ድርቅ በአፋር መከሰቱ – ዶይቸ ቬለ
አፋር መስተዳደር በተከሰተው ድርቅ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በማለቅ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፤ የአካባቢው ባለሥልጣናትም ተገቢና ፈጣን ምላሽ አልሰጡም፤ እንደውም ድርቁን ለመደባበቅ ይሞክራሉ ሲሉ አማረዋል። የፌዴራልና የክልል መንግሥት ግን ችግሩን ለመቋቋም በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። አፋር መስተዳደር በተከሰተ ድርቅ በቀን በመቶ የሚቆጠሩ ከብቶች እያለቁ መሆናቸው እየተነገረ ነው። በአካባቢው ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር አንስቶ ከ12 ወራት በላይ በቂ ዝናብ አለመጣሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። በአካባቢው በቂ ዝናብ አለመጣሉ ለድርቁ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ዋነኛው ነው ተብሏል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደሆኑ የገለጡልን ግለሰብ ድርቁ አሁን እየተባባሰ ነው ይላሉ። Listen