የዚምባቡዌ ፖለቲከኞች ሽኩቻ

የዛኑ-ፒ ኤፍ ፖለቲከኞች አንጋፋዉን የነፃነት አርበኛ እና መሪ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለመተካት እርስ በርስ እየተጠላለፉ ናቸዉ።ከዛኑ-ፒ ኤፍ ጋር ተጣማሪ መንግሥት የመሠረተዉ የዴሞክራሲያዉዊ ለዉጥ ንቅናቄ (MDC) አንዳድ ፖለቲከኞችም የፓርቲዉ መሪ ሞርጋን ሻንግራይ ሥልጣን ያስረክቡ የሚል ጥያቄ አንስተዋል