የፖሊዩ ቫይረስ በሺታ በኢትዩጵያ እና ሶማሊያ በወረርሺኝ መልክ መከሰቱን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ።
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፖሊዩ ቫይረስ በተከሰተበት አካባቢ ሳይታወቅ ጉደት አድርሶዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት በበሺታው መጠቃታቸውን በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡ በሐገራችን ኢትዩጵያ እና አጎራባች አገሮች የተከሰተውን የፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የፖሊዩ ቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት አስፈላጊ …