የኢትዮጵያ መንግስትና “ኣርበኛዊ” ዲፕሎማሲ (እርምጃ)

በሳውዲ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካና ሊብያ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግር ባጋጠመ ጊዜ በቦታው የሌሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በነዛ ኣገራትና ቡድኖች ላይ እንዲወስደው የሚጠብቁት እርምጃ ኣርበኛዊ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ጥሎበት (በባህሪው) ኣርበኛዊ ዲፕሎማሲ ኣያራምድም፡፡ ቢያንስ መንግስት በኣንዳንድ ወገኖች የሚነሳበትን የ”ወኔ-ቢስነት” ክስ ለመከላከልና ለዜጎቹ እንደሚቆረቆር ለማሳየት ያክል እንኳን (ባያደርገዉም) በቴሊቪዥን ብቅ ብሎ ዘራፍና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ኣይሆንለትም ወይም ኣያምንበትም፡፡ ይሄ ማለት ግን መንግስት ምንም ኣይነት እርምጃ ኣይወስድም ማለት ኣይመስለኝም ፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግርና ጥቃት በደረሰ ቁጥር እኛ ዜጎች እንደምናሳየው ኣይነት ቁጣ የመንግስት ፊት (ግንባር) ላይ ባናየዉም በጊዜው እንደየሁኔታው የተሻለ የሚለው እርምጃ ይወስዳል የሚል ግምት ኣለኝ፡፡ ይሄንን ባህሪው ተቃዋሚዎቹ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ኣንዳንድ ደጋፊዎቹ ደግሞ የሚደግፉትን ፓርቲ/መንግስት ባህርይ በደንብ ካለመረዳት ኣሊያም በስሜትና ሃዘኑና ጥቃቱ በሚፈጥርባቸው ተፅእኖ ምክንያት መንግስትን ይወቅሳሉ፡፡ ለነገሩስ የኛን ስሜትና ምክር እየተከተለ እርምጃ የሚወስድ መንግስት ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ከሱዳንና ግብፅ (በኣባይ ምክንያት)፣ ከሳውዲ ኣረቢያ (በዜጎች ምክንያት)፣ ከኤርትራ (በሄሊኮፕተር ምክንያት) እንዲሁም ከሌሎች ኣገሮች ጋር ጦርነት ውስጥ እንገባ ኣልነበር ? የሰሞኑ የ ISIL ጉዳይ ግን ትንሽ ስሜትን ይፈታተናል፡፡ ድህነት ኣንገሽግሽዋቸውና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለመቀየር የሰሃራ በረሃን ኣቋርጠው የመሞትና የመትረፍ ኣጋጣሚው እኩል የሆነበትን የሜዲትራኒያን ባህር የጀልባ ጉዞ ለማድረግ የተዘጋጁትን ወጣት ወገኖች በኣደባባይ ኣንገታቸው ሲቀላና ሰረሸኑ ማየትን የሚያክል ዘግናኝ ነገር የለም፡፡ ህዝባችን በሃዘንም በቁጭትም ኣደባባይ ወጥቶ ሆ ቢል፣ እስቸኳይ የኣጸፋ እርምጃ እንዲወሰድ ቢጠይቅ ኣይገርምም፡፡ ጥያቄው […]