የአንድነት ፓርቲ ውዝግብ| ምርጫ ቦርድ ለነትግስቱ አወሉ ቡድን የፈረደበት ሙሉ ቃል

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ /አንድነት/ በተመለከተ የፓርቲዉ የቦርድ ዕዉቅና ያለዉ መተዳደሪያ ደንብ የ2004 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ቦርዱ የrፓርቲዉን እንቅስቃሴ ከዚሁ የቦርዱ ዕዉቅና ካለዉ ደንብ አንጻር ሲመረምር እንደቆየና አሁንም ከዚያዉ አኳያ የመረመረ ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ከፓርቲው ውስጠ ደንብ መግቢያ ስንነሳ፡- መግቢያ አንዱና ዋነኛዉ የህግ አዉጭዉን አካል ሃሳብ የምንረዳበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ መግቢያ መረዳት እንደሚቻለዉ መተዳደሪያ ደንቡ የፓርቲዉ አመራሮችና አባላት የሚመሩበትና የሚገዙበት እንደሆነ፣ በፓርቲዉ አደረጃጀት መሰረት የተለያዩ አካላት ጤናማና ዴሞክራሰያዊ የሥራ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ የሚያስችል፣ የስራና ኃላፊነት ክፍፍል የሚፈጥር እና ግልጸኝነትና የተጠያቂነት መርህ የሚፈጥር እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ይሄንን የህግ አዉጭዉን ሃሳብ ተከትሎ ስራዎች ሲተገበሩ አይታዩም፡፡ ደንብ የሚያወጣዉ የፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ ሌላ አካል ቦርዱን ጨምሮ ማንም ሊያወጣላቸዉ አይችልም፣ አይገባምም፡፡ ነገር ግን ደንብ ከወጣ እና ለቦርዱ ቀርቦ ዕዉቅና ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲዉ አመራርም ሆነ አባላት ለደንቡ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ ቦርዱም በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. እና በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ ዓ.ም. መሠረት ይሄንን ደንብ የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን በኩል የተፈጸሙ ዋና ዋና የህግ ጥሰቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡ 1ኛ. የፓርቲዉ ፕሬዝዴንት ጨምሮ ኃላፊዎች አመራረጥ በተመለከተ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 572/2000 አንቀጽ 8/2/ረ/ እና በፓርቲዉ ደንብ አንቀጽ 13.3.1 መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ መመረጥ […]