ጣታችን ወደ ራሳችን እንቀስር! – ደሀን እናቱም ኣትወደዉም
የኢኮኖሚ ችግር ሲፈጠር ስደተኛዉን ኢላማ ኣድርጎ ጥቃት መሰንዘር በደቡብ ኣፍሪካ ብቻ የታየ ችግር ኣይደለም። ግሪክ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ሩስያ እና በብዙ ኣገሮች የታየ የተለመደ ክስተት ነው። ህንዳውያን በግሪክ ጎዳና ለመንቀሳቀስ ኣዳጋች እየሆነባቸው እንደሆነ ሁሉ ሞስኮም ኣሁን የውጭ ዜጋ እንደልቡ እማይንቀሳቀስባት ከተማ ሁናለች፤ ለምን ቢባል የኢኮኖሚ ችግር።በነዚህ ኣገሮች ከፈተኛ የፀረ ስደተኛ ጥቃትም እሚፈፀምባቸው ኣገሮች እየሆኑ ነው:: ይሄ ነገር ከዘር እና ከጥቁረት እያገናኙ ደቡብ ኣፍሪካውያንን የቀኝ ገዢዎች ንድፈ ሃሳቦች እየተጠቀሙ “ድሮስ ጥቁር….ለነፃነት ኣቅም ያልደረስ እንስሳ” ምናምን እያሉ የትምክህት ቃል መሰንዘር የጉዳዩን ትክክለኛ ገፅታ ኣለመረዳትን ነው እሚያሳየው። የኢኮኖሚ ችግር ወደ ፖለቲካዊና የፀጥታ ችግር እንደሚቀየር ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው። በሩዋንዳም በሌሎች ኣገራትም የታየው ይህ ነው። እንዲህ ኣይነት ሁኔታ ለሰነፍ ፖለቲከኞች ጥሩ ኣጋጣሚ ይፍጥራል፤ የሰነፍ ፖለቲካ ደግሞ ቀላል ግን ኣውዳሚ ስለሆነ ዉጤቱ ኣሁን ደቡብ ኣፍሪካ ላይ እያየን ያለነው ኣይነት እልቂት ያስከትላል።ኣንዱን በማስወገድ “መፍትሄ” ለመሻት መጣር ነው የሰነፍ ፖለቲካ ማለት።ለዚህ መዋቅራዊ መደላድል እሚፈጥረው ግን የኢኮኖሚ ችግር ነው። ሁቱዎች ቱትሲዎች ላይ ገጀራቸውን ከማሳረፋቸው በፊት የዋጋ ንረት እና ስራ ኣጥነት ሂወታቸው ላይ ገጀራዉን ኣሳርፎ ነበር። ይህ ቀቢፀ ተስፋነት ሰለፍ ፖለቲከኞች ተመቻቸው እና ዘርን ለማጥፋት ተጠቀሙበት። ደቡብ ኣፍሪካ ላይ እየተፈፀመ ያለ ነገርም ከጄኔቲክ ሳይሆን ከኢኮኖምያዊ ሁኔታ መመሰቃቀል እሚመነጭ ነገር ነው። የደቡብ ኣፍሪካ ለየት እሚያደርገው የኣፓርታይድ ስርኣት በፖለቲካው ረገድ “ሲገረሰስ” የኢኮኖሚው ሁናቴ በነጮች እንደተያዘ እንዲቀጥል መፈቀዱ ነው። ማንዴላ ከዚ ዉጪ ኣማራጭ […]