የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒትን (performance-enhancing drugs) በመመርመር ረገድ አይኤኤኤፍ (IAAF) “ወሳኝ ደረጃ ላይ” ካስቀመጣቸው አምስት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት ተብሏል። ሌሎቹ ኬንያ፣ ሞሮኮ፣ ዩክሬይንና ቤላሩስ ናቸው። ምርምራውን ካላካሄደች ያለው አማራጭ የአለም የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት የሚቆጣጠረው ድርጅት (World Anti-Doping Agency)እርምጃ እንደሚገጥማት ምናልባትም ከአለም-አቀፍ …

ኢትዮጵያ 200 በሚሆኑ አትሌቶች ላይ ህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት ተጥቅመው እንደሆነ ምርመራ ትጀምራለች – VOA Read more »

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል። ቃጠሎው መድረሱን ያረጋገጡት የዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ በሕይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ቃጠሎው ዳመራ በሚባለው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የተማሪዎች ማደሪያ ላይ የተነሣው ትናንት፤ ማክሰኞ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ እንደነበረ …

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቃጠሎ ደረሰ – VOA Read more »

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል። በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ …

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል – VOA Read more »

Artist Getachew Mekuria. አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. April 4, 2016):- በ1927 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ ጥበብን የተቀላቀላት በመንገድ ላይ ታንቡር መቺ በመሆን ነው። ይህ የሆነው በ1940 ዓ.ም. ነበር ። በኋላም ጥበብን እየተከተላት እሷም ወዳለችበት እየጠራችው በ1948 ዓ.ም. በመዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በፊት ከሚያደንቃቸው በኋላም ለረጅም ዓመታት አብረውት ከሠሩት ከአርቲስት ተፈራ አቡነወልድና ከአርቲስት ወዳጄነህ ፍልፍሉ ጋር ተቀላቀለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Ethnic apartheid in Ethiopia. የጎሣ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡- ይህ “የጎሣ ዘረኝነት/አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ መደበኛ በሆነ መልኩ እያዘጋጀሁ የማወጣው ተከታታይ ትችት ሁለተኛው ክፍል ነው። የዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ጥንድ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሓት) አድራጊ ፈጣሪነት ተመስርቶ እየተቀነቀነ ያለው አውዳሚ የፖለቲካ ሥርዓት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰፊው የጥቁሮች ህዝብ የበላይ አገዛዝ ሥርዓት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ነጮች የዘረኝነት የበላይ አገዛዝ ከነበረው የአፓርታይድ ዘረኛ አገዛዝ ተሞክሮ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት እና

2ኛ) ጥልቀት እና ስፋት ያለው ክርክር እና ውይይት በማካሄድ ከጎሣ ዘረኝነት የጸዳች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባቱን አስፈላጊነት ለመፍጠር እንዲቻል የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረዮሐንስ (ከጀርመን)

Ethiopian federalism map. የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ

የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ገለታው ዘለቀ

በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ሕብረተሰብ የጋራ ሀብት ወይም የማኅበራዊ ካፒታል ዋና አካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማኅበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት አንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሀብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Blue party. ሰማያዊ ፓርቲ

የፖለቲከ ስህተትና የሳንባ ነቀርሳ ጠንቆች የተመሳሳይነት ባህርይ አላቸው። ሁለቱም ችግሮች በለጋነታቸው ወቅት ከተነቃባቸው ችግሮቹን የማስወገድ ዕድል ከፍተኛ ነው። ችግሮቹ ሥር ከሰደዱ በኋላ የሚደረገው መሯሯጥ ግን ፈውስ የማስገኘቱ ሁኔታ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ሊሆን ይችላል። (ማርጋሪት ታቸር የእንግሊዝ ጠ/ሚ የነበሩ)

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሊ ጓንጉል

Daniel Kibret. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ይህ ጽሁፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ‘“ሀገር ማለት ሰው ነው”! እስቲ ሙት በለኝ!’ ሲል ለለቀቀው ጽሁፍ መልስ ነው። … እስካሁን ድረስ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚባል ዘፈን መኖሩን ሰምቼም አይቼም አላውቅም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ኖሮ እኔ ያላወቅሁ እንኳን ቢሆንም፣ “ሀገር ማለት ሰው መሆኑን” ሊያስክድ የሚችል አንዳችም ነገር ያለ አይመስለኝም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ጨርሶ ሳይኖር፣ የበድሉ ዋቅጅራን “ሀገር ማለት የኔ ልጅ … ሰው ነው …” በሚል ርዕስ የሚታወቀውን ታላቅ ግጥም እንዲሁ “ዘፈን” በማለት ለመተቸት ወይም ለማውረድ ከሆነ ደግሞ፣ ዲያቆኑን የባሰ የታሪክ፣ የኃይማኖት እና ከሁሉም በላይ የስነ-ጽሁፍ ድህነቱን ይናገርበት ይመስለኛል። ምክንያቱም ሀገር ማለት ሰው ነው! ላስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነፃነት ዘለቀ

Panda

የታያቸውን አላውቅም ከምን ጊዜውም በላይ ወያኔዎች ሰሞኑን ክፉኛ ተጨንቀዋል። እነሱና እኔ ከጥንት ጀምሮ የተለዬ “ዝምድና” ያለን በመሆናችን ነገረ ሥራቸውን በደንብ አውቀዋለሁ። ሲጨነቁና ሲጠበቡ እንዴት እንደሚሆኑና ምን እንደሚያደርጉ በረሃ ሳሉ ጀምሮ በሚገባ እንተዋወቃለን። ከዱሮው ለማጣቀስ ያህል አንዳች አደጋ አንጃቦባቸው ሲጨነቁ ትላልቅ ባለሥልጣኖቻቸውን በቃለ-መጠይቅ መልክ እያቀረቡ ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ጀሌያቸውን ያጽናናሉ፤ ያበረታታሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

“ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም”

TPLF funeral. "ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም"

እኔ ከምኑም የለሁበት ተቀዋሚም ደጋፊም አይደለሁም በሚል ጭንብል ተሸፍኖ የሚኖረው ክፍል ሲቀር ሌላው በሁለቱ ጎራ ይመደባል። በወያኔ ጎራ ያለው ወገን ለአባልነትም ይሁን ለደጋፊነት ያበቃው ምክንያት ምንም ይሁን ባለው አቅም በሚችለው መንገድ የወያኔን ዕድሜ ለማራዘም ያስችላል ብሎ ያመነበትን ይሠራል። እንደውም አንዳንዱ ያለ ወያኔ መኖር እንደማይቻል ራሱን አሳምኖ ሞቴን ከወያኔ ጋራ ያለ ነው የሚመስለው። በዚህ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሆነ ብለው አቅደው ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ናፍቀው የወያኔን ዕድሜ በሚያሳጥር ተግባር ላይ አይሰማሩም። የውስጥ አርበኞች ካልሆኑ በስተቀር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባለፈዉ ክረምት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ግድቦች የሚጠበቀዉን ያህል ዉሃ እንዳልያዙና ያ ለእጥረቱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የማለዳ ወግ …

* በኀዘን የሚላወስ እንስፍስፍ የእናት አንጀት

* የኮንትራት ሠራተኛዋን እህት ቤዛን አፋልጉኝ!

ነቢዩ ሲራክ

ሆዴን ያላወሰው የእማማ ሎሜ አደራ

Beza Ashenafi Engida and her mother Lome Regass. እህት ቤዛ አሸናፊ እንግዳ እና እናት ሎሜ ረጋስ

የእናትን መሪር ኀዘን ሰምቼ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ኀዘን ተረድቼ ሕመም መታመሜ እውነት ሳለ፤ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃና መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ሕመሜን አክብዶታል። ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ፣ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ፣ ነገ ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ፤ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “የልጄን ነገር አደራ! እባክህ ነፍሴን አሳርፋት” …

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበታትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማኅበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው …

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! – ዳንኤል ክብረት Read more »

የኢትዮጵያ መንግስት ለመሰረተ-ልማት ግንባታዎች ከቻይና ብቻ 17.6 ቢሊዮን ዶላር ተበድሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሰፋፊ የመሰረተ-ልማት ግንባታዎች እና የማምረቻ ዘርፉን ለማሳደግ ከውጭ አገራት የሚበደረው ገንዘብ መጠን ያሰጋቸው ባለሙያዎች ግን ከአመት አመት በሚጨምረው ብድር ምክንያት አገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያሰጋታል እያሉ ነው።

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Quo Vadis Ethiopia: Where Are You (not) Going?

(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን ከተማ (ዋሽንግተን ዲሲ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው።) …

“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አስፋ ጫቦ

Ato Assefa Chabo. አቶ አስፋ ጫቦ

ትዝታ ነው የሚርበን

ላናገኘው ላይጠግብን ብሏል ወዳጄ የነበረው ጸጋዬ ገብረ መድኅን

ለመሆኑት ትዝታ ምንድነው? ዘፈፍን ነው? እንጉርጉሮ? ኩርኮራ? ማላዘን?ሐሳብ ልጓም የለውምና እንዳሻው ወደላይ ወደታች፤ ወደውስጥ ወደውጭ፤ ወደፊት ወደኋላ፣ ወደየሚታይ ወደሊታይ ወደማይቻል ይሔዳል፤ ይጓዛል፤ ይተናል፤ ይበናል፤ ይመላለሳል፣ ይመለሳልም። “ማን አለኝ ከልካይ!” መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

Heineken ethiopia

የሆላንድ ዜምብላ[1] ጋዜጠኞች የኦሮሞ ፀሐፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። “መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን …”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

Prof. Getachew Hahile. ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

የክርስቲያኖቹ መጽሐፍ “ግብር ለሚገባው (ሹም) ግብር ገብሩ” ይላል። ግብር ለማይገባው እንደወያኔ ላለ ገዢ ግን ግብር ስለማይገባው አንዲት ቀይ ቤሳ አታቅምሱት ማለቱ ነው። ጊዜ ስለሰጠው ቀምቶ ይወስዳል። ግን ብዕሬ ስቦኝ ነው እንጂ ለማለት የፈለግሁት እንኳን “አድናቆት ለሚገባቸው የኦሮምኛ ተናጋሪ የጎሣ ፖለቲከኞች አድናቆት ስጧቸው” ለማለት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

በአጋዚ ጦር በአምቦ ከተማ የተገደለው የግርማ ረጋሳ ቤተሰቦች

ሁለት ወንድማማቾች ናቸው። ቃየን እና አቤል ይባላሉ። በዘፍጥረት ምዕራፍ 4 ላይ የተጻፈው ነው። “ቃየን አቤልን ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ አቤል ላይ ተነሳበት። ገደለውም” ይለናል ቃሉ። ደም ፈሰሰ። የወንድም ደም በወንድም እጅ። እግዚአብሔር በሆነው ነገር አዘነ። ለቃየንም ጥያቄ አቀረበለት። “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። ቃየንም መለስ “ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በየነ ሞገስ ጽሁፌን በእውነተኛ ኑዛዜ ልጀምረው፡፡ ሰሞኑን በመጽሐፍት አዟሪዎች እጅ ‹በዓሉ ግርማ – ሕይወቱና ሥራዎቹ› በሚል ርዕስ የቀረበ መጽሐፍ ተመልክቼ ነበር፡፡ በዓሉን በተመለከተ ብዛት ያላቸውን ጋዜጦች፣ መጽሐፍት፣ መጽሔቶችና የተለያዩ ጹሑፎች የተመለከትኩና ቃለ መጠይቆች የሰማሁ መሆኔን በማመን ‹ምን አዲስ ነገር ይኖራል?› …

የመንፈስ ታዳጊ ያገኘው በዓሉ ግርማ – በየነ ሞገስ Read more »

የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና በንቁ የፖለቲካ ተሳትፎው የሚታወቀው አባል አቶ አብረሃም ብዙነህ በጂንካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ እስራቱ የተፈጸመው መጋቢት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ቤታቸው ከማለዳው 12 ሰዓት እስከረፋዱ 4፡20 ከተፈተሸ …

በደቡብ ኦሞ የኦህዲኅ መሪ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና አንድ ጠንካራ አባል ታሰሩ – ግርማ በቀለ Read more »

የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።

በፍቃዱ ኃይሉ

የሥም ነገር ሳልወድ በግዴ ያፈላስመኛል። ሥም ተራ መለያ መጠሪያ ብቻ ነው ብዬ አልቀበልም። ምናልባት መጀመሪያ ላይ እንዲያ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁን፣ ሥም በባሕልና የሥልጣኔ ዝግመተ ለውጥ ሒደት (evolution of civilizations) ውስጥ ብዙ ውስብስብ ነገሮችን እያነገበ በጊዜ ባቡር ተሳፍሮ ውስብስብ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሥም የባሕል መገለጫ፣ የፖለቲካ አመለካከት መንፀባረቂያ፣ የወላጆች ለልጆች ውርስ ነው። ለዚያም ይመስለኛል “ሥምና ማንነት” የሚለው ጉዳይ የመጽሐፍ ምዕራፍ እና የጥናት ርዕስ ለመሆን እየበቃ ያለው።  አባቶቻችን በፈረንጆች ‘የሊትሬቸር’ አጻጻፍ ደምብ ስላልጻፉልን ፍልስፍና መስለው ያልታዩን አፈላሳፊ አባባሎች አሏቸው። የሊቃውንቱ “ሥሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ” (ሥሙ ተግባሩን ይመራዋል) የምትለው አባባላቸው አሁን ምዕራባውያን እያጠኑት ያሉት ጉዳይ ላይ እነርሱ የደረሱበት ድምዳሜ ነው። በነገራችን ላይ በተቀራራቢ ሮማውያንም ‹nomen est omen› (ሥም ዕጣፈንታ ነው) የሚሉት አባባል አላቸው፡፡ ሳይንቲስቶች «ሰው ወደሥሙ ወይም ከሥሙ ወዲያ (እየተጎተተ ወይም እየተገፋ) የሚኖር ብኩን ፍጡር ነው» ወደማለቱ እየዳዳቸው ነው። ለመሆኑ አንድ ሰው ለመለያ ይሆነው ዘንድ የተሰጠው ሥም ማንነቱን ያሳብቃል? ባሕሪው ላይ ወይም ተግባሩስ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል?

የሥም ቅርፅ

ሥም ከአገር አገር ብቻ ሳይሆን ከዘመን ዘመን ቅርፁና ፀባዩን እየቀያየረ ይሄዳል። ለምሳሌ ምዕራባውያን ‘የቤተሰብ ሥም’ የሚሉት እኛ የለንም፤ አንዳንዶች የጎሳ ሥም እሱን ይተካል ይላሉ። በጊዜ መሥመር ደግሞ ለምሳሌ በኢትዮጵያ በ19ኛው ክ/ዘመን (ከ1900ቹ በፊት) የኢትዮጵያውያን ሥም የሚጻፈው (የሚገለጸው) ‘ከአያት ሥም➡ የአባት ሥም ➡ የልጅ ሥም’ በሚለው ቅደም ተከተል ነበር። ከዚያ ወዲህ ግን (‘የእከሌ ልጅ’ ዘመን አልፎ፣ ‘የእከሌ አባት’ ዘመን ሲጠባ) በተቃራኒው ተደርጓል። በቱርክ እ.ኤ.አ. ከ1943 በፊት የቤተሰብ ሥም የሚባል ነገር አልነበረም። አንዱን ሰው ከሌላኛው ለመለየት ሲባል እስከ ሦስት ሥሞች ድረስ ይወጡለትና በዚያ መደዳ (በእኛ እስከ አያት ሥም በምንለው መንገድ) ይጠራ ነበር። በዚህ የአሰያየም ስርዓት የአባትና የልጅ ሥም ምንም የሚያዛምዳቸው ነገር የለም። ለምሳሌ የቱርክ አባት የሚባለው አታቱርክ (Atatürk) ሥሙ ሙስጠፋ ከማል ነበር። አታቱርክ የተጨመረው ኋላ ለክብሩ ሲባል ነው። የአባቱ ሥም ደግሞ አሊ ሪዛ ነበር። በቱርክ የተጠፋፉ ዘመዳሞች በሥም ተፈላልገው የመገናኘት አማራጭ አልነበራቸውም ማለት ነው። በሌላው ባሕል የልጅ ሥም፣ የአባት ሥም፣ የቤተሰብ ሥም… የምንለው ነገር ዝምድና መቁጠሪያም ጭምር ነው ማለት ነው፡፡

በአገራችን በተለያዩ ማኅበረሰቦች የተለያየ ዓይነት የሥም አወጣጥ አላቸው። ለምሳሌ በጋምቤላ የአኙዋክ ብሔረሰብ ሥም አወጣጥ ሥሙን ሰምቶ ስለሰውዬው ጥቂት ቤተሰባዊ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በአኙዋክ፣ የመጀመሪያ ልጅ ኡመድ ይባላል፤ ሁለተኛ ኡጁሉ፣ ሦስተኛ ደግሞ ኦባንግ እያለ ይቀጥላል። አንዳንዴ አባትና ልጅ አንድ ዓይነት ሥም ሊኖራቸው ይችላል። ታላላቆቹ ሴቶች ሆነው መጀመሪያ የሚወለድ ወንድ ኦማን ይባላል። ለምሳሌ እኔ ከአኙዋክ ቢሆን የተወለድኩት ኦማን እባል ነበር እንደማለት ነው።…

በአማራ ተወላጆች ዘንድ ደግሞ ትንሽ ለየት ይላል። ለምሳሌ መንዞች “ርስትና ውትድርና ይወዳሉ” ይባልላቸዋል። ይህም በሥማቸው ሳይቀር ይስተዋላል። ለምሳሌ “ሸዋጉልቱ” የመንዜ ሥም ነው። አምበርብር፣ ደምሰው፣ ዳምጠው፣ አሸብር፣ የመሳሰሉትም የመንዜ ሥሞች ናቸው። ጎንደሬ ደሞ “ሹመት ይወዳል” ይባላል። የጎንደሬ ሥሞች ሹመቴ፣ መኳንንት ወይም መኮንን የመሳሰሉት ናቸው (ወይም ነበሩ)። ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሥም አወጣጥ እንደጊዜው ይለዋወጣል። ጎጃም የሄድን እንደሆነ ደግሞ ከልጅ እስከ አባት (ወይም አያት) ያለው ሥም ተገጣጥሞ ዓረፍተ ነገር የሚሰጥበት ጊዜ አለ። በጣም ታዋቂ ከሆኑት መካከል ብንጠቅስ እንኳ ሐዲስ ዓለምአየሁ፣ በዕውቀቱ ሥዩም፣ ፍቅር ይልቃል፣ እያደር አዲስን ማግኘት ይቻላል።

ሥም እና ፖለቲካ

ሥም የፖለቲካ መሣሪያም ነው። የአብዮቱ ሰሞን የተወለዱ ልጆች ‘አብዮት’፣ ‘ትቅደም’… የሚል ሥም ተሰጥቷቸው ዕድሜያቸውን እንኳ እንዳይደብቁ ሆነዋል። አሁንም ያ ባሕል ቀጥሎ “ሕዳሴ” ከሥም ዝርዝሮች ውስጥ ገብቷል። የኦሮሞ ብሔርተኞች ‘የአማራ’ ሥማቸውን እየቀየሩ ቢሊሱማ (ነፃነት)፣ ኒሞና (አሸናፊ) የመሳሰሉት የወጣት ‘አክቲቪስቶች’ ተመራጭ ሥሞች እየሆኑ ነው። ኦቦ ሌንጮ (“አንበሳው” እንደማለት) ለታ (ከዮሐንስ ለታ) እና ብዙዎቹ የኦነግ አንጋፋዎችም ሥሞቻቸውን በመቀየር ነው ትግላቸውን የጀመሩት። በዕውቀቱ ሥዩም የአያቱ ቀዳማይ ሥም በዻዻ መሆኑን መጥቀሱ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን ለመተቸት እንደነፃ ፈቃድ ሆኖለታል (ወይም ተጠቅሞበታል)። ዮናታን ተስፋዬ ደግሞ የአባቱን ቀዳማይ ሥም (ቴሬሳ) ፈልጎ የተጠቀመው የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በአዎንታዊ መንገድ መረዳቱን ለማመልከት ነበር። በተመሳሳይ በ‘ያ ትውልድ’ ዘመን ሥምን ለፖለቲካ ዓላማ ራስን ለመደበቅ ሲባል መቀየር የተለመደ ነበር። ሕወሓቶች የሞቱ ጓዶቻቸውን ሥም ይወርሱ ነበር። ለገሰ ዜናዊ መለስ ዜናዊ እንደሆኑት ማለት ነው። በሕወሓት ለፖለቲካ ዓላማ ስዩም መስፍን ከአረቦች (ሶርያዎች) እርዳታ ለማግኘት ራሳቸውን ሙስሊም አስመስለው ለማቅረብ የአባታቸውን ሥም ሙሳ ነው ብለዋል። ብዙዎቹ የኦህዴድ ሰዎችም ከምርኮ ወደትግል ሲገቡ የ“አቢሲኒያ” ሥሞቻቸውን ወደ “ኦሮሞ” ቀይረዋል።

ሥምን ለፖለቲካ አገልግሎት መቀየር በዓለም ዙሪያ የተለመደ ነው። አምባገነኑ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ ‘የአውሮጳውያን’ ነው ያሉትን ሥማቸውን ቀይረው ነው ሴሴ ሴኮን በማስጨመር የትግል ሥም ያገኙት። በአገራቸው ዛየር (የአሁኗ ኮንጎ) የክርስቲያን ሥም (Middle Name የሚባለው) ‘የእብራይስጥን ሥም’ ለአፍሪካውያን ሲሰጥ የተገኘ ቄስ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስር እንዲቀጣ የሚያደርግ ሕግ አውጥቷል። ጥቁር አሜሪካዊው ታጋይ ማልኮም ኤክስ የቤተሰቡን ሥም በ‘X’ የተካው እና ሌሎችም አጋሮቹ እንደዚያው ያደረጉት “የነጮች” ነው ያሉትን የክርስትና ሥም ለመቃወም ነበር።

ሥም እና ሃይማኖት

መጤ ሃይማኖት ነባር ባሕሎችን ሁሉ ደምስሶ የመተካት አቅሙ ኃያል ነው። ክርስትና እና እስልምና የዓለም ሥም አወጣጥ ቅርፅን የለወጡት በዚሁ ኃይላቸው ነው። በዓለማችን ላይ በብዛት ወንዶች የሚጠሩበት ሥም ‘መሐመድ’ ነው የሚል ነገር ማንበቤ ትዝ ይለኛል። በአገራችን ወላጆች ለልጆቻቸው ሥም ሲያወጡ ወይ አምላካቸውን መጥቀስ ወይም ከቅዱስ ባለታሪኮቻቸው የአንዱን ታሪክ መጥቀስ ይቀናቸዋል። በሱፍቃድ (በእግዜር ፍቃድ)፣ ዋቅጅራ (እግዜር አለ)፣ ገብረእግዚኣብሔር (የእግዜር ሥራ)… ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው።

በቅዱሳን ባለታሪኮች ልጅን መሰየም በተለይ አሁን አሁን ፋሽን እየሆነ መጥቷል። አገር በቀል ሥሞችን ለልጆች ማውጣት ልጆቹን “ፋራ” (ወይም “አራዳ” ያልሆኑ) የሚያሰኝ ይመስላል።

በሌላ በኩል በቀድሞ ጊዜ ለንግሥና ሲባል ሥምን መቀየር የተለመደ ነበር። ብዙ ጊዜ ንግሥናን በጳጳሳት ተቀብቶ ለማፅደቅ ሲባል በክርስትና ሥም መጠራት ደንብ ነበር። (ነገሥታት ራሳቸውን ሥዩመ-እግዚአብሔር ይሉ ነበር። ስለዚህ ንግሥና ፖለቲካዊ ብቻም ሳይሆን ሃይማኖታዊም ነበር) ተፈሪ መኮንን [ቀዳማዊ] ኃይለሥላሴ የተባሉት በዚያ መንገድ ነው። “ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ እስከ እስራኤል ይገዛል” የተባለውን ትንቢት ወይም ጥንቆላ ተከትሎ ነው ካሣ ኃይሉ ራሳቸውን [ዳግማዊ] ቴዎድሮስ ብለው ያነገሡት። ቀዳማዊ ቴዎድሮስም ሥማቸውን ያገኙት በትንቢቱ መሠረት እሰከ እስራኤል የመግዛት (ካልሆነም ትንቢቱን ሰምተው በሥም የሚግገዙላቸው እንዲያገኙ) ተመኝተው ነው። አውሮጳውያን አፍሪቃዊ ኃያል የክርስቲያን መንግሥት መሥርቷል ብለው በአንዲት ደብዳቤ መነሻ ብዙ ያወሩለት የነበረውን ቄስ ዮሐንስ (Prester John) ለመሆንም ሲባል ነው እስከ አራተኛ የተደረሰው። ዐፄ ዮሓንስ እና የወሎ ሙስሊሞች የገቡበት ቁርሾ መነሻም የዐፄው እንደሥማቸው የማደር ምኞት ይመስለኛል።

ሥም እና ስርዓተ—ፆታ

ሥም ስርዓተ-ፆታን የሚገልፅበት ሁኔታም ቀላል አይደለም። ወንዶች በአማራው ተወላጅ ዘንድ በጥቅሉ ምናባዊ ጀግንነትን የሚያጎናፅፍ ሥም ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ ወንዳፍራሽ፣ ናደው፣ ሺመክት፣ መኩሪያ፣ የመሳሰሉትን ሥሞች መጥቀስ ይቻላል። በኦሮምኛ ሌንጮ (አንበሳው)፣ ኬራንሶ (ነብሩ፣ ደፋሩ)፣ ዋንጎ (ቀበሮው) የሚሉ በኃይለኛ አራዊቶች ሥም ለወንዶች የሚሰጡ ስያሜዎች ጀግንነትን ለወንድ የማልበሱ ማኅበራዊ ትውፊት አካል ናቸው። ጫላ (ቀዳሚው)፣ ሁንዳራ/ኢራና (የበላይ)፣ ኩማራ (ሺመክት) የመሳሰሉትም የተጠቀሰውን ምናባዊ ጀግንነት አልባሽ ኦሮምኛ ስያሜዎች ናቸው። በሲዳምኛ አዳቶ (ደፋሩ)፣ ዳፉርሳ (የማይዳፈሩት) የመሳሰሉት ሥያሜዎች የላይኞቹ ዓይነት ሚና አላቸው። በሌሎቹም ቋንቋ እና ባሕሎች ውስጥ ተመሳሳይ አጠራሮች አሉ።

ለሴቶች ሲሆን ውበታቸውን፣ ወይም በቁስ የሚተመን ዋጋቸውን የሚገልፅ ሥም ይሰጣቸዋል፦ መድፈሪያሽ ወርቅ፣ ሺብሬ፣ ወርቂቱ፣ ብሪቱ፣ ሸጊቱ፣ ቆንጂት…የሴቶች ሥም አወጣጥ ሴቶችን በአትክልትና ፍራፍሬ የሚመስልበትም ጊዜ ቀላል አይደለም፤ አበባ፣ ወይኒቱ፣ ትርንጎ፣ ብርቱኳን፣ ሸዊት (በትግርኛ “እሸት” ማለት ነው) ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። በኦሮምኛ ቢፍቱ (ብሩህ፣ ፀሐይቱ/ጣይቱ)፣ ፋኖሴ (መብራቴ)፣ መጋሌ (ጠይም/ቆንጆ)፣ ዱንጉጄ (ሽንኩርት፣ አጭር ቆንጆ)፣ በከልቻ (ኮኮብ፣ ለዓይነ ቆንጆ) የመሳሰሉት ሥሞችና በሲዳምኛ ዳንቺሌ (ቆንጆ፣ ፀባየ ሸጋ)፣ ደራርቱ (አበባ፣ ፍካት (ኦሮምኛም ነው)) ሴትን በውበቷ የመግለፅ ትውፊታዊ ወግ ያሳያሉ።

ሥም እና የቤተሰብ ታሪክ

ሥም አንዳንዴ የሐዘን መግለጫ ነው። አባቱ (ተፀንሶ እያለ ወይም በልጅነቱ) ወይም ታላቅ ወንድሙ የሞተበት ልጅ ለምሳሌ በአማርኛ ምትኩ፣ ማስረሻ… ይባላል፤ በትግርኛ ካልኣዩ፤… ታላላቆቹ ሲወለዱ እየሞቱ እሱ ግን ያንን መሰናክል ያለፈ ልጅ ለምሳሌ በአኙዋክ ኞም ይባላል፤ በሲዳማ ሪቂዋ ይባላል።

ሥም አወጣጥ ልጁ በተወለደ ጊዜ ወላጆች የነበራቸውን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ወዘተ የሚናገርበትም ሁኔታ አለ፤ ለምሳሌ አስማማው፣ አስታርቄ… የመሳሰሉት ሥሞች ብዙ ጊዜ የሚወጡት እየተጥጣሉ (በተለይ በልጅ እጦት) የነበሩ ጥንዶች የልጅ መገኘቱን ተከትሎ ሲስማሙ ነው። ወላጆች ልጅ ሲወልዱና የጥሩ ዕድል (በተለይ የሀብት) መምጣት ከተገጣጠመ ልጃቸውን ሀብታሙ፣ ጥጋቡ፣… ብለው ሊሰይሙት ይችላሉ። በተቃራኒው ከገጠማቸው ደግሞ ያንኑ የሚያንፀባርቅ ሥም ይሰጡታል፤ ለምሳሌ ‘በድሉ’ የሚለው ሥም በዕድሉ ይደግ ከሚለው የመጣ ነው፤ ወይም ሳይታቀድ ከመጣ ነው። በኦሮሞ ትውፊት ተጨማሪ ልጅ የማይፈልጉ መሆኑን ለመግለጽ ወላጆች ለ“መጨረሻ” ልጃቸው ጉታ የሚል ሥም ያወጣሉ።

«ሥምህን ንገረኝና ማንነትን እነግርሃለሁ»

የኒው ሳይንቲስት ጋዜጠኛ ጆን ሆይላንድ “nominative determinism” (ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት) የሚለው ነገር አለው። ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ የሚወክለው በሥማቸው ተገፍተው ለስያሜያቸው የሚስማማ ሙያ ሲከተሉ ነው። ለምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩም ኃይለኛ ቦክሰኛ ቢሆን ኖሮ ሥሙ ከሙያው ጋር አይሰምርም እንል ነበር። በቡጢው ሥዩም ይሆን ነበርና። ስለዚህ የበዕውቀቱ ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ ኋላ ቀር የሚለውን ስርዓት (social order) በነውጥ/ነፍጥ ሳይሆን በዕውቀት በመሞገት መንገሥ/መሰየም ነው።

ብዙ መንግሥቱ፣ ንጉሡ የተባሉ ሰዎች መራኄ መንግሥትነት ማዕረግ ሳያገኙ አንድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ቦታውን መቆናጠጡ ብቻ መንግሥቱ የተባለ ሰው ሁሉ የመንግሥት ኃላፊ ይሆናል ማለት ባይቻልም ሥማቸው ግብራቸውን ቀድሞ እንዲመራው በማድረጉ ረገድ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል በሚለው ግን መስማማት እንችላለን፡፡

በአማራው ማኅበረሰብ ዘንድ ‹ደመላሽ› የሚለው ሥም የሚሰጠው “ደም የተቃቡ” ቤተሰቦች መካከል ከአንደኛው ወገን ተበቃይ ባልነበረበት ጊዜ ለተወለደ ልጅ ነው፡፡ የዚህ ልጅ ዕጣፈንታ ባስተዳደግ ይወሰናል፡፡ ሥሙን ያወጡለት ሰዎች ሥሙን ለምን እንዳወጡለት ብቻ ሳይሆን ምን እንዲያደርግላቸው እንደሚፈልጉም ጭምር እያስተማሩት ነው፡፡ ስለሆነም፣ አድጎ “ጠላት” የሚለውን ወገን ለመግደል መሠማራቱ ሰፊ ዕድል ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ነው የሚሆነው፡፡

ሥም እና ማንነት ግንኙነት አላቸው የሚሉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ “ሥማችን – ወይም ሰዎች ሥማችንን ሲሰሙ በሚያሳዩት ግብረ-መልስ ወይም የማንነት ግምት ላይ ተመሥርቶ ባሕሪያችንን ይወስናል፡፡” ወደድንም ጠላንም በሥማችን ብቻ ሰዎች ዘውጋዊ ማንነታችንን፣ የቤተሰባችንን ሁኔታ፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ግምቶችን ስለኛ ያሳልፋሉ፡፡ እኛም ይህንኑ ስለምንረዳ የሰዎቹን ግምት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል የበኩላችንን ጥረት በማወቅም፣ ባለማወቅም ማድረጋችን አይቀርም፡፡

ሥም በባለቤቱ ላይ የሚያመጣውን ማንኛወንም ዓይነት ተፅዕኖ ለመቀነስ የተለመደ-ሥም (popular name) መስጠት እንደመፍትሔ ይጠቆማል፡፡ ልጆች በሥማቸው ማንነታቸው እየተገመተ፣ እነሱም በምላሹ በሥማቸው እና ሥማቸውን ሰምተው ሰዎች በሚያሳልፉት ግምት ተፅዕኖ ሥር እየወደቁ ‹የሥማቸው ፍሬ› እንዳይሆኑ ሲባል ለልጆች በሚያድጉበት አካባቢ የተለመደ የሚባለው ዓይነት ሥም ቢሰጣቸው የገዛ ሥማቸው ሰለባ ከመሆን ይድናሉ፡፡ 


እንደ ዋቢ:-
– የነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ድርሰቶች፣
– Atatürk (biography), by Andrew Mango
– Wax and Gold, by Donald Levine
– ፍቅር እስከ መቃብርን የጻፉት «ሐዲስ» ናቸው ወይስ «ዓለማየሁ»? (የሚከራዩ አማት እና ሌሎች)፣ በዳንኤል ክብረት
– ሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ በገብሩ አሥራት
– ሥምና ማንነት (ከአሜን ባሻገር)፣ በበዕውቀቱ ሥዩም
– Typology of Oromo Personal Names, by Tesfaye Gudeta Gerba
– እና የተለያዩ ድረገጾች እና ሌሎችም…

አህመድ 29 ዓመቱ ነው። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ፤ ከኬንያ ደግሞ በብራዚል በኩል አድርጎ ወደ ፐሩ ኢኳዶር፤ ኮሎምቢያ፤ ፓናማ ይሸጋገርና በማእከላዊ አሜሪካ ደግሞ ወራት የፈጀውን የኮስታሪካ፤ ኒካራጓ፣ ሆንዱራስ፤ ጓቲማላ፣ ከዚያ በሜክሲኮ በኩል ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ያደረጉትን ጉዞ ያብራራል።

ዶክተር መረራ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚካሄድ ”Vision Ethiopia”  የተባለ ሲቪል ማህበረሰቦችና የፓለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ሊያደርጉ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሊመጡ ነበር።

ግርማ ካሳ

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ | ምስጢራዊ መረጃ

በቅርቡ አንድ በትግሪኛ የተዘጋጀ ሚስጥራዊ ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። ህወሓት በወልቃይት ዙሪያ ያጋጠመውን ፈተና ለመመከት እንዲያስችለው ያዘጋጀው ሰነድ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ናኦሚን በጋሻው

Lencho Leta. ኦቦ ሌንጮ ለታ

በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር፣ ኦዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮች በጣም የተከበሩ በሳል አመራሮች ናቸው። ለዓመታት በትግሉ ውስጥ ያለፉ፣ በርግጥም ለኦሮሞው ማኅበረሰብ የሚበጀውን እና የሚጠቅመውን የተረዱ። በኦሮሞውና በሌላው ማኅበረሰብ መካከል አለመተማመን እና መጠራጠር እንዳለ፣ ይሄንንም ለመግዛት እና ለመበዝበዝ እንዲያመቸው ሆን ብሎ ያደረገው ሕወሃት እንደሆነ በሚገባ የሚያውቁ። የኦሮሞው ማኅበረሰብ ከሌላው ጋር ያለውን ግንኙነትና ትስስር አጠናክሮ ለሁሉም እኩል የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ይቻል ዘንድ ፍላጎት አላቸው። በፖለቲካ አመለካከታቸው ጥሩ መስመር ላይ ያሉ ነው የሚመስሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጓድ ካፍትሌ

ጥያቄ ለአንባገነኖች፤ ዓለምን የሚገዛው ኃይል የቱ ነው?

“Whoever wishes to foresee the future must consult the past; for human events ever resemble those of preceding times. This arises from the fact that they are produced by men who ever have been, and ever shall be, animated by the same passions, and thus they necessarily have the same results.” Machiavelli

የዴሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ በዓለም ላይ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የተለያዩ የአስተዳደር ስልቶች ተግባራዊ ለማድረግ ተሞክሯል። አብዛኞቹ የአስተዳደር ስልቶች ግን ኃይልን መሠረት ያደረጉ ስለነበሩ በመሪና በተመሪዎች መካከል ከፍተኛ ቅራኔን ሲያሳድር ኖሯል።መሪዎቹ ለሚገዙት ሕዝባቸው ወፍራም ዱላ ካሳዩ ሕዝቡ ቀጥ ለጥ ብሎ ይገዛልኛል ብለው ስለገሚገምቱ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም የሚሊዮኖችን ደም በከንቱ አፍስሰዋል። የአንድ ቀን የሥልጣን ዕድሜያቸውን በአንድ ሺህ ሰዎች ደም ያቆዪታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሊ ጓንጉል

አያሁለት ማዞሪያ (ሃያ ሁለት ማዞሪያ)፣ ምሿለኪያ (መሿለኪያ)

የተሰደዱ እና ባገር ውስጥ በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች እና ጸሃፍትን ብዛት ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረአብ

PM Halemariam Dessalegn daughter wedding. ጠ/ሚ ኃይለማርያም በቅርቡ ሴት ልጃቸውን የሞቀ ሠርግ ደግሰው ሲድሩ

ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሣምንት ያደረጉት ቃለመጠይቅ አነጋጋሪ ነበር። ከኦሮሞ ህዝብ አመጽ ጋር በተያያዘ የሰነበተውን ችግር ሌላ አካል ላይ ማላከክ እንደማይገባ መናገራቸው ከኢህአዴግ ጠባይ አንፃር ያልተለመደ ነበር። በውስጥ ባለ ችግር ምክንያት የህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ህዝብና መንግሥት ተቃቅረው ጉዳዩ ወደ ግጭት ደረጃ መድረሱን ማመናቸው አንድ እርምጃ ወደፊት ነው። ችግሩ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን መግለፅ መቻላቸው ይደነቃል። ኃይለማርያም በዚህ ደረጃ ችግሩን አምነውና ተቀብለው ሲያበቁ፤ በመጨረሻ ለተፈጠረው ችግር በጥቅሉ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታ ጥየቃው ካንገት በላይ ነው ወይስ ካንገት በታች ለጊዜው ባናውቅም፤ ይቅርታ መጠየቅ በራሱ ሥልጣኔ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች፥ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሁለት ሣምንታት በፊት የመኪና መተላለፊያ መንገድ ዘግታችሁ ነበር ተብለው የታሠሩ 11 ተማሪዎች ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ PM Hailemariam Desalegnግርማ ሠይፉ ማሩ

“የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፤ ሥልጣን ግን አንለቅም” መሆኑ ነው?
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሪፖርትን በወፍ በረር ስንቃኛው የሚከተለው ይዘት እንዳለው መረዳት እንችላለን። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓመቱ ከመጠናቀቁ ቀደም ብለው የዕድገት ቅናሽ እንደሚኖር በሰበብ ደግፈው አምነዋል። ይህም ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከአስራ አንድ በመቶ የእድገት ልክፍት በግድም ቢሆን መላቀቁን የሚያሳይ ነው። ከዚህ ቀደም የፈለገውን ያህል ተግዳሮት ቢፈጠር ያልተተገበሩ ግዙፍ ዕቅዶች ዝርዝር ቢቀርብም “ቢሆንም 11 ከመቶ አድገናል” እንደ ነበር አንዘነጋውም። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የእድገት ቅናሽ መኖሩን ቢያምኑም “ትንሽ ቅናሽ ያሳያል” በሚል ማለፋቸው ዝናብ ከዘነበ መልሶ ለማቅራራት ዝግጅት እንዳለ አመላካች ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ገለታው ዘለቀ

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፕሮሸንኮ በረሃብ የሞቱትን ሰዎች በመታሰቢያ ሐውልቱ ስር ሲያስቡ። President of Ukraine Petro Poroshenko attending a memorial on November 22, 2014 in Kyiv for the victims of the Holodomor, or the Famine-Genocide conducted by the Soviets in Ukraine in 1932-1933, which killed millions of Ukrainians. (Image: ImagineChina)

ታላላቅ ረሃቦች ተብለው በዓለም ታሪክ ከሚዘከሩት ውስጥ የቻይናውያን ረሃብ አይዘነጋም። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1958-1961 ድረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ረሃብ ተከስቶ ወደ ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ ረግፏል። ብዙ ምሁራን እንደሚሉት ለዚህ አስከፊና ቻይናውያን ሊረሱት ለማይችሉት ረሃብ አንደኛ ተጠያቂ ማዖ ዚዳንግን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ

ያሬድ ኃይለማርያም

የፌዴራል ፖሊስ ሠላማዊ ሰልፈኞችን ሲበትን

በአንድ ማሕበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማሕበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። በእንዲህ አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ ለውጦች ብዙም አይስተዋሉም። አንዳንዶቹም ለውጦች የቁልቁለት ጉዞ ውጤቶች ይሆኑና በራሱ ብቻ ሳይሆን በአያቶቹም ቁስል የሚማቅቅ፣ መቃብር ቆፋሪና ሸክሙ የከበደው ትውልድ ይፈጠራል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

March 21, 1960 Sharpeville Massacre in South Africa

በየዓመቱ በአፍሪካ ውስጥ የተፈጸሙ ሁለት የህዝብ እልቂቶችን አስታውሳለሁ።

በወርሃ መጋቢት በደቡብ

አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት ዘረኛ አገዛዝ/apartheid በሻርፕቪሌ ከተማ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/1960 የፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት አስታውሳለሁ። እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት በሌለው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2005 እና ከህዳር 1-10/2005 እንዲሁም ከ14-16 በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሓት) የጥቂት ጥቁሮች የበላይነት የጎሳ አገዛዝ/apartheid የተፈጸመውን አሰቃቂ እልቂት አስታውሳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ ከቤልጂየም፤    መጋቢት 14፣ 2016 እ.ኤ.አ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማህበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በእንዲህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ […]

ከግርማ ሞገስ የዛሬው ያረጀ አምባገነናዊ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት እንደ ትናንቱ ታላቅ ወንድሙ የደርግ መንግስት የኢትዮጵያችንን የነገ ተረካቢዎች ህጻናት እና ወጣቶች እያሰረ እና በጥይት እየገደለ የስልጣን ዘመኑን ማራዘም ብልህነት አድርጎ ተያይዞታል። 100% መርጦኛል የምትለውን ህዝብ እየገደልክ በስልጣን ላይ መቆየት አትችልም። ያረጀው ወጣቱን …

ኢትዮጵያ ወዴት? (ግርማ ሞገስ) Read more »

በዛሬው እለት በ6/07/08 የአዲስ አበባና የአዳማ ዩኒቨርስቲዎች ሞትን በታጠቁ የወያኔ ጦረኞች ተከበዋል፡፡በተለይ ትላንትና ምሽቱን በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎች በእሳት ሲጋዩ ማደራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። እንዲሁም ዛሬ ጠዋት 1፡30 አከባቢ ላይ ትጥቃቸውን የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጃንሜዳ ከሚገኘው የማዘዣ ጣቢያቸው በከባድ የጭነት መኪናዎች በገፍ እየተጫኑ የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ካምፓስ ሲወሩ አርፍደዋል። ገጀሌው የወያኔ መንግስት ከየአቅጣጫው የሚወረወርብትን […]

 የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን እይታ በዚህ ወር መግቢያ ላይ ኢትዮጵያዉያን የአድዋን መቶ ኻያኛውን ያመት በዓል በያሉበት በአድናቆት አክብረውታል። በየሬድዮ ጣቢያዎቹ፣ በየፓልቶኮቹ፣ በየማኅበራዊ ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን በየተሰበሰቡበት ሁሉ ስለአድዋ ያልተናገረ፣ ያላሰበ፣ ወኔው ያልተቀሰቀሰ የለም ማለት ይቻላል። እንደታላቅነቱና ታሪክነቱ ከሆነ፣ የአድዋ ድል ያንድ ቀን ብቻ በዓል መሆን የለበትም። የትም አገር ሂደን ታሪክ ብንመረምር፣ መዛግብታቸውን ብንገለባብጥ፣ የአድዋን ዐይነት ታሪክ የሠራ […]

ይገረም አለሙ

People has been taken by federal police in south Ethiopia, Sumra.  በደቡብ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሱምራ ብሔረሰብ አባላትን በገመድ አስሮ እየደበደበ አሰቃየ

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸመን የባሪያ ፍንገላን ዘመን የሚያስታውስ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚያሳይ ፎቶ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ተሰራጭቶ አጀኢብ ጉድ ብለናል። ነገሩ ትናንትን እየረሳን ዛሬ ለሚያጋጥመን ነገር አዲስ እየሆንን ጉድ ጉድ ለምንለው ለእኛ ነው እንጂ አዲስነቱ ለወያኔ ከበረሃ ጀምሮ አብሮት የኖረ ተግባሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረአብ

Prof. Ephraim Isaac ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ

ዝነኛው አሸማጋይ ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ መሰንበቻቸውን ሥራ እንደበዛባቸው ተሰምቷል። የኦሮሞን ህዝብ አመጽና ጥያቄ በሰላም ለመጨረስ እዚህም እዚያም እየደዋወሉ ልብ የሚነኩ እግዚአብሔራዊ ቃላት ተናግረዋል። የፕሮፌሠሩ ጥረት በደፈናው የሚነቀፍ ባይሆንም አይሳካላቸውም። የሽማግሌው የእርቅ መንገድ ጥሎ ማለፍ ይዘት እንዳለው ካለፈ ድርጊታቸው ትምህርት ተገኝቷል። በተጨማሪ ድርድር ወይም እርቅ ሲታሰብ መላ የኢትዮጵያን ህዝብ የመብት ጥያቄዎች ታሳቢ በማድረግ እንጂ፤ ጉልበት ካገኘው ኃይል ጋር ብቻ የመደራደር ዝንባሌ ያለፈውን ስህተት መድገም ይሆናል። በመሰረቱ ወያኔ በስውር ሽማግሌ መላክ መጀመሩ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ ከልብ እርቅና መደራደር ፈልጎ እንደማይሆን ይገመታል። ከፋፍሎ የማዳከም የህወሓት አካሄድ ገና ድሮ ተባኖበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

TPLF / ህወሓት

ወያኔዎች ለትግል በረሃ ገባን የሚሉበት ግዜ የንጉሡ ሥርዓት ፈርሶ ኢትዮጵያ ወዴት እንደምትሄድ አይደለም የት ላይ እንደቆመች እንኳን በቅጡ ያልየበት ወቅት ስለነበር፤ ለብሶት ዳርጎ ወደ ጫካ የሚያስኬድ ቀርቶ ከተማ ተቀምጦ ለማኩረፍ የሚያበቃ በደል ነበር ለማለት አይቻልም። ስለሆነም ወያኔዎች በዛን ወቅት ለትግል የተነሱት የአጼ ዮሐንስን ቤተ መንግሥት ይዘው የትግራይን መንግሥት የመመስረት ህልማቸውን ለማሳካት መንግሥት አልባው ወቅት ምቹ ሆኖ ስለታያቸው ነበር። ቢዘገይም ካሰቡት በላይ ተሳክቶላቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፡- ነጻነት ለሀገሬ)

Ethiopian taxi drivers strike

በአሜሪካ “ባለሦስት-ጥፋት ሕግ“ እያሉ ይጠሩታል። ወንጀለኞች ሦስት ከባድ ወይም ደግሞ አስከፊ ወንጀሎችን የሰሩ ከሆነ ከ25 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያደርስ ቅጣት ይበየንባቸዋል።

ዘ-ህወሓት በኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ ጦርነት አውጇል!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሕዝብና መንግሥት እንዲወያዩ ጥሪ ቀረበ፤ ጸሎትና ምሕላ ታወጀ፤ ስለ ሶሻል ሚዲያና ድርቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ!
 (ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2016፤ የካቲት 30/2008 ዓ.ም )፦ የብፁዕ አቡነ ናትናኤልን እረፍትና ቀብር ተከትሎ ከየሀገረ ሰብከታቸው የመጡ አበው የቅ/ሲኖዶስ አባላትን መሰባሰብ ተከትሎ የተጠራው አስቸኳይ ጉባኤ እንደተካሄደ መዘገቡ ይታወሳል። የተሐድሶ ድረ ገጾች “ማህበረ ቅዱሳን ያስጠራው ስብሰባ ነበረ፤ ከሸፈ” ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች ደግሞ ፓትርያርኩ የሚያካሒዱትን የቤተ ክህነቱን አስተዳደርና አሠራር እንዲሁም የቅ/ሲኖዶስን የበላይነት የሚያስተሐቅር ርምጃ እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው በሰፊው ዘግበዋል። ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ በር ያለው እልህ አስጨራሽ ስብሰባ ካለቀ በኋላ የወጣው መግለጫ ብዙ ቁምነገሮች ይዞ እናገኘዋለን። ከነዚህም ውስጥ ሕዝብና መንግሥት እንዲወያዩ ጥሪ መቅረቡን፤ ጸሎትና ምሕላ መታወጁን፤ ስለ ሶሻል ሚዲያና ድርቁ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ማንሣት ይቻላል።

የፖለቲካው አስተዳደር ከብረት የጠነከረ እጅ ጨምድዶ በያዘው ቤተ ክህነት ውስጥ የሚደረጉ ነገሮችን በላይላይ ንባብ ብቻ አነብንቦ ማለፍ ትክክለኛ ትርጉምን አያስገኝም። ለአገራቸውና ለሃይማኖታቸው ቁርጠኛ የሆኑ አባቶች የሚያደርጉትን እውነተኛ እንቅስቃሴ ሳይረዱ በመቅረት ያልሆነ ትርጉም ወደመውሰድ ሊመራም ይችላል። ከዚህ አንጻር ቅዱስ ሲኖዶሱ የወሰነውና ለሕዝብ ይፋ የተደረገው መግለጫ አበረታች ውሳኔዎችን የያዘ መሆኑን መገንዘብ ይገባናል።

ለአብነት ያህል፤ አሁን በአገራችን ያለውን ቅጥ ያጣ የመንግሥት ጭፍጨፋ እና የንብረት ውድመት፤ እንዲሁም የሕዝብ ተቃውሞ “በአንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ሁሉንም የሚያሳስብ ሆኖ አግኝተነዋል” ተብሎ ተገልጧል። ትርጉሙ“ውጥረቱ ከፍያለ ለውጥ ሊወልድ የተዘጋጀ አገራዊ ምጥ ነው” ማለት ነው። መንግሥት በሚዲያዎቹ ዕለት ተዕለት ሊያሳየን ከሚሞክረው ሥዕል ጋር እጅግ የተራራቀ ነው። “አይዟችን፤ አገር አማን ነው” የሚለውን ማሞኛ ሕዝቡም አባቶችም አልተቀበሉትም።

አሁን ያለው ችግር ተራ ችግር ሳይሆን ክቡር የሰው ልጅን ነፍስ እያጠፋ ያለ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ ግሩም የሆነ ግንዛቤ አግኝቷል። “በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀብትና የንብረት ውድመት፣ በተለይም የሕዝብ መገልገያ የሆኑ የእምነት ተቋማት መቃጠል የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን” ብለዋል። በርግጥም በየክፍለ ሀገሩ የሚኖሩ አባቶች እንደመሆናቸው ያለውን ችግር በቅርብ ያውቁታል። “ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ሁኔታ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን” ማለታቸው የሕዝቡ ስቃይ ምን ያህል እንደተሰማቸው ማሳያ ነው። መፍትሔውንም አጠይመው ለመግለጽ “ሁላችሁም ልጆቻቸን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ችግራችሁን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከተው እንድታቀርቡ፣ መንግሥትም የሕዝቡን ችግርና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት” ጥሪ ማቅረባቸውን ልብ ይሏል። በርግጥ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ በጭካኔ እየጨፈለቀ ያለው ማን መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም። ነገሩን ለማጠየም መሞከራቸው እንጂ።

ሌላው ይበል የሚያሰኘው የመግለጫቸው አካል መንግሥት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ረሃብ እንደሌላ ለማሳመን የሚዳክርበትን የችጋሩን ጉዳይ ያቀረቡበት መንገድ ነው። “ሕዝባችንና ሀገራችን በርኀብ፣ በድኅነትና በበሽታ ቸነፈር በተቸገረበት ወቅት” የሚለው ሐረግ ብዙ ይናገራል። “ቸነፈር” ተራ ቃል አይደለም። ከባድ በሽታን የሚወክል ቃል ነው። የረሃቡንና የችጋሩን ጽኑዕነት በበሽታው ቃል ለማስቀመጥ የሞከሩ እንጂ ይህንን ያህል ከባድ የሆነ በሽታ ገብቶ ስለርሱ ለመናገር የፈለጉ አይመስልም።

ሶሻል ሚዲያው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውስጥ አንድ ቦታ አግኝቶ የመግለጫ አካል ለመሆን በቅቷል። የሶሻል ሚዲያውን ሁኔታ በንቃት የሚከታተሉ ብዙ ብጹዓን አባቶች እንዳሉ ግልጽ ነው። የሚጻፈውንና የሚነገረውን ነገር በቅጡ ይገነዘባሉ፤ የሕዝቡንም የልብ ትርታ ያውቃሉ ማለት ነው። በርግጥ ፈር የለቀቁ አንዳንድ አፍራሽ የሶሻል ሚዲያ እንቅስቃሴዎች እንዳሳሰቧቸውም ግልጽ ነው። “ኅብረተሰቡን የሚለያይና የሚያራርቅ መረጃ (ኢንፎርሜሽን) ዕለት ዕለት ብታስነብቡት ትርፉ መራራቅን እንጂ መቀራረብን፤ መለያየትን እንጂ መግባባትን አያመጣም” ማለታቸው በግርድፉ ስናየው ትክክል ነው። ይሁን እንጂ ሶሻል ሚዲያው ባይኖር ኖሮ የመንግሥትን ቅጥ ያጣ ጭፍጨፋ እና ኢሰብዓዊ ተግባሮች ልንረዳ የምንችልበት ምንም አጋጣሚ አይኖርም ነበር። ስለ ጭፍጨፋው አትናገሩ ሳይሆን ጭፍጨፋውን አቁሙ የሚለው መፍትሔ ትክክለኛ ይሆናል።

በአጠቃላይ ብፁዓን አባቶቻችን ያስተላለፉት ውሳኔ ይበል የሚያሰኝ እና ከዚህ ቀደም በጉባኤ እየተናገሩ በመግለጫ ላይ ግን እንዳይገለጽ የሚጣልባቸውን ገደብ አልፈው ሐሳባቸውን ለምእመናቸው ለማድረስ መጣራቸውን የሚያሳይ ትልቅ እመርታ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ቢሠሩ እና ምእመናቸውን ከክፉ ለመታደግ ቢሞክሩ ያስመሰግናቸዋል። ከዚህ በፊት እንጀመሩት በማፍረስ ተግባራቸው ቢገፉም የራሳቸውን ስምና ታሪክ ከማጉደፍ ያለፈ የሚያመጡት ለውጥ እንደማይኖር ከቀዳሚያቸው ሊማሩ ይገባቸዋል። ምእመናንም አባቶቻቸው የሚናገሩትን ንግግር ምንነት ለመረዳት በመጣር፣ እነርሱ ያሉበትን ችግር በመገንዘብና አባቶቻቸውን ለመርዳት በመሞከር የልጅነት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባቸዋል። ፈረንጆች “reading between the lines” እንደሚሉት ከተጻፈው ነገር በላይ ያለውን ትርጉምም ለመረዳት መሞከር ይገባቸዋል። “ፊደል ይገድላል ትርጓሜ ያድናል” እንዲል። ዘመኑን በተርታ ንባብ ሳይሆን በትርጉም እንረዳው።

ቸር ወሬ ያሰማን፤

አሜን      

================== የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ማንበብ ይቻላል። ======

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

“ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ”

(የአገርን ሰላም እሹ ፈልጉ የአገራችሁ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)

 የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ፥ ሰላም ከእግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል፤ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖሩባት የዓለም ምሳሌ ናት፡፡ ይህን ዓለምን የሚያስደንቅ ገጽታችንን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲከተለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት፤

ኢትዮጵያ አህጉረ ሰላም (የሰላም አገሮች) ከሚባሉት ከዓለም አገሮች አንዷ ስትሆን በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ሁሉንም የሚያሳሳብ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ከዚህም ጋር ባለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ያልተጠበቀ ችግር፡

1.በአንዳንድ አካባቢ የሰው ሕይወት ሲጠፋ፤ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፤ የንግድ ተቋማት፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት ሲወድም፤ የሕዝባችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ሲናጋ ሁሉም ኅብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ ሆኗል፤ የዚህ ዓይነቱ ድርጊት በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የሕዝባችን ህልውናና የትውልዱም የወደፊት ዕድል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡

2.ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ሁኔታ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ልጆቻቸን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ችግራችሁን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከተው እንድታቀርቡ፣ መንግሥትም የሕዝቡን ችግርና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡

3. ሕዝባችንና ሀገራችን በርኀብ፣ በድኅነትና በበሽታ ቸነፈር በተቸገረበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መሠረታዊ ወደሆነው የልማት የሰላምና የድርቅ ጉዳይ በማተኮር መልስ ሰጭ መሆን ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡

4. ወገኖቻችን ሆይ፣ በአሁኑ ጊዜ የወቅቱ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ (ብሎገሮችና የፌስቡክ) ተጠቃሚዎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ከሞያችሁ ከዕውቀታችሁ ተጠቃሚዎች የመሆን ምኞታቸው የላቀ ነው፡፡ ሆኖም መልካሙንና ለዕድገት የሚያግዛቸውን ዕውቀት እንጂ ኅብረተሰቡን የሚለያይና የሚያራርቅ መረጃ (ኢንፎርሜሽን) ዕለት ዕለት ብታስነብቡት ትርፉ መራራቅን እንጂ መቀራረብን፤ መለያየትን እንጂ መግባባትን አያመጣም፤ ከዚህ አንጻር የእናንተም ጥረትና ድካም ከንቱ ሆኖ ይቀራል፡፡ በመሆኑም የተከበረ ዕውቀታችሁን፣ ሞያችሁን፤ ለሕዝባችን ፍቅርና አንድነት፤ ለሀገራችን ሰላምና ዕድገት እንድታውሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትጠይቃለች፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን፤

ተቻችሎና ተረዳድቶ የመኖር የተቀደሰ ነባር ባህላችንን የሚያጎድፍ ማናቸውንም አስተሳሰብና እንቅስቃሴ በአንድነት መቋቋም እንደሚገባ አበክረን እየገለጽን፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን በሙሉ፣ በተለይም አገር ተረካቢ ትውልድ የሆናችሁ ወጣቶች፣ ሁከትና ብጥብጥብን ከሚያስከትሉ መጥፎ ድርጊቶች እንድትቆጠቡ፤ ለአገር ሰላምና ልማት ጠንክራችሁ እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም አጥብቀን እያሳሰብን በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀብትና የንብረት ውድመት፣ በተለይም የሕዝብ መገልገያ የሆኑ የእምነት ተቋማት መቃጠል የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፡፡

ይልቁንም ከሁሉም በላይ ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር አምላካችን፤ ለኢትዮጵያ ለሀገራችን ሕዝቦች ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ይስጥልን ዘንድ፤ ድርቁን ረኀቡን አስታግሦ መጪው ጊዜ ዝናመ በረከቱን ይሰጠን ዘንድ በያዝነው በዐቢይ ጾም ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ..

አዲስ አበባ

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ክንፉ አሰፋ

Jawar Mohamed ጃዋር መሐመድ

መገናኛ ብዙኀንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር ተቀብሎ በዜሮ የሚሸኝ ጀግና ነው። በዚህ ተግባሩ አድናቂው ነኝ። “እኔ-ነኝ” ያለ የዲሲ ፖለቲከኛን ሳይቀር ከአንዴም ሁለቴ እንደማስቲካ እያኘከ መትፋቱን እንመሰክራለን። የጡት አባቱ የሆነው ኦነግንም ቢሆን ‘A Critical Assessment of the Oromo Liberation Front” በሚለው መጣጥፉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ የጠረበ ፍጡር ነው። ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ የ”ነፍጠኛውን ሜድያ” ለመጠቀም የማይሞክርበት ምክንያትም የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዳዊት ዳባ

ዛሬ እየሰፋ እየገዘፈና ጉልበት እያገኘ የመጣው ህዝባዊ እንቢታ ከዐረቡ ሀገሩ ህዝባዊ አልገዛም ባይነት የጀመረ ይመስለኛል። ያኔ ከዚህ ሥርዓት በዚህም መንገድ መገላገልም ይቻላል ለካ? የሚለው እሰቦት በአዕምሮው ያልዞረ ኢትዮጵያዊ ነበር ለማለት አይቻልም። የሥርዓቱም ደጋፊዎችም ቢሆኑ በግልባጩ እንቅልፍ ያጡበት ጉዳይ ነበር። አልገዛም ባይነቱ በኛ ሀገር ይሄ-ያ ይጎድለዋል። ይህ አደጋ አለው። በዚህ አንመሳሰልም ይሉ የነበሩትም ቢሆን ግምት ውስጥ አስገብተው አስበውበት ስለነበር ነው። ኃላፊነት ወስደው ይሠሩበት የጀመሩ ስብስቦች እርግፍ አድርገው ቢተዉትም። ድርጅቶች የስትራተጂ ለውጥ ቢያደርጉና ትኩረታቸው ወደሌላ ቢያዘነብልም ሂደቱ የሚገታ አልሆነም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

SMNE announced the formation of the Ethiopian Council for Reconciliation and the Restorative of Justice (ECRRJ) at a public meeting held at the Sheraton Hotel in Silver Springs, Maryland (February 14, 2016)

በአቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመራው ድርጅት አዘጋጅነት በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ስብሰባቸውን ያጠናቀቁት በሀገራችን ዕርቅ አስፈላጊ መሆኑ ላይ በመተማመንና ለዚህም ተግባራዊነት ዕርቅን ከራስ መጀመር እንደሚገባ አጽንኦት በመሰጠት መሆኑን ሰምተናል። የእስከዛሬው ተሞክሮአችን ተግባራዊነቱን እንድንጠራጠር ቢያደርገንም የአሰባሳቢዎቹ ተግባርም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የደረሱበት ድምዳሜ የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ ድጋፍ ሊቸረው የሚገባ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …