በሕግ የተሰጠውን መብት በፍርድ ቤት የተገፈፈው ኩባንያ
(ኃይለሚካኤል ዘስላሴ) በዓለም ያለት የተለያዩ የሕግ ሥርዓቶች ከሚሰማሙባቸው የሕግ ጽንስ ሐሳቦች አንዱ የሕጋዊ ሰውነት ጽንስ ሐሳብ ነው፡፡ በዚህ ጽንስ ሐሳብ መሠረት ከተፈጥሮ ሰው በተጨማሪ እንደተፈጥሮ ሰው የሚቆጠር ወይም ሰው የሆነ አካል አለ፡፡ በዚህም መሠረት ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ ማለት ነው፡፡ አንደኛው ሰው የተፈጥሮ ወይም ግለ ሰብ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ደግሞ በሕግ የሰውነት መብት (ግዴታም ጭምር) ያለው ወይም የተሰጠው አካል ማለትም ማኅበር፣ የንግድ ማሕበር ወይም ድርጅት ነው፡፡ በመሠረቱ ማነኛውም ሰው የተፈጥሮም ይሁን በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ወይም ያለው አካል የመብትና የግዴታ ባለቤት ነው፡፡ በዚህም ውል መዋዋል፣ የነብረት ባለቤት መሆን፣ መክሰስና መከሰስ ይችላል፡፡ ከቤተሰብ ሕጎች እና ከአንዳንድ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች በስተቀር የየአገሩ ሕጎች በተፈጥሮ ሰውና በሕግ የሰውነት መብት ያለው አካል በእኩልነት ተፈጻሚነት አላቸው፡፡ የተፈጥሮ ሰው የመብትና ግዴታ ባለቤት የሚሆነው እና በሕግ ኃላፊነት የሚኖረው በተፈጥሮ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ግዑዝ የሆኑ አካላት ማለትም ማሕበራት የንግድ ማኅበራት እንዲሁም ድርጅቶች እንደ ተፈጥሮ ሰው የሚቆጠሩትና በሕግ የሰውነት መብት ይጣቸዋል የሚል ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ንደፈ-ሐሳቦች ተቀምሯል፡፡ እነዚህ በርካታ ንድፈ-ሐሳቦች በሁለት ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያወ ምናባዊ ወይም ሕግ ወለድ ንድፈ ሐሳብ (fiction theory) የሚባለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እርግጠኛ ንድፈ ሀሳብ (Real theory) በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ እነዚህ ንደፈ ሃሳቦች ጥልቅ መሠረት እና ትንታኔ ያላቸውና አመሠራረታቸውና ዕድገታቸው ሰፊ እና ከመንስት አመሠራረት ጋር የተያያዘ ቢሆንም ለአጠቃላይ ግንዛቤ ይረዳል በሚል በሁለቱም ንድፈ […]