የዘንድሮው ምርጫ በታሪክ ማህደር
የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ተጠናቆ ሙሉ ውጤቱ ይፋ ከሆነ እነሆ ሳምንታት አለፉ። የምርጫው ሂደት ያስነሳው የፖለቲካ ትኩሳትና አቧራ በርዶ ፤ የምርጫው ተዋናዮች ግርግርና አስረሽ ምቺው ሰክኖ ምርጫ 2010 ከሰበር ዜናነት ወደ ታሪክ ማህደርነት የሚተላለፍበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የዚህን ምርጫ ታሪካዊ አንድምታና በታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚኖረው ስፍራ በታሪክና ሶሻል ሳይንስ ተመራማሪዎች ወደፊት የሚለካ ሲሆን ይህ ጽሁፍ የዚህን ምርጫ ሁለት ለየት ያሉ ባህርያት ላይ ትኩረት በመስጠት ለመቃኝትና ለመዳሰስ ይሞክራል። በመጀመሪያ ይህን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ የሚያደርገው ለምርጫ የወጣው ህዝብ ብዛት (turn out) ሲሆን ከተመዘገበው 36.8 ሚሊየን ህዝብ 34.8 ሚሊየን ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በምርጫው ተሳትፏል። በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁ ቀጥተኛና ነጻ የሆነ ህዝባዊ ተሳትፎ የታየበት የፖለቲካ ክስተት ያደርገዋል። ይህን መሰል ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የታየበት ምርጫ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በብዙ አገሮች ከሚታዩት የህዝብ የምርጫ ተሳትፎዎች ጋር ሲንጻጸር ከፍተኛ አሃዝ ከተመዘገበባቸው አንዱ የሚያደርገው ሲሆን ይህም የምርጫውን የዲምክራሲያዊ መሰረት ያሰፋ፤ ፉክክራዊ ባህርይውን ያጎለበትና ለተአማኒነቱንም ዋስትና እንዲኖረው ካደረጉት ምክንያቶች እንደ አንዱ ሆኖ ሊጠቅስ የሚያስችል ነው። ከሁሉ በላይ ግን ለምርጫ ከወጣው የህዝብ ቁጥር አሃዝ ጀርባ ያለው ዋናው ቁምነገርና ይህንን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በይዘት የተለየ የሚያደርገው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት መብቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋትና በጥልቀት እየተረዳ መምጣቱ የተንጸባረቀበት፤ ለዲሞክራሲ ስርአት ያለው ፍላጎትና ቁርጠኝነት እየሰፋና እየጎለበት መምጣቱን በግብር ያረጋገጠበት ምርጫ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫን የማይገሰስና የማይቀለበስ ቋሚ ባህሉ […]