በድርቁ ጉዳይ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ምን ነካቸው…?

 

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በድርቁ ጉዳይ መግለጫ ይሁን የመከላከል ስራ ሳይሰራ ቆይተዋል።ትናንት 07/02/2008 ዓ/ም በድርቁ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሳቸው ወረዳዎች ኣንዱ ወደ ሆነው ኣፅቢ ወንበርታ ደርሰው ጉዳቱ ተመልክተዋል።ኣፅቢ ወንበርታ በርካታ እስሳት ሙተዋል፣ የሰው ሂወትም ኣልፎበታል።

በርሃቡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሳቸውና ሂወታቸው በኣጣብቂኝ ውስጥ የገቡ በርካታ ሰዎች፣ በርሃብ ምክንያት ትምህርታቸው ያቋረጡ ህፃናት፣ ለስደትና ለልመና የተጋለጡ ወገኖች በወረዳዋ አስቸኳይ የምግብ ኣቅርቦት የሚፈልጉ ወገኖች በብዛት ኣይተዋል።

ይሄ ካዩ በሗላ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ለትግራይ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በጣም ኣስገራሚና ራሱን በራሱ የሚምታታነበር። የድርቁ ክብደት ለመደበቅ ያካሄዱት ጥረትም ሳይሳካላቸው ቀርቶ በተገላቢጦሽ ሓቁ ኣምልጦ ዝርግፍ ብሎባቸዋል።

ኣቶ ኣባይ ወልዱ “……በኣሁኑ ሰዓት በክልላችን 900 ሺ ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል……” ብለው ገለፁ።

ኣቶ ኣባይ በድርቁ የተጠቁ ኣከባቢዎች ሲዘረዝሩ “…የተወሰኑ ቀበሌዎች …” ብለው ኣሳንስው ሲያበቁ በድርቅ የተጠቁ ዞኖች ሲገልፁ ደግሞ ያለ ሰሜን ምዕራብ ሁሉንም ዞኖች በተጎጂነት ጠቅሰዋል።

እስቲ “… የተወሰኑ ቀበሌዎች…” ብለው የገለፁት ሓሳባቹውና ” 900ሺ ኣስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል ” ያሉበት ኣገላለፅ ኣነፃፅሩልኝ።

ኣቶ ኣባይ ወልዱ ድርቁ ኣቃልለውና እንደተቆጣጠሩት ለመግለፅ ቢሞክሩም ሃቅ ሙልጭልጭ እያለች ከኣፋቸው ስታመልጥባቸው ኣይተናል።

“…በረሃብ የሚሞት ሰው ኣይኖርም…” ብለውናል።

እስካሁን የሞቱት ሰዎች ሪፖርት ከህዝቡ እየተላከላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።
እነዛ በረሃብ የሞቱ ሰዎችስ ምን ብለን እንጥራቸው?

እስካሁን “የማዳበርያ እዳ፣ የደደቢት ብድር ያልከፈሉ፤ ልጆቻቸው የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ፣ ከኣንድ በላይ ከብቶች ያላቸው ዜጎች እርዳታ ኣይሰጡም” ተብለው መታገዳቸውና የረሃብ ብሎም የሞት ሰለባ እንዲሆኑ እያደረገ ያለው የወረዳና የቀበሌ መዋቅር የእርስዎ ትእዛዝ የለበትም ማለት ነው…? ወይስ የተለመደው የመንግስትዎ የፈጠራ ሪፖርት ኣካል ነው ??

ኣቶ ኣባይ የኣፅቢ ህዝብ ሲያነጋግሩት “…ራበን፣ ተቸገርን፣ ልጆቻችን በረሃብ ምክንያት ትምህርት ቤት መሄድ ኣቋረጡ፣ ስደት በጣም በዝቷል፣ እንስሶቻችን ኣለቁ፣ ወገኖቻችን ማጣት ጀምረናል፣ በሞት ኣፋፍ ያሉ ወገኖቻችንም ቤታቸው ይቁጠረው፣ እኛ ኣስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገናል…” ኣላሎትም……!

ስለዚ ህዝቡን እንድታደምጡት በጉባኤ ኣሸንፈው እንዲወጡ በረዳዎት የ1 ለ 5 የኔትወርክ ኣደረጃጀት ይዤቷለው ።

‪#‎ህዝብና_ንዓንግል‬…!

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO…!

Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.