54 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ታሰሩ – ዶይቸ ቬለ
የኬንያ ፖሊስ በሕገ- ወጥ አገሪትዋ ዉስጥ የሚኖሩ ያላቸዉን 54 ኢትዮጵያዉያን ማሰሩ ተመለከተ። እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ በኬንያ ናይሮቢ ካሳራኒ በሚባል አካባቢ ሦስት ክፍል ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን የተያዙት ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ እንደሆነ ገልጾአል።
የኬንያ ፖሊስ በሕገ- ወጥ አገሪትዋ ዉስጥ የሚኖሩ ያላቸዉን 54 ኢትዮጵያዉያን ማሰሩ ተመለከተ። እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ በኬንያ ናይሮቢ ካሳራኒ በሚባል አካባቢ ሦስት ክፍል ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን የተያዙት ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ እንደሆነ ገልጾአል።
የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበዉ መድረክ ዛሬ ባወጣዉ በመግለጫዉ የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ «ሕገ-ወጥ» በማለት ተቃዉሞታል። ዕቅዱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይላት በወሰዱት እርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን፤ በመቶ የሚቆጠሩ መቁሠላቸዉንም መድረክ አስታዉቋል።
የኦሮምያ ክልል መንግሥት እቅዱ በአዲስ አባባ ከተማ አካባቢ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችን ለማሳደግ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና ከተሞቹንም ዘመናዊ ለማድረግ የታሰበ እቅድ እንጂ የህዝቡን ጥቅሞች አሳልፎ ለመስጠት ያለመ አይደለም ፣ተቃውሞውም የተሳሳተ መረጃን መሠረት ያደረገ ነው ሲል ይከራከራል ።
በአፍሪቃ ሕብረት መቀመጫ መዲና አዲስ አበባ ላይ ስድስት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረዉ የጥበብ አድባር፤ በርካታ የጥበብ ፈርጦችን አፍርቷል። በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ጉልህ ድርሻ ያበረከቱት አንጋፋ አርቲስቶች ያላቸዉን እዉቀት ለአዲሱ ትዉልድ እያሻገሩ ብሔራዊ ቲያትር ዳግም 60ዓመታት እንዲጨምር የሞያ ትግል የሚያደረጉ ባለሞያዎች ምሥጋና ይገባቸዋል።
ለመጀመርያ ጊዜ ለሳቅ ዉድድር ጀርመን ሀገር እንደመጣ የሚናገረዉ ለዓለም የሳቅ ንጉሱ ለበላቸዉ ግርማ፤ ሳቅ ፍቅር ነዉ፤ ሳቅ መላ አካላትን የሚያንቀሳቅስ ስፖርት ነዉ፤ ሳቅ ሰላምን መፍጠርያ መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ጤና ነዉ፤ ሳቅ ደስታ ነዉ፤ ሳቅ ሕይወት ነዉ፤ ሳቅ የሰላም መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ የፍቅር መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ወጣት የሚያደርግ ነዉ።
መቀመጫዉን ዬኤስ አሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ላይ ያደረገዉ ለጋዜጠኞች የሚሟገተዉ ድርጅት «ሲፒጄ» የተባለ ተቋም ለዞን ዘጠኝ ጦማርያን የ 2015 ዓ,ምን ዓለማቀፍ የፕሪስ ነፃነት ሽልማት አበረከተ።
ጋዜጠኞች ከመንግስት አካላት መረጃ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸዉ ተመለከተ። ይህ የተገለፀዉ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ዛሬ በሂልተን ሆቴል ባካሄደዉ የምክክር መድረክ ነዉ።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 25.11.2015
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጠለዉ ቁርቁስና፣ ፖለቲካዊ ዉዝግብ አሁን ደግሞ በስፖርቱ ላይ ጫናዉን ያሳረፈ መስሏል። ኢትዮጵያ ከሕዳር 11 ጀምሮ ለ 15 ቀናት በምታስተናግደዉ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገሮች «ሴካፋ» የእግር ኳስ ሻምፒዮናን ኤርትራ እንዳትካፈል ኢትዮጵያ አግዳለች ሲል አሶሺየትድ ፕረስ ያወጣዉን ዘገባ ተከትሎ፤
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን በተመለከተ፤ የፌድራል መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ምክር ቤት፤ ሕዝብን ጠርቶ ያላወያየበት ምክንያት፤ የኦሮሞ ወይም የአከባቢ አርሶ አደሮችን አፈናቅለዉ መሬት ዘረፋ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ለማድርግ በመታቀዱ ነዉ ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ።
የዞን ዘጠኝ የድረ-ገጽ ጻሕፍት አባል የሆነው ዘላለም ክብረት የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ተሟጋች ድርጅት ሽልማትን ለመቀበል ወደ ፈረንሳይ ለመጓዝ ሲሞክር ተከለከለ። በእስር ቆይተው ከተፈቱት ጋዜጠኞችና የድረ-ገጽ ጻሕፍት መካከል ፓስፖርቶቻቸው ያልተመለሰላቸው ወደ ቀድሞ የስራ ገበታቸው መመለስ የተከለከሉ መኖራቸውንም አስታውቀዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት በአዳጊ ሃገራት የሚገኙ 225 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች እርግዝና እንዳይከሰት ለማድረግ ወይም ለማዘግየት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የወሊድ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ያመለክታል።
የመልካም አስተዳደር መጓደል በልማት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ማነቆ ነው። ሕዝብንም የልማት ውጤት ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደርጋል፣ በሚል ሕዝብ እና መንግሥት አዘውትረው በቅሬታ ሲናገሩ ይሰማል።
በፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት እንደሚያደርግ የተነገረው 7ኪሎ የተባለ መጽሔት ሰሞኑን በዩናይትድ ስቴትስ ሲልቨርሰፕሪንግ ሜሪላንድ ግዛት ተመርቋል።
የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ በተለያዩ መንገዶች ከሀገር የወጡ በርካታ ቅርሶችን እንዲመለሱ ለማድረግ ምሁራንና ባለሞያዎችን አወያየ።
«በጀርመንየኢትዮጵያተማሪዎችናምሩቃንማሕበር» ከጥቂት ቀናት በፊት 6ኛውን ዓመታዊ ስብሰባ አካሂዷል።
ላለፈዉ ስድስት ወራት የህዳሴ ግድብ በመባል የሚታወቀዉ እንዲያጠኑ የፈረንሣዩ «ቢአርኤል» እና የኔዝርላንዱ «ዴልታሬስ» የአማካሪ ኩባኒያዎች መሃል የተፈጠረዉን ኣለመግባባት ካልተፈታ ከሌሎች አመራጮች ዳግም ጨረታ ማዉጣት እንደሚጠበቅባቸዉ በዉሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።
ከምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ አባል አገራት አንዷ በሆነችው ቡሩንዲ መንግስት የጦር መሳሪያ አሰሳ እያካሄደ ነው። በአገሪቱ በተቃዋሚዎችና በፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ጅምላ ፍጅት እንዳያመራ አስግቷል።
« ሞት በኩላሊት ይብቃ» የተባለው የኩላሊት ህሙማን ማህበር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት የማከሚያ መሣሪዎች በነፃ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርቧል።
ሩስያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ግብፅ ውስጥ የሚገኙ 11,000 ሀገር ጎብኚ ዜጎቿን አስወጣች። ዛሬ እሁድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርካዲ ድዎርኮቪችን ዋቢ አድርጎ የሩሲያ ዓለም አቀፍ የዜና ኤጀንሲ (RIA) ዘግቧል።
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና listen
የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳ ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የ«ባላገሩ ምርጥ» የሙዚቃ ዉድድር በድምፅ አሸናፊ የሆነው ዳዊት ፅጌ ነው።
የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት በኤርትራ ላይ በጎርጎሪዮሳዊው 2009 ዓም የጣለውን የጦር መሪያ ማዕቀብ ባለፈው ሳምንት እስከ እስከ ኅዳር፣2016 ዓም አራዘመ። ምክር ቤቱ የወሰደው ይህ ውሳኔ የአውሮጳ ኅብረት በስደተኞች ጎርፍ የገጠመውን ቀውስ የስደተኞች መፍለቂያ ከሆኑት ኤርትራን ከመሳሰሉ ሃገራት ጋር ባንድነት መፍትሔ ለመሻት በያዘበት ወቅት ነው።
«ሥዕል ለኔ ሰላም የሚሰጠኝ፤ ሃሳብ ሲበዛብኝ፤ የሚያስጨንቁና የሚያሳዝኑ ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ፤ ነፃ የምሆንበት መሳርያዬ ነው፤» ይሉናል
በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች፣ ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ የሚላከው ገንዘብ መጠን እያደገ በመሄድ ላይ መሆኑ ተገለፀ። በዚህ መንገድ ወደ ሁለቱ ሃገራት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ጋር በንፅፅር ሲታይ ከፍተኛ መሆኑን የዓለም ባንክ አስታውቋል።
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና listen
የጀርመኑ ኮሜርስ፤የዩናይትድ ስቴትሱ ሲቲ እና የኬንያው ንግድ ባንኮች በአዲስ አበባ ቢሮ የመክፈት እቅድ ሰንቀዋል። በኢትዮጵያ ቢሮዎቻቸውን የከፈቱት የውጭ ኩባንያዎች ግን በዘርፉ ያለምንም ገደብ የመስራት ፈቃድ የላቸውም።
አፌን መረረኝ፤ ጠረን አመጣብኝ፤ የተለያዩ ሰዎች ሲናገሩት የሚደመጥ ችግር ነዉ። የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል? ዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ፤ አፍን ሊያመርሩ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ነዉ በዝርዝር ያብራሩት። ዶክተር ቶሌራ የተለያዩ በሽታዎችም አፍ ላይ ምሬት እንዲሰማን ሊያደርጉ …
ዶይቸ ቬለ Listen
መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከሚያወጣው ወጪ ባነሰ ታሪፍ አገልግሎት እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ ወጪውን ለማካካስ 50 በመቶና ከዚያም በላይ ሊደርስ የሚችል ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል መባሉን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስተባበለ።
ፍሪደም ሃውስ የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በዓለማችን ላይ የኢንተርኔት አፈና እየጨመረ መሄዱን በ2015ቱ የኢንተርኔት ነጻነት ሪፖርቱ ላይ ገለጸ። ድርጅቱ በጥናቱ ካካተታቸው 65 ሃገራት መካከል 32ቱ የኢንተርኔት ሳንሱርና አፈናን አጠናክረዋል ብሏል።
«ወቅቱ ክረምት ነዉ ካፊያ የሚጥልበት፤
መንገዱ ጠባብ ነዉ፤ ኮሮኮንች የበዛዉ ሰዉ የማይሄድበት፤
ላይጨልም ጨልሞ አይን ያጭበረብራል፤
ይህ የሕይወት አረም ወቅትን ተገን አድርጎ፤
ዓይንን ከጋረደ ማ ማንን ይለያ።»
የኢትዮጵያ መንግሥት «ድሕነትን ታሪክ እናደርጋለን» ባለበት፤ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት በድርብ አሐዝ ማደጉ በሚነገርበት ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ዳግም ምፅዋት መማፀናቸዉ በርግጥ ግራ-አጋቢ አነጋጋሪም ሆኗል
የሩሲያ A-321 የመንደኞች አዉሮፕላን ሲና በረሃ ግብፅ ዉስጥ ዛሬ ተከሰከሰ። 217 መንገደኞች እና 7 ሠራተኞችን የጫነዉ አዉሮፕላን በደረሰበት አደጋ ተሳፋሪዎቹ እንዳልተረፉ በግብፅ የሩሲያ ኤምባሲ በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለፁን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 01.11.201500
በየዓመቱስለጡት ጥቅምት ወር ካንሰር ግንዛቤ የማስጨበጫ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ ሃገራት ይካሄዳሉ። አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ከማድረግ አንስቶ የሰዉነት እንቅስቃሴ ማዘዉተር የትኛዉንም የአካል ክፍል ከሚያጠቃ ካንሰር ለመከላከል የሚረዳ ተቀዳሚ ርምጃ መሆኑን ሃኪሞች ይመክራሉ።
ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል።
በሣይንሳዊው መላ ምት ዘመናዊው የሰው ልጅ ምድር ላይ ተገኘ የሚባለው ከዛሬ 200,000 ዓመት በፊት ነው። ይኽ በሣይሳዊ አጠራሩ ሆሞ ሳፒያንስ (Homo Sapiens)፥ በላቲን ትርጓሜው ደግሞ «ጥበበኛው ሰው» አለያም «አዋቂው ሰው»፣ «ብልሁ ሰው» የሚል ስያሜ ያገኘው ዘመናዊ ሰው ምንጩ ከአፍሪቃ ብሎም ከኢትዮጵያ እንደሆነ ይነገራል።
ዞን ዘጠኝ በመባል በሚታወቁት አራት የድረገጽ ጸሐፍት እና አንድ ጋዜጠኛ ላይ በሽብርተኝነት የቀረበባቸዉን ክስ ፍርድ ቤት ዛሬ ዉድቅ አደረገ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበዉ ማስረጃ ሁሉ ደካማ መሆኑን ማመልከቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ ሊያደርጋቸው ባቀዳቸው ነጥቦች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር ዕርብ ዕለት ተወያይተዋል።
የኢትዮጵያ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርሪዎች አዲስ በተከናወነዉ የመንግሥት አባላት ሹመት እና አሠራር ላይ አስተያየት ሰጡ።
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የአዲሱ ካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ። ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ሲያሳውቁ አብዛኞቹ የመንግስት ባለስልጣናት በነበሩበት ሲቀጥሉ ጥቂት ለውጦች ደግሞ በሹመኞቹ ዘንድ ታይተዋል።
አንጋፋዉ ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ በ79ዓመቱ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቅርብ ጓደኞቹ የብዕር አርበኛ እያሉ የሚያወድሱት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ፀጋዬ ገብረመድህን አርአያ በሚል የብዕር ስምም ይታወቃል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሬፐንሊክ ኤምባሲ ለ 14 የቀድሞ ሠራተኞቹ ከ 25 ወራት በላይ ደሞዛቸውን ሳይከፍል መቅረቱን ፤ ክፍያ ያላገኙት ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ወቀሳ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
በአመታዊው የሐጅ የጸሎት ስነ-ስርዓት ላይ በደረሰው አደጋ ከሞቱት አብላጫውን ቁጥር የያዙት ኢራናውያን ናቸው። የኢራን መንግሥት464 ዜጎቹ መሞታቸውን አረጋግጧል።የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 13 መድረሱን አስታውቋል። የሟቾች ቁጥር ግን ከዚህም በላይ ነው እየተባለ ነው።
በአውሮፓ የተሻለ ህይወት ለመምራት ያሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ሰምጠው ሞተዋል። ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው። የስደተኞቹ ጩኸት እና የድረሱልን ጥሪያቸው በሀገሮቻቸው ሰሚ አላገኘም።