በመኪና አደጋ ያጣናት አርቲስት ሰብለ ተፈራ ባለቤት ከደረሰበት ሃዘን በተጨማሪ በህብረተሰቡ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል – ያዳምጡ
በትናንቱ ምርጫ 35.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው ፓርቲያቸው ሲሪዛ «ነፃይቱ ግሪክ» በአህፅሮቱ Anel ከተባለው ፓርቲ ጋር ተጣምሮ መንግሥት እንደሚመሰርት ተገልጿል ።
በትናንቱ ምርጫ 35.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው ፓርቲያቸው ሲሪዛ «ነፃይቱ ግሪክ» በአህፅሮቱ Anel ከተባለው ፓርቲ ጋር ተጣምሮ መንግሥት እንደሚመሰርት ተገልጿል ።
ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት»ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተዋጊዎቻቸዉ ጋር ከጥቂት ቀናት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋአል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።
ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «CPJ-በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ» ኢትዮጵያዉያኑን የዞን ዘጠኝ አምደ-መረብ አምደኞች «ብሎገርስ» ሸለመ።
የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ
በአዲሱ ዓመት ሰላማዊ ትግላቸዉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ አድርገዉ እንደሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።
አርቲስት እንድሪስ አህመድ ከ45 አመታት በፊት ነበር በብሄራዊ ቴዓትር ስራ የጀመሩት። ወሎ ክፍለ ሃገር ቢወለዱም ዳንስ የተማሩት በቅጽል ስሙ ውቤ በርሃ ተብሎ በሚታወቀው ደጃች ውቤ ሰፈር ነበር። አርቲስ እንድሪስ አህመድ ቡጊና ትዊስት ከደነሱበት ብሄራዊ ቴዓትር በጡረታ ቢሰናበቱም አሁን በፊልም ትወና ላይ ተሰማርተዋል።
ከትናንት ሐሙስ አንስቶ ለ 10 ቀናት የሚዘልቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ዩናይትድ ስቴትስ- ኒው ዮርክ ከተማ ተከፍቷል። በዚህም አውደ ርዕይ ላይ የ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።
በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አካባቢ አርሶአደሮች ያለ አግባብ ከይዞታችን ተፈናቅለናል ሲሉ ማማረራቸውን አንድ የዓይን ምስክር ተናገሩ ። ከተማይቱን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ በሺህዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ እና አርሶአደሮቹም ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለዶቼቬለ አስረድተዋል። …
የግንባሩን መሪዎች መርጧልም።እስካሁን ባለዉ ልምድ መሠረት የግንባሩ ዉሳኔዎችና መሪዎች ማለት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ወይም መርሕና መሪዎች ናቸዉ። ጉባኤዉንና ዉሳኔዎቹን ለዚሕ ሳምንት ዉይይታችን ርዕስ ያደረግነዉም ዉሳኔ፤ ምርጫዉ መላዉ ኢትዮጵያን ሥለ ሚነካ ነዉ።
የሚስረቀረቀዉ ድምፅዋ በመሰንቆ ጋር ሲታጀብ የስንቱን ባህላዊ ሙዚቃ አፍቃሪ ልብ እንዳሸፈተ ለአድማጭ እንተዉ። በተለይ አዲስ አበባ ቂርቆስ አካባቢ ይገኝ በነበረዉ የምሽት ክበቧ ትታወቃለች።
ከተለያዩ የሃገራት ወደ አዉሮጳ የሚፈልሰዉ ስደተኛ እጅግ በጨመረበት በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሰደዱ አፍሪቃዉያን ቁጥርም ጨምሯል። በሳምንቱ መጀመርያ ወደ 100 የሚጠጉ ኢትዮጵያን በአንድ የጭነት ማመላለሻ ታጭቀዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ በማምራት ላይ ሳሉ በዛምቢያ ፖሊስ መያዛቸዉ ተዘግበዋል።
ባደጉት አገሮች የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የሳይንስ ትሩፋቶች የሰው ልጅን የዕለት ተለት የኑሮ እንቅስቃሴ እየለወጡት ነው። ኡበር የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ አፕልኬሽን የታክሲ አገልግሎት ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም በተለምዷዊው ስርዓት አገልግሎት አቅራቢዎች ግን ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት ይደመጣል።
ከአለፉት 24 ዓመታት ወዲህ በስልጣን ላይ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ትናንት ባጠናቀቀው ድርጅታዊ ጉባዔ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ነው ተባለ። የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ችግሩ መፍትሄ ካላገኘ ለስርዓቱ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
(ደሕዴግ) ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝን የፓርቲዉ ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መርጧቸዋል።የግንባሩን መሥራች ዶክተር ካሱ ኢላላን ደግሞ አሰንብቷል።የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በበኩሉ የቀድሞዉን የፓርቲዉን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሠን ጨምሮ ቢያንስ ሠወስት ነባር ባለሥልጣናቱን አሰናብቷል
በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረደ በተነሳዉ ግጭት 85 አባዎራዎች ማለትም 305 ሕዝብ በአጎራባች ደቡብ ክልል መፈናቀሉንና 124 ቤቶች መቃጠላቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገ/ እግዚአብሄር የላከልን ዘገባ ያመለክታል።
ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ሳዑዲ አረቢያ በሃኪም ቤት ዉስጥ ከሰመመን ሳይነቃ የተኛዉ ኢትዮጵያዊ እናት ለተፈጠረዉ የሕክምና ስህተት እንዲከፈላቸዉ የታዘዘዉን ካሳ እንደማይቀበሉ አስታወቁ። 2.4 ሚሊዮን ሪያል ወይም 13 ሚሊዮን በላይ ብር የካሳ ክፍያ የተወሰነላቸው እናት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።
በኢትዮጵያ ከሚገኙት ከ30 ከሚበልጡት የመንግሥት እና በብዛት ከተከፈቱት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮ ከ90 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ተመርቀዋል። ዩኒቨርሲቲዎቸች እና የኮሌጆች ምሩቃን የቀሰሙትን እውቀት እና በሥልጠና ያገኙትን ሙያዊ ክሂሎት የተሻለ ኑሮ እድል ከፋች አድርገው ተመልክተውታል። ይሁንና፣ ገሀዱ እንደጠበቁት ሆና ሳያገኙት …
ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።
አፋር መስተዳደር በተከሰተው ድርቅ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በማለቅ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፤ የአካባቢው ባለሥልጣናትም ተገቢና ፈጣን ምላሽ አልሰጡም፤ እንደውም ድርቁን ለመደባበቅ ይሞክራሉ ሲሉ አማረዋል። የፌዴራልና የክልል መንግሥት ግን ችግሩን ለመቋቋም በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። አፋር መስተዳደር በተከሰተ ድርቅ …
ኦሮሞ ጥናት ማህበር ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በዋሽንግተን ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ ስብሰባውን አካሄደ። ከተያዩ ሃገራት የሄዱ የኦሮሞ እና ኦሮሞ ያልሆኑ ምሁራን በዚሁ ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን አቅርበዋል። ጥናቶቹ በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ አኗኗር፣ እንዲሁም፣ በማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ …
ኤርትራ በርካታ ዜጎችዋ ሃገርዋን እየለቀቁ ለአስከፊ ስደት የሚዳርጉበትን ሁኔታ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት እንዲያጣራ ጥሪ አቀረበች። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን ፍርድ እንዲያሰጥ የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መግለጫ ጠይቋል። Listen
ፍጥነቱ ጋብ አለ እንጂ በምዕራብ አፍሪቃ ሙሉ ለሙሉ አልተወገደም፤ኢቦላ። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 መገባደጃ ላይ ተቀስቅሶ ከ11 ሺህ በላይ አፍሪቃውያንን ቀጥፏል። ህፃናትን ከወላጆች፣ ዘመድን ከዘመድ አለያይቶ ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስም ፈጥሯል ይኸው የኢቦላ ተሐዋሲ። Listen
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና
ዶይቸ ቬለ የአማርኛ ዜና → LISTEN
የአማፂው ቡድን የታሊባን መሪ ሙላህ ሞሐመድ ኦማር መሞታቸውን የአፍጋኒስታን ታሊባን ከፍተኛ የአመራር አባላት ዛሬ አረጋገጡ። የአመራር አባላቱ የታሊባን ምክር ቤት ፣ ባለፉት 3 ዓመታት የኦማር ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አክታር ማንሱርን የሙላህ ተተኪ አድርጎ መምረጡንም አስታውቀዋል ። መሞታቸው ትናንት የተነገረው …
ኬንያን እና ኢትዮጵያን የጎበኙት የመጀመሪያው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እነዚሁ ሃገራት የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እንዲያሳስቡ 17 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚደንቱ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል። ደብዳቤውን በተናጠል እና ባንድነት ከላኩት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መካከል አንዱ «ፍሪደም …
በዓለማችን የ3,2 ሚሊዮን ሕዝብ የጤና ስጋት ነዉ። በየዓመቱም እስካሁን ግን ምንም ዓይነት የመከላከያ ክትባት አልተገኘለትም። በዚህ በሽታ ምክንያት ከሚጠፋዉ ሕይወት ዘጠና በመቶዉ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። ወባ በትንሿ ፍጥረት በትንኝ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ። ሰሞኑን ተስፋ ሰጪ ዜና እየተነገረለት ነዉ። Listen
የኢትዮጵያዊነት ውርስ እና ቅርስ ማህበረሰብ ዕሁድ ዕለት አምስተኛውን ክብረ በዓል በሰሜን አሜሪካ አክብሯል። በዚሁ ዕለት ኢትዮጵያውያን ፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከዋሽንግተን ዲሲ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል። ይህ ድርጅት፤ የቀድሞ ታሪክና ቅርፅን በመጠበቅ ለአሁኑ ትውልድ እና ለመጪው በክብር …
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና
ዛሬ ማምሻውን ኬንያ ይገባሉ ተብለው ለሚጠበቁት ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አቀባበል ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በመደረግ ላይ መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP አስታወቀ። እጅግ ብዙ ፀጥታ አስከባሪዎች በዋና ከተማይቱ ናይሮቢ ለጥበቃ ተሰማርተዋል ። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አውሮፕላኖችም ከተማዋን ከአየር …
የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርግሬት ታቸር በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የሚመራዉን መንግሥት ለመጣል ተጠቅመዉበታል የተባለ የከፍተኛዉ ምሥጢር ማስታወሻ ሰነድ በቅርቡ ይፋ ሆነ። Listen 1203
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና
ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሀደዉ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋና እና የፓርቲያቸዉ ከፍተኛ የአመራር አባላት ወታደራዊ ትግል ለማካሄድ ወደሚንቀሳቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለዉ መሄዳቸዉን አንድ የንቅናቄዉ አመራር አባል አስታወቁ። ቁጥራቸዉ ይፋ ያልተደረገዉ የአርበኞች ግንቦስ ሰባት የአመራር አባላትን ይዘዉ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ወደኤርትራ …
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እየመለሰ መሆኑን አስታወቀ። እስካሁን ድረስ 1,429 በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት 4,442 በኢትዮጵያ መንግስት ስደተኞች መመለሳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት 284 ኢትዮጵያውያን በጀልባ ወደ ጅቡቲ ለማጓዝ አቅዷል … Listen
በሺህዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የሚረዱት የ40 ዓመቱ አባ ሙሴ እጎአ ለ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከታጩት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተዘግቧል ። አባ ሙሴ ለዚህ ሽልማት መታጨታጨታው ክብሩ ለርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃውያንም ጭምር ነው ይላሉ ። አባ ሙሴ ዘርዐይ እዚህ አውሮፓ …
በምስራቃዊ ኢራቅ ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በጣለው የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 120 ሰዎች መገደላቸውንና 130 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸው ተገለፀ። ከኢራቅ ዋና ከተማ 35 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና የሺዓ እስልምና ተከታዮች በሚኖሩባት የካን ባኒ ሳድ ከተማ በመኪና ላይ የተጫነው …
ሰማያዊ ፓርቲ ገዚው ቡድን ይፈጽማቸዋል ካላቸው «ሕገ-ወጥ እና የማንአለብኝነት ተግባሩ እንዲቆጠብ፣ የዜጎች ሰብአዊ እና ዲሚክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ደጋግሞ» መጠየቁንና ማሳሰቡን ዛሬ ጠዋት በመግለጫው አሳስቧል።
የድንቅነሿ-ድንቅ ሐገር-ኢትዮጵያ ግን ከጋዜጠኛዉ እስከ ጠበቃዉ፤ ከፖለቲከኛዉ እስከ መብት ተሟጋቹ እንዳሉት ከግራ-አጋቢ፤ ዘፈቀዳዊ እርምጃ፤ ካሻቸዉን አድራጊ ሾሞችዋ ጋር በመቶ-ከመቶ የምርጫ ዉጤት ታጅባ ትቀበላቸዋለች።
በርካታ አፍሪቃውያን በሊቢያ በኩል የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮጳ ተሰደዋል። ብዙዎቹ ሲሳካላቸው ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ በረሀ መሀል ሞተዋል፣ ሌሎች ባሕር ውስጥ ሰምጠው ቀርተዋል። ፀሐዬ አያሌው፤ አውሮፓ ከገባ 11 ወር ሆነው።
ለአምስት ዓመታት በእስር የቆየችዉ የጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ ዛሬ መፈታቷ ተሰምቷል። የሽብር ተግባር በማሤር በሚል ክስ ተመሥርቶባት የነበረችዉ ርዕዮት 14ዓመት እስራት ተፈርዶባት በይግባኝ ወደአምስት ዓመት ዝቅ መደረጉ ይታወሳል። ።
የኢትዮጵያ መንግስት ለስለላ አገልግሎት ከአንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል ተባለ። አርቲክል 19 ተብሎ የሚጠራው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሃኪንግ ቲም ከተባለው ኩባንያ በሚያገኛቸው ግልጋሎቶች የራሱን ዜጎች ይሰልላል ሲሉ የኢትዮጵያን መንግስት ተችተዋል።
አንዳንድ የአፍሪቃ መሪዎች ከ20 እና 30 ዓመታት በላይ በሥልጣን መቆየታቸው አልበቃ ብሏቸው የየሀገራቸውን ሕገ-መንግሥት ለመቀየር ሲጥሩ፤ በዚህ ሰበብም ገሚሱ ዳግም ላይነሳ ተንኮታክቶ ሲወድቅ ታይቷል።
በኤርትራ መንግሥት ተንኳሽነት ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስጠነቀቁ።
የፊደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በነአቡበክር አህመድ መዝገብ በፀረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በሐምሌ ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተነግሯል። ፕሬዝደንቱ በአፍሪቃ በሚያደርጉት ጉብኝት የአባታቸዉ ሀገር ኬንያን እንደሚጎበኙ ቀደም ብሎ ነበር የተሰማዉ። ቆየት ብሎ ደግሞ ኢትዮጵያንም እንደሚሄዱ ተነገረ።