የማንነት መገለጫ ዓይነቶች- በዓለም እና በኢትዮጵያ
(አዲስ ከድሬዳዋ) የቀድሞ ዩጎዝላቪያ አካል የነበሩት ክሮሺያና ሰርቢያ (የቦስኒያ ሙስሊሞችን እና ሞንቴኔግሮዎችን ጨምሮ) ሶሻሊዝም ሲንኮታኮት ከተበታተኑት የዩጎዝላቪያ ሪፑብሊኮችና ራስገዝ አስተዳደሮች መካከል ናቸው፡፡ እነኚህን ሪፑብሊኮች ቀድሞዉኑ ምን አንድ አደረጋቸው፣ በኋላስ ለምን መለያየት ፈለጉ የሚለው ትንሽ ግራ ያልተለመደ የሚመስል ነገር አለው፡፡ ከዩጎዝላቭ ሪፑብሊኮች በህዝብ ብዛትና ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ቀዳሚ የነበሩት ሰርቦች እና ክሮአቶች ቋንቋቸው የዲያሌክትን(ቀበሌኛን) ያህል እንኳ የማይለያይ ተመሳሳይ ነው፡፡የቋንቋ ምሁራንም ለየብቻ ማስቀመጥ ከብዷቸው ሰርቦክሮአት ይሉት ነበር ቋንቋውን(አሁን ለየብቻ ነው ብዙ ቦታ ላይ የሚፃፈው)፡፡ ዘራቸውም እንደስማቸው ሁለቱም ዩጎ ስላቮች(የደቡብ ስላቮች) ናቸው፡፡ ታሪካቸውን ያየን እንደሆነም ብዙ ነገሮችን ይጋራሉ፡፡ ኢኮኖሚያቸውን ያየን እንደሆነም ከአውሮፓ ድሀ እና በአንፃራዊነት ኋላቀር ከሚባሉ ህዝቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ በምንድን ነው የሚለያዩት – በሐይማኖት- አለቀ፡፡ በሀይማኖት ብቻ፡፡ ሰርቦች ኦርቶዶክስ ናቸው፣ ክሮአቶች ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰርቦች የኦሮቶዶክሱ ቅዱስ በፈጠረው ሲርሊክ ፊደል ይፅፋሉ፣ ካቶሊኮቹ ክሮአቶች ደግሞ ሮማዊ በሆነው ላቲን ፊደል ይፅፋሉ፡፡ እነዚህ ህዝቦች የደቡብ ስላቭ አንድነት አቀንቃኝ በነበረው ቲቶ አንድ ሆነው ሲኖሩ ቆይተው(አንድነቱ ግን ወደህዝቡ ያልሰረጸ እና በቲቶ ተሰሚነት ላይ የተመሰረተ ስለነበረ) ማርሻል ቲቶ ሲሞት አንደኛው ህዝብ ከሌላኛው ብሔር በወጣ መሪ ለመተዳደር ዝግጁ ስላልነበር ዩጎዝላቪያ በእቁብ መመራት ጀመረች፤ ዘንድሮ ከሰርቢያ፣ ቀጥሎ ከሞንቴኔግሮ፣ ከዚያ ከክሮሺያ፣ ከዚያ ከሜቄዶኒያ፣ ከዛ ከስሎቬኒያ፣ . . .እያሉ በየአመቱ በፈረቃ ዩጎዝላቪያን ሲያስተዳድሩ ቆዩ፡፡ ያው አስተዳደራቸው ራሱ ምንያህል አንድነት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነውና ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ሪፑብሊኮችና ራስገዝ […]