሀግብር…ወዘተ
    ተብሎ የወገን ሀብት ሢመዘበር አሁን ከየት አምጥተው ይተኩት ይህ ተትረፈረፈ
    ያሉን እህል እንኳ የእህል ጎተራ በሌለበት ሀገር በበቂ እና ዘመናዊ በሆነ መንገድ
    ባለማዘጋጀታቸው ጭምር ነቀዝ በላው ብለው የማሻሻጥ ድለላውሥጥ ገብተው
    ባዶ አረጉት ይህ ነው ግብርናው ኢንደሥትሪውን መራው እያሉ የሚያሽሟጥጡት
    እንኳን እሡን ገበሬው ራሡን ቤተሠቡን በደናውም ግዜ ማትረፍ አልቻለም።
    GTP2 ግብርናው ባቡርን እየመራው ነው እንዳይሉን ብቻ….

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*