የገንዘብ ርዳታ ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት
የአውሮጳ ህብረት፣ የዓለም ባንክ እና ሌሎች ያካባባ የልማት ባንኮች ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ስምንት ቢልዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገቡ። ይህ ዜና ይፋ የሆነው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ከዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ኪም ጋር ዛሬ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ ነው።
የአውሮጳ ህብረት፣ የዓለም ባንክ እና ሌሎች ያካባባ የልማት ባንኮች ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ስምንት ቢልዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገቡ። ይህ ዜና ይፋ የሆነው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ከዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ኪም ጋር ዛሬ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ ነው።
የፊደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት ሳምንት በፊት በማነሳሳት ጥፋተኛ ነህ ያለዉን ታዋቂ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የሶስት ዓመት እስራት በይኖአል።
የምስራቅ ዩክሬይን ቀዉስ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ዩክሬይን አዲስ ፓርላማን መርጣለች። መፍቀሬ አዉሮጳ ፓርቲዎችም አብላጫ ድምፅን አግኝተዋል።
ጀርመን ፍራንክፈርት ላይ ለ 33 ኛ ግዜ በተካሄደዉ የማራቶን ዉድድር ከወንዶች ኬንያዊው ማርክ ኪብቶ አንደኛ በመሆን አጠናቆአል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሚና ይመለከታል። ችግር እና መፍትሔው ምንድን ነው?
ውይይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሚና ይመለከታል። ችግር እና መፍትሔው ምንድን ነው?
የአረብ አብዮት የትዉልድ ቦታ በሆነችዉ በቱኒዝያ ዛሬ የመጀመርያ የፓርላማ ምርጫ ሲደረግ ዋለ።
ዛምቢያ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ከተላቀቀች ትናንት፡ እአአ ጥቅምት ሀያ አራት፡ 2014 ዓም ሀምሳ ዓመት ሆናት። የነፃነቱ ዓወዳመት ትናንት በመላ ዛምቢያ በይፋ የተከበረ ሲሆን፡ የሀገሪቱ ዜጎች ዕለቱን በዚህ በያዝነው የጥቅምት ወር በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ራስን ከኤድስ ፣ ካልታቀደ እርግዝና እና ከተለያዩ የአባለዘር በሽታዎች ለመከላከል፤ በኮንዶም መጠቀም እንዳለባቸው፤ ትምህርት የሚሰጡ የተለያዩ ማስታወቂያዎች በየጊዜው ቀርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሰዎች በነፃ ወይም በገንዘብ መከላከያውን የሚያገኙበት አጋጣሚዎች ተፈጥረዋል።
የፈረንሳይ መንግሥት ጠቡን ለማርገብ አንድ መቶ ያሕል ተጨማሪ ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ ከተማይቱ አዝምቷል።ሥለት የታጠቁ ወጣቶች ጭምር በተሳተፉበት ግጭት ቢያንስ ስድስት ስደተኞች መቁሰላቸዉ ተዘግቧል። ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን ከየሐገራቸዉ ተሰደዉም ለመደባደብ አልሰነፉም።
ከሰባት ዞኖች የተወጣጡ የፓርቲዉ አመራር አባላት እንደሚሉት የፓርቲዉ ብሔራዊ ምክር ቤት የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ በላይ በፈቃዱን መተካቱ ሕገ-ወጥ ነዉ
ስለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ሲወሳ፣ የውጭው ዓለም ከመቅጽበት የሚያስበው ስለጦርነት ፤ ቀውስ የተፈጥሮ አደጋና የመሳሰለው ነው። አፍሪቃን አጨለምው ለሚመለከቱ ወገኖች የሆነው ሆኖ ፣ የቦትስዋና ይዞታ አስተሳሰባቸው መሠረተቢስና አሉታዊነት የተሞላ መሆኑን
ባለፈው እሁድ ፣ አንድ ስባሪ ኮከብ ወደ ማርስ ከዚያ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ መጠጋቱ ፤ ለምን የሥነ ፈለክ ጠበብትን ትኩረት ሳበ? ስባሪ ከዋክብት ከየት ነው መነሻቸው? 9ኛው ፕላኔት አይደለም ተብሎ እ ጎ አ በ 2006 ከ ዝርዝር እንዲወጣ የተደረገው
በካናዳዋ ኦታዋ ከተማ ምክር ቤት ትናንት ከደረሰዉ ድንገተኛ ጥቃት በኋላ የሀገሪቱ መንግሥት ለደህንነት እና የፀጥታ ጉዳይ ተቋማት ሰፋ ያለ መብትና ስልጣን ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ክትባቶቹን ለማምረትና ለማሰራጨት የሚያስፈልገዉን በቢሊዮን የሚቆጠር ወጪ ያስፈልጋል።ወጪዉን የሚሽፍነዉ ወገን እስካሁን በግልፅ አልታወቀም።ጥረቱ በብዙዎች እምነት የዘገየ ያም ሆኖ ገዳዩን በሽታ ድል ለማድረግ ተስፋ ሰጪ ነዉ።ተስፋዉ ግን የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣን እንደሚሉት አሁንም በብዙ ጥያቄዎች የተከበበ ነዉ።
የጎርጎረሳዉያኑ መስከረም ወር በገባ በሶስተኛዉ ቅዳሜ በጀርመን የባቫርያ ግዛት መዲና በሆነችዉ ሙኒክ ከተማ ላይ የሚጀምረዉ ባህላዊዉ የቢራ ድግስ፤ ዘንድሮ ከተለያዩ የዓለም ሀገራትና አካባቢዎች የተሰባሰቡ 6, 3 ሚሊዮን እንግዶችን አስተናግዶ የዛሬ አስር ቀን ግድም ተጠናቅዋል።
በተደጋጋሚና ተራበራ ወጣት ሴቶች የሞቀ ቤታቸዉ እየጣሉ ወደሶርያና ኢራቅ በጦር ፍልሚያዉና እስላማዊ መንግሥት እዚያ አብሮ በማቋቋሙ ሂደት ላይ ራሳቸዉ እንደሚሉት ለመሳተፍ ከአዉሮጳና ከአሜሪካ እየተነሱ መንጎድ ከጀመሩ ጊዜዉ ትንሽ ሰንበት ብሏል።
ለሶማሊያ ቋሚ ፌደራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ይበጃል በሚል የሚወያይ ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ በአፍሪቃ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነዉ።
የአውሮፓ ፓርላማ ጥቅምት 22 ቀን 200 7 ሥልጣን የሚረከቡትን ፣ አዲሱ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዣን ክሎድ ዩንከር ያቀረቧቸውን የኮሚሽን ሹማማንት የሥልጣን ቦታ በዛሬው ዕለት በድምጽ ማጽደቁ ተነገረ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ፤ ከገዥው ፓርቲ የተለየ አማራጭ የፖለቲካ አጅንዳዎች ይዘው የቀረቡ 9 የተቃውሞ ፓርቲዎች፤ በሚያስሟሟቸው ጉዳዮች ተባብረው ለመሥራት መስማማታቸው ተገለጠ።
ባለፈው እሁድ ፣ አንድ ስባሪ ኮከብ ወደ ማርስ ከዚያ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ መጠጋቱ ፤ ለምን የሥነ ፈለክ ጠበብትን ትኩረት ሳበ? ስባሪ ከዋክብት ከየት ነው መነሻቸው? 9ኛው ፕላኔት አይደለም ተብሎ እ ጎ አ በ 2006 ከ ዝርዝር እንዲወጣ የተደረገው
መኪናቸዉን እያሽከረከሩ ከቤታቸዉ ቅጥረ-ግቢ ሲገቢ የታጠቁ ሰዎች ተከትለዋቸዉ— «ዘዉ።» ዘበኛዉ ጮኸ—«ሊገድልዎት ነዉ—»እያለ።ለሐኪሙ የተዘጋጁት ጥይቶች የዘበኛዉን አካል በረቃቀሱት—ሞተ።
የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት በሉክዘንበርግ ባካሄዱት ስብሰባ የኤቦላ ተሐዋሲ መዛመት ስለሚገታበት ርምጃ ተወያይተዋል።
በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ግዛት ዉስጥ በደረሰ ጥቃት በጥቂት ቀናት ከሃምሳ ሰዉ በላይ ህይወቱን አጥቷል።
ቀደም ባሉ ዓመታት የበለፀጉት ሃገራት በሽታዎች ተብለዉ ከሚፈረጁት ካንሰር አንዱ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተዉ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የኗኗር ሁኔታ መለወጥን ተከትሎ በአዳጊና ደሀ ሃገራትም መስፋፋቱ ይታያል።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሙያ በመጋበዝ ስለኤቦላ ወረርሽኝ ገለፃ ማድረጉን የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።
በሳምንቱ መጨረሻ ቻይና ቤጂንግ፤በታላቅዋ ብሪታንያ በርሚንግሃም፤ እንዲሁም በሆላንድ አምስተርዳም የተለያዩ የአትሌቲክስ ዉድድሮች ተከናዉነዋል።
ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው በትልቁ የህዳሴ ግድብ ሰበብ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ የኢትዮጵያ ፣የግብፅ እና የሱዳን ተወካዮች እና ባለሙያዎች ባለፈው ሐሙስ እና ዓርብ ካይሮ ውስጥ የሶስትዮሽ ውይይት አካሄዱ።
አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቦኮሃራም ያገታቸው ከ200 የሚበልጡ ልጃገረድ ተማሪዎችን ይፈታ ይሆን?የናይጄሪያ መንግሥትና ቦኮሃራም የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ከተሰማ ካለፈው ዓርብ አንስቶ ትልቅ ተስፋ ተጥሎ ነበር። ይሁንና በሳምንቱ መጨረሻ በመካሄድ ላይ ያሉት ጥቃቶች ተስፋውን የሚያመናምኑ ናቸው።
ኢቦላ-ባለፉት ሰባት ወራት አራት ሺሕ ስድስት መቶ ያሕል ሰዎች ገድሏል።ከአስር ሺሕ በላይ ለክፏል።የሰወስቱን የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ምጣኔ ሐብት አሽመድምዶታል።ዩናይትድ ስቴትስ እና ስፓኝም ቢያንስ አራት ዜጎቻቸዉ ተለክፈዋል።ዛሬ ሁሉም ዓለም ከISIS ቀጥሎ የመቅሰፍቱን ታላቅነት ያወራል።መቅሰፍቱን ለማስወገድ ግን አሁንም ሩቅ ነዉ።
በግሉ መስክም የየራሳቸዉን ድርጅቶችና ተቋማት የመሠረቱ የሚመሩና የሚያስተዳደሩ ሴቶች ቁጥር እያደገ ነዉ።የእድገቱ ደረጃ፤ እድገቱን ለማገዝ የሚያስፈልገዉ ድጋፍና ፖሊሲ፤ ፖሊሲዉን ገቢር ለማድረግ ያለዉ ፍላጎት ግን አሁንም አነጋጋሪ ነዉ።
የተበከለ አየር ባጠላባት የቻይና መዲና ቤጂንግ ውስጥ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆኑ። በውድድሩ ወደ 25000 የሚጠጉ ሯጮች ተሳታፊ መሆናቸውም ተዘግቧል።
የናይጄሪያ መንግሥት እና ቦኮ ሃራም ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ቡድኑ ለ6 ወራት አግቷቸው የቆዩ ልጃገረዶች በሚመጡት ቀናት ነፃ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል።
የናይጄሪያ መንግሥት እና ቦኮ ሃራም ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ቡድኑ ለ6 ወራት አግቷቸው የቆዩ ልጃገረዶች በሚመጡት ቀናት ነፃ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ከሽብርተኞች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ጥቃት እናደርሳለን የሚል ማስጠንቀቂያ እንደደረሰዉ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት ላይ አስታዉቋል።
የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዶቻችን ፤ታክሲ ላይ የሚያገለግሉ ወጣቶች ናቸው። ከደሞዛቸው እየቆጠቡ እና እቁብ እየጣሉ ፤ ህይወታቸውን እንዴት በመቀየር ላይ እንደሚገኙ ያጫውቱናል።
የአዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ ያስከተለዉ መጥለቅለቅ እየቀነሰ መሆኑ ተነገረ።
«በዘመናዊ አቅድ ስዕል ራሱ ሐሳብ ነው። የአንድ ነገር ሁኔታ የአንድ ነገር ትርጉምና ስሜት ነው…። ዛሪ ስው ራሱን ብቻ መመልከት ትቶ ዓለም ከብዙ ርቀት ከብዙ በኩል ሲታይ ምን አይነት ስሜት አንደሚስጥ – ዓለማዊ ዘላለማዊ የሆነውን ነገር በመተርጎም – በዓይን የሚታይ፥ የቀለም፥ የመስመርና የቅርጽ ሙዚቃ ለመፍጠር ይጥራል።»
የአዉሮፓ ኅብረት የጤና ሚኒስትሮች ኤቦላ ከተስፋፋባቸዉ የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የሚመጡ ተጓዦችን በየአዉሮፕላን ማረፊያዉ የሚቆጣጠሩበትን ስልት ባስቸኳይ ዳግም ለመከለስ ተስማሙ።
የአፍሪቃ የገበያ ቦታዎችን ወደዘመናዊ የገበያ ማዕከልነት ለማሻገር እንዲቻል በወጣ ዓለም አቀፍ የስነሕንፃ ንድፍ ዉድድር ሁለት ኢትዮጵዉያን የዘርፉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንድፍ ማሸነፉ ከወደፓሪስ ተሰምቷል። የንድፍ ዉድድሩን ያወጣዉ መቀመጫዉን በፓሪስ ፈረንሳይ
ባለፈዉ እሁድ የተመረጡት የአንደነትለዴሞክራሲናለፍትሕፓርቲ (አንድነት) ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ በመጪው እሁድ የስራ አስፈጻሚ አባሎቻቸውን ያስመርጣሉ።