ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ቀውስ ያሰጋት ይሆን? – ዶይቸ ቬለ

የኢትዮጵያ መንግስት ለመሰረተ-ልማት ግንባታዎች ከቻይና ብቻ 17.6 ቢሊዮን ዶላር ተበድሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሰፋፊ የመሰረተ-ልማት ግንባታዎች እና የማምረቻ ዘርፉን ለማሳደግ ከውጭ አገራት የሚበደረው ገንዘብ መጠን ያሰጋቸው ባለሙያዎች ግን ከአመት አመት በሚጨምረው ብድር ምክንያት አገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያሰጋታል እያሉ ነው