ዶክተር ብርሃኑና የፓርቲያቸዉ አመራሮች የትግል ርምጃ – ዶይቸ ቬለ

ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሀደዉ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋና እና የፓርቲያቸዉ ከፍተኛ የአመራር አባላት ወታደራዊ ትግል ለማካሄድ ወደሚንቀሳቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለዉ መሄዳቸዉን አንድ የንቅናቄዉ አመራር አባል አስታወቁ። ቁጥራቸዉ ይፋ ያልተደረገዉ የአርበኞች ግንቦስ ሰባት የአመራር አባላትን ይዘዉ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ወደኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በወታደራዊ ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዢ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የንቅናቄዉ የአመራር አባል ተናግረዋል። ለንደን የሚኖሩት የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባል ዶክተር ታደሰ ብሩ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ዶክተር ብርሃኑ እና ጓዶቻቸዉ ትግሉ ወደሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች ያመራሉ። መጀመሪያ ኤርትራ ቢሄዱም ግማሾቹ ታጋዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ ስላሉ ወደኢትዮጵያም ገብተዉ ለታጋዮቹ አመራር እየሰጡ እንደሚታገሉ ገልጸዋል። ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል → Listen

Berhanu Nega visit to Eritrea 120125495