ነገሮች አዲስ የሚሆኑት፣ በእኛ ትናንትን መርሳት
ይገረም አለሙ

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸመን የባሪያ ፍንገላን ዘመን የሚያስታውስ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚያሳይ ፎቶ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ተሰራጭቶ አጀኢብ ጉድ ብለናል። ነገሩ ትናንትን እየረሳን ዛሬ ለሚያጋጥመን ነገር አዲስ እየሆንን ጉድ ጉድ ለምንለው ለእኛ ነው እንጂ አዲስነቱ ለወያኔ ከበረሃ ጀምሮ አብሮት የኖረ ተግባሩ ነው።