ጄኔራል ጻድቃንና ጤዛዋ ማሌሊት…በ40ኛው (በዶ/ር አረጋዊ በርኸ)

Editor’s note:በቅርቡ ከጄ/ል ጻድቃን ጋር ያደረግነውን ቃለ-መጠይቅ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በቃለ-መጠይቁ ከተነሱት ርዕሰ-ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ አስተያየታውን ልከውልናል፡፡ዶ/ር አረጋዊ ከህወሓት መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ እስከ1971 በሊቀመንበርነት፣ እስከ1978 ደግሞ በወታደራዊ መሪነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከተደረገው የአመራር ሽግሽግ በኋላ ድርጅቱን ለቅቀው በአውሮፓ ነዋሪ ናቸው፡፡ ጄ/ል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ ደግሞ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ ከ1978 ጀምሮ ደግሞ የማሌሊት የፖሊት ቢሮ አባል እና የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ በመሆን እስከትጥቅ ትግሉ ማብቂያ አገልግለዋል፡፡ —- (ዶ/ር አረጋዊ በርኸ) ባለፉት ሳምንታት ህወሓት የተመሰረተበት 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢህኣዴግ ባጠቃላይ መጀመርያ በመቀሌ ቀጥሎ በኣዲስ ኣበባ ተሰባስበው ለኣንድ ወር ሙሉ የሃገሪቱን ሃብት ሲያባክኑና ሲዝናኑበት እንደከረሙ ተገንዝበናል። መቸም የኣምባገነኖች ጭንቀት ማስተንፈሻ ነው መሰለኝ፣ ህዝብ በረሃብና በስራ-ኣጥነት ሲጠቃ፤ ሃገርን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ስትታፈን ሁሉም ኣምባገነኖች ማስተዳደር ሲያቅታቸው ምክንያት እየፈጠሩ በሃገርና በህዝብ ንብረት እንዲህ መቀለዳቸው የተለመደ ለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ የደርግ ኢሰፓና የነፃድቃን ማሌሊት ምስረታ ፌስታ ማስታወሱ በቂ ነው። ኣሁንም ሃገር በቀልና ዓለምኣቀፍ ጥናቶች እንደሚያስረዱት፣ ኢትዮጵያ የተጠመደችበትን ዙርያ-መለስ ቀውስና ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ስቃይ መረኑ ኣልፎ ሃገሪቱ ጭራሽ ስርዓት-ኣልባ ወደ እምትሆንበት ደረጃ እያሽቆለቆለች መሆንዋን በጥናት የተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም፣ ግብዞቹ የኢህኣዴግ መሪዎች መራር ሓቁን ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ሃገሪቱ የበለፀገች – ህዝቡ የደላው ይመስል፣ ኣሸሼ-ገዳሜ ሲሉ ይገኛሉ። ህወሓት/ኢህኣዴግ 40ኛ ዓመት-በዓል ብሎ ቅጥ ያጣ ድግስ በጣለበት […]