ቴምርን የመመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

✓ ለአጥንት ጤናማተትና ጥንካሬ
ቴምር በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ኮፐር እና ማግኒዚየም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚ እንዲሆን ይደርገዋል።

✓ ለሆድ ድርቀት
ቴምርን መመገብ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። የሆድ ድርቀት የሚያስቸግርዎ ከሆነ ቴምርን በውሃ ዘፍዝፈው በማሳደር ጠዋት መመገብ እጅግ ውጤታማ የሆነ መፍትሄን ይሰጣል።

✓ ሀይልን ይሰጣል
በተፈጥሮአዊ ስኳር ፤ ጉሉኮስ፣ ፍሩክቶስ እና ሱክሮስ የበለፀጉ ስለሆነ ጥሩ ሀይል ሰጬ መክሰስ መሆን ይችላል።

✓ ለልብ ጤናማነት
ቴምር ለልብ ጤናማነት ጠቃሚ ነው። ቴምር መትፎ የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

ጤና ይስጥልኝ
http://www.honeliat.com/health-benefits-of-dates/