ሚ/ር ሬድዋን:- የተጠና የሁከት ድራማ ተሞክሯል – 7 ፖሊሶች ተጎድተዋል
ኢስላሚክ ስቴት ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት በሊቢያ በኢትዮጲያውያንን ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመውን ግድያ ቪድዮ ባለፈው እሁድ ማሰራጨቱን ተከትሎ፤ ድርጊቱን ለማውገዝ ዛሬ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ ያንን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስተር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከጽ/ቤቱ ያገኘነውን የመግለጫው ጭማቂ ጽሑፍ ከዚህ በታች አትመነዋል፡፡ 1) የተሳካ ሰልፍ ተካሂዷል፣ * ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ወጥቷል፣ * በሰላማዊ መንገድ በጋራ ሀዘኑ ዙሪያ፣ በቀጣይ የጋራ ጥረቶች ዙሪያ ያጠነጠነ መልዕክቱን አስተጋብቷል፣ * አንድነቱን በማጉላት ሽብርተኞች ለመፍጠር የፈለጉትን የመከፋፈል ሴራ ሙስሊም ክረስቲያን ሳይል በጋራ ተሰልፎ በመምጣት አክሽፏል፣ * ሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ መሰረት እንደሌለው በማንኛውም ሃይማኖት ጀርባ መሸሸሸግ እንደማይገባ አረጋግጧል፣ * ISIS ማንኛውንም ሃይማኖት እንደማይወክል ፅንፈኝነትና አክራሪነትን እንዲሁም የሽብር ተግባርን ብቻ እንደሚወክል ስለዚህም የጋራ ጠላት መሆኑን በአንድ ድምፅ አስረግጧል፡፡ * የፀረ ሽብርና አክራሪነት ትግሉን ከመንግስት ጎን ቆሞ ለማጧጧፍ ያለውን ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፡፡ * ህገ ወጥ ስደትን በመላ ህዝቡ ተሳትፎ ማስወገድ እንደሚገባ በቁጭት ገልጿል፣ * በሀገራችን ሰርቶ መለወጥ የሚቻልበት ዕድል እየተፈጠረ በመሆኑ ከነክብራችን በሀገራችን ሰርተን እንለወጥ የሚል ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፣ * የሃይማኖት አባቶችንና የመንግስትን መልዕክት በጥሞናና በትእግስት አዳምጦ የቀጣይ ትግል ባለቤትነቱን አረጋግጧል፣ * በመሆኑም መንግስት የከበረ ምስጋና ያቀርባል፣ * ከህዝቡ በተጨማሪም የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከአንዳንዶች በስተቀር የደረሰው አደጋ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ኢሰብአዊ ድርጊት መሆኑንና የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀዘን መሆኑን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረትም የበኩላቸወን ድርሻ የሚወጡ መሆኑን በፓርቲዎች […]