በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የኢቦላን ተኀዋሲ መስፋፋት መግታት ይቻል ዘንድ ባለሙያዎችን ያሠማራው የአፍሪቃ ሕብረት አዲስ ተስፋ መኖሩን አስታወቀ። የሕብረቱ ጽ/ቤትና የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽኑ በሕብረት በመሰለፍ፤ ተስፋው ፤

በቅርቡ ሐገሩን ጥሎ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ከትናንት በስተያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የጋዜጠኛ ሚሊዮን ባልደረቦች እና ጓደኞች እንደሚሉት ሚሊዮን ያረፈዉ ለሁለት ሳምንት ያሕል ከታመመ በሕዋላ ነዉ።

በዓለም ዙሪያ ፣ የዓለም የምግብ ዋስትና ዕለት ታስቦ ይውላል። በኢትዮጵያም በዋዜማው ይታሰባል። ጥቅምት 6 ወይም (Oct 16) የሚታሰበው ፤ በመጪው 2015 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 70 ዓመት የሚደፍነውን ፣ የተባበሩት መንግሥታትን የምግብና የግብርና ድርጅት ምሥረታ መንስዔ በማድረግ ነው።

በላይቤሪያ የተከሰተው የኤቦላ ወረርሽኝ ታማሚዎችን ብቻ ሳይሆን የጤና መኮንኖችዋን እና ሀኪሞችዋን ጭምር ስጋት ላይ ጥሎዋል። የጤና መኮንኖቹ እና ሀኪሞቹ በኤቦላ የተያዙትን ሰዎች በማስታመሙ ተግባራቸው ላይ

በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡባት የመን ዛሬም የተረጋጋች አትመስልም። ከሰንዓ የሚወጡ የተለያዩ የዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚለዉ በሁቲ አማፅያንና በአልቃይዳ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደዉ ዉጊያ ቢያንስ የ12 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል።

የሴቶችና እናቶችን የስነተዋልዶ ጤና ለማሻሻል ከሚረዱ እንቅስቃሴዎች አንዱ ነፍሰ ጡር እናቶች በሚገላገሉበት ጊዜ በተገቢዉ መንገድ በሰለጠኑ አዋላጆች መረዳት መቻላቸዉ ነዉ። ይህን እድል ያላገኙና የማያገኙ ደግሞ በተራዘመ ምጥ ምክንያት ለፊስቱላ ተጋልጠዉ የከፋ ህይወት ለመግፋት ይዳረጋሉ።

ኢትዮጵያ በመጪው ጥር ወር መጀመሪያ ላይ የዓለም የካፒታል ገበያን እንደምትቀላቀል ሮይተርስ የገንዘብ ሜኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ ባለፈዉ ሳምንት ዘግቧል። ውሳኔው መንግስት የሚያከናውናቸውን የመሰረተ-ልማት ግንባታዎች ለመደገፍ የሚያስችል

የኢቦላ በሽታ ከምዕራብ አፍሪካ እስከ ሰሜን አሜሪካ ድረስ ዓለምን እያተራመሰ ነው። በተኅዋሲው የተያዘ ሰው ከከስድስት እስከ አስራ ስድስት ባሉ ቀናት ዉስጥ ከታደለ ከህመሙ ይፈወሳል።አብዛኞቹ ግን ይሞታሉ። ለዓለም ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ ነው የተባለው የኢቦላ ወረርሽኝ በተባበሩትመንግስታትድርጅትየአስቸኳይጊዜግብረ-ሃይል ተቋቁሞለታል።

በዛሬው የስፖርት ክፍለ ጊዜ ባሳምንቱ መጨረሻ የተካሄዱትን የአፍሪቃ እና የአውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎች፣ አትሌቲክስ፣ የሜዳ ቴኒስ እና ፎርሚውላ 1 የመኪና እሽቅድምድም ውድድር ይቃኛል።

አርቲስት ተሾመ አሰግድ ለኪነ ጥበብ ላበረከተው አስተዋፅዖ ክብር እና ምሥጋና ተቸረው። ባለፈው ቅዳሜ በዩኤስ አሜሪካ የሚኒያፖሊስ ከተማ በተደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ አርቲስት ተሾመ በሕይወት ጎዳና ያጋጠሙትን ፈተናዎች በፅናት በማለፍ ፣ በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ላይ ጉልህ ሚና መጫወት መቻሉ እና ለሌሎችም አርአያ ሊሆን መቻሉ ተገልጾዋል።

ገንዘቡ እንደ ቃሉ ሁሉ ይንዥቀዠቅ ይሆናል።ለጋዛ ነዋሪዎች ሲሚንቶ፤ ብርድ ልብስ፤ የዱቄት ወተት ይገዛ-ይታደልበት ይሆናልም።ለወደፊቱ ተስፋና ዋስትና መሆኑ ግን ወይዘሮ አል ሔሉዉ እንደሚሉት ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።

የአፍሪቃውያት ሀገራት ሚንስትሮች አደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ስለደቀነው ስጋት ሰሞኑን መከሩ። አፍሪቃ ብዙ አደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ባይመረትባትም፣ ለሕገ ወጡ ዓለም አቀፍ የአደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ መሸጋገሪያ መሆኗ የአህጉሩን መንግሥታት በማሳሰቡ፣ ይህንኑ ሕገ ወጥ ንግድ መቆጣጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ በስፋት ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ጥቅምት 2/2007 ዓ.ም. አቶ በላይ ፈቃዱን በፕሬዝደንትነት መምረጡን አስታውቋል። አቶ በላይ በፕሬዝደንትነት የተመረጡትየቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢንጂኔር ግዛቸው ሽፈራው ስላጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ መሆኑን የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ ስዩም መንገሻ ተናግረዋል።

ለጋዛ ሰርጥ የመልሶ ግንባታ ካይሮ ውስጥ የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የለጋሾች ጉባኤ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከፈቱ። በጉባኤው ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቃል መገባቱ ተነገረ።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በ30 እና 40 በመቶ ይገመት የነበረዉ የኢትዮጵያ የደን ይዞታ ባለፉት ሁለትና ሶስት አስርት ዓመታት ዉስጥ በየጊዜዉ እየቀነሰ ወደ3በመቶ ገደማ መቅረቱን የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁሟል።

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ካለፉት ወራት ወዲህ ወደፊት መራመድ ተስኖታል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ተፋላሚዎቹ ወገኖች ገላጋይ ሀሳብ ላይ እንዲደርሱ ለማስገደድ ፍላጎቱ እና አቅሙ የጎደለው ይመስላል።

የዘንድሮ የሰላም የኖቤል ሽልማት ለፓኪስታንና ህንድ የሕጻናት ጉዳይ ተቆርቋሪዎች ተሰጠ። ኦስሎ ኖርዊ የሚገኘዉ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ዛሬ እንደለገለፀዉ ፓኪስታናዊትዋ ማላላ ይሱፍዛይ እና ህንዳዊዉ ካይላሽ ሳትያርቲ በፀረ -ሕጻናት እና ወጣት እንቅስቃሴ እንዲሁም ሕጻናት በሙሉ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ባደረጉት ትግል ለሽልማት በቅተዋል።

የቤልጅግ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ፣ባለፈው ግንቦት ወር በተደረገው ምርጫ፣ አብላጫ ድምፅ ያገኙት የቤልጅግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት ለማቋቋም መስማማታቸውን አስታወቁ።ከ 135 ቀናት ውይይትና ድርድር በኋላ መንግሥት ለመመሥረት የተስማሙት የሊብራልና

ባለፈዉ ዓመት540 ሰዉ የጫነት አንዲት ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ዉስጥ ስትሰጥም ወደአራት መቶ የሚሆኑት ህይወታቸዉ ማለፉ ይታወሳል። ሁኔታዉን አሳፋሪ የታሪክ ጥላሸት ሲሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተችተዉታል። የእሳቸዉን አባባልም አብዛኞች ደግመዉታል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ፣ ከተቀናቃኙና ተፋላሚው ኃይል ጋር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርድ ፤ በኢጋድ ሸምጋይነት የሰላም ውይይት በመካሄድ ላይ ቢሆንም፣ የመንግሥት ለውጥ እንዲደረግ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያና ኖርዌይ የሚያደርጉትን ጉትጎታ ዋናው ሸምጋይ

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በሶስት የግል መጽሄቶች ባለቤቶች ላይ በሌሉበት ውሳኔ ማሳለፉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል። እንደዘገባዉ ፍርድ ቤቱ መጽሔቶቹ ሎሚ፤ አዲስ ጉዳይ እና ፋክት የተሰኙት ሲሆኑ ውሳኔው በአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።

የ 90 ዓመትዋ ደራሲ ሩት ቫይስ እትብታቸዉ የተቀበረበት ሀገረ ጀርመንን የሚያዉቁት እጅግ በጥቂቱ ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ ግን አዛዉንቷ በሥነ-ጽሑፍ ስራቸዉ እጅግ ታዋቂና የተከበሩ ናቸዉ፤ ምናልባትም ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሩት እጅግ ታዋቂዋና ብቸኛዋ የጀርመናዊት ጋዜጠኛ ናቸዉ ማለትም ይቻላል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት « አይ ኤም ኤፍ» የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአሁኑ 2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት አድጓል ሲል አስታወቀ። ይኸው የኤኮኖሚ ዕድገት በዋናነት በከፍተኛ የግብርና ምርት፤ በመንግሥትና በውጭ መዋዕለ ንዋይ የታገዘ መሆኑን የተቋሙ

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በዛሬዉ ዕለት በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና ከ70 በላይም መጎዳታቸዉን የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የጠቀሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ከላይቤሪያ የተመለሰው አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመምተኛ ቶማስ ኤሪክ ዳንከን ትናንት በዳላስ ቴክስስ ካረፈ ወዲህ ይህን አደጋና በሽታ ለመታገልና ለመግታት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያሻ በመነገር ላይ ነው።

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።

ሰብል በመስክ ላይ እያለ ወይም በሚደርቅበት፣ በሚከማችበት ወይም በሚጓጓዝበት ጊዜ በሚፈጠር ሻጋታ ውስጥ የሚገኘው አፍላቶክሲን የሚባለውን መርዛማ ንጥረ ነገር በአፍሪቃ በቆሎን እና ለውዝን የመሳሰሉ የግብርና

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።

ከሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ወደ ደቡብ እስከ ምድር ሰቅ የሚዘልቁና ወደመጡበት ሳይደናገሩ የሚመለሱ አእዋፍ ምንቃራቸው አጠገብ በቀኝ በኩል አቅጣጫ አመላካች የተፈጥሮ «ኮምፓስ» አላቸው። የሌሊት አእዋፍ ፣ ዓይን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ አቅጣጫ ጠቋሚ አላቸው።

በምዕራብ አፍሪቃ ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በተከሰተው እና በዓለም እስከዛሬ አስከፊ መሆኑ በተነገረለት የኤቦላ ወረርሽኝ የ3,431 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱን፣እንዲሁም፣ በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴየራ ልዮን ወደ 7,470 ሰዎች ደግሞ በኤቦላ አስተላላፊ ተሀዋሲ መያዛቸውን የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አስታውቋል።

የሶማልያ ብሄራዊ ጦርና የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል ‘አሚሶም’ከአሸባብ አክራሪ ኃይል ጠንካራ ይዞታዎች መካከል አንዷ ነች የተባለችውን የባራዌ የወደብ ከተማ ከቀናት በፊት ነፃ አዉጥተዋል። ለበርካታ ዓመታት ከሶማልያ ማዕከላዊ መንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆና የቆየችው የባራዌ ከተማ ለአሸባብ ዋንኛ የገቢ ምንጭም ነበረች።

በሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየሳምንቱ በሊቢያ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ። የአንዳንዶቹ እጣ ፋንታ በሜዲትሪያን ባህር ሰምጦ መሞት ሲሆን በህይወት የተረፉት ደግሞ በስፓኝ፣ በማልታ፣ በግሪክ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በኢጣሊያ አድርገው ወደሰሜን አውሮፓ ለመግባት ይሞክራሉ።

አፍሪቃ ዉስጥ በስተምዕራብ በሚገኙ አራት እና አምስት ሃገራት ቀስ በቀስ የተስፋፋዉ ኤቦላ ወደአዉሮጳም እንዳይዛመት ስጋቱ አሁንም አለ። ዓለም ከገዳዩ የኤቦላ ተሐዋሲ ጋ የተያያዘዉን ፍልሚያ ገና በድል ሳያጠናቅቅ እሱን መሰል ማርቡርግ የተሰኘ አደገኛ ተሐዋሲ ዩጋንዳ ዉስጥ መታየቱ ተሰምቷል።

ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በዋለባቸው ያለፉት ሁለት ዐሠርተ- ዓመታት ውስጥ በዓለም ሕዝብ ፤ መንግሥታትና ተቋማት የርስ በርስ ግንኙነት ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን በማበረታታት ሃገራት ዓመታዊ የምርት መጠናቸውን (GDP) እንዲያሳድጉ በር ከፍቷል።

ግላስኮው ያስተናገደችው እና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊዎች የነበሩበት አምስተኛው የስኮትላንድ ታላቅ ሩጫ ፣ የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ2014 ዓም የዓለም ምርጥ አትሌት ዕጩዎችን ስም ይፋ ማድረጉ፣ በቅርቡ

ሚስተር የንስ ስቶልቴንበርግ 28 አባል መንግሥታት የሚገኙበትን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶ አዲስ ዋና ጸሐፊ ሆነው ስራቸውን በይፋ የጀመሩት ባለፈው ረቡዕ ነበር። ስቶልቴንበርግ ግዙፉ የምዕራባዉያን ወታደራዊ ግንባር ከዚህ ቀደም በበላይነት የመሩት አንደርስ ፎኽ ራስሙሰንን ነው የተኩት።

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ የጋራ ስብሰባ አካሄዱ። ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ ሀገሪቱ በአዲሱ ዓመት 2007 የሚጠብቃትን እንቅስቃሴ እና ባለፈው ዓመት የታዩትን ጉድለቶች በዝርዝር ገልጸዋል።

ራሱን «አይ ኤስ» ወይም እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ከአንድ ዓመት በፊት በሶርያ አግቶት የነበረውን የ47 ዓመት እንግሊዛዊ አለን ሄኒንግን አንገት ቀልቶ መግደሉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በጥብቅ በማውገዝ የብሪታንያ መንግሥት በቡድኑ እና በሀገሪቱ አሉ በሚባሉ የቡድኑ ደጋፊዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።