የኬንያ ፕሬዝደንት እና «አይ ሲ ሲ»
የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው። የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ የኬንያ ምርጫን ተከትሎ በሃገሪቱ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የብሄር ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት ፕሬዝደንቱ ወደ ዘሄግ ሲያቀኑ መንበረ ስልጣናቸውን በጊዜያዊነት ለምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ያስረክባሉ።
የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው። የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ የኬንያ ምርጫን ተከትሎ በሃገሪቱ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የብሄር ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት ፕሬዝደንቱ ወደ ዘሄግ ሲያቀኑ መንበረ ስልጣናቸውን በጊዜያዊነት ለምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ያስረክባሉ።
ዜና 03.10.2014
በዕለቱ የእንወያይ ቅንብር የኢትዮጵያ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸው ፈተናዎችና ዕድሎቻቸው በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ከሦስት ባለሙያዎች ጋር ውይይት አዘጋጅተናል። በውይይቱ የቆዳ ውጤቶችና የልብስ ዲዛይነር ዮናታን በቀለ፤የሶፍትዌርና ድረ-ገጽ ባለሙያ ሳሙኤል አርከበ እና የኢኮኖሚ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ ተሳትፈዋል።
ከአፍሪቃ እና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደ አውሮጳ የሚጎርፉ ስደተኞች በፈረንይዋ የወደብ ከተማ ካላይ አሳብረው በቅርብ ርቀት ወደ ምትገኘው እንግሊዝ ለመግባት በመጉረፍ ላይ ናቸው።
የጀርመን መንግሥት እራሱን እስላማዊ መንግሥት እያለ የሚጠራዉን አሸባሪ ቡድን ሰሜን ኢራቅ ውስጥ ለማጥቃት የሚደረገዉን ጥርት እያጠናከረ መሆኑ ተዘገበ። የጀርመኑ መከላከያ ሚኒስቴር ተልዕኮዉ በምን ሁኔታ ሊሆን እንደሚችል እየተጤነ እንደሆነም ተገልፆአል።
መራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል በጀርመን 25ኛ የውኅደት ቀን ዛሬ ሐኖቨር ከተማ ለተሰበሰቡ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ታዳሚያን ንግግር አደረጉ። መራሒተ-መንግሥቷ ጀርመንን በምሥራቅ እና ምዕራብ ጎራ ከፍሎ የነበረው የበርሊን ግንብ የዛሬ 25 ዓመት እንዲደረመስ አስተዋፅኦ ያደረጉ የምስራቅ ጀርመን ሰልፈኞችን ጀግንነት እና ጥረት በንግግራቸው አወድሰዋል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጋምቤላ መስተዳድር በጎደሬ ወረዳ ለረጅም ጊዜ በዚያ ሠፍረው ይኖሩ በነበሩ ና በአካባቢው መዠንገር ነባር ብሔረሰብ አባላት መካከል በተከሠተ ግጭት ብዙ ሰዎች መሞታቸው ተነግሮአል። ወደተለያዩ ቦታዎች የተሰደዱትም ጥቂቶች አይደሉም።
«ኦይሮፋይተር» የተባለው ዘመናዊ የጦር አይሮፕላን ሰውም ሆነ ዕቃ የሚጫንበት ዋናው አካል እንከን አለበት በማለት ጀርመን ለጊዜው ተጨማሪ ዩውሮፋይተር ከእንግዲህ ላለመግዛት ትናንት ካሳወቀች ወዲህ፤ አይሮፕላኑን በጋራ የሚሠሩት ኩባንያዎች፣ ላጋጠመው
የቱርክ ፓርላማ ፤ የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ከድንበር ማዶ ወደ ኢራቅና ሶሪያ በመግባት የ IS ታጣቂዎችን እንዲወጋ በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት መደገፉ ተነገረ። ከ3/4ኛ በላይ የሕዝብ እንደራሴዎች ያጸደቁት ውሳኔ በተጨማሪ የውጭ ሃገራት
በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል፤ ያለዉ የትምርት የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ ግንኙነት እጅግ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ከጎርጎረሳዉያኑ 1624 እስከ 1704 ከኖረዉ ጀርመናዊ ምሁር ሂዮብ ሩዶልፍ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ምሁራን በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ጥንታዊ ቅርሶች፤
ይህ በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተጀመረው 8028 አዲስ ነጻ የስልክ መስመር ነው። ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እገዛና ምክር የሚያገኙበት ነጻ የስልክ መስመር ግልጋሎት ከተጀመረ ጥቂት ወራት ተቆጠሩ።
በኢትዮጵያ ዘላቂ የመሬት አያያዝን ለማጠናከር በሚል የዓለም ባንክ እና ተባባሪ ደጋፊ ድርጅቶች ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከ100 ሚልዮን ዶላር በላይ ብድር ለመስጠት ፈቀዱ። ገንዘቡ የአፈር መመናመንን እና የደኖች መራቆትን
የቀድሞ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር የንስ ስቶልትንበርግ አዲሱ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ፣ ኔቶ ዋና ጸሐፊ በመሆን ትናንት በብራስልስ ስልጣናቸውን በይፋ ጀምረዋል። የ55 ዓመቱ ስቶልትንበርግ እአአ ከ2009 ዓም
ወደ ጀርመን እና አውሮጳ ለሚመጡ ስደተኞች መብት የሚሟገተው «ፕሮ አዙል» የተባለው መንግስታዊ ያልሆነው የጀርመናውያን ድርጅት በሜዲትሬንያን ባህር በኩል አድርገው ወደ ኢጣሊያ ለመግባት ሲሞክሩ ባህር ውስጥ ሰምጠው የሚሞቱትን ስደተኞች አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ አወጣ።
ኣንድ ዘመን ሁለቱም የአንድ ፓርቲ አባላትና ጓዶች ነበሩ፣ ፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍና ማሪና ሲልቫ! ከ 4 ቀናት በኋላ በሚካሄደው አቀፍ- አቀፍ ምርጫ ፣ የሆነው ሆኖ የመሪነቱን እርፍ ለመጨበጥ ሁለቱ ወይዛዝርት ብርቱ ፉክክር በማድረግ ላይ ናቸው።
ግብረ-ሃይሉ በ60 ቀናት ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት አስቧል። እንደ አንቶኒ ባንበሪ አሁን አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ ዓለም ከፍተኛ አደጋ ሊገጥመው ይችላል።
የባሕርዳሩ ድርድር ጥሩ ተስፋ እየታየበት ነዉ።እዚያዉ ደቡብ ሱዳን ዉስጥም ግጭቱ እየቀዘቀዘ ነዉ።ይሁንና የድርድሩ ሒደትም ሆነ የግጭቱ መቀዛቀዝ፤ አምባሳደሩ እንደሚሉት ለዘላቂ ሠላም ዋስተና ከሚሆኑበት ደርጃ አልደረሱም።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ልዩ ዘጋቢ የሆኑት ሼኢላ ኬቴሩት ሰኞ ዕለት ጅርጅታቸው ይፋ ባደረገው ዘገባ እንደገለፁት በኤርትራ ባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ የተነሳ በርካታ የሀገሪቱ ሰዎች ከነዚህም ውስጥ በተለይ ወጣቶች ሀገሪቷን ለቀው ለስደት ተዳርገዋል።
በምዕራብ አፍሪቃ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛዉን የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረቱ እንደቀጠለ ነው። ጀርመን በኤቦላ ተዋኅሲ ለተጠቁ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት አስር ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
ወደ ጀርመን እና አውሮጳ ለሚመጡ ስደተኞች መብት የሚሟገተው «ፕሮ አዙል» የተባለው መንግስታዊ ያልሆነው የጀርመናውያን ድርጅት በሜዲትሬንያን ባህር በኩል አድርገው ወደ ኢጣሊያ ለመግባት ሲሞክሩ ባህር ውስጥ ሰምጠው የሚሞቱትን ስደተኞች አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ አወጣ።
በጀርመን የኖርድራይን ቬስትፋልያ ፌዴራዊ ግዛት የሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጠባቂዎች በስደተኞች ላይ ፈፀሙት የተባለው በደል በሀገሪቱ ብርቱ ወቀሳ እና ቁጣ አፈራርቋል። ድርጊቱን ያወገዘው የጀርመን መንግሥት ባስቸኳይ እንዲጣራ
በዋሽግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ትናንት በተቃዋሚ ሰልፈኞች እና በኤምባሲው የፀጥታ ሰራተኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ወቅት አንድ የኤምባሲዉ ሰራተኛ ተኩስ መክፈቱን ዜና ምንጭ ሮይተርስ ዘገበ።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ልዩ ዘጋቢ የሆኑት ሼኢላ ኬቴሩት ሰኞ ዕለት ጅርጅታቸው ይፋ ባደረገው ዘገባ እንደገለፁት በኤርትራ ባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ የተነሳ በርካታ የሀገሪቱ ሰዎች ከነዚህም ውስጥ በተለይ ወጣቶች ሀገሪቷን ለቀው ለስደት ተዳርገዋል።
የቻይና ልዩ አስተዳደር ግዛት፥ ሆንግ ኮንግ ተማሪዎች መብታቸው እንዲከበር እና ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ በመጠየቅ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ በመጠናከሩ ድርጊቱ የሆንግ ኮንግን አስተዳደርን ብቻ ሳይሆን የፔኪንግ መንግሥትንም አስደንግጧል።
በአዲስ አበባ የአፍሪቃ አዳራሽ ዛሬ በአረንጓዴ ኤኮኖሚ እና በአካባቢ አየር ለውጥ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ሲካሄድ ውሏል። የጉባዔው ተሳታፊዎች እንዳመለከቱት፣ ተፈጥሮን በሚጠብቅ እና የአካባቢ አየርን በማይበክል ሁኔታ ምርታማነትን በዘላቂነት
ባለፈው ዓመት ከዚህ አለም በሞት በተለዩት ካርል ሄንዝ በም የተቋቋመው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ለ1862 በትራኮማ ለተጠቁ ሰዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ማቅረቡን አስታወቀ። ድርጅቱ ትራኮማን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።
በትናንቱ የበርሊን የወንዶች የማራቶች ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተሰብሯል።
ዘንድሮ የተስፋ አድማሥ ጨልሟል።ለመግለፅ በሚከብድ እርምጃ የዋሐን በመገደላቸዉ ልባችን ደምቷል።የቀዝቃዛዉ ጦርነት የጣረ ሞት ድባብ ተምልሶ በዚሕ ዘመንም እያደነን ነዉ።የአረብ አብዮት በሁከት ሲደመደም አየን።ዓለም ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲሕ አይታዉ በታዉቀዉ ሥደተኛ፤ተፈናቃይና ጥገኝነት ጠያቂ ሕዝብ ተጥለቅላቀች—
የሞ ኢብራሒም ተቋም በየዓመቱ ፤ በመልካም አስተዳደር፣ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ፤ በልማት ፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፍ የአፍሪቃ ሀገራት የት እንደሚገኙ የሚገመግምበትን ሰንጠረዥ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ዛሬ በጀርመን በርሊን ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያቱ ትርፊ ፀጋዬ እና ፈይሴ ታደሰ ተከታትለው በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ ወጡ። በእዚሁ የበርሊኑ የማራቶን ሩጫ ፉክክር ኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ የዓለም ክብረ ወሰን ሰብሯል።
የናይጀሪያ ጦር በቦኮ ሀራም አንፃር በጀመረው ትግሉ እንደቀናው ገለጸ። የናይጀሪያ ጦር ባለፉት ጊዚያት በአሸባሪው ድርጅት ቦኮ ሀራም አንፃር በተደጋጋሚ አሰመዘገብኩት ያለው ድል ብዙ ማነጋገር ይዞዋል።
በብሔራዊ በዓልነቱ የሚታወቀዉ የኢትዮጵያውያን የመስቀል በዓል፤ በሀገሪቱ ዙርያ በደማቅ ተከብሮ ውሏል።
በይርጋለም ከተማ የሚገኘው የቤዛዊት የወጣቶች ማዕከል ባዘጋጀው የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃግብር የተሳተፉ ወጣቶችን እና ስራዎቻቸውን ዝግጅቱ ባጭሩ ይቃኛል።
ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) መሰረት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ለስደት በመዳረግ ኤርትራን ተከትላ ከአፍሪቃ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ መንግስት በአከራካሪው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ጋዜጠኞችን ለእስር፤እንግልትና ስደት ይዳርጋል ሲሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይተቻሉ።
በአዉሮጳ ሀገራት ለስደተኞች የሚከራከሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ሰሞኑን ለሁለት ቀናት የዘለቀ ዓውደ ጥናት ብራስልስ ላይ አካሂደዋል።
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለቱ ሀገራት ዙርያ ዉይይት አደረጉ። የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ትናንት ኒዮርክ ላይ ዉይይት ከማድረጋቸዉ በፊት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤
ርዕሰ አዉዳ ዓመት፤ ወርኃ አደይ ወርኃ ጽጌን ተከትሎ በኢትዮጵያ በተለያዩ ብሄር ብሔረሰቦች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ለመከበር በጉጉት የሚጠበቀዉ የመስቀል በዓል፤ ከሐይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ባህላዊ ገፅታዉ አከባበሩ ህብረ- ቀለማዊ ነዉ።
የተመድ አባል ሀገራት ፅንፈኞችን ለመቆጣጠር ጠንካራ ርምጃ እንዲወስዱ የየተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ባሳለፈው ውሳኔ አሳሰበ። ሽብርተኝነትን ለማሸነፍ አባል ሀገራት ባጋራ መስራት እንዳለባቸው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ተማፀነዋል።
ስኖደን የተሸለመዉ በዓለም የማትደፈረዉን ሐያል ሐገር በማጋለጥ ለመናገር ነፃነት መከበር መቆሙን በማረጋገጡ ነዉ።ለወትሮዉ የተሸላሚዎች ሥም ዝርዝር በይፋ የሚነገርበት የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ግን መስሪያ ቤት ግን የዘንድሮ ተሸላሚዎች ስም ዝርዝር ከቢሮዉ እንዳይነገር አግዷል
ተበዳዮቹ እንደሚሉት ተጠርጣሪዉ ክስ ተመሥርቶበት ከሐገር እንዳይወጣ በፍርድ ቤት ቢታገድም በኬንያ አቋርጦ ዱባይ መግባት አልተሳነዉም::
የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ዶክተር ክርስቶፈር ዳይን እንደሚሉት ችግሩ ፈጥኖ ካልተገታ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት በፖለቲካዊ ቀዉስ መናወጣቸዉ የማይቀር ነዉ።የዳይን ጥናት እንደሚማመለክተዉ የኤቦላ ስርጭት በዚሑ ከቀጠለ የተለካፊዉ ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ ከሃያ ሺ ይበልጣል።
አዲስ አበባ ዉስጥ በተፈራረሙት ዉል መሠረት ሁለቱ ሐገራት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ አርባ ኢትዮጵያዉያን የምሕንድስና ተማሪዎችን በጋራ ያስተምራሉ።
የኤኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በጋሻዉ ግን ሁለቱ ተቋማት የአሜሪካና የአዉሮጳን ጥቅም ከማስከበር አልፈዉ ለአፍሪቃ የሚረዳ ነገር መክረዉ፤አድርገዉም አያዉቁም።ኢትዮጵያም የዕዳዋን መጠን ለመቆጣጠር የራስዋን ጠቃሚ መርሕ መከተል ነዉ የሚገባት።