በደንማርክ መዲና በኮፐንሄገን፣ ከኅዳር 28 እስከ ታኅሳስ 9 ቀን 2002 ዓ ም፣ በዓለም ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ የተባለው ዐቢይ የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ነክ የመሪዎች ጉባዔ ከተካሄደ ወዲህ ፣ በቀጣይነት ካንኩን ሜክሲኮ ላይ ፣ 194 መንግሥታት የተወከሉበት ተመሳሳይ ጉባዔ ከተጀመረ እንሆ …

የካንኩኑ ጉባዔና አሳሳቢው የዓለም የአየር ንብረት ጉዳይ፣ Read more »

የኤኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት፡ በምህጻሩ ኦ ኢ ሲ ዲ በስድሳ አምስት ሀገሮች የሚገኙ ወደ አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከተሳተፉበት በምህጻሩ ፒሳ የተባለው የተማሪዎች ዕውቀት መለኪያ ፈተና በኋላ ትናንት በበርሊን ይፋ ባወጣው የ 2009ዓም ዘገባ መሰረት፡ የጀርመን የትምህርት ደረጃ …

ጀርመን እና የፒሳ ዘገባ Read more »

መንዙማ አንዱ የታሪካችን የባህላችን መገለጫ ነዉ። የባህል መድረካችን የያዘዉ ርዕሱ ነዉ። መንዙማ ምንድን ነዉ። ታሪካዊ መነሻዉስ? በእዚሁ ርዕስ ስር ከአስር ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በኢትዮጽያ ጥናት እና ምርምር ተቋም በርካታ ምሁራኖች

ፕላኔታችን ከተቀጣባት የጥፋት አደጋ እንድታመልጥ፣ አየሩን የብሱንና ባህሩን ከብክለት ለመከላከልም ሆነ ለማጽዳት፤ በአጭሩ የተፈጥሮ አካባቢን ለመጠበቅ፣ ይበጃሉ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ ፣ ዓለም አቀፍ ጠበብትና ውሳኔ ሰጪ መሪዎች በየጊዜው በጋራ ከመምከር አለመቦዘናቸውን እንሰማለን።

አፍሪቃና የአውሮፓ ሕብረት ሕዝባዊት ቻይናን የመሳሰሉት በፍጥነት በመራመድ ላይ ያሉ ሃገራት የአፍሪቃን ክፍለ-ዓለም የተፈጥሮ ጸጋ መሻማት በያዙበት በአሁኑ ወቅት መሰናክል ገጥሞት የቆየ የኤኮኖሚ ትስስራቸውን ለማጠናከር ሰሞኑን ትሪፖሊ ላይ ባካሄዱት የመሪዎች ጉባዔ ተስማምተዋል።

ከትናንት በስትያ በግብፅ የተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ማጭበርበር እንደተከሰተበት ተቃዋሚዎች ገለፁ። ሁኔታዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በምክር ቤቱ ምርጫ የፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ ፓርቲ ከፍተኛ መቀመጫ እንደሚያገኝ ተገምቷል። ተቃዋሚዎች ውጤቱን እንደማይቀበሉት እየዛቱ ነው። ማንተጋፍቶት ስለሺ ዝርዝር ዘገባ አጠናቅሯል።

(DW) — ዊኪ ሊክስ የተሰኘው የኢንተርኔት መረብ ሰሞኑን ይፋ ያደረጋቸው ሚስጥር ነክ መረጃዎች ከአሜሪካን እስከ ጀርመን ዓለምን እያነጋገሩ ነው። ዊኪ ሊክስ በአሜሪካን የጦር ሄሊኮፕተር አብራሪዎች ኢራቅ ውስጥ ተፈፀመ ያለውን የሰላማዊ ሰዎች ግድያ የሚያሳየውን ቪዲዮ ጨምሮ እስካሁን በርካታ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። …

የዊኪሊክስ መረጃዎች በርካታ መንግስታትን እያወዛገበ ነው Read more »

በ 32 የተለያዩ ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ ፕሮግራሞችን የሚያሠራጨው ዶቸ ቨለ ራዲዮ ጣቢያ፣ ቋሚ ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ዘጋቢዎቹም በየጊዜው ሙያዊ ማሠልጠኛ እንዲያገኙ ያደርጋል።

የታዋቂዉ ጋዜጠኛ እና ደራሲ አበራ ለማ ናጋቲ ካ ያ ጓሼ ኮ ከሚለዉ ለሎሪት ጸጋዮዪ ገብረመድህን ማስታወሻነት ከጻፉት የተወሰደን ግጥም ነዉ በመፕሮግራሙ መጀመርያ የምታደምጡት የጋዜጠኛና የደራሲ አበራ ለማ ሃያ አምስት ምርጥ ስነ-ግጥሞች ስብስብ በዲቪዲ በከለር ድምጽ ቅንብር ለታዳሚዎች እይታና ጆሮ ቀርበዋል።

የአውሮፓ ሕብረት በአሕጽሮት ኤ.ሢ.ፒ. በመባል ከሚታወቁት ከአፍሪቃ፣ ካራይብና ፓሢፊክ አካባቢ አገሮች ጋር የኤኮኖሚ ሽርክና ውል ለማስፈን በሚያደርገው ግፊት ዕርምጃው ሚዛን የጠበቀ አይደለም ሲሉ የሚወቅሱት ታዛቢዎች ብዙዎች ናቸው።

« እነዚህ ደንቦች በርግጥ ለመረዳት ቀላል ናቸው ። እዚህ መኖር የሚፈልግ ጀርመንኛ መማር አለበት ። እዚህ የሚኖር ሰው ህጎቻችንንና እሴቶቻችንን ማክበር ይገባዋል ። ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በኛ ዘንድ ተቀባይነት አለው ። ይህን ማድረግ የማይፈልግ ማዕቀብ ይጠብቀዋል ። ያን ያህል …

የውህደት ትምሕርት በጀርመን Read more »

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከብዙ ክርክርና ድርድር በኋላ ያነሷቸው ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ትምህርት አቁመው መሰንበታቸው ተጠቆመ። ሰኞ ህዳር 13ቀን 2003ዓ.ም. ደግሞ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውም ተገልጧል። ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ሴቶች ጉዳይ …

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርት አቋረጡ Read more »

…በአዲሱ የኔቶ-ሥልት መሠረት ሚሳዬል መከላከያ ጦር መሳሪያ ለመገንባት ግን አለም አቀፍ የሰላም ንቅናቄ ባልደረባ ራይነር ብራዉን እንዳሉት የኔቶ አባላት በፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬጋን ዘመን ለጦር መሳሪያ ከወጣዉ ከፍተኛ ገንዘብ ይበልጥ ቢሊዮነ-ቢሊዮናትን ለመከስከስ ተስማሙ።

በኮሎኝ ከተማ የኢትዮጲያውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማህበር በጀርመንኛ ምህፃሩ(DÄSAV)ከተመሰረተ አንድ አመት ሆኖታል። እራሱን ለህዝብ ሲያስተዋውቅ ግን ያለፈው አርብና ቅዳሜ የመጀመሪያው ነው።

የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሁለት ሳምንት በፊት አጠቃላይ የአሸባሪዎች ጥቃት ሥጋት መኖሩን አስታዉቀዉ ሕዝቡ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችንና ሰዎችን ለፖሊስ እንዲጠቁም መክረዉ ነበር።ያሁኑ ማስጠንቀቂያቸዉ ግን ካለፈዉ ጠንካራና በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ነዉ።