የምርጫ ክርክር – ካለፈው በመማር ሊታረም የሚገባው
ነብሱን ይማረውና ነውጠኛው ቅንጅት በ1997ዓ.ም የማይናቅ የህዝብ ድምጽና ድጋፍ ያገኘው ከኢህአዴግ የተሻለ ብቃት ስለነበረው ወይም ያቀረበው የፖሊሲ አማራጭ ሳቢ ስለነበረ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ወይም የህዝባችን ኑሮ ሊቀይር የሚችል የመነጠቀ ሐሳብ በማቅረብ አልነበረም፡፡ ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል እንደሚባለው የኢህአዴግ ንዝህላልነትና ቸልነትነት እንጂ! ይህን ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ከቅንጅት ቡድን ጋር ለክርክር ሲቀርብ ማሰብ እና ማድረግ የነበረበት ብዙ ስትራተጂዎች ነበሩ፡፡ እንደምናስታውሰው ቅንጅቶች በነበረባቸው የብልጣ ብልጥነት (ተራ የአራዳነት) ስብእና በከፍተኛና በሚያስገርም ጥበብ የኢሀአዴግን ደካማ ጎን ተጠቅመውበታል፡፡ የኢህአዴግ ቸልተኝነት፣ በክርክር ታክቲክ በልጦ አለመገኘት እንዲሁም እዚህም እዛም ይታዩ የነበሩ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ የአፈጻጸም ግድፈቶች እና የልማት እጥረቶችን በሚሊዮን ግዜ በማጋነን ፣ ልብ የሚነኩ ቃላቶች በመደርደር የተወሰነ ህብረተሰብን በማሳመን ረገድ ቅንጅቶች ከፍተኛ ብልጫ አሳይተዋል፡፡ በኔ ግምት ይህን ሊያደርጉ የቻሉበት ዋናው ምክንያት 1ኛ የኢህአዴግ ጠንከር ላለ ፖለቲካዊ ክርክር በቂ ዝግጅት አለማድረግ እና የሰራውን ስራ በሚማርክ ቃለት እና በሚመጥን መልኩ መግለጽ አለመቻሉም ጭምር ነው፡፡ 2ኛ ደግሞ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ አጀንዳው በኢህአዴግ የፖለቲካ መስመር ፣ ርእዮት ዓለምና ኢህአዴግ በሚመራው የመንግስት የፖሊሲ አፈጻጸም ዙርያ መሆኑ ነው፡፡ ታድያ ብልጣ ብልጦች የቅንጅት ተከራካሪዎች እነሱ ገምጋሚዎች ኢህአዴግዬ ደግሞ ተገምጋሚ ሆና መቅረብዋ ምን ያህል ለነሱ አመቺ ሜዳ እንደነበረ ማንም ሰው ሊስተው አይችልም፡፡ ቅንጅቶች ይህን ክፍተት በመጠቀም ኢህአዴግ የሰራውንና ያልሰራውን ስራ አፈር ድሜ አበሉት፡፡ ኢህአዴግ በትምህረት ፣ በልማት ፣ በጤና ፣ በድህነት ቅነሳ […]