የኢትዮጵያዊነት ውርስ እና ቅርስ ማህበረሰብ ክብረ በዓል በዋሽንግተን ዲሲ
የኢትዮጵያዊነት ውርስ እና ቅርስ ማህበረሰብ ዕሁድ ዕለት አምስተኛውን ክብረ በዓል በሰሜን አሜሪካ አክብሯል። በዚሁ ዕለት ኢትዮጵያውያን ፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከዋሽንግተን ዲሲ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
ይህ ድርጅት፤ የቀድሞ ታሪክና ቅርፅን በመጠበቅ ለአሁኑ ትውልድ እና ለመጪው በክብር የማስተላለፍ ዓላማን ሰንቆ ይንቀሳቀሳል። የዘንድሮው ዝግጅት በተለይ በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪቃ በግፍ ለተገደሉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ እንደሆነም ተገልጿል። ከዋሽንግተን ዲሲ እና ሜሪላንድ ክፍለ ግዛቶችም ለበዓሉ እውቅና የሰጠ የምስክር ወረቀቶችም ተበርክቷል። Listen
