በዚህ ወር የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ VOA የአማርኛ ፕሮግራም አራት የሚዲያ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ያደረጉትን ውይይት አድርገው ነበር፡፡ በሁለት ክፍል የተሰራጨው ውይይት ተሳታፊዎች፡- ጽዮን ግርማ፣ አርጋው አሽኔ፣ ዳንኤል ብርሃነ እናመስፍን ነጋሽ ነበሩ፡፡ የፕሮግራሙ ርዕሰ-ጉዳይ (በVOA ድረ-ገጽ ላይ የሠፈረው) ጽሑፍ እንደሚከተለው ሲሆን፡- ነጻና ሚዛናዊ ምርጫ ለማካሄድ የሁሉንም ተወዳዳሪዎች ፕሮግራም ለሕዝብ የሚያደርስ በነጻነት የሚዘግብ መገናኛ ብዙኃን ወሳኝነት የዲሞክራሲ ባሕልና መሠረትም ነው። በርካታ ጋዜጠኞች እስር ላይ በሚገኙባትና ያንኑ ያህል ቁጥራቸው የበዛ አገር ጥለው በተሰደዱባት ኢትዮጵያ በነጻነት መዘገብ የሚችሉ ጋዜጠኞች መኖር እያነጋገረ ነው። ለጋዜጠኞች መብት ከቆሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ Freedom House በቅርቡ ስለ አገሮች የነጻ ፕሬስ ይዞታ ባወጣው ዓመታዊ ሪፓርቱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥሎ ጋዜጠኞች የታሰሩባት አገር መሆንዋን ዘግቧል። በጸረ ሽብር ሕጉና በወንጀለኛ መቅጫ የተከሰሱ ቢያንስ አስራ ሰባት ጋዜጠኞች በእስራ ላይ እንደሚገኙ ሌሎች በርካቶች እንደተሰደዱ በሪፖርቱ ዘርዝሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለ ስልጣናት በተደጋጋሚ “ጋዜጠኛ ሰለሆነ የሚታሰር ማንም የለም። በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ብቻ ናቸው የታሰሩት፤” ይላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰለመጪዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ለመዘገብ የሚያስችል ነጻ የመገናኛ ብዙኃን ሕዋ አለ? ከአድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን መልስ ጨምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች ተጋብዘው ይወያያሉ። ውይይቱ በVOA የተላለፈው በታህሳስ 4 (Dec. 13) እና ታህሳስ 11(Dec. 20) ሲሆን፤ ሁለቱን ክፍሎች አንድ ላይ በማድረግ ከታች ባለው የድምጽ ፋይል አቅርበናቸዋል፡፡ – – – – – ********* More from Horn Affairs AmharicAudio […]

(ታምራት ኃይሌ) ርዕስ፡- የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይደራሲ፡- ሀማ ቱማተርጓሚ፡- ሕይወት ታደሰአጭር፡- ሥነ ጽሁፋዊ ምልከታገምጋሚ፡- ታምራት ኃይሌ የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ The case of the Socialist Witchdoctor የ 22 አጫጭር ትረካዎች መድብል ሲሆን ትረካዎቹ በሁለት ክፍል ተለይተው ቀርበዋል፡፡ በክፍል አንድ አድራሻቸውን ፍርድ ቤት ያደረጉና በክስ መዝገቦች፤ በክርክሮች፤ በጥፋተኝነት ና በቅጣት ውሳኔዎች ላይ የተመሰረቱ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ ትረካዎቹ አንድም አስራአንድም ናቸው፡፡ አንድነታቸውንም አስራአንድነታቸውንም በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በክፍል ሁለት እንደዚሁ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ እንደመጀመሪያው በአንድ ቦታ የሚከናወኑ አይደሉም፡፡ ስለዚህ እነዚህን አንድም አስራ አንድም ናቸው ማለት ባይቻልም ፍጹም አይመሳሰሉም ደግሞ ማለት አይቻልም፡፡ በግድ አንድ ለማድረግ ሳይሆን፤ እንቅልፍ በሚያሳጣ ጸጉር ስንጠቃም ለመለያየት ሳይሆን በዚህ በሁለተኛው ክፍል ውስጥ ከተዘረዘሩት ትረካዎች መካከል በአንደኛው ማለትም “በሽብር ሚዛን አስር” መግቢያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል የቀሩትን ትረካዎች የጋራ ፍሬ ነገር በማስረዳት ረገድ ለጥቅስ የሚበቃ ይመስላል፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ ትረካ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመራጭ የጊዜ ማሳለፊያ ቢሆንም፤አሁንም ጥቂት ተጠራጣሪዎች ከሰማኒያ በመቶ በላይ መሀይም ባለበት አገር ውስጥ ድሮም ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም በማለት ይናገራሉ፡፡ ለማንኛውም በዕድሜ የገፉ ሰዎች የተካኑበት ትረካ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተለወጠ የማይስማማ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ አሰቃቂዎቹና አስገራሚዎቹ ታሪኮች የሚተረኩት በሽማግሌና ባልተማሩ ሰዎች ሳይሆን በተማሩ ወጣት ካድሬዎችና መገናኛ ብዙሀን ተብሎ በሚጠራው አካል ነው፡፡በድሮ ጊዜ በአጠቃላይ ታሪኮች ለዘብ ያሉና ልጆችን ለማስፈራራት ያህል መጠነኛ ምትሀታዊ ጉዳዮች ያሉባቸው ነበሩ፡፡ ስለሚያወሩ ጥንቸሎች፤ስለሸረኛ ጦጣዎች ስለታላላቅ አናብስት፤ስለተንኮለኛ ጅቦች፤ […]

(ፋኑኤል ክንፉ) ከ26 ዓመታት በፊት የደርግ መንግሥት በትግራይ ክልል በሐውዜን ሕዝብ ላይ ያካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ በስተጀርባ የእሥራኤል መንግሥት እጅ እንዳለበት የቀድሞ የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ስብሃት ነጋ ይፋ አደረጉ። አቶ ስብሃት ይህን የገለፁት በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የደርግ 604 ኮር የተደመሰሰበትን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ አስመልክቶ ሰሞኑን በሽረ ከተማ በተሰናዳ የውይይት መድረክ ላይ ነው። አቦይ ስብሃት ሲያስረዱ፣ “የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ ታላቋ ሶቪየት ሕብረት መፈራረስ ጀመረች። ይህን ክስተት ተከትሎ ሶቪየት ሕብረት ከኢትዮጵያ እየወጣች መጣች። በእሷ እግር የተተካውም የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ አገዛዝ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጠ። ይህን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምዕራብ ዓለም እና የእሥራኤል መንግስት ከደርግ ጋር ወዳጅ ሆኑ። የደርግ አገዛዝን መውደቅን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካል ኃይል አሰላለፍ በመፍራት የምዕራቡ ዓለምና እሥራኤል  ደርግን ወዳጅ አድርገው በእኛ የትግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” ብለዋል። አያይዘውም፣ “በወቅቱ ሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅሙ እየጠነከረ እየመጣ በመሆኑ አሜሪካና እሥራኤል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። የአዲስ አበባው መንግስት ወዳጅ ስለሆኑ እንዴት ከተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊያድኑት እንደሚችሉ ብዙ መንገዶችን ሞክረዋል። በጊዜው ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምዕራብ ሀገር አልነበረም። ሁሉም የሚችለውን አድርጓል። አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እሥራኤል ግን የተለየ ሚና ወሰደች” ሲሉ ወንጅለዋል። “አሜሪካ አንዴ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን እንድንመጣ ጠራችን።  ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር አስጠርቶን የነበረ ቢሆንም፣ የደርግ ልዑካን ቡድን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን […]

በመጪው የካቲት ከሚከበረውን የህወሓት 40ኛ አመት የልደት በዓል ይከበራል፡፡ ከበዐሉ አከባበር ዝግጅት አንዱ የሆነው፤ ከትጥቅ ትግሉን ዋነኛ ሥፍራዎች የተወሰኑት ከታህሳስ 13 -16 ቀን 2007 በታዋቂ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡ ጉብኝቱ የተጀመረው በደደቢት ሲሆን፣ በዚያው ቦታ ላይ በተዘጋጀ ግዜያዊ የሣር ዳስ ውስጥ ገለጻ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በዕለቱ ተናጋሪ የነበሩት የህወሓት መሥራቾች አባይ ፀሐዬ፣ ስብሐት ነጋ፣ ስዩም መስፍን እና አቦይ ካህሳይ እንዲሁም የብአዴን መሥራች በረከት ስምዖን ነበሩ፡፡ የገለጻቸውን ቅጂ ከታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ፡፡ —— *********** More from Horn Affairs AmharicAudio | በኦሮሞ ተማሪዎች ስለተካሄዱት ተቃውሞዎች የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘገባAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫAudio| ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመቐለ ያደረጉት ንግግርበደቡብ ሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስታቸው እንዲታደጋቸው ይሻሉሚኒስትር ሽፈራው:- በቅርቡ ለሚመረቀው ተንዳሆ ስኳር መዘግየት ህንዶችን ወቀሱዓባይ ወልዱ፡- ህወሓትን ለድል ያበቃው የውጭና የሌሎች ድጋፍ ሳይሆን የጠራ ሕዝባዊ መስመር ነው

(ወልደብርሃን ስሁል) የዛሬ መቶ ሰባ ዓመት አካባቢ አንዲት “ሚጢጢየ” አውሮፓዊት ሃገር ማንም ሳይቀድማት ኢትዮጵያን በጉልበት ይዛ ቅኝ ለመግዛት “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብላ” ቆርጣ ተሰናዳች። በቆዳ ስፋቷ አንድ ትልቅ ወረዳ እምታክል ናት። አፍሪካ ውስጥ ግን የራሷን መቶ እጥፍ የሚያክል ግዛት መቆጣጠር እሚያስችል አቅምና እብሪት ነበራት። ህልሟን ለማሳካት ፕሮጀክት ቀርፃ feasibility study አካሄደች። እቅዷና ጥናቷ ያነጣጠረውም በዘመነመሳፍንቷ ኢትዮጵያ ላይ ነበር። የቀይ ባህር አካባቢ ደከም ባለ አውሮፓዊ ሃይል እንዲያዝ ትሻ የነበረችው ታላቋ ብሪታንያም ይሁንታ ሰጠቻት፤ በወርራ ቅኝ ልትገዛን ቆርጣ ለተነሳችው ቤልጅየም! ቤልጅየም ለኢትዮጵያ ያሰበችው ፕሮጄክት ብሎንዲል ከሚባል እብሪተኛ ሰው የጀብድ ልክፍት ጋር የተቆራኘ ነበር። ግብፅ በወርኔር ሙዚንጀር፤ ጣልያን በፔትሮ አንቶኖሊ ምን እንዳደረጉን ጠንቅቀን እናውቃለን። ከነሱ በፊት ቀድሞ ስለተሰናዳልን የብሎንዲል Humanitarian Mission ግን ብዙ አናውቅም። ነገሩ ያስገርማል እንጂ አያስቅም። “ገድለ‐ብሎንዲል” በጥቂቱ እንዲህ ነበር፦ የቤልጂግ መንግስት መጀመርያ በ1841 ከፍተኛ በጀት መድቦ ብዛት ያላቸው የስለላ ወኪሎቹን ወደ ግብጽ አሰማራ። ወኪሎቹም “ለሳይንሳዊ ጥናት እና ለሰብአዊ ተልእኮ” በሚሉ ሽፋኖች ካይሮ ላይ ከትመው ስለ ኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩ። ማንኛውንም ዓይነት መረጃ በዝርዝር እየቀራረሙ ከሚያቀርቡት ሪፖርት የቤልጂየም ንጉስ ቀዳማዊ ሊዮፖልድ “በውስጧ ሁከት የነገሰባት ኢትዮጵያን” በቀላሉ መውረርና መቆጣጠር እንደሚችል አመነ። ለወረራም ቋመጠናም የሰላዮቹ አስተባባሪ በአካል ወደ ኢትዮጵያ ሂዶ “ሰብዓዊ ተልእኮ” የሚል ስም ያለው ጉብኝት እንዲያካሂድ አዘዘው። ዋናው ተልእኮው ግን ለወረራ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር እና ባስቸኳይ እሚተገበር የድርጊት መርሃ ግብር እንዲያዘጋጅ ነበር። […]

«ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) እና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ያካሄዱትን የትጥቅ ትግል በድል ያጠናቀቁት የውጭና የሌሎች ድጋፍ አግኝተው ሳይሆን የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው» ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር አስታወቁ። ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደቢት በረሃና ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ ጥረት እንደ ሚያደርጉ ታሪካዊ ስፍራዎችን የጎበኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል። የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በመጪው የካቲት የሚከበረውን የህወሓት 40ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ የትጥቅ ትግል የተካሄደባቸውን ስፍራዎችና የማዘዣ ጣቢያዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱ የጉብኝቱን መርሐ ግብር መጠናቀቅ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን በመቀሌ በተዘጋጀው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጡ የቻሉት የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው። የክልሉ ህዝብ ቀደም ሲሉ በነበሩትና በደርግ ሥርዓቶች ሲደርስበት የቆየውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስወገድ ህወሓት የትጥቅ ትግሉ መጀመሩን ገልጸው፤ በወቅቱ የተሳሳተ ዓላማ ያነገቡ ኃይሎች ትግሉን ገና ከጅምሩ በእንጭ ጩ ለማኮላሸት ተንቀሳቅሰው እንደነበር አስታ ውሰዋል። «ህወሓት የያዘውን ህዝባዊ ዓለማና ትክክለኛ መስመር የሚደግፉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ከጎኑ እያሰለፈ ህዝቡን የትግሉ ባለቤት ማድረጉ ትግሉን በአሸናፊነት እንዲወጣ አስችሎታል» ብለዋል። ሊቀመንበሩ እንዳሉት ህወሓት በወቅቱ ሲያጋጥሙት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶችና እንቅፋቶችን ተቋቋሞ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጣ የቻለው የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዙና ባለው የዓላማ ፅናት ነው። ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግሉን ያካሄዱት ይደርስባቸው የነበረውን […]

(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) አንድ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሆነ ሔሊኮፕተር ተጠልፎ በኤርትራ ምድር ማረፉ በዚህ ሳምንት ተሰምቷል፡፡ የጠለፋውን አጠቃላይ አገራዊና አለም አቀፋዊ እንድምታ ለማየት ድርጊቱ ከግለሰቡ ስሜት የሚመነጭ ተራ የዜጋ ክህደት ነው ወይስ በአገራቱ መካከል በተፈጠረ መሻከር የተነሳ የፖለቲካ ትግላቸው አንድ አካል የሚለውን ለይቶ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በቅድሚያ የድርጊቱ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ጠቃሚ ነው፡፡ የድርጊቱን መነሻ ለማወቅ ፓይለቱ ለድርጊቱ ያነሳሳው የራሱ የግለሰቡ ተራ የሆነ የግለሰብ ስሜት ነው ወይስ ከጀርባው የተለየ ተልዕኮ አለ የሚሉትን ሁለት መነሻዎች ለይቶ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከሁለቱ አንዱን መምረጥ የሚያስችሉ የአሳብ መነሻዎችን ማየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ዋናው መነሻ ግለሰቡ ከሌሎች አገሮች ኤርትራን ለመድረሻ የመረጠበት ምክንያት እና ግለሰቡ የኤርትራን ድንበር አቋርጦ ሲሄድ በሰላም መስተናገዱ ምንአልባት ግለሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ መንግስት ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በድብቅ ሲሰራ እንደቆየ ሊያመላክት ይችላል፡፡ የኤርትራ መንግስት እንደጠላት ከሚያያት አገር የጦር ሄሊኮፍተር ድንበሩን አቋርጦ ሲገባ የአፀፋ ምላሽ አለመስጠቱ አስመራው አስተዳደር ድርጊቱ እንደሚፈጸም ቀደም ብሎ ያውቅ እንደነበረ ሊያመላክት ይችላል፡፡ እነደዚህ ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ጠላት ያለው በራሱ ጉያ እንጂ በሚሊየን ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡ የተጠናከረውን የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት አልፎ ተልዕኮውን ማሳካቱ የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ ተልዕኮ እንዳልቀረ ያመላክታል፡፡ የኢትጵያ መንግስት ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? በዋናነት ውድ ዋጋ ያለው ሀብት በመወሰዱ ሳይሆን በሁለቱ አገራት […]

(ቃለየሱስ በቀለ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብረት የሆነ ተዋጊ ሔሊኮፕተር ባለፈው ዓርብ ተጠልፎ ኤርትራ ግዛት አሰብ ማረፉ ተረጋገጠ፡፡ የዘወትር የበረራ ልምምድ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሩሲያ ሠራሽ ኤምአይ 35 ተዋጊ ሔሊኮፕተር ይዞ ወደ ኤርትራ የኮበለለው ዋና አብራሪ ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ ይህንን ዓይነት ተግባር ይፈጽማል ብለው እንደማያስቡ ባልደረቦቹ ገልጸዋል፡፡ ከሻምበል ሳሙኤል ጋር በኢትዮጵያ አየር ኃይል አብረው የሠለጠኑና የሠሩ የሥራ ባልደረቦቹ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግለሰቡ መልካም ባህሪ ያለውና በፖለቲካ አቋሙ ገለልተኛ የሚባል ነው፡፡ ‹‹እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ የመንግሥት ተቃዋሚ አልነበረም፡፡ ራሱን ከፖለቲካ ጉዳዮች የሚያገል፣ ሥራውን ብቻ የሚሠራና ልጆቹን በኃላፊነት የሚያሳድግ ሰው ነበር፤›› ብለው በድርጊቱ ግራ መጋባታቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በትንሽ ነገር የሚከፋና የሚደሰት፣ በቅጽበት የሚለዋወጥ ባህሪ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በግል ሕይወቱም የሚበሳጭበት ጉዳይ እንደነበርና አልፎ አልፎም በዚሁ ጉዳይ ይደበት እንደነበር አልሸሸጉም፡፡ ሻምበል ሳሙኤል ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል የገባው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን፣ የቅጥር ውል የፈረመው በታህሳስ ወር 1995 ዓ.ም. ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ በ2003 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወደ ዳርፉር ሱዳን ያሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል በመሆን ለአንድ ዓመት ያህል እንዳገለገለና በዚያም ተልዕኮ ዳጐስ ያለ ዶላር ይዞ መመለሱን ባልደረቦቹ ተናግረዋል፡፡ ሻምበል ሳሙኤል ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መሆኑን፣ ወላጆቹ የመቀሌ ነዋሪ መሆናቸውን ባለቤቱና ሁለት ልጆቹ ቢሾፍቱ እንደሚኖሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ባለፈው ዓርብ ማለዳ ከረዳት አብራሪው መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝና የበረራ ቴክኒሺያን […]

የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ሰላማዊም የትጥቅም፣ በባህሪው ትብብርን ይጠይቃል። ሕብረተሰብ በማሳትፍ የሚደረግ የትብብር ሥራ ነውና። የኢትዮጵያ ገዥ ጥምር ድርጅት አንድ አካል የኾነው ህወሓት የፈር ቀዳጅነት ሚናውን ወስዶ የዛሬ አርባ ዓመት በትግራይ በረኻዎች የትጥቅ ትግል ጀምሮ በሚያካሂድበት ጊዜ፣ “ተወዲቡ ብጽንዓት ዝተቓለሰ ይዕወት” (ሲተረጎም፣ ተደራጅቶ በጽናት የታገለ ለድል ይበቃል) የሚል መፎክር ከአነገባቸው መፎክሮች አንዱ ነበር። በነገራችን ላይ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ኢህአዴግ እንደ መንግስት ሀገር ሲመራ የተከተለው ህዝብን አደራጅቶ እና አስትፎ የመስራት ባህልም ከዚኽ መፎክር የተወረሰ ሳይኾን አይቀርም። ለዚህም ነው ኢህአዴግ ነጥሮ በመውጣት በትጥቅ ትግሉም ሀገር በመምራቱም ወቅት ውጤታማ ሊኾን የበቃው። አሁን በፖለቲካው ተደራጅተው ሳይደራጁም እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተቃውሞ፣ ሕጋዊ የኾኑትም ያልኾኑትም በዋናነት የዚኽ የተባብሮ መስራት ድክመት ስላለባቸው ነው ለውጤት ያልበቁት። ሲጣመሩ፣ ሲቀናጁም ኾነ ሲያብሩ፣ የአብሮ መስራት ምክንያታቸው የመላው ህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና ፖለቲካዊ ፕሮግራም ነጥሮ የወጣ ፖለቲካዊ አቋም ይዘው መስዋእት ለመክፈል ተዘጋጅተው ሳይኾን በጥላቻ እና የስልጣን ጥም ብቻ መሰረት አድርገው ነው ወደ አንድ የሚሰባሰቡት። በዚኽ አካሔድ ደግሞ ጠብ የሚለ ውጤት አላገኙም። በተለይ ለመስዋዕትነቱ የሚመርጡት ሌላ አካል እንዲኾንላቸው ይፈልጋሉ። እነሱ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመፈናጠጥ እንዲያስችላቸው። ከዚኽ አንጻር የሀገራችን ተቃዋሚዎች ትጥቅ ትግል አውጀው በሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩት እና በስመ አክቲቪዝም የሚከትሏቸው (ሁለቱንም መንገድ የሚያጣቅሱ ቡድኖች) እንዲኹም በሰላማዊ ሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት በተደጋጋሚ የመተባበር እና ለህዝብ መስዋዕት የመኾን መሰረታዊ ባህሪ ስለሚጎድላቸው እና የስልጣን […]

(አሥራት አብርሃም – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ‹‹የአንድነት እስትራቴጂ ከሁሉም ይለያል!›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ ገጹ ያተመው) በምርጫው እንደሚሳተፉ እርግጠኛ ሳይሆኑ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ ፓርቲዎችና በሂደቱ በደመነፍስ ከገቡ ፓርቲዎች አንድነት በእርግጠኝነት የተሻለ አቅጣጫ ያስቀመጠ ፓርቲ ነው። የፖለቲካውን ምህዳር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በማስፋት በምርጫው ላይ በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗልና። አንድነት በባዶ መሬት ህዝቡን ሳያደራጁ ህዝባዊ አመፅ ከሚጠሩትም በእጅጉ የተሻለ እቅድ ያለው ፓርቲ ነው! አሥር ሰው ይዞ ፓርቲ መመስረት ይቻል ይሆናል አሥር ሰው ይዞ ስርዓት መቀየር ግን የሚታሰብም፤ የሚቻልም አይደለም። ስለዚህ እስኪ በመጀመሪያ ህዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ ይደራጅ፤ እስኪ በምርጫው ሂደት በንቃት እንዲሳተፍ እናድርገው፤ ከዚያ ባግባቡ የተደራጀ ህዝብ ምን ማድረግ እንደሚችል ለማየት ቀላል ነው የሚሆነው። መምረጥ የሚችል ዜጋ ሁሉ በትክክል የህዝብ ታዛቢዎች ይምረጥ፤ የምርጫ ካርድ በነቂስ ወጥቶ ይያዝ፤ እንደገናም በነቂስ ወጥቶ ይምረጥ ይህን ሁሉ ሂደት ከታለፈ በኋላ ምርጫው የሚዘረፍ ከሆነ ያኔ ይህ የተደራጀ ህዝብ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማካሄድ በቂ የሆነ ምክንያት ይኖረዋል። የአንድነት እቅድ ይሄ ነው፤ ሌላ እቅድ አለኝ የሚል ካለ መብቱ ነው፤ አንድነት በእኔ እቅድ አጨብጫቢ ሆኖ ይሰለፍ ማለት ግን ተገቢ አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም። አንድነት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ መዋቅር ያለው፣ ስለአባላቱና ስለህዝቡ ሀላፊነት የሚሰማው ፓርቲ ንው። ከዚህም ባሻገር የነገው መንግስት መሆን የሚያስችለው ቁመናና ስብስብ ያለው ፓርቲ ነው። በዚህ ምክንያት በእርሱ ክብደት ድልድዩን አንቀጠቀጥነው ለማለት ለሚመኙ ሁሉ የሚመች ፓርቲ አይሆንም፤ ከሆያሆዬ ፖለቲካ ነጥሮ ከወጣም ቆይቷል። […]

(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) የተቃዋሚዉ ጎራን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት አብይት ፖለቲካዊ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ትግል ሲኮላሽ የመድረክ ደግሞ ቀዝቀዝ ያለ በሚመስል መልኩ ተስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በተስተጓጎለ በሳምንቱ የመድርኮቹ መሳካቱ ምን ሊያመላክት ይችላል የሚለውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የመድርኩን ሰልፍ ከራሱ ከመድርክ፣ ከመንግስትና ከህዝብ አንፃር ሊኖረው የሚችለውን እንድምታ አጠር ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን፡፡ ሀ) ከመድረክ አንፃር መድርክ ከሌሎችና ፓርቲዎችና ከራሱም ያለፈ የትግል ልምድ የተማረው ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ፓርቲው ቀድሞ ከነበረበት ጽንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ በተወሰነ መልኩ ለዘብ እያለ መምጣት የሚያሳዩ ሁሄታዎችን መታዘብ ይቻላል፡፡ መድረክ ከሌጋሲው የተማረው ጉዳይ ቀድም ሲል በነበው ፅንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ የመንግስትን የቁጥጥር ጫና እንዲሚያጠብቀው ሳይማር እንዳልቀረ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ባልተለመደ መልኩ ሌሎች ተቃዋሚዎች ክፉኛ የሚጥሉትንና መንግስት እየተጠቀመበት ያለውን ባንዲራ በሰልፍ ውስጥ መጠቀሙ በተወሰነ መልኩ ከአክራሪነት ለዘብ ያለ አቋም እያሳየ ለመምጣቱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲው ወዶም ይሁን ተገዶ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢህአዴግ ጋር መመሳሰል ባይችል እንኳን መንግስት ከሚፈልገው የአቋም መለሳለስ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ፍንጮች እንዳሉ መውሰድ ይቻለላል፡፡ በሌላ መልኩ መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን ዉጤት ተከትሎ መንግስት የሚሰጋባቸውን ችግሮች እንዳይከሰቱ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማድርግ ከመንግስት ጋር ስምምንት ላይ ሳይደርስ እንዳልቀረ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ፡፡ በአቋም እየተለሳለሰ መምጣቱና ለሰልፉ ኃላፊነቱን ከመንግሰት ጋር መጋራቱ ሰልፉን ስኬታማ ለማድረግ ሳይግዘው እንዳልቀረ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በ2002 ምርጫ ከኢህአዴግ ጋር […]

* ‹‹በትጥቅ ትግልም የተሳተፈ፣ ዴሞክራሲ፣ ሰላም፣ ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲመጣ ለማድረግ መስዋዕት የከፈለ ትውልድ አለ። ከእርሱ ትውልድ ተቀብሎ ደግሞ 2ተ ኛው ትውልድ ሥራ ጀምሯል።›› * ‹‹አንዳንድ ሀገሮች ያኔ 25 እና 30 ሚሊዮን እርዳታ ሲሰጡን ትልቅ እርዳታ ተደርጎ ነበር የሚታየው። ዛሬ እኛ የደረስንበት ደረጃ ሲታይ ደግሞ የህዳሴ ግድብን የመሰለ ወደ 4ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ግድብ በራሳችን ለመስራት መጀመራችን…›› * ‹‹በቅርቡ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ፕሬዚዳንት በምንም ተዓምር ይህን ግድብ መጥቼ ማየት አለብኝ፣….እናንተ ለእኛም ሞራል ሆናችሁናል፣ ከእናንተ ቀጥሎ እኛም መስራት አለብን ብለው አቋም ይዘው ግድቡን መጎብኘት አለብኝ ብለው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል፣ በቅርቡም መጥተው ያያሉ።›› * ‹‹በዘንድሮ ዓመት በዋና ዋና ሰብሎች የባለፈው ዓመት የዘንድሮን ሳይጨምር 2006 ዓመት ላይ ማለት ነው በዋና ዋና ሰብሎች 250 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል፤ ከዚያ በላይ ደግሞ የስራስር ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች የቅመማ ቅመምና ቅባት እህሎች፣ ቡና የመሳሰሉት ሲጨመሩበት ከ300 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማምረት የቻለ አገር ሆኗል። ይሄ በህዝብ ቁጥር በሚከፋፈልበት ጊዜ ሀገሪቱ ራሷን በምግብ እህል መቻሏን ያስረዳል።›› – – – – –  አዲስ ዘመን፡- ሕገመንግሥታችን የአገራችንን የቁልቁለት ጉዞ ቀልብሶ የኢትዮጵያ ህዳሴ መሰረት እንዲጣል ያደረገ ነው ይባላል፤ ይህ ምን ማለት ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፡ – በኢትዮጵያ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የኢትዮጵያን ህዳሴ ሊያረጋግጥ የሚችል ድል ተገኝቷል። ሕገ መንግሥታችን በዚህ ድል ላይ የተገነባ ሕገመንግሥት ነው፤ ከድሉ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና […]

(የሰማያዊ ፓርቲ ዘገባ) በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ታፍሰውና ደብደባ ተፈጽሞባቸው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ፣ መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት በማውደም፣ በሁከትና ብጥብጥ›› እና በመሳሰሉት ክሶች ተከሰው እስከ 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው የነበሩት የሰማያዊና የሌሎች የ9ኙ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ፡፡ ከእስረኞቹ መካከል ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ) ታስረው የነበሩት ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› ክስ 14 ቀን፣ ፖፖላሬ ታስረው የነበሩት ‹‹መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት በማውደም›› 7 ቀን፣ እንዲሁም ቤላ እስር ቤት ታስራ የነበረችው ወይንሸት ንጉሴ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠርና ህዝቡን በመረበሽ›› 7 ቀን፣ እንዲሁም ኮተቤ ታስረው የነበሩት እነ ፍቅረማሪያም በተመሳሳይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር›› 10 ቀን ተቀጥሮባቸው የነበር ቢሆንም ከቀጠሯቸው ቀን ቀድም በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡ በሶስተኛ፣ ፖፖላሬ፣ ቤላና ኮተቤ የነበሩት እስረኞች ከትናንት ጀምሮ በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ፖሊስ አንዳንድ እስረኞችን በተለይ ፖፖላሬና ሶስተኛ ታስረው የነበሩትን ነጥሎ ለማስቀረት ባደረገው ጥረት የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲፈቱ የተነገራቸው እስረኞች ‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ አንወጣም›› በማለታቸው ሳይፈቱ አድረዋል፡፡ ዛሬ ታህሳስ 2/2007 ዓ.ም ደህንነቶች ሶስተኛ ታስረው የነበሩትን መርከቡ ሀይሌ፣ ሳሙኤል አበበ፣ ምኞት መኮንን እና ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም ፖፖላሬ ታስረው የነበሩትን ዮናስ ከድርና ተስፋዬ መርኔ ‹‹አብራችሁን ካልሰራችሁ አትወጡም!›› ብለዋቸው እንደነበር ታውቋል፡፡ ሆኖም በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ የተነገራቸው እስረኞች ‹‹እነሱ ካልወጡ እኛም አንወጣም›› በማለታቸው በአራቱም እስር ቤቶች የሚገኙት ሁሉም ታሳሪዎች የመታወቂያ ዋስ አቅርበው እንዲለቀቁ […]

ዕለቱ 9ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እና የሕገ-መንግስታችን 20ኛ የልደት በዓል የሚከበርበት ህዳር 29፤ ቦታው ደግሞ ለዚሁ በዓል ተብሎ በፍጥነት እንዲደርስ የተደረገው የአሶሳ ከተማ ስቴድየም ነው፡፡ የኢ.ፌ.ድሪ ጠቅላላ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የፌደሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣የጎረቤት ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስቴሮች፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የባህል ቡድኖች…ብቻ ምን አለፋችሁ ኢትዮጵያ በስቴድየሙ ከትማለች፡፡ በዓሉ ሰፊ፣ ደማቅና ብዙ ሊባልለት የሚገባ ነበር፡ ስለዚህ ሌላው በይደር ይቆየንና ለዛሬ አንድን ለየት ያለ ክስተት መርጨ ላውጋችሁ።   ለበዓሉ ከታቀዱት ትርኢቶች አንዱ፣ ለ26 ቀናት ሀገሪቱን በመዞር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 204 ሚልዮን ብር የሰበሰበው እና ከታላቁ መሪ ለኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦች የተበረከተው የህዳሴ ግድብ ዋንጫ፣ ግድቡንም በአሉንም ወደምታስተናግደው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ መግባት ነበር፡፡ ዋንጫው ወደ አሶሳ ስቴድየም እንዲገባ የታሰበውም ለየት ባለ መንገድ ነበር፤ በሄሊኮፕተር ከሰማይ። በእርግጥ ይህ ለየት ያለ አቀራረብ የታሰበለትን በአሉን የማድመቅ ግብ መትቷል ፡፡ ግቡን የመታው ግን አዘጋጆቹ ባሰቡት መንገድ አልነበረም። ታሪኩ እንዲህ ነዉ። አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፡ የሚመራውን ቡድን በመያዝ የስቴድየሙን መሀል ከተቆጣጠረ የቡድኑን 26 ቀን ሀገር አቀፍ ጉዞ በሰፊው መተረክ ከመጀመሩ ነበር ዋንጫውን ያዘው የመከላከያ ሄልኮፕተር በድንገት ከተፍ ያለው፡፡ ሄልኮፕተሩ ወደ ሜዳው መሀል ጉዞውን ቀጥሏል፤ ሰራዊት ፍቅሬም ትረካዉን። ሄሊኮፕተሩ ወደ መሀል እስኪደርስ የተነቃነቀ ሰው አልነበረም፣ ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የገመተ የነበረም አይመስል። ልክ ሄልኮፕተሩ ሜዳው መሀል ደርሶ ከፍታ […]

ከትብብሩ የተሰጠ መግለጫ በአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ትግላችን አይቆምም! የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 27/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡ ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በየእስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ከ300 በላይ የትብብሩ አመራሮችና አባላት የታሰሩ ሲሆን የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ድርሶባቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቤል ኤፍሬም ራሱን እስኪስት ተደብድቧል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ሴት አመራርና አባላት አንድ አገርን እየመራሁ ነው ከሚል አካል በማይጠበቅ መንገድ በጭካኔ ተደብድዋል፡፡ እነዚህ በጭካኔ የተደበደቡ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጥበቃ ሰራተኝነት የሚሰሩ የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር ከስራ ሲወጡ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱና እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቀ ሲሆን ይህም አገዛዙ የመጨረሻው የአረመኔነት ደረጃ ላይ እንደደረሰና […]

(በአማን ነጸረ) ባለፈው ጽሑፍ እንዳመለከትኩት፡- ሁለት ጽንፍ የያዙ ኃይላት ያገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ተቆጣጠረዋል–ያንድነት ኃይላት ነን ባዮችና ብሔረሰባውያን፡፡ የየራሳቸው በጎ ጎን እና መነሻ እንዳላቸው የምረዳ ቢሆንም በጎ በጎውን ላቆየውና የሚያሥከፋኝን ልናገር፡፡ (ባለፈው ጽሑፍ ስለአማራ ልሂቃንና አስተሳሰባቸው ያወሳሁ ሲሆን አሁን ደግሞ የኦሮሞ ልሂቃንን እቃኛለሁ፡፡ 1– ያለፈው ሥርዓት የሕዝብ ለሕዝብ ማኅበራዊ ገጽታ የሌለው ይመስል ስለጭቆና ዘላለም እያወሩ ፖለቲካውን ብቻ ማጮኽ ርካሽነት ነው!!በፖለቲካውም ቢሆን የኃይለሥላሴን ከፊል-ፊውዳል ሥርዓት በመታገል ረገድ እንደ ልሂቅም፤እንደ ማኅበረሰብም በግልና በነጠላ የሰሜኑ ክፍል ያደረገው ጥረት ከኦሮሚያው ያነሰ አይመስለኝም፡፡ትረካው ቢስተካከል!! 2— “ለእኛ እስከተመቸን ድረስ ሌላው ስለ እኛ ፖሊሲ አያገባውም” የሚል አስበርጋጊና በተለይ ሀቀኛ የኦሮሞ ትግልን ሳይቀር ሌላው ማኅበረሰብ በጥርጣሬ እንዲመለከት ማድረግ ለሌላው ስሜት አለመጨነቅ ነው–ራስ ወዳድነት!!ቢቻል ትግላችን ጭቆናውን ለሚያለባብሰው ልሂቅ የሚተርፍ እንዲሆን መስራት፣ካልሆነም መብታችን ላይ የቆመውን ልሂቅ ነጥሎ ብቻውን ማስቀረት ሲቻል በልሂቁ ሰበብ ሕዝብ ማስቀየም ማንንም አይጠቅምም!!መጀመል ይቅር!! 3– ምኒልክ በሰላም እጅ ያልሰጠውን የኦሮሞ ክፍል በኃይል ማስገበሩ ባይካድም በሂደቱ በተፈጠው አብሮነት አድዋ ላይ የውጭ ወራን በጋራ መመከታችንና በዚህም ዛሬ ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ የትም አገር ቀና ብሎ እየሄደ፣በግንኙነቱ እንደ ነጭና ጥቁር የልዩነት አጥር ሰርተን ሳይሆን በማ/ሰብ ደረጃ እንደ ማንኛውም ኢ/ዊ ርስ በርስ ከመሳፍንቱ ሳይቀር ተጋብተን ተዋደን መኖራችን እየታወቀ፣“የኢ/ያ ታሪክ የ100 አመት ነው” የሚለውን ትረካ በበኩሌ በፍጹም ባልቀበለውም እሱም ቢሆን የጋራ ማንነት ለመገንባት ከበቂ በላይ መሆኑን ባለማስተዋል፣ምኒልክ ሲዘምቱ በአከባቢያዊ ገዥዎች ቅርምት የተያዘች እንጅ አንድ […]

(በፍቃዱ ወ/ገብርኤል) የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ዘጠነኛ አመቱን የያዘ ሲሆን በአገረ አሜሪካም ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሎምበስ ኦሃዮ ይከበራል። የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለዘመናት ተጨቁነውና ተመዝብረው፤ ተንቀውና ተገልለው በሁለተኛና ሶስተኛ የዜግነት ደረጃ ይታዩ የነበሩትን ብሄር ብሄረሰቦች መብትና ነጻነት ያረጋገጠውን የፌደራል ስርአት ለመዘከርና አጽናኦት ለመስጠት ሲሆን በዚህም በአል ብሄር ብሄረሰቦች በተወካዮቻቸው አማካይነት ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና ከሌሎች የሚተዋወቁበት፤ ልምዳቸውንና አገራዊ ጉዳዮችን የሚወያዩበት፤ የጋራ እምነታቸውንና ተስፋቸውን የሚጋሩበት የአንድነታቸው የደስታ መግለጫ መድረክ ነው። የኢትዮጵያ ፌደራል ስርአት የህዝቦችን እኩልነት ያረጋገጠና ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ለአገሪቱ አንድነት ሰላም መረጋጋትና እድገት መሰረት የጣለ አዲስ ግኝት ነው። ይህ ህያውና አዳጊ ተመንዳጊ የሆነ የአንድነት መሰረት ዛሬ ኢትዮጵያ በጽናት እንድትቆም ያስቻላት ብቻ ሳይሆን በምታደርገው ፈጣንና ሁለገብ የዕድገት ጎዳና ጉዞ ከምትራመድበት ሁለት እግሮችዋ መካከል የመጀመሪያው ነው። እንደሚታወቀው ሁለተኛው ደግሞ የምትመራበት የልማታዊ መንግስት መርሃ ግብር ነው። የብሄር ብሄረሰብች ቀን ሲታሰብና ሲዘከር የዛሬዋ ኢትዮጵያ የመንፈስና የነፍስ አባት (Founding Father) ከሆነው ከታጋዩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ስሙ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ዋልልኝ መኮንን ነው። የብሄር ብሄረሰቦች የመብትና የእኩልነትን ጥያቄ በአደባባይ በማስተጋባት የአደባባይ ምስጢርንቱ ተገፎ በኢትዮጵያ የፖሊቲካ መድረክ የመሃል መስመር ስፍራ (main stream politics) እንድሆን ካበቁት ስመ-ጥር የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦች ልጆች መሃል ዋለልኝ መኮንን አንዱ ነው። ዋለልኝ መኮንንን የተለየ ቦታ እንዲሰጠው የሚያደረገው የንጉሱን ስርአት ጸረ-ህዝብነትና በህዝቦች ላይ የተጫነውን ‘fake’ የ”ኢትዮጵያዊንትን” ጭንብል በዛ በጭለማ ዘመን በሰላ ብዕሩ በአደባባይ ማራቆቱ […]

(በአማን ነጸረ) ሁለት ጽንፍ የያዙ ኃይላት ያገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ተቆጣጠረዋል–ያንድነት ኃይላት ነን ባዮችና ብሔረሰባውያን!! 2ቱም የየራሳቸው በጎ ጎን እና ለሀሳባቸው አሳማኝ ምክንያቶች እንዳላቸው እረዳለሁ፡፡ሆኖም በጎ በጎውን ላቆየውና የሚያሥከፋኝን ልናገር፡፡ያደፋፈረኝ የልሂቃኑን የብሔር መነሻ ከአመለካከታቸው ለማስተሳሰር የደፈረው የዶ/ር መረራ መጽሐፍ ነው፡፡ 1– ትናንት የተፈጸሙ በደሎችን ሽምጥጥ አድርገው ይክዳሉ ወይም ያለባብሳሉ፡፡ “እኔ አልጨቆንኩህም ሥርዓቱ ነው” ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ነገር ግን ተጨቆንኩ ብሎ ያመነን ማኅበረሰብ–ያውም ስለጭቆናው ከአያት ቅድመ – አያቱ ብቻ ሳይሆን ከበዙ የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ሊረዳ የሚችልን ፊደል የቆጠረ ትውልድ ስለ አንተ አለመጨቆን ታሪክ እጽፍልሀለሁ ማለት ግብዝነት ነው!! “ነገሥታቱ እናንተን ብቻ ሳይሆን እኛንም ጨቁነዋል” የሚለው መከራከሪያ እኔ ራሴ ብዙ ጊዜ ብጠቀምበትም በኢ/ያ የጭቆና ትረካ አቀራረቡ ትክክል አልሆንልህ ይለኛል፡፡ምክንያቱም የአንድ ብሔር የራስ በተባለ ሰው (ብሔር) መንገላታትና ከራስ ውጭ ባለ ሰው(ብሔር) መንገላታት ያለው ትርጉም ይለያያል፡፡ለምሳሌ፡- የአጼ ቴዎድሮስ የሸዋን መሳፍንት እጅ መቁረጥ እና የአጼ ምኒልክ የኤርትራውያንን ምርኮኞች እጅና እግር መቁረጥ ታሪኩን እንደሚዳኘው ሰው የብሔር ማንነት ትርጉሙ ሊለያይ እንደሚችል መረዳት አለብን፡፡የምኒልክ ንጉሥ ተ/ሃይማኖትን እምባቦ ላይ መውጋት ራሱን እንደ ምኒልክ ልጅ ለሚቆጥረው የዛሬ ዘመን የጎጃም ልሂቅ ምንም ላይመስለው ይችላል፤ለወላይታው ልሂቅ ግን የምኒልክ ጦናን መውጋት የአባት ተግባር ሳይሆን በማንነት ላይ የተቃጣ የጎረቤት ትንኮሳ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡የምኒልክ የደቡብ ሕዝቦችን የማስገበር ሂደት አፈጻጸሙ ታይቶ “ባልተወለደ አንጀቱ…” ቢባል አይግረመን፡፡ “እኔ ስላልተሰማኝ ለምን ይሰማችኋል??” አንበል!!በቃ!! የተሰማው የተሰማውን በተሰማው መጠን ይናገር!!ድርጊቱን እስካመንን ድረስ ቢያንስ […]