በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክንበመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡
የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል፡፡
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል፡፡
በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣ ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል፡፡
ተጠያቂነትም በተመለከተ ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራም ለሚያስከትለው ማንኛውም የወንጀል ድርጊት ወይም የፍትሐብሄር ጉዳት የፕሮግራሙ ሃላፊና የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪው በአንድነት ተጠያቂ ይሆናሉ ይላል፡፡
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራምን ቁጥጥርን በተመለከተ ከህብረተሰቡ በቅሬታ መልክ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመመርመር፣ተቆጣጣሪ የመመደብ ስልጣን ወደፊት ለሚቋቋመው ባለስልጣን መ/ቤት ሃላፊነቱን ይሰጣል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የቴሌቪዥንን ከአናሎግ ወደዲጂታል ሽግግርን ለማቀላጠፍና የግል ቴሌቪዥን ለመፍቀድ ይረዳል ተብሎአል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢትዮጵያ የሚዲያ ባለስልጣን የሚባል መ/ቤት ይቋቋማል፡፡
የብሮድካስት አግልግሎት የሚመራበትን ሥርዓት ለመደንገግ ከ15 ዓመታት በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 178/1991 የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ፈቃድ ለግል ባለሃብቶች የፈቀደ ቢሆንም ይህ ተግባራዊ ሳይሆን አዋጁ በቁጥር 533/1999 የተሻሻለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተሸሻለውም አዋጅ ቢሆን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያ የተፈቀደ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ኢትዮጵያ ለዚህ ደረጃ ገና አልበቃችም በማለት አዋጁ እንዳይፈጸም እስካሁን ድረስ መከልከሉ የሚታወቅ ነው፡፡

ናትናኤል በርሔ (ኖርዌይ)

የኢትዮጵያ መንግስት(EPRDF) በ1988፣1992፣1997 እና 2002 ዓም አገር አቀፍ የምርጫ እንቅስቃሴ አድርጎዋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ላለፉት 24 ዓም በሞኖፖል ያስተዳደረ መንግስት ሲሆን በዚሁ አገዛዝ ዘመን በዘር፣በጎሳ፣በሃማኖት የመከፋፈል እያስተዳድረ ሲሆን በ 2002 ዓም ላይ በተደረገው የምርጫ ዘመን በፓርላማ በነበረው 547 የምርጫ ወንበር ውስጥ 545(99.6%) በብቸኝነት ያሸነፈ መንግስት ነው። በሚመጣው ዘመን 2007 ዓም እነሱ እንደሚሉን ከሆነ የምርጫውም ውጤት 11% ያሳድጉት እና 547 መቀመጫውን ይወስዱት ይሆን ? አሁን እንኳን ስለምርጫ ለመናገር ሳይሆን በአገራችን ውስጥ እየተፈፀመ ስላለው ዜጎች ከቀያቸው (መኖሪያ ) አካባቢ ሳይፈልጉ መፈናቀል፣ መሰወር ፣ የሰራ ዋስትና ማጣት ፣ሰብዓዊ ክብራቸውን ማዋረድ፣ያለበቂ ማስረጃ ማሰር፣ እና ሌሎችንም ምክንያቶች እየተጠቀመ የሚያደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተስፋፋ በመሔድ ላይ ይገኛል። አንዳንድ ግዜ መንግስት በማን አለብኝ ያሰራቸውን ሰዎች ፍርድ በቤት ለማቅረብ መረጃዎችን አይኖራቸውም ስለዚህ ያለው አማራጭ እስረኞቹ እንዲናዘዙ ማድረግ ብቻ ነው።ለምሳሌ በኢትዮጵያ ወንጀል መቅጫ ህግ አንቀፅ 27 መሰረት አንድ ተከሳሽ ወንጀሉን ሰርቻለሁ ብሎ የእምነት ቃሉን እስከሰጠ ድረስ መረጃ ባይቀርብበትም እንኳን ተጠያቂ ይሆናል።

በ1997 እስር ቤት ውስጥ በድብደባ ህይወታቸው ካለፉ ግለሰቦች መሃከል ፣

1.ገድሉ አየለ ሁሉአንተ

2.ፀጋዮ አየለ ይግዛው
3.እርጋት(አርጋት) ጎበና ማሩ

የተባሉ ግለሰብ በደረሳባቸው ከፍተኛ ድብደባና ህክምና በመነፈጋቸው ህይወታቸው አልፎዋል።እንዲሁም ውቢት ሌንጋሞ የተባለች ነፍሰጡር ሴትም ክፉኛ በመደብደቧ ጽንሷ አጨናግፈውታል።

በቅርቡ በ2006 ዓም ዘመን ብቻ

1.ተስፋሁን ጨመዳ

2.ኒሞና ጥላሁን

3.ኑረዲን ሀሰን

4.አህመድ ነጃሺ
ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ዜጎች ለነፃነት በሚያደርጉት ትግል ዛሬም አሁንም እየሞቱ ይገኛል።

“ጠመንጃን ተገን አድርጎ በህዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓትና አራማጆቹ፤የህዝብን ሰላማዊ ኑሮ ለማተራመስ አማራጭ አድርገው እየተጠቀሙበት ያለው ስልት “ጠንካራ ናቸው

የሚሉዋቸውን” ተቃዋሚዎች ወደ ዘብጥያ መወርወር ሆኗል”
የኢሕአግ መሰረታዊ ዓላማም ወታደራዊ ሃይሉን መከታ አድርጎ በሕዝብ ጫንቃ ላይ በጉልበት የተጫነውን የወያኔ አገዛዝ በተባበረና በሁለገብ የትግል ስልት ለሕዝብ ወሳኝነት እንዲበረከክ ማድረግና ከአንድነትና ከዴሞክራሲ አንፃር ሀገሪቱ የተደራጀ ሃይል በማጣቷ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ትግሉ ያለው መራራነት ግልፅ ቢሆንም አማራጭ ለዚህም መፍትሔው በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ገዥውን መንግስት ከስልጣን ማወረድ ነው።ህዝቦችን በዘር፥ በብሄር፥ በቋንቋ፥ በሀይማኖት፥ በቀለም፥ ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት፥፥ እርስ በእርስ እንዳይስማሙ፥ አብረው እንዳይኖሩ፥ አንድንት እንዳይፈጥሩ፥ በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ፥ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ፥ ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ።

“ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት፥በመልካም አስተዳደር፥በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ፥፥ ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፥ ነፃ ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ (ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ) ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ በተጨማሪም በከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ከሀገር ውጨ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፉዋቸውን ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ማፈንና ከነዚህም ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን ግለሰቦች ኮተት የሆነ የውሸት ክሶች በመደርደር በአሸባሪነት እየከሰሰ ህዝቡ መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም አድርጎዋል” የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ነፃነት “በእርግጥ ሀሳብን በነፃነት መግለጽ አሸባሪነት ከሆነ፤”አሸባሪዎች”ተባሉትን ጋዜጠኞች ብዕር አንስተን ጥቁር ሽብር ያፋፈመውን ወያኔ ኢህአዴግን በሽብር ማንቀጥቀጣችን በእርግጠኝነት የሚቀጥል ይሆናል” ሲሉ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበርና በስደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። Article 19 ማንኛውም ሰው ነፃ ፕሬስ በነፃነት የማንሸራሸር መብት አለው ብለው ያምናሉ።በ አፍሪካ ካሉት ጨቋኝ አፋኝ ይሉት አገራት ግን ይህን የመሰለ መብት ለመተግበርም ሆነ ለመፈፀም ፈቃደኝነት ካለመታየቱም በተጨማሪ “በሽብርተኝነት ስም” እየፈፀባቸው ያለውን ግፍና በደል አገርን ጥሎ ለመሠደድ ያበቃቸውል።

በአሁኑ ጊዜ በትንሹ ከ250 በላይ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በስደት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ይህን ያህል ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች ከአገር በማሰደድ ኢትዮጵያ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር እንደሆነች፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ) በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በ2014 እአአ አሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ እስቴት ዘገባ ከሆነ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ ያላትን አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እያስቆለቆለ እና እየባሰበት በመወረድ ላይ ይገኛል።በዘገባም ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ጉዳዮችን ፌደራል ፖሊስና የፀጥታ ቡድን አባላት በተናጠል፣ በቡድን በማድረግ ግለሰቦችን ከተፈጥሮ ውጭ ህገወጥ ግርፋት፣እስራት፣መግደል ይፈፀማሉ።ያለ በቂ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስራት መዳረግ የግለሰቦችን እና የቡድን መብት መጣስ፣ጋዜጠኞች፣ብሎገሮች እንዲሁም የመጽሔት አታሚዎችን እና ባለንብረቶችን ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ መብቶችን መንፈግ።የመሰብሰብ መብት በተቃዋሚ ፖርቲዎች ላይ የስልጣን ጉልበት በሀይል በመጠቀም በፀጥታ ሀይሎች እና በፌዴራል ፖሊስ ተፅእኖ በመፍጠር በመበጥበጥ ሊገኙ ይችላሉ በሚባሉ ነገሮች ላይ አፍራሽ ሃሳቦችን በመፍጠር የመንግስት ሠላዮች አብሮ በማስገባት ብጥብጥ ሁከት መፍጠር ስራየ ብሎ ተያይዞታል።እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሁለተኛ አለም የሚኖሩ ህዝቦች ጨቋኝ መንግስት ዜጋዎቹን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር (human traffiking ) የመጀመርያ መጨረሻው ነው።

ፀረ ሽብር ህግ በመንግስት ህግ ሆኖ በወጣበት ቅርብ አመታት ጊዜያት ብዙዎችን ለእስራት፣ግድያ እንዲሁም በውል በቁጥር ለማይታወቅ ዜጋ ለስደት ዳርጎታል።እንደ ሰብዓዊ መብት ተማጋች (human Right Watch) እምነት ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ consisted to express their right to freedom of expression ይህም ማለት ህጉ ምን ያህል አፋኝ እንደሆነ ለመጥቀስ ይክል በትንሹ March 2011-December 2011 ብቻ በዚሁ ወራቶች 108 የፖለቲካ አባላት አመራር እንዲሁም 6 ጋዜጠኞችን ለእስራት የዳረገ አፋኝነቱን ያመለክታል።አንድ የአንጎላ ጋዜጠኛ እንዳለው ከሆነ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ በመግለፃቸው ምክንያት በገፍ ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ ህብረቱ ዝምታን መምረጡ እጅግ አሳፋሪ ነው ሲል ተናግሮዋል። አያይዞም አንጎላዊ ጋዜጠኛው ራፋየል ሲነገር ጋዜጠኞች በእስርና በእንግልት እየተሰቃዩ ባለበት ሁኔታ የህብረቱ አዲስ አበባ መቀመጥ አስመሳይነት ነው ብሎ አክሎዋል 53 አገሮችን የሚወክለው የአፍሪካ ህብረት ለሰብአዊ መብትና ለግልጽነት ቀርጠኛ መሆኑን ይግለፅ።አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚንገላቱ ለሞያ አጋሮቻቸው መቆርቆር አለባቸው።ይህ ሁሉ በደል እየተፈፀመ ባለበት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ባለቤት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች የህብረቱ መቀመጫ በሰብአዊ መብት አያያዝ መልካም ስም እና ዲሞክራሲ መብቶችን ወደ ሚከበርበት አገሮች መዘዋወር እንዳለበት ዘመቻ መጀመር አለባቸው ብሎዋል።

የ ፖለቲካ ነፃነት ስንል በፖለቲካ ለህብረተሰብ ይበጃሉ ይጠቅማሉ እንዲሁም ለአገሪቱ ካለችበት ብሔራዊ ጥቅም የተሻለ የተለወጠ የእድገት ለውጥ ለማምጣት የሚከናወንበት መድረክ ማለት ነው።በእኛ አገር ግን ይህን የመሰለ ፖለቲካን በነፃነት ለማራመድ ካልታደሉት አገሮች ተርታ ትመደባለች።የፖለቲካ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ማለት የተገላቢጦሽ በገዢው መንግስት መፈረጅ ነው።ለዚህም ምሳሌ አስረጂነት የአንድነት ዲሞክራሲና ፍትህ ፣የሰማያዊ ፖርቲ፣የግንቦት 7 አመራርና ሌሎችም አባላት ላይ እየተደረገ ያለው ነገር ለዚህ ሁሉ አስረጂ ነው።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የመብት ገፈፋ የድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ ከ357 እስር ቤቶች በላይ ይገኛል ከዚህ ውስጥ ዴዴሳ፣ጦላይ፣ታጠቅ፣ብር ሸለቆ፣ዝዋይ፣ብላቴ፣ሰንቀሌና በሌሎችም ማረምያ ቤቶች 37,000 በላይ ሰዎች የፖለቲካ እስረኞች ሆነው በየእስር ቤቶ እየተሰቃዩ ይገኛል።

የሲቪክ ማህበራት ግንኙነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዘመን ቁርኝነት ከነበራቸው መሰል ማህበራት አንዱ ነው።እነዚህ ማህበራት የበጉ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጄንሲ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 2009 እኤአ ከወጣው አዋጅ ማህበራትን የሚሰጡትን አገልግሎት በማፈንና ከአገልግሎት ውጭ ከማድረጉም በላይ የብዝሀን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት አሳጥቷል።ከዚህም አፋኝ አዋጅ የሲቪክ ተቋሞችን ሊገኝ የሚችሉን የአለም አቀፍ መብቶችን፣የሰብአዊ መብት፣የሴቶች መብት፣የህፃናት መብት፣በህገመንግስታዊ ስም የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት ለማስታረቅ ከመርዳታቸውም በላይ የሰውን መብት ለማስከበር ይረዳሉም ይጠቅማሉ።ያለመታደል ሆኖ የሲቪክ ተቋም የዚሁ አካል ተተቂም ለመሆን ቻለ።

ከቀያቸው በልማት ስም ማፈናቀል የተለመደ ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው።አንድን አካባቢ በልማት ስም ሲፈናቀሉ ዘርን(ብሔር) መከታ ያደረገ ነው። መሰረተ ልማት የሚፈለግን አካባቢ በመጀመሪያ ለህብረተሰቡ ፍላጎት መሟላት የሚገባቸው መሰረታዊ ስራዎችን መስራት ተገቢ ነው።ከክልሉ የሚነሱ የጤና፣የትምህርት ቤት፣የውሀ መጠጥ፣በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ መሆን አለበት።ማፈናቀል ማለት የህብረተሰቡን የማህበራዊ ኑሮ በማናጋት ህዝብን ወዳልተፈለገ ስደት፣ለጎዳና መዳረግ ነው።ለዚህ ሁሉ ማሳያ ይሆን በአለም አቀፍ ያለን ደረጃ እንመልከት።

-2009-2012 Global Competives index Ethiopia 118 ከ 133

-2009 Global Peace index Ethiopia 128 ከ144

-2011Corruption Perceptions index Ethiopia 120 ከ 182

-2012Human Developemet index Ethiopia 173ከ187

-2014 Global Slavery Index Ethiopia 71 ከ 167

-2014ReporterWitthoutBoarder Index Ethiopia 143 ከ 180

*ሰብአዊ መብቶቻን ለመመለስ የግድ ልማታዊ መሆን አየጠበቅብንም መብታችን ይመለስ።

*ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ በማንኛውም መልኩ የስልጣን ጥምን ማራዘም አይቻልም።

ቸር እንሰንብት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
አስተያየትለመስጠት:- [email protected]

በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩን የምትፈጥሩት እናንተ ሆናችሁ ሳለ እኛን መፍትሄ አምጡልን ማለታችሁ ተገቢ አይደለም በማለት በከተማዋ የሚታዩ የጸጥታና የኢኮኖሚ ችግሮችን በማንሳት ለባለስልጣኖቹ ሲያስረዱ ውለዋል።
ሀሙስ ከሰአት በሁዋላ በቴፒ መውጫ በሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቅኝት ማድረግ መጀመራቸውና አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ መሰማቱ በከተማው ህዝብ ላይ አለመረጋጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቴፒ ካምፓስ ፈንጅ ተገኝቷል በሚል የተጠናከረ ፍተሻ ሲካሄድ ሰንብቷል።

የሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች ከፌደራልና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንደሚያደርጉም የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በሌላ ዜና ደግሞ ለወራት በጋምቤላ በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ። ቁጥራቸው 50 የሚጠጉ የጋምቤላ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው ዘግቧል።
“ከጋምቤላ ክልል የመጡት ዜጎች በአራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ተመሳሳይ ሰዓት የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ የሚቀርቡ በመሆኑ በዚህ ችሎት ለመታደም የሄደው ህዝብ ከጋምቤላ የመጡትን ዜጎች ተከትሎ በተደረገው ጥብቅ ምክንያት ከፍተኛ ፍተሻ ” መደረጉን ገልጿል፡፡
ጥቅምት 19/ 2007 ዓ.ም ወደ ማታ አካባቢ ከጋምቤላ የመጡ በርካታ ዜጎች በአውቶቡስ ተጭነው ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
መንግስት በክልሉ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ግጭት ሲፈጥሩ ነበሩ ያላቸውን ሰዎች መያዙን አስታውቋል። የአካባቢው ግጭት የህወሃት ሰዎች ከሚያደርጉት የመሬት ቅርምት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች መግለጻቸውን ተናግረዋል።

ናትናኤል በርሔ ( ኖርዌይ ቲንግቮል)

ለአንድ አገር አስተዳደር መንግስት ለዜጎቹ መሰረታዊ ፍላጎቶች ከሆኑ ነገሮች አንዱ የሆነው ሰው ስራውን ሰርቶ በቂ የላፋቱን ዋጋ ማግኘት መብት ነው በተለይ በአሁኑ ሰዖት መንግስት እከተለዋለሁ ከሚለው መርህ የተገላቢጦሽ እየሆነ ዜጎች በገዛ አገራቸው በተፈጥሮዋዊ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ የኢኮኖሚ ግሽበት ከድጡ ወደ ማጡ እየተሸጋገሩ ይገኛል።የቀድም ጠቅላይ ሚኒስተር የሽግግር መንግስቱ ሲመሩበት በነበር ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ october 1995 በተጠየቁት ጥያቄ ” የዛሬ 10 ዖመት ወይም 20 ዖመት በሗል ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ባየው ደስ ይለኛል ብለው የሚያስቡት” ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ እሳቸው ሲመልሱ የዛሬ 10 ዖመት ይሆናል ብየ ተስፋ የማደርገው እና የምመኘው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን 3 ጊዜ ምግብ ያገኛል የሚል ነው።ከዛም ቀጥሎ ምናልባት በጣም የተሳካልን እንደሆን በአመት 2 ቅያሪ ወይም 3 ቅያሪ ልብስ ያገኛል እንዲሁም ከዛ በጣም የተሳካልን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ ግፋ ቢል ከመንገድ 2 ሰዖት ርቀት በላይ ይኖራል።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝብ ምግብ አማርጦ ይበላል።ነገር ግን ከ19 ዖመት በፊት የተናገሩት ቃል የተስፋ ቃል ከመሆን ያለፈ እና የዘለል አልሆነም።የኑሮ ውድነቱ ይልቁንስ የታችኛው ክፍል <!–more–>ህብረተሰብ ፈተና ውስጥ እና አደጋ ውስጥ ከቶታል።በተለይ የደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ጭማሪው ይመለከተናል የተባለው የመንግስት ሰራተኞች አብዛኞቹ ይጨመርላቸዋል የተባለው ጭማሪ የኑሮውን ሁኔታ ከመቅረፍ ይልቅስ ኑሮው የባሰ የሚያደገረሽ እና ገንዘብ የመግዛት አቅም ያሳጣዋል።መንግስት ከወራት በፊት የደምዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለቱ ምክንያት በአንዳንድ ምርቱን አምራች ፋብሪካዎች የምርት አቅርቦታቸው ላይ ጭማሪ አሳይተዋል።

በዚህም በተያያዘ ዜጎች፣ገበሬዎች፣ተማሪዎች፣ክሊኒኮች፣ሆስፒታሎች፣ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች የጥራት መጋደል እና በበቂ ሁኔታ ያለመቅረብ ችግሮች ያመጣል።ነጋዴ እና ቸርቻሪ ነን ባዮች ሕዝቡን ጨርቁን አስጥሎ ለመስደድ ቆርጠው የተነሱ ይመስል ከመንግስት ጋር እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ መንግስት ዋጋ ተምንኩ ሲል፣ እነሱ ከላይ ከላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ሸማቹ ግን የእነሱን ጭማሪ ያክል እድገት በየወሩ እንደማያስመዘግብ የታወቀ ነውና ግራ መጋባትን ሲጋፈጥ ይስተዋላል ይህ መተረማመስ ወራትን ተሻግሮ እንደ ከዚህ በፊቱ ድስት ጥዶ የዘይቱን ማለቅ ያየ ሮጥ ብሎ ከሱቅ ማግኘት አልቻለም፡፡ ብዙዎችም ቡና በጨው ሳይወዱ ለመጠጣት ተገደዱ፡፡ ልብሳቸውን በአመድና በእንዶድ ማጠብ እስኪከጅሉ ድረስ የሳሙና ዋጋ የማይቀመስ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ መንግስት የቸርቻሪነትና የአከፋፋይነት መብቱን መንግስት ነክ ለሆኑ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እውነት ይሄ ግና እስከምን ድረስ ያስኬዳል ?
ለመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ በፊት ደሞዝ ሲጨምር አብረው ዋጋ የሚጨምሩትን ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ተብሎ የዋጋ ተመን መደረጉ በብዙ ሚዲያዎች ተወራ፡ ፡ ደስ ብሎን ሳናበቃ የደሞዝ ጭማሪው ምን ያክል እንደሆነ ሳናውቅ የዋጋ ጭማሪን መንግስት ራሱ አንድ ብሎ ጀመረው፡፡ ማባሪያና ማቆሚያ ያጣው የየወሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያልነካካው ማን አለ?

በመጀመሪያው ወር የትራንስፖርት ወጭው አንድ መቶ ብር የነበረ ግለሰብ፣ በሁለተኛው ወር ወደ አንድ መቶ አስራ አምስት ብር፤ በሶስተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር፤ በአራተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ስልሳ ብር እያደገ ይገኛል፡ ፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ነው በየወሩ ይህንን ያክል ጭማሪ መሸከም የሚችለው; በደሞዙ ወይም በገቢው ይህን ያክል ጭማሪ መቋቋም የሚያስችል እድገት እያገኘ ያለው የትኛው ሰው ነው? ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች እጅግ እጅግ አስጨናቂ በሆኑበት በዚህ ዘመን በእግር መሄድን ምርጫ ማድረግ የብዙዎች
ግዴታ እየሆነ ነው፡፡

መንግስት ነዳጅ ወር እየጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ የዚህን ምክንያት በተመለከተ በየጊዜው ምክንያቶች ይደረደራሉ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የአረብ ሀገራት በአብዮታቸው ምክንያት ያቀርቡት የነበረው የነዳጅ መጠን ስለቀነሰ ወዘተ ይባላል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም ? ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ ?

የደሞዝ ጭማሪው የተደረገው ለመንግስት ሰራተኞች እንጅ ለሁሉም የሀገሪቱ ሰራተኞች አይደለም፡፡ እንደውም ይህንን ልብ ብለን ከተመለከትነው ከምሬት ብዛት ሊያስቀን የሚደርስ እውነታ እናያለን፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ሁለት መምህራንን ብናነጻጽር፣ ይህንን እውነታ ማየት እንችላለን፡፡ ለነገሩ የግል መስሪያ ቤቶች ጉዳይ አሁንም ስግብግብ ነጋዴዎችን የሚመለከት ቢሆንም፣ ተቀጥረው የሚሰሩት ግን እንደዜጋም፣ እንደነጋዴም፣ እንደሰራተኛም ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡

መንግስትም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪ በታች እንደ ጨመረ ብዙዎች ይስማማሉ፡ ፡ በሰላሳና አርባ ፐርሰንት ብቻ የሚወሰን ጭማሪ ያደርጋል ብሎ ላለመገመት ታላቁ መነሻ መንግስት ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የሚያጓጉ መግለጫዎች ነበሩ፡፡የሆነው ሆኖ፣ ሀገራችን ይህን በመሰለ የወል እውነታ ውስጥ እንዳለች እየታወቀ፣ የኑሮ ውድነት ከእለት እለት ሲባባስ፣ አሁንም መፍሄ እየተባሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግር ሲያባብሱ እንጅ ሲያሻሽሉ እያየን አይደለም፡፡

ሰሞኑ የተጨመረው የደምዝ ጭማሪ ውጤታማ እና አመርቂ አለመሆኑን በሰራ ላይ እናየዋለን ለምሳሌ ያክል ስኳር አቅርቦትን መንግስት አገር ውስጥ የሚያደርሳቸውን ምርት ለህብረተሰቡ በበቂ ከማዳረስ ያለፍ ገበያውን በማን አለብኝነት ተቆጣጥሮ ድሃውን ህዝብ የዕለት ጉርሱን በመንጠቅ ለረሃብ እና እርዛት ዳርጎታል።ታሪክ
እንደሚያወሳው ከሆነ በንጉሱ ዘመን የመጨረሻ ስርዓት መውደቅ ለፊውዳሉ የቀረቡና የንጉሱን ቤተሰቦች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ስልጣን ላይ መቀመጥ መሞከር ትልቁ ምክንያት በትራንስፖርት ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ላይ በመደረጉ ነበር።የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን በተረከበ ዘመን ኢኮኖሚውን በምኒተሪ እና በፊሲካሊ ፖሊሲ በነፃ የንግድ ስም ህዝቡን እያታለሉ በማደናገር የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚደረግ ስልታዊ መንገድ ነው።

በአገራችን የምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል፣የፖለቲካው ነፀብራቅ ነው።የዚህ ምስቅልቅል በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚው እና ፖለቲካው ዙሪያው ባጠኑት ጥናት ተቋማት የኢትዮጵያ ዜጎቿ ለኑሮ የማይመርጧት ሀገር እንደሆነች ተዘግቧል። 46% የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገራቸው ውጭ በስደት የመከራን ሕይወት ለመግፋት ተገደዋል።ዜጎች ባገራቸው ሰርቶ የመኖር ዕድሉን ማግኘት ካልቻሉበት ሀገር፣ስደት መምረጣቸው ፣የትምህርት፣የስራ ፣የቁጠባ ዕድል ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ ግድ የሚል በተለይ ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ እህቶቻችን የሚደርስባቸው ግፍና ውርደት ፣ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው።ሁሉም አንገት የሚያስደፋ ሆኖዋል።በነዚህ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰሩበትን የደመወዝ ይከለከላሉ፣ ዜጎች በቂ ጥሪት እንዲያፈሩ ከማገዝ ጎን ለጎን ይደበደባሉ፤ ይደፈራሉ፤ በግፍ ይታሰራሉ፤ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ይገደላሉ፡፡ ይህ ዓይነት የዜጎች መብት በድርጅት፣በማህበረሰብን ጥቅም መብት ማስከበር አልቻለም።በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ግፊት ማድረግ አለበት።በምርጫ ሰምን የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ ማስተካከያ ህዝብን መደለል አይቻልም።ቸር እንሰንብት፡፡