የልማት ርዳታ፤ የምዕራቡ ዓለምና የኤርትራ ግንኙነት

ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረችዉ ኤርትራ ከምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ጋ ያላት ግንኙነት የቀዘቀዘ መሆኑ የሚታይ ነዉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ትንሽ ሀገር በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ሃገራት ጋ ያላት ግንኙነትም የሞቀ የሚባል አይደለም።