ሁከት በፍራንክፉርት

የጀርመኗ ፍራንክፉርት ከተማ ትናት በዓመጽ ስትናጥ ነበር። መኪናዎች እና ጎማዎች አደባባዮች ላይ ሲነዱ፣ ቁሳቁሶች ሲወረወሩ የተቃውሞ ሰልፉ የተኪያሄደበት የከተማው ክፍልም በጥቁር ጢስ ተውጦ ታይቷል። የግጭቱ መንስዔ ደግሞ በፍራንክፉርት ከተማ አዲስ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው።