የኦባማ የአፍሪቃ ጉብኝት እና የ«ፍሪደም ሀውስ» አስተያየት – ዶይቸ ቬለ

ኬንያን እና ኢትዮጵያን የጎበኙት የመጀመሪያው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እነዚሁ ሃገራት የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እንዲያሳስቡ 17 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚደንቱ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል። ደብዳቤውን በተናጠል እና ባንድነት ከላኩት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መካከል አንዱ «ፍሪደም ሀውስ» የተባለው ነው። የፖለቲካ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የሰብብዓዊ መብት ሁኔታ አሁንም እንደሚያሳስባቸው መንበሩን ዋሽንግተን ያደረገው የ«ፍሪደም ሀውስ» ፕሬዚደንት ማርክ ሊጋል ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። LISTEN