ብርቱካን ሚደቅሳ “ምህረት” ያገኙበት “ይቅርታ”
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር የወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከእስር መለቀቅ በብዙዎች ዕይታ ሠናይ ክሥተት ነው ። በሌላ በኩል፣ ውሳኔው የራሳቸው ቢሆንም፣ የተለቀቁበት ሁኔታ እና የወደፊት የፖለቲካ እጣ- ፈንታቸው ማነጋገሩ አልቀረም ። በዚህ ጉዳይ፣ የጀርምን ድምጽ ዜና ዘጋቢ ተክሌ የኋላ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀምንበርንና አንድ የህግ ባለሞያ አነጋግሮ ተከታዩን ዘጋባ አጠናቅሯል።