የአእምሮ ጤና አሳሳቢ ችግር
በኢትዮጵያ ከሶስቱ አንዱ በህይወቱ በሆነ አጋጣሚ በአዕምሮ ህመም እንደሚሰቃይ ሰሞኑን የወጣ አንድ ዘገባ አመለከተ።
በኢትዮጵያ ከሶስቱ አንዱ በህይወቱ በሆነ አጋጣሚ በአዕምሮ ህመም እንደሚሰቃይ ሰሞኑን የወጣ አንድ ዘገባ አመለከተ።
ከህዝብ የተደበቁ የጦር ሜዳ ውሎ ታሪኮችን በመዘርዝር ጥናት አስደግፎ የሚያቀርበው «ዊኪሊክስ መረጃ ሰብሳቢው መረብ» የኢራቅ ሰነድ በተሰኘው ርእሱ ዙሪያ በቦንብ ፍንጣሪ ተመትተው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ጭምር በማስታወስ ነው የጻፈው፣
የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት (ቡንደስታኽ) አባላት ኢትዮጵያን፣ ጋናንና ሴራሊዮንን ጎበኙ።
ሰሞኑን፣ ከአዲስ አበባ 157 ኪሎሜትር ርቀት ላይ፣ በሰሜን ሸዋ፣ ሙስ፣ ወይም ቀይት እየተባለ በሚጠራው ሥፍራ ፣ ከ 22 ሚልዮን ዓመታት በላይ ያስቆጠረ የአንስሳትና ዕፅዋት ቅሪተ-አካል መገኘቱ ተነገረ።
በድሬዳዋ ከተማ ከመቶ ዓመት በላይ የሆናቸው የተለያዩ የክኒን ዛፍ፡ ቁርቁራ ጎራዴ ወዘተ የመሳሰሉ ዛፎች የመድረቅ ወይም የመገንደስ ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ተገለጸ።
በዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ትንታኔ የዓለም መንግስታትን በአንድነት እንደሚያስተሳስር የሚነገርለት የተመድ ዘንድሮ 65ኛ ዓመቱን ትናንት አከበረ።
የአፋር መድረክ ዓመታዊ ጉባኤ ባሳ,ፍነዉ ሳምንት ማለቂያ ቤልጂየም ብራስልስ ላይ ተካሂዷል።
ግጥም ከስነ-ጽሁፎች አንዱ ቢሆንም በዉበቱ እና በጥራቱ ግን ከሌሎች ላቅ ያለ ሃይልን የተቸረ ነዉ ይሉናል የለቱ እንግዳችን ኢትዮጽያዊዉ የስነ-ጽሁፍ ሰዉ አቶ ደስአለኝ ከበደ።
ለሴት ተማሪዎች ለታቀደው ነጻ የትምህርት ዕድል ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ዩኤስ ኤይድ ሰጥቷል።
ሚኒስትር ቬስተርቬለ በጀርመን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ አንድ ሰዓት የፈጀው ንግግር አድርገዋል። አፍሪካን በተመለከተ የጀርመን ፖሊሲ በንግግራቸው ትኩረት አልተሰጠውም።
በአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ለማስከበር የተረቀቀዉ የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ቻርተር የኅብረቱ አባል አገራት በሙሉ እንዲፈርሙ የአፍሪቃ ኅብረት ዋና ጸሐፊ ጥሪ አቀረቡ።
የገንዘብ ሚኒስትሩ ጆርጅ ኦስቦርነ ይህን ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ የተባለውን የበጀት ቅነሳና የቁጠባ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ ከተቃዋሚዎች የምክር ቤት አባላት ጠንካራ ነቀፌታ ገጥሟቸዋል።
እንደ እርዳታ ድርጅቶች ግምት በአለም ዙርያ 250.000 ያህል ህጻናት በዉትድርና ተሰማርተዉ ይገኛሉ። ባለፉት ሃያ አመታት በዩጋንዳ ብቻ 30.000 ህጻናት በዉትድርና ተግባር እንዲሰማሩ ታፍነዉ ተወስደዋል አልያም የወሲብ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
የሰዎች ዝውውር በጀርመን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለመደ እየሆነ መጥቷል። በተለይም በጀርመን ሴተኛ አዳሪዎች ሊገኙ በሚችሉባቸው የተለዩ ቦታዎች በግድ ለዝሙት ስራ የሚጋዙ አፍሪካውያን ሴቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው።
በዓለምአቀፉ የፊናንስና የኤኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ ባለፈው ዓመት አቆልቁሎ የነበረው የጀርመን ኤኮኖሚ መንኮራኩር የሆነው የውጭ ንግድ በዚህ ዓመት መልሶ ከፍተኛ ዕድገት እየታየበት ነው።
በያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም በርካታ አፍሪቃዉያን አገሮች ከቅኝ ግዛት የተላቀቁበትን አመት ቢያከብሩም ቅሉ አፍሪቃዉያን ጋዜጠኞች ዛሪም የፕሪስ ነጻነታቸዉን አላገኙም ሲል አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አመታዊ ዘገባዉን ይፋ አድርጎአል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከኢትዮጵያ የሚያገኘውን የልማት ርዳታ ህዝቡን ለመጨቆን ይጠቀምበታል ሲል በመክሰስ ያወጣው ጽሁፍ ሚዛናዊ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የስነ ምግባራት እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት መምርያ ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ አሰፋ ገልጸዋል።
ፈንጣጣ፣ ከገጸ-ምድር የጠፋበት ብሥራት ፣ በ 1980(እ ጎ አ) ከተነገረ ወዲህ ለአያሌ ምዕተ-ዓመታት የቀንድ ከብቶች ዐቢይ መቅሠፍት ሆኖ የቆየው ደስታ(ሪንደርፔስት)ከምድራችን ሳይጠፋ እንዳልቀረ ባለፈው ሰሞን ተገልጿል።
መንበሩን በኒው ዮርክ ያደረገው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፡ ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ ሀገሮች የሚያገኘውን የልማት ርዳታ ህዝቡን ለመጨቆን ይጠቀምበታል ሲል ከሰሰ።
ስለካንሰር ሲነገር ብዙዎች የማይድን በሽታ አድርገዉ ያዩታል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ርዕሰ ብሄር ግርማ ወልደጊዮርጊስ መስከረም ሀያ አራት ቀን ሁለቱን ምክር ቤቶች ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግርና ሀገራዊ መመሪያ ላይ ዛሬ ሲመክር አረፈደ።
የእንግሊዛዊቷ የኢትዮጵያ አርበኛ የወ/ሮ ሲልቪያ ፓንክረስት ሀምሳኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በእርግጥ በእድሜ ከወጣትነቱ ወደ ጎልማሳነቱ ሊሻገሩ ነው። ወደ ፖለቲካው የገቡት እንደሌሎቹ ቀደም ብለው ባይሆንም በዙም ደግሞ አልዘገዩም።
የመካከለኛው ምስራቅ የካቶሊክ ጳጳሳት ሲኖዶስ በሮማ ቫቲካን እየተካሄደ ይገኛል።
ሶማልያ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾመች። መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ ይባላሉ።
መድረክ ከሚያስተናብራቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንዱ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከእስር ከተፈቱ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በጠራዉ ጋዜጣዊ ጉባኤ የሐገሪቱን ችግሮች —
በመልማት ላይ ባሉ ሐገራት ተጨማሪ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተባለ መሬት ለዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በረዥም ጊዜ ኪራይ ወይም በሽያጭ መቸብቸቡ እንደቀጠለ ነው ።
በአለም እጅግ ትልቅ ስለ ሚባለዉ ስለ ፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ፣ እንዲሁም ስለ ሚባለዉ ስለ ፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ፣ እንዲሁም ሰባኛ አመት የትዉልድ ቀኑ ታስቦ ስለዋለዉ ስለ ታዋቂዉ የቢትልስ የሙዚቃ ባንድ አባል ስለ ጆን ሌነን አልናስደምጥ የያዝነዉ ርእሳችን ነዉ
ለ 69 ቀናት በማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የቆዩትን 33 የቺሊ የማዕድን ሠራተኞች የማውጣቱ ስራ ያለ አንዳች እንከን ተጠናቋል ።
ከአዋጅ ባለፍ በጫት ነጋዴዎች ወይም ሸማቾች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አድርጎ አያዉቅም ነዉ።አሁን ግን ሸባቦች በጫት ላይ ጠጠር ብለዋል።በዚሕም ምክንያት፥-ሶማሊያዊዉ ጋዜጠኛ ሙስጠፋ ሐጂ አብዲኑር እንዳለዉ ሞቃዲሾ ዉስጥ ከትናንት ጀምሮ ጫት የለም።
በርካታ የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት ተወካዮች የተሳተፉበት የዓለም የምግብ ዋስትና ኮሚቴ ጉባኤ ሮም ኢጣልያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው ።
የሰሜን ሱዳን የደቡብ ሱዳን ተጠሪዎች የነዳጅ ዘይት ሀብት ክምችት ባላት በአቢዮ ግዛት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት ድርድር ያለ ውጤት አበቅቷል ።
በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን ፣ የሁምቦልትን ዩኒቨርስቲ 200ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ፣ የአለክሳንደር ፎን ሁምቦልትን የጉዞ ምርምር፣ እንዲሁም ፣ የጀርመን መዲና በርሊን፣ ለምዕተ-ዓመታት የነበራትን የሳይንስ ምርምር ማእከልነት እንዳስሳለን።
የዓለም ባንክና ዓለምአቀፉ የምንዛሪ ተቋም አይ.ኤም.ኤፍ የዘንድሮ ዓመታዊ ጉባዔያቸውን ባለፈው ሰንበት ዋሺንግተን ላይ አካሂደዋል።
«ክርስትና ያለ ጥርጥር የጀርመን ነው ። የይሁዳ ዕምነትም ያለ ጥርጥር የጀርመን ነው ። ይህ የይሁዳና የክርስትና ታሪካችን ነው ። ሆኖም አሁን እስልምናም በጀርመን ቦታ አለው ። »
የኢትዮጵያ መንግሥትና ኦ ብ ነ ግ፣ የሰላም ውል መፈራረማቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ዛሬ የሰላም ስምምነት ተፈራርሟል፣
በዓለም ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለዉ አረቢካ ቡና መገኛ የሆኑት ሁለት የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ደኖች ዓለም ዓቀፍ እዉቅና አገኙ።
ለመብት የሚሟገት ሰዉ ነፃነቱን ማጣቱና ክትትል የሚደረግበት መሆኑ በሥራ ላይ እንደሚያጋጥም አደጋ የሚታይ ነዉ።ይሕ የሥራዉ አካል ነዉ።በሌሎቹ አይን አንተ እንደ ታላቅ ሰዉ ወይም እንደ ጀግና ትታይ ይሆናል።ይሁን እንጂ አንተ (በሌሎቹ ለመደነቅ ሳይሆን) ምግባርሕ የራስሕ ምርጫ መሆኑን በግልፅ መገንዘብ አለብሕ
አፍሪቃውያን ህጻናት፣ በማደጎ ሥም፣ ወደ ምዕራቡ ዓለም መጋዛቸው፣የብሩኅ ተስፋ እውንነት ወይስ ዐይን ያወጣ ብዝበዛ!? በአሁኑ ጊዜ፣ ማሳደግ ለሚችሉ ባዕዳን ፣ ልጆቻቸውን ለጉድፈቻ የሚሰጡ አፍሪቃውያን ወላጆች ቁጥር እጅግ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።
ጀርመናዉያን ከአራት አስርተ አመታት ክፍፍል በኋላ አንድ ሆነዉ በፍቅር መኖር የጀመሩበትን ሃያኛ ዓመት መታሰቢያ በደማቅ አክብረዋል።
ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ የ2010 ተሸላሚ የሆኑ አራት ጋዜጠኞችን መርጧል። ከእነዚህም አንዱ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባ ዳዊት ከበደ ነው።
የኖርዌዉ የኖቤል ኮሚቴ የ2010ሩ የሥላም ኖቤል ሽልማት ለመሠረታዊ ሠብአዊ መብት መከበር ለረጅም ጊዜ ላደረጉት ሠላማዊ ትግል ለ ሊዩ ሺኦቦ እንዲሰጥ ወስኗል
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር የወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከእስር መለቀቅ በብዙዎች ዕይታ ሠናይ ክሥተት ነው ። በሌላ በኩል፣ ውሳኔው የራሳቸው ቢሆንም፣ የተለቀቁበት ሁኔታ እና የወደፊት የፖለቲካ እጣ- ፈንታቸው ማነጋገሩ አልቀረም ። በዚህ ጉዳይ፣ የጀርምን ድምጽ ዜና ዘጋቢ ተክሌ የኋላ፣ …
ትናንት ብራሰልስ ውስጥ የተካሄደው 13 ተኛው የአውሮፓ ህብረትና የቻይና ጉባኤ የጋራ ትብርን ለማጠናከር ና ወደፊት በጋራ ጉዳዮች ላይ የሚካሄደውን ውይይት ለመቀጠል በመስማማት ተጠናቋል ።
ፓወር ኢንጅነሪንግ ሜጋዚን በየዓመቱ ፕሮጀክቶችን መርጦ ይሸልማል። የተከዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለሽልማት ታጨ ።
የዲናሚት (ዳይናማይት ) ፈልስፊ በሆኑት እስዊድናዊ የሥነ-ቅመማ(ኬሚስትሪ) ሊቅ አልፍረድ ኖቤል ስም ፣ እ ጎ አ ከ 1901 ዓ ም አንስቶ በያመቱ በሳይንስ፣ ሥነ ጽሑፍና ሰላም አሸናፊዎች የሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ሥም እንደሚገለጥ ሁሉ፣
በአለም እጅግ ትልቅ እንደሆነለት የሚነገርለት የመጽሃፍ ዐዉደ ርዕይ በፍራንክፈርት ከተማ በመካሄድ ላይ ነዉ።
ደቡብ ጀርመን የምትገኘዋ የሽቱትጋርት ከተማ ካላፉት ጥቂት ወራት ወዲህ የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበች ነው ።
ባለፈው ግንቦት 15 በተካሄደው አራተኛው ዙር ብሄራዊ ምርጫ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ከምክር ቤት መቀመጪያዎች 99.6 በመቶ ማሸነፉ መገለጹ ይታወሳል።
የአየር ንብረት ለዉጥን ለመታደግ የየአገራቱ መንግስታት ሊያደርጉ ይገባቸዋል፤ በሚል የሚጠበቀዉ ስምምነት ዘንድሮም እንደአምናዉ መጓተቱን ቀጥሏል።