‹‹በእነሀብታሙ ላይ የተደረገው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሳፋሪ ነው›› ‹‹ኢንጂነር ግዛቸው በአንድነት ቤት እንደጀግና መታየት አለባቸው›› ‹‹ከመኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ጋር ተዋህደን መስራት አለብን›› አቶ በላይ ፍቃዱ /የአንድነት ሊቀመንበር ‹የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አሸባሪ ነው›› ‹‹ዘንድሮም አዋጁ ይሰረዝ ብለን መጠየቃችንን እንቀጥላለን›› አቶ ግርማ ሰይፉ /የፓርላማ ተወካይ የአንድነት ም/ፕሬዚዳንት/ ——————————– ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ.ም፣ አንድነት […]

የወያኔ መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል

• ‹‹የወያኔ መንግስት የብርን ዋጋ በቅርቡ ‹ዲቫሊዌት› ሊያደርግ ይችላል››
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ነገረ ኢትዮጵያ
Image
ነገረ ኢትዮጵያ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (cercular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡
በመሆኑም አሁን ላይ ዜጎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹በተለየ ሁኔታ የሚሸጥላቸው ሰዎች ከጉዞ ወኪላቸውና ከበላይ አካል ይዘውት በሚመጡት ደብዳቤ መሰረት ብቻ ነው ምንዛሬ ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ግን እንደበፊቱ ማንም የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይችልም›› ሲል አንድ የንግድ ባንክ ሰራተኛ ገልጹዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ የተከሰተው በዶላር ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የውጭ ምንዛሬዎች ላይ መሆኑንም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በጥቁር ገበያ እስከ 22 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል ከብሄራዊ ባንክ አካባቢ የደረሱት የነገረ ኢትዮጵያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መንግስት ቀደም ሲል በIMF የቀረበለትን የ‹ዲቫሊዌሽን› ጥያቄ መቀበሉ እንደማይቀር ታውቋል፡፡ ‹‹አሁን ያለው ሁኔታ እንደሚያሳየን መንግስት የብርን ዋጋ በቅርቡ ‹ዴቫሉዌት› ማድረጉ አይቀሬ መሆኑን ነው፡፡ አንዳንድ ‹አርቲፊሻል› የውጭ ምንዛሬ እጥረቶች ቢኖሩም ዋናው የችግሩ መነሻ ግን የ‹ዴቫሊዌሽኑ› ጉዳይ ነው›› ሲሉ የብሄራዊ ባንክ የኢኮኖሚ አጥኚው ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
ሰሞኑን መንግስት ለወራት ተከልክሎ የነበረው የአረብ ሀገራት የስራ ጉዞ እንደገና እንዲጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ይህም ወደ አረብ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎች ተጨማሪ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ከማሰብ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡

ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ወደ እውነት ያመጡ ህጎች በኢትዮጵያ አሉ የሚለው ወያኔ ህዝቦች ግን በተግባር ተጠቃሚ ሲሆኑ አላየንም::ህጎቹ በተግባር ይዋሉ ይህንን ህጎች በመመሪያ በደብዳቤ እና በስልክ የሚቀይሩ የሚደፈጥጡ በጥቅም የሚሸጡ የሚረጋግጡ የሚለውጡ ከየወንበራቸው ተሽቀንጥረው ይጣሉ:: የቀን ተቀን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ሂደት ውስጥ እጃቸውን እያጠለቁ ፍትህን የሚያዛቡ አስተዳደራዊ በደሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናት የህዝብን ማህበራዊ ህይወቶች ከማፋለሳቸውም […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

Image
ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።
Minilik Salsawi Via ፍሰሃ ደስታ

በመከላከያ ሚኒስተር ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ምንጮቼ እንደላኩልኝ የወያኔ መንግሰስት ቀኝ እጁን አጥተዋል። በዘመነ አቶ መለስ አድርግ የተባለውን ያለማወላወል የሚያደርግ : በ97 በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት የፈፀመው የኢህአዲግ ታማኙና ፈጥኖ ደራሹ የአጋአዚ ክፍለሰራዊት ከወያኔ መንግስት ጋር የነበረው ቆይታውን በፍቺ ሊፈፅመው መሆኑ ምንጮቼ ገልፀዋል።

እንደ ፍሰሃ ምንጮች ገለፃ በአጋአዚ ክ /ሰራዊት የሚገኙ ሀይሎች ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከቤተ መንግሰት ወጥተው ወደ ሱማሊና ደቡብ ሱዳን ጸጥታ ለማስከበር በሚል እንደተሰማሩ የሚታወቅ ነው። ከሀገር ውጭ እስከሁለት ዓመት ያክል ቆይተው ሲመለሱ ሊከፈላቸው የጠበቁት: ገንዘብ በተባበሩት መንግስታት ስኬል በመሆኑ ከፍ ያለ ነበር የተሰጣቸው ግን ሀምሳ ሽህ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው። ለምን ብለው የጠየቁት ደግሞ የርግጫ የምንትሴ እየተባለ ተቆርጦ እንደቀረ ተገልፆላቸዋል።

ተቆርጦ ተገምዶ ሊያገኙ ከጠበቁት ሩቡን እንኩዋ አላገኙም።በዚህም ምክንያት የክፍለ ሰራዊቱ አባላት መንግስት ላይ ኩፍኛ አንዳኮረፉና በተለይ የሁለት ሀይሎች አብዛኛው አባላት መልቀቅያ እንዳስገቡ: መልቀቅያቸው እንዲቀዱ የተለያየ ተስፋ ቢሰጣቸውም: ለመዓርግ እድገት ቢታጩም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም። ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።በነገራችን ላይ የአጋአዚ ሰራዊት ከውትድርና ውጭ ሌላ ሂወት የለንም ሲሉ እንደነበር ይነገራል ታድያ አሁን ከውትድርና ሂወት ወጥተው ምን ሊሆኑ ነው? ግንቦት ሰባት ጥሪ ሊያደርግላቸው ይችላል የሚል እርግጠኛ ያልሆነ ጥርጣሬ አለኝ።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በዚምባብዌ ገዢው የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ የፊታችን ታህሳስ በሚያካሂደው ጉባዔው የሀገሪቱን ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ የፓርቲ መሪነት ሥልጣናቸውን እንደገና እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ከአቢይ አፈወርቅ

– ደማቅ ውይይትም አድርገዋል።

ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የመተዳደርያ ደንቡን ማሻሻያ ረቂቅ ለግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ ማኅበሩ በጊዜአዊነት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ለመምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪ ኾኖ አገልግሎቱን በመፈጸም ይቆያል፡፡ ጠቅላይ ቤቴ ክህነቱ ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት መከተሉ ማኅበሩ ከፋይናንስ ሥርዐቱ ጋራ የሚጣጣሙ የሒሳብ ሰነዶችን ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡ የኤጲስ ቆጶሳት …

የቡርኪና ፋሶ ጦር ሰራዊት ኮሎኔል ዚዳን የሽግግር መንግሥቱ መሪ ሲል ሰየመ። ለረዥም ዓመታት ቡርኪና ፋሶን በፕሬዚዳንትነት ያስተዳደሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ሥልጣናቸዉን ከለቀቁ በኋላ ከ24 ሰዓታት በላይ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረዉ ከፍተኛ ባለስልጣን ማን መሆኑ በግልፅ የታወቀ ነበር አልነበረም።

ደማቅ ውይይትም አድርገዋል

አቢይ አፈወርቅ
Prof. Mesfin Woldemariam in Sydney, 26 October 2014

ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በቡርኪና ፋሶ ወታደራዊው ኃይል የአስተዳደር ሥልጣኑን ከተረከበ በኋላ እሁድ፣ ጥቅምት 23 ቀን 2007 ዓ. ም. መዲና ዋጋዱጉ ዳግም በተቃዋሚ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃ ዋለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ጎዳና በመዉጣት የሽግግር መንግሥቱ መሪ ሆነዉ ቅዳሜ የተሾሙትን ኮሎኔል ይሳቅ ዚዳን ተቃዉመዋል።

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሥራ አንደ በመቶ በላይ፣ ለበርካታ አመታት እንዳደገ ይናገራል። በአገሪቷ በተለይም በአዲስ አበባ ግንባታዎች ይታያሉ። መንገዶች ይሰራሉ። ነገር ግን ግንባታዎቹ በአብዛኛው ከዉጭ በልምና በመጣ ገንዘብ የተሰሩ እንደመሆናቸው የኢትዮጵይን ምርታማነትና እድገት አመልካች አይደለም። የብር የመግዛት አቅም ከማሽቆልቆሉ የተነሳ፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መጥቷል።

የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ተመዝግቧል የሚሉት የኢኮኖሚ እድገት በርግጥ እድገት ነው ወይ ? ከሆነስ ስለምን ህዝቡ የእድገቱ ተካፋይ ሊሆን አልቻለም ? ለሚሉት ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በጥናትና በመረጃ ላይ ያተኮረ መልስ ለማግኘት፣ በቃሌ የፓልቶክ ክፍል የቀረበ፣ በአንድነት ደጋፊዎች የተቀናበረና የተዘጋጀ፣ ገለጻ ያዳምጡ።

https://www.youtube.com/watch?v=rxVV-Jx … e=youtu.be

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሥራ አንደ በመቶ በላይ፣ ለበርካታ አመታት እንዳደገ ይናገራል። በአገሪቷ በተለይም በአዲስ አበባ ግንባታዎች ይታያሉ። መንገዶች ይሰራሉ። ነገር ግን ግንባታዎቹ በአብዛኛው ከዉጭ በልምና በመጣ ገንዘብ የተሰሩ እንደመሆናቸው የኢትዮጵይን ምርታማነትና እድገት አመልካች አይደለም። የብር የመግዛት አቅም ከማሽቆልቆሉ የተነሳ፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መጥቷል። የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ተመዝግቧል የሚሉት […]

በትናትናው ዕለት ጥቅምት 19/2007 የአንድነት ኦዲቶሪያል ቦርድ እንዳዲስ የተዋቀረ ሲሆን በአዲሱ የኦዲቶሪያል ቦርድ አባላት ሆነው የተመረጡት አቶ ሰሎሞን ስዩም፣ አቶ ዳኒኤል ተፈራ፣ አቶ ጌታቸው ሃይሉ፣ አቶ ደረጀ ጣሰው፣ አቶ አስራት አብርሃም እና አቶ ሲሳይ ሲሆኑ፤ አቶ ሰሎሞን ስዩም የኦዲቶሪያሉ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ደረጀ ጣሰው ደግሞ ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል። የፍኖተ ነፃነት ዋና አዘጋጅ አቶ ነብዩ ሃይሉ […]

ውሳኔው በዋናነት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስንና መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃን ይመለከታል በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር በተቀጡበት ድርጊታቸው ከተገኙ ክህነታቸው እንዲያዝ ተወስኗል ፓትርያርኩ ‹‹አጀንዳው መያዙን አላውቅም›› በሚል ውይይት እንዳይካሔድ ተቃውመው ነበር *          *         * ‹‹እምነት አለው ለማለት ይከብዳል፤ የሙስና አባትና የሰላም ጠንቅ ነው፤›› የተባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ የነበሩትም ያሉትም ፓትርያርኮች ችግር ዋነኛ መንሥኤ እንደኾኑ ተሠምሮበታል በብፁዕ አቡነ …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ10 ተከሳሾች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ተከሳሾች ከግንቦት7 እና ከደሚት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለዋል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት  ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም  ሲሰየም ተከሳሾች በመቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሉዋቸው ክሶች ደርሷቸዋል። የግንቦት7 አመራር ነው የተባለው ዘላለም ውርቅአገኘሁ፣ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃረርና የድሬዳዋ ወኪሎች እንደዘገቡት ከጥቅምት 17 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የመጡ የፌደራል የጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አባላት መሆናቸውን የገለጹ እንዲሁም የፌደራል ፖሊሶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኢንትርኔት ቤት ባለቤቶችን ይዘው በማሰር ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ድርጅቶቻቸውና ቤቶቻቸው የተፈተሹባቸው ሲሆን፣ ንብረቶቻቸውም ተጭነው ተወስደዋል። በሀረር በገሊል ህንጻ ላይ የሚገኘው የአሜን ፕሮዳክሽን …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንግሊዝ አገር የሚታተሙ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ በቂ ሽፋን አይሰጡም በሚል ሲተቹ ቢቆይም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማንሳት እንግሊዝ በኢትዮጵያ የምትከተለውን ፖሊሲ የሚነቅፉ ዘገባዎችን እያወጡ ነው። ዘ ቴሌግራፍ ” እርዳታችን ለተበላሹ እጆች” በሚል ርእስ ባወጣው ሃተታ፣ በቅርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመኖሪያ ቤቶችን እጥረትን ለመፍታት ዳግም በተደረገው ምዝገባ ከ993 ሺ በላይ ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውንና ይህን የቤት ፍላጎት ለማርካት በመንግስት በኩል እየተካሄዱ ያሉ ግንባታዎች አፈጻጸም ደካማ መሆኑን ከኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። እንደመረጃው ከሆነ የአዲስአበባ ቤቶች ግንባታ ለማየት በተካሄደው የመስክ ግምገማ የአዲስአበባ የቤቶች ግንባታ አፈጻጸም በዝቅተኛ …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ27 አመታት አገሪቱን የመሩት ብሌስ ካምፓወሬ፣ እንደገና ለመመረጥ የነበራቸውን ፍላጎት ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ መተዋቸውን ካስታወቁ በሁዋላ፣ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት በመሆን ለማገልገል መፈለጋቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ካልተባረሩ ተቃውሞአችንን አንተውም በማለታቸው፣ ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። ተቃውሞቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ሁሉ የመሪውን መውረድ እንደሰሙ ደስታቸውን ገልጸዋል። የአገሪቱ …

“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”

Image
ቡርኪናፋሶን ያለገደብ ሲመሩ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ለተጨማሪ ዓመታት ሥልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ሙከራ በመክሸፉ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ገለጹ፤ ለአንድ ዓመት የመሸጋገሪያ መንግሥት ተመስርቶ ምርጫ እስከሚደረግ በሥልጣን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሕዝቡና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን ይህንን የሚቀበሉበት ትከሻ እንደሌላቸውና የኮምፓዎሬ አገዛዝ አሁኑኑ መውረድ እንዳለበት በተቃውሟቸው እየገለጹ ነው፡፡ ከ27ዓመት አምባገነናዊ ሥርዓት በኋላ ቡርኪናፋሶ ወደ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ልትሄድ እንደምትች ተጠቆመ፡፡

በቀድሞው ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳንካራ ዘመን የመንግሥት ባለሥልጣንና የሳንካራ ወዳጅ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ፤ ቶማስ ሳንካራ ባልታወቀ ሁኔታ በመፈንቅለ መንግሥት ከተገደሉ ከዛሬ 27ዓመት ጀምሮ ቡርኪናፋሶን መግዛት ጀመሩ፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱን በመምራት የተሳተፉት ኮምፓዎሬ የሳንካራን መገደል በወቅቱ “ድንገተኛ” በማለት ከመጥቀስ በስተቀር ምርመራ እንዲካሄድ አላዘዙም፤ ምስጢሩም እንዳይወጣ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ቶማስ ሳንካራን ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ ለሦስት ዓስርተ ዓመታት ያህል የዘለቀውን አገዛዛቸውን የጀመሩት ኮምፓዎሬ እኤአ በ1990ዎቹ በተደጋጋሚ የተመረጡት ሲሆን የአገሪቱ ሕገመንግሥት ከተሻሻለ በኋላ በሁለት ሺዎቹም ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል፡፡

በአገዛዝ በቆዩበት ዘመን ሁሉ የአውሮጳውያንና የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሥልጣናቸው ሳይደፈር በአምባገነንነት ለመቆየት ችለዋል፡፡ አክራሪ እስላማዊነትን እዋጋለሁ በማለት የአሜሪካ ወዳጅነታቸውን ያጠናከሩት ኮምፓዎሬ በላይቤሪያና ሴራሊዮን እጅግ አስከፊ ጭፍጨፋ ያካሄዱትን እና በአሁኑ ወቅት 50ዓመት እስራት የተበየነባቸው የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ቻርልስ ቴለር የቅርብ ወዳጅ ነበሩ፡፡ ሳንካራን ለመገልበጥና ለመግደል የቴይለር ጦር እንደተሳተፈና በምላሹ ኮምፓዎሬ ለቴይለር ወደ ሥልጣን መምጣትና ከዚያ ጋር ተያይዞ ለተፈጸመው ወንጀል ተባባሪ ናቸው በማለት ሁኔታዎችን የሚያገናኙ ወገኖች አሉ፡፡

በአገራቸው የሚነሱ ተቃውሞዎችን ስልታዊ በሆነ መንገድና በምዕራባውያን ድጋፍ ሲያከሽፉ የኖሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ በአካባቢው አገራት ዘንድ የሰላም ዘንባባ አቅራቢ፣ አስታራቂ፣ አስማሚ፣ ሸምጋይ፣ … ሆነው ምስላቸውን እና ማንነታቸውን ሲገነቡ ቆይተዋል፡፡ በአምባገነንነት በቆዩባቸው ዓመታት በሙስና በተለይም ከአልማዝ ሽያጭ ከሚገኘው ገንዘብ ያላቸው ተሳታፊነት ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡

በቀጣዩ የአውሮጳውያን ዓመት 2015 ሥልጣናቸው የሚያበቃው ኮምፓዎሬ “ደህና ሁኑ” ብለው ለመሄድ የተዘጋጁ አልነበሩም፡፡ በመሆኑም የአገሪቱን ሕገመንግሥት በማሻሻል እንደገና ለመመረጥ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ፡፤ ፓርላማቸውን አሰብስበው ሕገመንግሥቱ እንዲሻሻል በማድረግ ሂደት ላይ እያሉ ሕዝቡ “በቃኝ” አለ፡፡

የ27 ዓመታት አገዛዝ የመረራቸው ዜጎች ሐሙስ ዕለት ፓርላማውን ጥሰው በመግባት ድምጽ እንዳይሰጥ ከማድረግ አልፈው በእሣት አጋዩት፡፡ ተቃውሞ በየቦታው ፈነዳ፡፡ ቡርኪናፋሶ መጋየት ጀመረች፡፡ ሁኔታው ያላማራቸው ኮምፓዎሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፤ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡ ሕዝቡ “ይህንን አገዛዝ አንፈልግም፣ በቃን” አለ፡፡ ሕዝባዊ ዓመጽ በየቦታው ተቀጣጠለ፡፡ በተለይ ዋና ከተማዋ ዖጋዱጉ የዓመጹ ዋና ማዕከል ሆነች፡፡

መንግሥት ሥራ አቆመ፣ ፓርላማውም ፈረሰ፡፡ ድህነት ያስመረራቸው ዜጎች አሁንም ተቃውሟቸውን ቀጥሉ፡፡ ኮምፓዎሬን ማየትም ሆነ መስማት በጭራሽ አይፈልጉም፡፡ ወታደሮች በየአካባቢው ሥነሥርዓት ለማስጠበቅ እየጣሩ ቢሆንም ዓመጹ ግን ቀጥሏል፡፡ ንብረት እየወደመ ነው፤ ባንኮችም ተዘርፈዋል፡፡

ዛሬ አርብ ዳግም ለመመረጥ ሲመኙ የነበሩት ኮምፓዎሬ ሥልጣን በቃኝ፤ መንግሥት ፈርሷል፤ ፓርላማውም አይሰራም፤ ከሥልጣኔ እለቃለሁ ነገር ግን በ2015 ምርጫ እስከሚካሄድ የሽግግር አስተዳደር ተመስርቶ ሁሉም ነገር መረጋጋት አለበት በማለት አስቀድሞ በተቀዳ የቴሌቪዥን መልዕክት ቢያስተላልፉም ሰቆቃ የመረራቸው፣ ኑሮ ያቃጠላቸው፣ ነጻነት የጠማቸው ዜጎች ግን አሁንም “አንሰማም” ብለው ተቃውሟቸውን በመቀጠል ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል፡፡

ሰላሳ አራት የሚሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ፕሬዚዳንቱ ያቀረቡትን ቅደመ ሁኔታ አንቀበልም ብለዋል፡፡ ለኮምፓዎሬ ምላሽ ሲሰጡም “አንድ የምንቀበለው አጭርና ግልጽ ቅድመ ሁኔታ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ብሌዝ ኮምፓዎሬ ከሥልጣን እንዲለቁ ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡

ጦሩ ሥልጣኑን የተረከበ እንደሆነ እየተጠቆመ ሲሆን አገሪቱን በበቂ ሁኔታ ለማረጋጋት እንዳልቻለ ከዋና ከተማዋ የሚመጡ ዜናዎች ይጠቁማሉ፡፡ የሕዝቡ ዓመጽም ወደ ሌሎች ከተሞች እየተዛመተ መሆኑን ከተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እየተሰማ ነው፡፡

በአንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ከአረብ ጸደይ ቀጥሎ የተጀመረ “የአፍሪካ ጸደይ” ሊሆን ይችላል በማለት ግምት የሰጡበት የቡርኪናፋሶ ሕዝባዊ አመጽ ተመልሶ በአምባገነናዊ አገዛዝ እንዳይወድቅ ስጋት አላቸው፡፡ ለዚህም ጠንካራ ተቋማት መመሥረት አስፈላጊነትን ያሰምሩበታል፡፡ በተለይ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ሕዝባዊ ሥርዓት በሚደረግ ጉዞ በቅድሚያ የሚደረጉ መሰናዶዎች ሳይከናወኑ በጭፍን አምባገነኖችን ከሥልጣን እንዲወርዱ ማድረግ በበርካታ አገራት እንደተደረገው መልኩን የቀየረ አምባገነናዊ ሥርዓት ለመመሥረት እንደሚጋብዝ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አንጻር የሕዝብ ንቃተ ኅሊና መዳበር፣ የእርሰበርስ ውይይት መጀመር፣ የተቋማት መመሥረት፣ … ወሳኝነት ያላቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንደሆኑ ያሰምሩበታል፡፡

*********************
“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”
ቡርኪናፋሶ ከአምባገነን ወደ አምባገነን?
http://www.goolgule.com/it-is-over-for- … rkinafaso/

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ቡርኪና ፋሶ ከፈረንሳይ ቅኝ ነጻ ከወጣችበት እ.ኤ.አ. 1984 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምታውቀው ሁለት መሪዎች ብቻ ነው። አፍሪካዊው ቼ ጉቬራ ይባሉ የነበሩት ቶማስ ሳንካራን እና ብሌዝ ኮምፓዎሬን ። ብሌዝ ኮምፓዎሬ ወደ ስልጣን የመጡት ቶማስ ሳንካራ በወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ እ.ኤ.አ. በ1987 ዓ.ም. ነበር።

ኢትዮ -ኮሎኝ የተባለው የስፖርት እና የባህል ማህበር በኮሎኝ ከተማ ከአንድ የስደተኞች ምክር መስጫ ማዕከል ጋር በመተባበር የብዙ ስደተኞችን ጥያቄ የሚመልስ ድረ ገፅ በአማርኛ ተርጉሞ ለስደተኞች አቅርቧል። ስለዚሁ ድረ ገፅ በዛሬው የወጣቶች ዓለም እናወራለን።

የዛኑ-ፒ ኤፍ ፖለቲከኞች አንጋፋዉን የነፃነት አርበኛ እና መሪ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለመተካት እርስ በርስ እየተጠላለፉ ናቸዉ።ከዛኑ-ፒ ኤፍ ጋር ተጣማሪ መንግሥት የመሠረተዉ የዴሞክራሲያዉዊ ለዉጥ ንቅናቄ (MDC) አንዳድ ፖለቲከኞችም የፓርቲዉ መሪ ሞርጋን ሻንግራይ ሥልጣን ያስረክቡ የሚል ጥያቄ አንስተዋል

የኢጋድ አደራዳሪዎች ኬንያዊዉ ጄኔራል ላዛሮ እና ኢትዮጳዊዉ አምባሳደር ስዩም መስፍን በጋራ በሰጡት መግለጫ ለደቡብ ሱዳን ጦርነት መቀጠል የሁለቱንም ተፋላሚ ሐይላት መሪዎች ወቅሰዋል።

Image
ስብሓት ነጋና የኤርትራ ጉዳይ
ስብሓት ነጋ በቪኦኤ የትግርኛ ፕሮግራም ላይ የሚከተለውን ብሏል (ግርድፍ ትርጉም ነው፤ ሙሉ ዝግጅቱ ሲቀርብ ወደ አማርኛ እንመልሰው ይሆናል) ፥
«የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ችግር ነው የሚለው አመለካከታችን ዳግም መፈተሽ አለበት። የአገዛዝ ችግር እንጂ የቅኝ ግዛት አልነበረም።»
ለምን አሁን???
«የኤርትራ ህዝብ ለነፃነት ከነበረው ጉጉትና ከደረሰበት ግፍ አንፃር፤ ነፃነቱን «በመረጠው መንገድ» መቀዳጀቱ ባያስቆጨንም፤ ችግሩ «የቅኝ ግዛት ችግር» ነበር የሚለው አመለካከታችን መስተካከል ያለበት ይመስለኛል።»
አሁንም በድጋሚ፤ ለምን አሁን???
የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ነበር የሚል አመለካከት የህውሓትና የሻዕቢያ ብቻ እንጂ የማንም እንዳልነበር ግልፅ ነው። (የኤርትራ ህዝብ ሳይቀር ከኢትዮጵያ ጋር በአብሮነት መቀጠል እንደሚፈልግ ቀደም ሲል በጥናት የተረጋገጠ መሆኑን በዘውዴ ረታ መፅሃፍ ላይ «የኤርትራ ጉዳይ» ያነበብኩ መሰለኝ። ) ሟች መለስ እስከ ግብአተ መሬቱ ፍፃሜ ድረስ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢ እንደነበረች ሲያውጅ ኖሯል። ችግራቸው የአስተዳደር እንጂ የቅኝ ተገዢነት አይደለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሳደዋል፤ ወዘተ። ችግሩ የቅኝ ግዛት ነው፤ ጥያቄውም የነፃነት ጥያቄ ተብሎ፤ ያለ ህዝበ ውሳኔ መፍትሄ ተሰጥቶበታል። መፍትሄውም ጦስና ግሳንግሱን በሁለቱ ህዝብ መሃል አራግፎ፤ ኤርትራን ህዝብ አልባ ዋሻ አድርጓታል። ስንት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በነሱ ምክንያት አልቀዋል።
ይሄ የአገሪቱ ብቸኛ «ሉዓላዊ ግለሰብ»፤ ይህ አመለካከታቸው ዛሬ መታረም እንዳለበት የሚነግረን ለምን ይሆን? ምን ተንኮል አስቦ ነው??

በሽብር ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ላይ የሚገኙት እነ ሀታብሙ አያሌው ልደታ ፍ/ቤት ቀረቡ
**************************************
በማዕከላዊ እስር ቤት ከ115 ቀን እስር በኋላ ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው
****************************

<a href=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg”><img src=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg” alt=”10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n” width=”252″ height=”144″ class=”alignleft size-full wp-image-15235″ /></a>
በትላናው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሊቀርቡ ያልቻሉት የፓርቲ አመራሮች፣ በድብቅ ትላንትናውኑ ልደታ ፍ/ቤት መቅረባቸውንና ዳኛ ባለመሟላቱ ለዛሬ ጠዋት ተቀጠረው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ከታሰሩበት ማዕከላዊ ፍርድ ቤ/ት ፖሊስ አጅቦ ቢያመጣቸውም ከቀኑ በግምት 5፡00 ሰዓት አካባቢ 4ኛ ወንጀል ችሎት ካስገቡዋቸው በኋላ፣ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ወደ መኪናቸው በመመለስ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት እንደሚቀርቡ ለመጣው ታዳሚ ከችሎት አስተናጋጇ በመገለጹ፣ ከሰዓት በ 8፡00 ሠዓት 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ችሎት መግባት ይከለከል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ታዳሚው ችሎት እንዲገባ ተፈቀደ፡፡

በችሎቱ የቀረቡት 10 ተከሳሾች ሲሆኑ እነሱም፡-

1ኛ. ተከሳሽ የአ/አ ዩኒቨርስቲ ማስትሬት ተማሪ የሆነው ወጣት ዘላለም ወርቅአገኘሁ
2ኛ. ሃብታሙ አያሌው
3ኛ. ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ. አብርሃ ደስታ
5ኛ. የሺዋስ አሰፋ
6ኛ. ዮናታን ወልዴ
7ኛ. አብርሃም ሰለሞን
8ኛ. ሰለሞን ግርማ
9ኛ. ባህሩ ደጉ
10ኛ. ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡

በችሎቱ ላይ 3 ዳኞች የተሰየሙ ሲሆን የመሀል ዳኛው የዘገየነው ዳኞች ባለመሟላታቸው መሆኑን ከገለጹ በኋላ ተከሳሾችን ክሱ እንደደረሳቸው ጠየቁ፡፡ ተከሳሶችም ክሱ እንዳልደረሳቸው መለሱ፡፡ ክሱ የቀረበው ጥቅምት 20 ቀን2007 ዓ.ም መሆኑን ዳኛው ከገለጹ በኋላ ክሱ እንዲታደላቸው አደረጉ፡፡

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉት ተከሳሶች አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚንቀሳቀሰው ራሱን ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት አባል በመሆን ከድርጅቱ አባሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አባላት በመመልመል፣ ህጋዊ የፖቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ ሕዝቡ በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ፣ በደቡብ ክልል ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ መግለጫ በመስጠት፣ እንዲሁም ትህዴን ከሚባል ድርጅት ጋር በህቡዕ ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም በዋና የወንጀል ድርጊት ተካፋይ በመሆን የተከሰሱ ሲሆን ከ6ኛ እስከ 10ኛ ድረስ ያለት ተከሳሾች ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ማህበራዊ ተቋማትን ለማፈራረስ የሽብር ድርጊቱን ለመፈጸም በውጭ ሀገር በተማሩት የማህበራዊ ድህረ ገጽ አጠቃቀም የተለያዩ የፌስ ቡክ አካውንቶችን በመጠቀም ለድርጊቱ መፈጸም ሲሰሩ እንደነበር የአቃቤ ህግ ክስ ያመለክታል፡፡

እንደ ቅደም ተከተሉ ክሳቸው ተነቦ ካለቀ በኋላ ዳኛው ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም ትችላላችሁ ወይስ መንግስት ያቁምላችሁ ብለው በጠየቁት መሰረት ከ8ኛው ተከሳሽ በስተቀር ሁሉም ጠበቃ እንደሚያቆሙ ገለጹ፡፡ ነገር ግን እኛ ጠበቃ ብናቆምም ከታሰርንበት ሀምሌ 1 ቀን ጀምሮ ከጠበቆቻችን ጋር መገናኘት አልቻልንም ክቡር ፍ/ቤቱ ልንገናኝ እንድንችል ትዕዛዝ ይስጥልን፣ እስካሁን ከታሰርንበት ማዕከላዊ ወደ ማረሚያ ቤት እንድንሄድ እንዲታዘዝልን በማለት አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍ/ቤቱ ጠይቋል፡፡

አቃቤ ህግ አንቀጽ ጠቅሶ በሽብር የተጠረጠረ የዋስትና መብትን አይፈቅድም ይላል በመሆኑም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ እንደረግ ጠየቀ፡፡

ዳኛውም በዋስትና ላይ ያላችሁን አስተያየት ይዛችሁ ረቡዕ ጥቅምት 26 ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት መልሳችሁን በጽሑፍ ይዛችሁ ቅረቡ ተከሳሾች በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ይደረግ በማለት ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

በሽብር ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ላይ የሚገኙት እነ ሀታብሙ አያሌው ልደታ ፍ/ቤት ቀረቡ ************************************** በማዕከላዊ እስር ቤት ከ115 ቀን እስር በኋላ ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው **************************** በትላናው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሊቀርቡ ያልቻሉት የፓርቲ አመራሮች፣ በድብቅ ትላንትናውኑ ልደታ ፍ/ቤት መቅረባቸውንና ዳኛ ባለመሟላቱ ለዛሬ ጠዋት ተቀጠረው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ከታሰሩበት ማዕከላዊ ፍርድ ቤ/ት ፖሊስ አጅቦ […]

Image
አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል
#Ethiopia #UDJ #Blueparty #Ginbot7 #EPRDF #MinilikSalsawi

– ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል
– እነ የሽዋስን ጨምሮ 10ር ተጠርጣሪዎች በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

Minilik Salsawi
በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡

የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-

1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው

ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡

ከሳሹ የፌደራል አቃቢ ህግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ እና የጸረ ሽብር ህግ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ክሶቹ በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ጭብጥ ‹‹ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት›› የሚል ሲሆን ‹‹ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ የመንግስትን መሰረተ ልማት በማፈራረስ፣ ህዝብን ለአመጸ በማነሳሳት መንግስትን መለወጥ አላማው አድርጎ ከሚሰራውና ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር አባል በመሆንና በወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ›› በሚል ቀርቧል፡፡

ሁለተኛው የክስ ጭብጥ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡

ከ2-5ኛ የክስ መዝገብ የሚገኙት ማለትም ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽ፣ አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ‹‹ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ከለላ በማድረግ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ቡድን አላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ፋሲል የኔ ዓለምና ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በስልክ በመነጋገርና በማህበራዊ ድህረ ገጸ የተለያዩ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ከግንቦት 7 በተጨማሪ ‹‹ደምኢት የተባለ ቡድን አባል ነው፡፡›› የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡

በስተመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው ረቡዕ ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም 3 ሰዓት ተከሳሾቹ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ጋር ተማክሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በሁለተኛነት ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቀደም ሲል ለአራት ወራት ወደቆዩበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤቱን ስለጠየቁ ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (3ኛ) እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተከሳሾቹ ትናንት ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ጠዋት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም እንደገና ወደማዕከላዊ ተመልሰው ከሰዓት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥረኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ መደበ፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ትላንት በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ በተደነገገው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ በምልአተ ጉባኤው የተመደቡት …

“አንድ ሰው በፖሊስም ሆነ በሌላ የሕግ አስፈጻሚ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ፤ ካልፈቀደ በስተቀር መልስ ያለመስጠት መብት አለው።” አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶ፤ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያ።

ነገም እኛ ከሕዝብ ጥያቄ እንደማናመልጥ ልናውቅ ግድ ይለናል!!!
Minilik Salsawi
እውነትን ብንውጣት ምናለ? በሃሰት ሕዝብን እያታለልን እስከመቼ እንኖራለን ? እስከመቼ ያልሆነ እንደሆነ ያልተደረገ እንደተደረገ እስከመቼ እየተደበቀ እየተሹለከለከ። የሕዝብን የነጻነት እና የመብት ጥማትን ተገን አድርገን በማይረቡ ወንፊቶች ስር ተሸሽገን የተሸሸግን መስሎን እየታየን ለምን ? የማያዛልቅ ጸሎት …. ባለፉት አመታቶች እኮ እያየን ነው ምንም ውጤት የለም አላየንም አልሰማንም የምንልበት ደረጃ ላይ ነን ያለነው። ታዲያ ምንን እንመን ? ማን እውነትን ይዟል እንበል? በፕሮፓጋንዳ አብዮት ተወጥረን እስከመቼ?

ያሌለ ነገር እንዳለ ያልተሰራ እንደተሰራ አይ አንቺ መሬት !! አዎን ያው እውነትን እንያዝ ለህዝብ ከህዝብ በህዝብ የሆነ ስኬታማ ትግል እናድርግ በማለታችን ምናልባት ልንሰደብ ልንዋረድ ልንዘረጥጥ እንችላለን ለምን በፕሮፓጋንዳ የሞሉን እውነትን መዋጥ ስለሚከብዳቸው መግቢያ ሲጠፋ ግለሰቦች ላይ ይዘምታሉ። ግለሰቦችን ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ውጪ ይሳደባሉ ያዋርዳሉ ይወነጅላሉ። ትላንትና ምን አሉ? ዛሬ ምን አሉ? ነገ ምን ይላሉ ? በትግል ላይ ነን እያሉን መስመሩ አያዋጣም ያሉ ሰዎችንስ እንዴት አስዋጡ ? እያንዳንዱን መለስ ቀለስ እያልን በፖለቲካ እና አገራዊ ህዝባዊ ምንዛሬ ላይ ካጤነው መጭውን ጊዜ ለመወሰን አንገታችንን የሚያስደፋን ነገር አፍንጫችን ስር ይወተፋል።

በግልጽ መውጣት ሲገባን ለሌላ የተለመደ ፕሮፓጋንዳ መስመር እና ስልት ቀይረን ስንመጣ ቀን ጠብቆ ከህዝብ ጥያቄ ማምለጥ እንደማይቻል ለመናገር እንደፍራለን። አለማቀፍ ድርጅቶች እና ሚዲያዎች የእሚነግሩን ሌላ መሬት ላይ ያለው ሌላ ፕሮፓጋንዳው የሚነግረን ሌላ ታዲያ የነጻነት ጥማታችንን እንዴት እንወጣ። ያለን የመጨረሻ እድል ሕዝቡ ሆ ብሎ አደባባይ እንዲወጣ ከማድረግ ውጪ አለ አለን በሚሉት ላይ መተማመኑ እንደማያዋጣ ሊሰመርበት ይገባል እኔም እንደ ዜግነቴ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል አውቅልሃልሁ የሚል የህሰት ፕሮፓጋንዳ አንገሽግሾናል ። ነጻነት በጃችን ነውና ራሳችንን ነጻ እናውጣ ።

በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩን የምትፈጥሩት እናንተ ሆናችሁ ሳለ እኛን መፍትሄ አምጡልን ማለታችሁ ተገቢ አይደለም በማለት በከተማዋ የሚታዩ የጸጥታና የኢኮኖሚ ችግሮችን በማንሳት ለባለስልጣኖቹ ሲያስረዱ ውለዋል።
ሀሙስ ከሰአት በሁዋላ በቴፒ መውጫ በሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቅኝት ማድረግ መጀመራቸውና አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ መሰማቱ በከተማው ህዝብ ላይ አለመረጋጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቴፒ ካምፓስ ፈንጅ ተገኝቷል በሚል የተጠናከረ ፍተሻ ሲካሄድ ሰንብቷል።

የሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች ከፌደራልና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንደሚያደርጉም የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በሌላ ዜና ደግሞ ለወራት በጋምቤላ በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ። ቁጥራቸው 50 የሚጠጉ የጋምቤላ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው ዘግቧል።
“ከጋምቤላ ክልል የመጡት ዜጎች በአራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ተመሳሳይ ሰዓት የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ የሚቀርቡ በመሆኑ በዚህ ችሎት ለመታደም የሄደው ህዝብ ከጋምቤላ የመጡትን ዜጎች ተከትሎ በተደረገው ጥብቅ ምክንያት ከፍተኛ ፍተሻ ” መደረጉን ገልጿል፡፡
ጥቅምት 19/ 2007 ዓ.ም ወደ ማታ አካባቢ ከጋምቤላ የመጡ በርካታ ዜጎች በአውቶቡስ ተጭነው ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
መንግስት በክልሉ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ግጭት ሲፈጥሩ ነበሩ ያላቸውን ሰዎች መያዙን አስታውቋል። የአካባቢው ግጭት የህወሃት ሰዎች ከሚያደርጉት የመሬት ቅርምት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች መግለጻቸውን ተናግረዋል።

 

የዩናይትድ ስቴትስ የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር – ናሳ የጠፈር ምልልሱን ሥራ ለግል ኩባንያዎች ኮንትራት እየሰጠ ነው፡፡

ከእነዚህ የግል ኩባንያዎች አንዱ ዋና መሥሪያ ቤቱ ቨርጂንያ የሆነው ኦርቢታል ሳይንስስ ኮርፐሬሽን በሚያንቀሳቅሰው የ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ኮንትራት ኅዋ ውስጥ ለሚገኘው ዓለምአቀፍ ጣቢያ ስንቅና ቁሳቁስ እየላከ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ተልዕኮዎች አንዱ ከትናንት በስተያ ተስተጓጉሏል፡፡

በአንታርስ ሮኬት ከቨርጂንያው ማስወንጨፊያ ከሁለት ቶን በላይ ውኃ፣ ምግብና የምርምር ቁሣቁስ ይዛ የተነሣችው መንኩራኩር ከተተኮሰች ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ፈንድታለች፡፡

በሰው ላይ ምንም ጉዳት አይድረስ እንጂ መላው ጭነት በፍንዳታውና በእሳቱ ወድሟል፡፡

የማስወንጨፊያው ማማ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

በናሳ…

በቅርቡ፣ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት ፣ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያና የኤርትራ ሞኒተሪንግ ግሩፕ በለቀቀዉ ሪፖርት ዙሪያ አንድ መግለጫ አዉጥቷል። አንዳንድ የተወሰኑ ድህረ ገጾች የግንቦት ሰባትን መግለጫ ለጥፈው፣የተባበሩት መንግስታ ሪፖርትን ግን ሳያያይዙ ቀርተዋል። ይሄን ሰነድ በሚከተለው ሊንክ ልታገኙት ትችላላሁ፡

http://www.un.org/ga/search/view_doc.as … S/2014/727

አስገራሚ መረጃዎችን ያካተተ ሰነድ ነው። ሰነዱ አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥቃቅን ግድፈቶች አሉት። ለምሳሌ ግንቦት ሰባትን የአማራ ድርጅት እንደሆነ የገለጹበት ሁኔታ አለ። ከዚያ ዉጭ ከሞላ ጎደል በሰነዱ የተካተተው ዝርዝር፣ የሚታመን ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ ሪፖርት ላይ በስፋትና በቅርብ ጊዜ ትንታኔ እንሰጥበታለን። ግን ለአሁን በግርድፉ አንብቤ ከሰነዱ ያገኙኋቸውን ጥቂት አንኰ ነጥቦች እንዳስቀመጥ ይፈቀድልኝ፡

1) ኦ.ኤን.ኤል፣ኤፍ ከአልሻባብ ጋር እንደሚሰራና ማእከሉን ከኤርትራ ወደ ሶማሊያ እንደወሰደና አሁን ኤርትራ ከበስተጀርባ ሆና መደገፏን እንደቀጠለች

2) ኦነግ የሚባል ነገር እንደሌለ

3) የግንቦት ሰባት ጦር ከ50 እስከ 70 እንደሆነ

4) ደሚት የሚባለው ድርጅት ትልቁና ጠንካራው እንደሆነ፣ ከሕወሃት ተቃዋሚነት አልፎ የኢሳያስ ክብር ዘበኛና ቅልብ ጦር እንደሆነና ከባባድ መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እየተወሰደ ወደ ደሚት እየተሰጠ እንደሆነ

5) ሻእቢያ ለግንቦት ሰባት ሆነ ለሌሎች ድርጅቶች የሚያደርገው እርዳታ የተባበሩት መንግስታትን ዉሳኔ የሚያፈርስ እንደሆነና ግንቦት ሰባት በተባበሩት መንግስታት ራዳር ዉስጥ እንደወደቀ

በቅርቡ ኢትዮጵያያ ሪቪው የተለያዩ ሪፖርቶች ሲያቀርብ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። የዚህ ሞኒተሪንግ ቡድን ሪፖርት በአብዛኛው ኢትዮጵያ ሪቪው ካቀረበው ጋር የሚዛመድ ነው።

በተያያዘ ዜና ደግሞ በኤርትራ ዉስጥ ከፍተኛ ተቃዉሞ በኢሳያስ አፈርቂ አገዛዝ ላይ እየተነሳ እንደሆነ ነው። ሃርነር አርቢ የሚባለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘ ነው። በጦር ሰራዊቱ ዉስጥ ሁሉ ዘልቆ ስለገባ ፣ ኢሳያስ ፊቷን ወደ ደሚት ለማዞር እስኪገደድ ድረስ።
በ ኤርትራ ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ እያለ የተከበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ ከአሜሪካን አገር ሳይወጡ ለምን የግፈኛው አቶ ኢሳያስ ተሟጋች እንደሆኑ አልገባኝም ? እርሳቸውስ እሺ ሌሎች የግንቦት አባላትና ደጋፊዎች፣ እንደ አበበ ገላው፣ መቼ ይሆን አንድ ግለሰብን ማምለክና መከተል አቁመው ለሕዝቡና ለትግሉ የሚጠቅም ነገር የማያደርጉት ?

የግንቢት ሰባት ንቅናቄ የተሳሳተ መንገዱን በአስቸኳይ መመርመር አለበት። ኢሳያስ ሊገነደስ ጥቂት ጊዜ የቀረው የበሰበሰ ዛፍ ነው። እስከመቼ ነው በበሰበሰ ዛፍ ላይ ተንጠልጥለው ትግሉን ብለው ወደነርሱ የመጡትን ለጋ ኢትዮጵያዉያን የሚያስበሉት ?

Image

የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና በማጽናት ተጠናቀቀ ::

+ የፓትርያርኩ ምሬትና ብስጭት ያሳሰባቸው ብፁዓን አባቶች ሲያረጋጓቸው አመሹ::
+ አቡነ ማትያስ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡

‹‹ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ አንዱንም የተቀበለኝ የለም›› በሚል የተመረሩት አቡነ ማትያስ ምክራቸው ያልሠመረላቸውን ሦስት አማሳኝ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡

ከትላንትናው የስብሰባ ውሎ መጠናቀቅ በኋላ ፓትርያርኩ የነበሩበት የምሬትና የብስጭት ኹኔታ ተነግሯቸው ወደማረፊያቸው የተጠሩት በሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ማትያስ በተጠሪነት ጉዳይ የተሟገቱለት አቋም የቤተ ክርስቲያን እንዳልኾነ፣ ለአጭር ዕድሜ የኖረው የቤተ ክርስቲያን ሕግ መለወጥ እንደሌለበት ይልቁንም የአማሳኞችንና የባዕዳንን ምክር ከመስማትና ከመቀበል ተጠብቀው ትላንት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ ኹነው የተከላከሉለትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማስከበራቸውን ቢቀጥሉ በእርሳቸውና በአባቶች መካከል ያለው ውጥረት ሊረግብና ሊተራረቅ እንደሚችል አመልክተዋቸዋል፡፡

ፓትርያርኩ በትላትናው ምሽት አማሳኞቹን በብስጭትና በምሬትም ቢኾን ከአበረሯቸውና በብፁዓን አባቶች ምክር ከተጽናኑ በኋላ በዛሬው የምልአተ ጉባኤው ውሎ ስብሰባውን በተረጋጋና በመግባባት መንፈስ ሲመሩና ‹‹እናንተ ካላችኁት አልወጣም›› እያሉ በጋራ ሲወስኑ ውለዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት(ልዕልና) በማረጋገጥ በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ አጀንዳ፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ(ጳጳስ) ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶሱ እንደኾነ ጸንቷል፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ ሲሠራበት የቆየው ልምድ በማሻሻያው ተካትቶ እንዲደነገግ ተወስኗል፡፡ በልዩነት ነጥቦቹ ላይ በተላለፉት ውሳኔዎች መሠረት ረቂቁ ተስተካክሎ ሲቀርብ በምልአተ ጉባኤው አባላት ፊርማ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በደቡብ አፍሪቃ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብና በምእመናን መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት መፍትሔ ለመስጠት በቀረበው የአጣሪ ልኡክ ሪፖርት ላይ የመከረው ምልአተ ጉባኤው÷ ብፁዕነታቸው ለጊዜው መንበረ ጵጵስናቸውን በናይሮቢ አድርገው በኬንያ፣ በጅቡቲና በሱዳን ተወስነው እንዲሠሩ፤ በደቡብ አፍሪቃ ደግሞ አገልግሎቱ በአድባራት አለቆችና በሰባክያነ ወንጌል ላይ ተመሥርቶ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሰሜን አሜሪካ በሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ጉዳይ መምከር ጀምሯል፡፡

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን የቻለ ሊቀ ጳጳስ ስለመመደብና በሀገረ ስብከቱ የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ በነገው ዕለት በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች