‹‹ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ አንዱንም የተቀበለኝ የለም›› በሚል የተመረሩት አቡነ ማትያስ ምክራቸው ያልሠመረላቸውን ሦስት አማሳኝ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡ ከትላንትናው የስብሰባ ውሎ መጠናቀቅ በኋላ ፓትርያርኩ የነበሩበት የምሬትና የብስጭት ኹኔታ ተነግሯቸው ወደማረፊያቸው የተጠሩት በሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ማትያስ በተጠሪነት ጉዳይ የተሟገቱለት አቋም የቤተ ክርስቲያን እንዳልኾነ፣ ለአጭር ዕድሜ የኖረው የቤተ …


 ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
“ሀረር ጌይ” በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ “ሀረር የባግዳድ እህት ናት” የሚል የረጅም ጊዜ ልማድ እንዳለ አጫውአችኋለሁ፡፡ ይህም አመለካከት የመጣው ሁለቱ ከተሞች የሚመሳሰሉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከተሞቹን ከሚያመሳስሏቸው የህይወት ዘርፎች መካከል አንዱ እምቅ የስነ-ቃል ሀብታቸው ነው፡፡ ከነዚህ የስነ-ቃል ሀብቶች ቀዳሚ ሆኖ የሚጠቀሰው ተረት ነው፡፡ የባግዳድ ተረቶችን በ“አንድ ሺህ አንድ ሌሊት” በኩል አንብበናቸዋል፡፡ የሀረር ተረቶች ግን በመጽሐፍ ያልተሰበሰቡ በመሆናቸው ከብዙኃኑ አንባቢ ዘንድ ሊደርሱ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ እነርሱንም በመጽሐፍ የሚሰበስብ የብዕር ጀግና ያስፈልገናል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ሁለት የሀረር ተረቶችን አጋራችኋለሁ፡፡ ሁለቱንም ተረቶች በልጅነቴ የማውቃቸው ቢሆንም በሀረር ከተማ ቆይታዬ በአዲስ መልክ ሰምቼአቸዋለሁ፡፡  
የሓኪም ጋራ መሰንጠቅ
በጥንት ዘመን ሀረር በድርቅ ተመታች፡፡ በድርቁ ሳቢያም ምንጮቿና ወንዞቿ ደረቁ፡፡ አንድ “ኤላ” (የውሃ ጉድጓድ) ግን በተአምራዊ መንገድ ከመጥፋት ተረፈ፡፡ ይሁንና መገኛው ያልታወቀ ትልቅ ዘንዶ ከጉድጓዱ አፋፍ ተቀምጦ “ኤላው የኔ ነው” በማለቱ ከኤላው ውሃ መቅዳት አስቸጋሪ ሆነ፡፡ የሀረር ህዝብ ከኤላው ውሃ መቅዳት ከፈለገ በየዓመቱ አንዲት ቆንጆ ወጣት መገበር እንዳለበት ዘንዶው በአዋጅ አስታወቀ፡፡ የመጠጥ ውሃ ማግኘት የቸገረው የሀረር ህዝብም አማራጭ ሲያጣ ለዘንዶው በመገበር ከኤላው ውሃ ለመቅዳት ተገደደ፡፡
ለዘንዶው የምትሰጠው ልጅ በእጣ ነው የምትወሰነው፡፡ እጣው የሚወጣበት ሁኔታ ግን ፍትሐዊ አልነበረም፡፡ የሀብታምና የባለስልጣናት ልጆች በስውር ዘዴ ከእጣው ውጪ እንዲሆኑ ይደረግና የድሃ ልጆች ብቻ እየተመረጡ ለዘንዶው ይሰጣሉ፡፡ ድሆቹ ይህንን በደል ቢያውቁትም ከሀብታሞቹ ጋር መፎካከር ስለማይችሉ ልጆቻቸውን ለዘንዶው እየገበሩ እምባቸውን መርጨት ግዴታ ሆነባቸው፡፡
ታዲያ በአንድ ዓመት ልጅ የመገበሩ እጣ የደረሰው ለአንዲት “ተቂይ” (አላህን የምትፈራ) ሴት ነው፡፡ ያቺ ሴት አንዲት ልጅ ብቻ ነበራት፡፡ ልጅቷንም ያገኘችው በስተእርጅና ሲሆን ባለቤቷ ከልጅቷ መወለድ በኋላ ሞቶባታል፡፡ በመሆኑም ሴትዮዋ አንድዬ ልጇን እንደ እናትና እንደ አባት ሆና ነው ያሳደገቻት፡፡  እንግዲህ እነዚያ እጣ አውጪዎች ሴትዮዋ በስተእርጅና ያገኛትንና በድህነት ያሳደጋችትን ያቺኑ ልጅ ለዘንዶው እንድትገብር ነው የፈረዱት፡፡
   ይሁንና ሴትዮዋ ልጇን ለዘንዶው አላስረክብም አለች፡፡ የሰፈሯ ሰዎች “እምቢ ካልሽ እኮ ዘንዶው አንቺንም ጨምሮ ይበላሻል” እያሉ ቢያስፈራሯትም ሴትዮዋ ወይ ፍንክች በማለት በቃሏ ጸናች፡፡ ሰዎቹም “በቃ! ውርድ ከራሳችን!! ዘንዶው ቢበላሽ ተጠያቂ አይደለንም” በማለት ብቻዋን ተዋት፡፡ ወደ ዘንዶው ሄደውም ስለሴትዮዋ እምቢተኝነት ነገሩት፡፡ ከዚያም በየቤታቸው ሆነው ተከታዩን ነገር መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ሴትዮዋም ልጇን ከምታስረክብበት ዕለት በፊት ባለው ምሽት የዘንዶውን ጭካኔና የእጣ አውጪዎቹን አሻጥር እያነሳች ፈጣሪዋን ስትለምን አደረች፡፡ በማግስቱም ከቤቷ ቁጭ ብላ ዘንዶው የሚያመጣውን መቅሰፍት መጠባበቅ ጀመረች፡፡
 ሴትዮዋ ልጇን የምታስረክበው ከጧቱ በሶስት ሰዓት ገደማ የነበረ ቢሆንም ዘንዶው በሰዓቱ ግብሩን አላገኘም፡፡ በዚህም የተናደደው ዘንዶ ሴትዮዋን ከነልጅቷ ሊውጣት እጅግ በሚያስፈራ ግርማ ወደ ቤቷ መጓዝ ጀመረ፡፡ የሰፈሩ ሰዎችም “ሊበላት ነው፤ ሴትዮዋ አለቀላት!” እያሉ በአድናቆትና በተመስጦ ትርዒቱን ይመለከቱ ገቡ፡፡
ዘንዶው አቧራውን እያቦነነ ከሴትዮዋ ቤት አጠገብ ደረሰ፡፡ ሴትዮዋንም ሊውጣት መንደርደር ጀመረ፡፡ ፍላጎቱን ከመፈጸሙ በፊት ግን ፈጣሪ ውጥኑን አከሸፈበት!! እጅግ ግዙፍ የሆነ ንስር (አሞራ) ከሀረር በስተሰሜን አቅጣጫ በመምጣት ዘንዶውን ከመሬት ላይ “ላጥ” አድርጎ አነሳው፡፡ ንስሩ ዘንዶውን ወደ ሰማይ በማውጣት ላይ ሳለም የዘንዶው ጭራ ሀረርን በደቡብ በኩል የከበበውን የሀኪም ጋራን በሁለት ቦታ ከፈለው፡፡
 
  ያ ከይሲ ዘንዶ ፈጣሪዋን የምትፈራው ሴትዮ ባደረገችው ጸሎት ተወገደ፡፡ በሀረር ከተማ ላይ የተጣለው ልጅን የመገበር ግዴታም ለዘልዓለሙ ተነሳ!! ይሁንና ያኔ በዘንዶው ጭራ የተከፈሉት ሁለቱ የሐኪም ጋራ ኮረብቶች በአንድ ላይ ሳይመለሱ እስከዚህ ዘመን ድረስ ዘለቁ፡፡
አሚር ሆይ! አንተ “ኸይሩ”ን ብቻ አስብ፤ “ለሸሩ” ባለቤት አለውና!!
——
በጥንት ዘመን አንድ ቅን ሰውዬ በሀረር ከተማ ይኖር ነበር፡፡ ይህ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ የመጀመሪያው ልጁ ርህሩህና የዋህ የነበረ ሲሆን ሁለተኛው ልጁ ግን ተንኮል እየፈጠረ ሰዎችን ማሞኘትና መሳቅ ይወድ ነበረ፡፡ አባትዬው ትንሹን ልጅ ቢመክረው አልሰማ እያለ አስቸገረው፡፡ ስለዚህ በትንሹ ልጅ ተስፋ የቆረጠው አባት ዘወትር ትልቁን ልጅ እየጠራው “ልጄ ሆይ! አንተ ደጉን ብቻ አስብ፡፡ ለተንኮል ባለቤት አለውና” የሚል ምክር ይሰጠው ነበር፡፡ አባት በዚህም ሳያበቃ ለትልቁ ልጅ “ዓሊ ኸይሮ” (ቅን አሳቢው ዓሊ) የሚል ቅጽል አወጣለት፡፡ ትንሽየውን ግን “ዓሊ ሸርሮ” (ተንኮለኛው ዓሊ) በማለት ሰየመው፡፡
 
   ከጊዜ በኋላ አባት የአዱኛውን ዓለም ተሰናበተ፡፡ በዚህም የተነሳ ልጆቹ ተቸገሩ፡፡ ኑሮ በጣም ከበዳቸው፡፡ በመሆኑም ወደ ሀረሩ አሚር ሄደው በችግር መቆራመዳቸውን ነገሩት፡፡ አሚሩ በአጋጣሚ የቤተ መንግሥት ከብቶችን የሚጠብቅ ሰው ይፈልግ ነበርና ወንድማማቾቹ ለእረኝነት እንዲቀጠሩ ጠየቃቸው፡፡ ወንድማማቾቹ ለስራው የሚሰጣቸውን ምንዳ ሲጠይቁት ከሚበሉት ምግብና ከሚለብሱት ልብስ በተጨማሪ በዓመቱ መጨረሻ ላይ አንዲት ጊደር እንደሚያገኙ አሳወቃቸው፡፡ ወንድማማቾቹም ከአሚሩ የቀረበላቸውን ጥያቄ በደስታ ተቀበሉትና ስራቸውን ጀመሩ፡፡
ወንድማማቾቹ በመቶዎች የሚቆጠሩትን የአሚሩን ከብቶች “አው-ሓኪም”፣ “አቦከር” እና “ሸድዳ ዋ መድዳ” ወደሚባሉት ተራሮች እያሰማሩ በትጋት ማገዱን ተያያዙት፡፡ ስራቸውን በደህና ሁኔታ እያከናወኑ ዓመቱን አገባደዱት፡፡ የዓመቱ መጨረሻ እየተቃረበ ሲመጣ ግን የ“አሊ ሸርሮ” ልብ በግለኝነት መመታት ጀመረች፡፡ ለምንዳ የምትሰጣቸውን ጊደር ጉዳይ ሲያስብ አዕምሮው በስስት ተወጠረ፡፡ በመሆኑም “ወንድሜን ገድዬው ጊደሪቱን የግሌ ማድረግ አለብኝ” በማለት ወሰነ፡፡ እቅዱንም በአው ሓኪም ተራራ ላይ ለመፈጸም ቆረጠ፡፡
ወንድማማቾቹ ከብቶቹን ወደ “ሓኪም” ተራራ በወሰዱበት በአንደኛው ቀን “አሊ ሸርሮ” ለወንድሙ “አንተ ከዚህ ሆነህ ከብቶቹን ጠብቅ፤ እኔ ተራራው ላይ ወጥቼ ለምለም ሳር እንዳለ ልይና ልመስ” አለው፡፡ “አሊ ኸይሮ”ም በቀረበለት ሃሳብ ተስማምቶ ከብቶቹን ለብቻው መጠበቅ ጀመረ፡፡ “አሊ ሸርሮ” ከተራራው ላይ እንደ ወጣ ትልቅ ድንጋይ አንቀሳቅሶ ወንድሙ ወዳለበት አቅጣጫ ቁልቁል ለቀቀው፡፡ ድንጋዩ ከተራራው ላይ እየተንከባለለ ወረደ፡፡ ከ“አሊ ኸይሮ” አጠገብ ሲደርስ ግን ወደ ወርቅነት ተቀየረ፡፡ “አሊ ኸይሮ” በዚህ ተአምር ተገረመ፡፡ “ወደ ወርቅነት የተቀየረው ድንጋይ እኔና ወንድሜ ሀብታም እንድንሆን ዘንድ ከአላህ የተሰጠን ነው” በማለት በደስታ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡ የተፈጠረውንም ተአምር ለወንድሙ ለመንገር በጉጉት ይጠባበቅ ጀመር፡፡
 
 “አሊ ሸርሮ” በበኩሉ “አሊ ኸይሮ በድንጋይ በመገደሉ “ጊደሪቱ የኔ ብቸኛ ሀብት ትሆናለች” እያለ በደስታ ከተራራው ወረደ፡፡ ወንድሙ ወደነበረበት ቦታ ሲደርስ ግን ያልጠበቀውን ነገር አየ፡፡ “ይህ ወርቅ ከየት ነው የመጣው?” በማለትም ወንድሙን ጠየቀው፡፡ አሊ ኸይሮም “አንድ ትልቅ ድንጋይ ከተራራው ላይ እየተንከባለለ መጥቶ እኔ ጋ ሲደርስ ይህንን ወርቅ ሆነ” በማለት መለሰለት፡፡ “አሊ ሸርሮም “ድንጋዩ የተንከባለለው ከስሩ የነበረውን ለምለም ሳር ለማየት ብዬ ስላንቀሳቀስኩት ነው፤ እዚህ ደርሶ ወደ ወርቅ ከተቀየረ እኔም የራሴ ወርቅ ሊኖረኝ ይገባል፡፡ ስለዚህ አንተም በተራህ ወደ ተራራው ውጣና ሌላ ድንጋይ አንከባልልኝ” አለው፡፡
“አሊ ኸይሮ”ም ከወንድሙ የሰማውን ሳይጠራጠር ወደ ተራራው ወጥቶ ትልቅ ድንጋይ አነሳና “አሊ ሸርሮ” ወደነበረበት አቅጣጫ አንከባለለው፡፡ ይሁንና ድንጋዩ ወደ ወርቅነት ሳይቀየር “አሊ ሸርሮ”ን ጭፍልቅ አድርጎ ገደለው፡፡ “አሊ ኸይሮ” ከተራራው ወርዶ ወንድሙ ወደነበረበት ስፍራ ሲሄድ ወንድሙ ሞቶ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም ደነገጠ፡፡ ወደ ሀረሩ አሚር ሄዶም የተከሰተውን ሁሉ አንድ በአንድ ነገረው፡፡ ሆኖም አሚሩ ሊያምነው አልቻለም፡፡ “ወንድምህን ራስህ ነህ የገደልከው” በማለትም ከሰሰው፡፡ በመሆኑም “ነፍስ ያጠፋ ሰው ይገደል” በሚለው የሀረር ከተማ ጥንታዊ ህግ መሰረት በድንጋይ ተጨፍልቆ እንዲሞት ተፈረደበት፡፡
 
“አሊ ኸይሮ”ም ፍርዱ ሊፈጸምበት ወደ “ሐኪም” ተራራ ግርጌ ተወሰደ፡፡ ከተራራው ላይ ትልቅ ድንጋይ ተንዶ ቁልቁል ተወረወረበት፡፡ ይሁንና ድንጋዩ “አሊ ኸይሮ” አጠገብ ሲደርስ እንደገና ወርቅ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ የቅጣቱን አፈጻጻም ለማየት በስፍራው ተሰብስቦ የነበረው የሀረር ህዝብም በተፈጠረው ነገር በጣም ተገረመ፡፡ “ይህ ተአምር ልጁ ወንድሙን እንዳልገደለ በሐቅ ይመሰክራል” በማለትም ደመደመ፡፡ የሀረሩ አሚር በበኩሉ “የዓሊ ኸይሮ”ን ተአምር ሲያይ “በህይወቴ ስፈልገው የነበረውን ሐቀኛ ሰው ዛሬ አገኘሁት” የሚል ቃል ተናገረ፡፡ “አሊ ኸይሮ”ንም የዙፋኑ ወራሽ በማድረግ ሾመው፡፡
—–
ወደ ሀረር ከተማ ከመጣችሁ “Amiroo! Kheyruma yaadi, Sharriin abbuma eeydii” የሚል አባባል ትሰማላችሁ፡፡ “አሚር ሆይ! አንተ ኸይሩን ብቻ አስብ፤ ለሸርሩ ባለቤት አለውና” እንደማለት ነው፡፡ ከአባባሉ ጀርባ ብዙ ታሪኮች ይነገራሉ፡፡ ከነዚያ ታሪኮች መካከል አንዱ ከላይ የቀረበው ተረት ነው፡፡
 በተረቱ እንደተገለጸው ተንኮለኛ ሰው በለስ የቀናው መስሎት ብዙ የሸር ትብታቦችን ሊተበትብ ይችላል፡፡ ይሁንና እንደዚህ ዓይነቱ ሰው አጓጉል ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡ የማታ ማታ ራሱ በሸረበው የተንኮል ድር መታሰሩ የማይቀር ነው፡፡ ስለዚህ በህይወት እያለ ደግ ደጉን ብቻ አስብ!! ለተንኮሉ ባለቤት አለውና!!
በድጋሚ Amiroo kheyruma yaadi, Sharriin abuma eeydi ብለናል፡፡
—-
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 20/2007
—–
The writer, Afendi Muteki, is a researcher and author of the ethnography and history of the peoples of East Ethiopia.  You may like his facebook page and stay in touch with his articles and analysis: Just click the following link to go to his page.
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 8/2007
ሀረር-ምስራቅ ኢትዮጵያ

የግብፅ መንግሥት በሀገሩ ሙሥሊሞች አኳያ የሚከተለውን ፖሊሲ ካልቀየረ በስተቀር በሲና በረኃ የአክራሪዎች ጥቃት እየተጠናከረ ሊሄድ እንደሚችል የፖለቲካ ታዛቢዎች አስጠነቀቁ። እንደሚታወሰው ፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በዚሁ አካባቢ

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት   የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል። …

የአሸባሪ ቡድን ድርጅቶች በመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመዝረፍና በከፍተኛ ገንዘብ በማግኘት ላይ መሆናቸዉ ተመልክቶአል። ይህን ጥንታዊ ቅርስ ከሚገዙት ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስ አድናቂዎች እና ሰብሳቢዎች መካከል ደግሞ ጀርመናዉያንም እንደሚገኙበት ተመልክቶአል።

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ያክል በታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲጸዳዳ መደረጉን፣ ለ3 ቀናት በጨላ ክፍል ውስጥ ታስሮ የበቀል እርምጃ እንደተወሰደበት ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ደግሞ በታፈነ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉን፣ በተቅማጥና በሌሎች በሽታዎች እየተሰቃየ …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በምዕራብ ሸዋ በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼክ ሙሃመድ አላሙዲጅ ንብረት በሆነው ” ኢትዮ ድሪም” ድሪም የአበባ እርሻ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው በመሆኑ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ሰራተኞች አቤቱታቸውን ለድርጅቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም መልስ ማጣታቸውን ገልጸዋል። አብዛኛው ሰራተኛ 600 ብር እንደሚከፈለው የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ከዚህ …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሪክ ማቻር የሚመራው የተቃዋሚ ቡድን ቤንቲዩና ሮቡክና የተባሉ ቦታዎችን መቆጣጠሩን መረጃዎች አመለክተዋል። ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስታረቅ በኢትዮጵያ በኩል ሲደረግ የነበረው ድርድር ውጤት አለማምጣቱን ታዛቢዎች ይናገራሉ። የሪክ ማቻር ሃይሎች ሃይላቸውን እያጠናከሩ በመሆናቸው ሌሎች ከተሞችንም ለመያዝ ተከታታይ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ ሲሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ገልጸዋል።

የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ ዶይቸ ቬለ በአሜሪካ የሚኖሩት አድማጩች ስርጭቱን በስልክ የሚያደምጥበት አገልግሎት መጀመሩ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ። ይህንኑ አገልግሎት ተግባራዊ ያደረገው በዩኤስ አሜሪካ የሚገኘው «አውዲዮ ናው » የተሰኘው ድርጅት የራድዮ ስርጭት በስልክ የማድመጡ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የግንቦት 2007 ምርጫን የጊዜ ሰሌዳ አፀድቆ ይፋ አደረገ። የቦርዱ ስራ ኃላፊዎች ዛሬ በሂልተን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጊዜው ሰሌዳ ከመፀደቁ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድርግ እና ማሻሻያዎችን በማከል የፀደቀ መሆኑን አመልክተዋል።

ወያኔ/ህወሓት ያደራጃቸው ምሊሽያዎች በአፋር ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ

አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

ትናንት ማክሰኞ 18/02/2007 በአፋር ክልል በሰሜናዊ ዞን በኮናባ ወረዳ በትግራይ ታጥቂ ሚሊሻዎች በኮናባ ፈራስዳገ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ጦርነት የከፈቱ ሲሆን ቦታውን በቶክስ እሩምታ ሲያምሱት ማርፈዳቸውን ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ለጊዜው ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የቶክስ ምላሽ አላገኙም! ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን የተጀመረው ይህ ቶክስን ተከትሎ ከኮናባ ወረዳ ብዙ ወጣቶች ተሰብሰበው በፍጥነት ወደ ቦታው የደረሱ ሲሆን በዛን ጊዜ የኔትዎርክ አገልግሎት ወዲያው ተቋርጧል። እስካሁን ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የተተኮሰ አንድ ጥይት የለም።

የቦታው ምንጮች አያይዘውም «ይህ ደግሞ የአፋር ወጣቶች ለሰላም ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው። ነገር ግን አስገዳጅ ነገር ከተፈጠረ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ከየቦታው ተሰብስበው ዝግጅት ላይ ናቸው።» ብለዋል። ከኮናባ አንድ ስሙን ሊናገር ያልፈለገ ወጣት እንደነገረኝ «ይሄ በህወሓት ሆን ተበሎ የሚደረግ ትንኮሳ በመሆኑ የአፋር ወጣቶች በበሰለ አስተሳሰብ ለሰላም ያላቸው ፈለጎት በትዕግስት አሳይተዋል።» ብሏል። አያይዞም «ኔትወርክ ራሱ የጠፋው ለሌሎች መረጃ እንዳይደርስና የአፋር ህዝብ እንዳይነሳ በመፍራት ነው» ሲል አክሏል። አሁንም ቦታው ውጥረት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኮናባ ወረዳ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊን አስተያየት ለማካተት ያደረኩት ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

ምንጭ ዘሃበሻ አማርኛ ገጽ

አቡነ ማትያስ÷ የሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ተጠሪነት ለፓትርያርኩ በማድረግ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት በፓትርያርኩ የበላይነት ለመተካት ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መሟገታቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት በመርገጥ በስም እንጂ በግብር የሥልጣን ልዕልና የሌለው ሲኖዶስ ለመፍጠር እየተጣጣሩ ነው፡፡ …

የፊታችን ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄዱ ምርጫዎች፥ ድምጽ ሰጪዎች በፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የመጨረሻዎቹ ሁለት አመታት የትኛው ፓርቲ የኮንግሬሱን የሕግ መወሰኛና የተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቆጣጠር ለመወሰን ድምጽ ይሰጣሉ።

በአንድ አገር ዴሞክራሲ እንዲጸናና ስር እንዲሰድ ሶስት አስፈላጊ ነጻነቶች እነርሱም የመጻፍ የመናገር ሃሳብ የመቀያየር፣ የተደራጀና ነጻ የሆነ የፓለቲካ ተቃዋሚ፣ እንዲሁም ገለልተኛና ነጻ የሆኑ ፍርደ ቤቶችና ዳኞች መኖር አለባቸዉ ይላሉ ፕሬፌሰር አድኖ አዲስ።

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ  ሚኒስትሮችን አወዛግቧል። አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ጸጋየ በርሄ፣ የፌደራል ኦዲተሩ ሪፖርት ለህዝብ በፍጹም ሪፖርት መደረግ የለበትም ብለው …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል ብሎአል። ኢህአዲግከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኝ መዋቅሩን …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ  ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል። የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ በዘገባው አመልክቷል። ‹‹አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ባለፈው አንድ ዓመት በፓርላማው መቀመጫቸው ላይ ታይተው የማያውቁ ሲሆን ለፓርላማው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ወይዘሮዋ  በራሳቸው ፈቃድ ከፓርላማ አባልነታቸው መሰናበታቸውን ገልጸዋል፡፡ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ማይክል ሳታ ህክምናቸውን በሚከታተሉበት እንግሊዝ ሃገር ትናንት ማክሰኞ ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። እአአ ከ2011 ዓም ጀምሮ በስልጣን የቆዩት ፕሬዝዳንት ሳታ ባለፈው ሳምንት የተከበረውን የዛምቢያ 50ኛ የነፃነት በዓል በጤና መታወክ ምክንያት መታደም አልቻሉም ነበር።

ለተንቀሳቃሽ ወይም የእጅ ስልኮች (ሴልስ፤ ሞባይልስ) መልሶ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሞላ «AKU»(አኩሙሌተር) የተለመደ መሣሪያ ነው ። የኤልክትሪክ አውቶሞቢሎች ከጸሐይ ኃይል የሚገኝ ኤልክትሪክ ጉልበት እጅግ ያስፈልጋቸዋል ፤ ዋጋው ደግሞ ተስማሚ ነው።

ተቃዋሚዉ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በዜጎች ላይ የሚደርሰዉን መፈናቀል፤እስራት እና ግድያ መንግሥት ካላስቆሞ ፓርቲዉ ሠላማዊ ትግል በሚጠይቀዉ አማራጭ በሙሉ መንግሥትን ይታገላል።

#Ethiopia #SouthSudan #OELF #ExEthiopianArmyOfficers #MinilikSalsawi

ሰው በላው መንግስቱ ሃይለማርያም መሞት ሆነ መኖር ማንችንንም ሊያስጨንቀን ሊያሳስበን አይገባም።
Minilik Salsawi

በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔን አምባገነን መንግስት ለማስወገድ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ተቃዋሚ ሃይሎች ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ጋር መገናኘታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።ከባለስልጣናቱ ጋር የተገናኙት በኤርትራ ውስጥ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ድርጅቶች እና በአስመራ ቢሮ የሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

በመጪው ጊዜያት ሊደረጉ ስለሚችሉ እና ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ሃይሎች ከጁባ መንግስት ተጽእኖ ስር ያልወደቀ የራሳቸው መንደርደሪያ መሬት እና ወታደራዊ ቤዝ የሚያገኙበትን ጉዳይ በተመለከተ መወያየታቸው ታውቋል። እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ ወታደራዊ እርዳት የሚደረግበትን ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ሲታወቅ በቀድሞ የደርግ መንግስት ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ዜግነታቸው ሃገራቸውን ለመካስ በወታደራዊ አማካሪነት ላይ የሚሰሩበትን አስመልክቶ የጁባው መንግስት ስምምነቱን ገልጿል።ምንጮቹ ከዚህ በላይ ዝርዝር ሁኔታ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

መንግስቱ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ተቃዋሚ የትጥቅ ትግል የሚፈልጉትን አካላቶች ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ያገናኛል የሚል ፍራቻ የተከሰተ ይመስል ይህን ሰሞን ከባለፈው አመታት በተወራረሰ መልኩ በቀጥታ ግልባጭ መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ አድርገው የሻእቢያ አቧራ አጫሽ ድህረገጾች ወሬውን እያቦነኑ ይገኛሉ። በባለፈው ጊዜ እኔ ራሴው መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ ተነፋፍሼ ነበር ከዛሬዎቹ አለን ባይ ምንጮቼ ያገኘሁትን ይዤ ።

የሆኖ ሆኖ በየእስር ቤቱ ስለታሰሩብን የፖለቲካ መሪዎቻችን ጋዜጠኞቻችን እና የሃይማኖት ምሁራን መጨነቅ እና ስለመጪው ትግል ሰፋ ያለ ስራ መስራት ይገባናል ። ሻእቢያ ይህን ሰሞን በኤርትራ የተነሳበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በሌላው ዘንድ አትኩሮት እንዳያገኝ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የመንግስቱ ሃይለማርያምን መሞት ሊያረዳን ይፈልጋል። ወይ ሻእቢያ እና ወያኔ ለማደናበር ማን ብሏቸው።

ለቁጥጥሩ ማኅበራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሞዴላሞዴል ይጠቀማሉ ዕውቅና የመስጠት፣ ደንባቸውን የማጽደቅና የመሰረዝ ሥልጣን የቅ/ሲኖዶሱ ኾኖ ጸንቷል በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያው የማኅበራትን ጉዳይ የሚከታተለው የመምሪያ ሊቀ ጳጳሱ ነው ማኅበረ ቅዱሳን በውሳኔው ማህቀፍ ውስጥ በሚሻሻልለት መተዳደርያ ደንብ ይመራል ስብሰባው የሊቃነ ጳጳሳትን ተጠሪነት በሚወስኑና በሌሎች የማሻሻያው ልዩነቶች ላይ  ቀጥሏል

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ሆኖ የመጀመሪያው
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሕንፃ ‹‹አፍሪካ
አዳራሽ›› በሚል ስያሜ በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴና በወቅቱ ሹማምንት ይፋ ከተደረገ ከ56 ዓመታት በኋላ
20ኛውን ሕንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና
የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን መረቁ፡፡ አዲስ አበባ በተመድ
ተቋማት እንቅስቃሴ፣ ከኒውዮርክና ከጄኔቫ በመቀጠል ሦስተኛዋ
ከተማ ለመሆን መብቃቷን ባን ኪ ሙን ገለጹ፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት በቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር መለስ ዜናዊ
የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው አዲሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን
ሕንፃ ለተመድ ልዩ ልዩ ተቋማት አገልግሎት የሚውል መሆኑን
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን በትናትናው ዕለት በይፋ ያስመረቁት ጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ከ50
ዓመታት በፊት የመጀመሪያውንና የአፍሪካ አዳራሽ ተብሎ
የተሰየመውን ሕንፃ ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አገልግሎት
እንዲውል በስጦታ አበርክታለች፡፡ በ1951 ዓ.ም. የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲመሠረት፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታዎች ለአፍሪካ ኮምጫጫ ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
የአፍሪካ ሕዝቦች ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት
የሚታገሉበት ጊዜ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ በውጭ የሚኖሩ
የአፍሪካ ልጆችም ለአኅጉሪቱ ነፃ መውጣት፣ ለሕዝቦች
እኩልነትና ክብር ሲታገሉ በነበረበት ወቅት ነበር የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዕውን የሆነው፡፡
ዕድምተኛውን ፈገግ በማሰኘት ንግግራቸውን የጀመሩት የተመድ
ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ በዓለም ላይ
ደጋግመው ከጎበኟቸው ከተሞች አንደኛ ሆና እንደምትገኝ
በማስታወስ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለ ማርያምን የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለት
በስህተት መጥቀሳቸው የታዳሚውን ፈገግታ ያጎረፈባቸው ባን
ኪ ሙን፣ ይቅርታ ጠይቀው የስም አጠራራቸውን በማስተካከል
ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡
አዲሱ ሕንፃ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን
ሒሮሺማ ከተማ ላይ ከተጣለው የአውቶሚክ ቦምብ የተረፉ
ዛፎች መጥተው እንደተተከሉበት አስታውሰዋል፡፡ ሕንፃውን
አምስት የተባበሩት መንግሥታት መሥሪያ ቤቶች እንደሚጋሩት
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን የገነባው አገር በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ባለሰባት ፎቅ የሆነውን
ዘመናዊ ሕንፃ ከኒውዮርክ በሚሰጠው ትዕዛዝና ቁጥጥር
እየታገዘ መገንባቱንና አረንጓዴ የግንባታ ይዘት ተብሎ
በሚጠቀሰው ቴክኖሎጂ መገንባቱን የኩባንያው ማኔጂንግ
ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ተድላ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ለሕንፃው ግንባታ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣
በ1800 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እዚያው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ
ኮሚሽን ቅጥረ ግቢ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡
የሕንፃው ግንባታ በሁለት ዓመታት እንዲጠናቀቅ ታስቦ ግንታው
ቢጀመርም፣ ሦስት ዓመት ፈጅቷል፡፡ ይህም ከመጀመሪያውኑ
ከርክክብ ሒደቱ ጀምሮ የተለያዪ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ
በማስገባት ሒደት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማግኘትና
በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደሆነ አቶ ፍሬው ተናግረዋል፡፡
ይህም ሆኖ ሕንፃው በሶላር ኢነርጂና በኃይል ቆጣቢ
ቴክኖሎጂዎች የታገዘ መሆኑን፣ ሰዎች ሕንፃው ውስጥ ሲሆኑ
የሚበሩ፣ ሰዎች በሌሉ ጊዜ ደግሞ በራሳቸው የሚጠፉ
የመብራት ይዘቶችንም አካትቷል፡፡
ራማ ኮንስትራክሽን በሐንኪን ቢራ ፋብሪካ ግንባታ፣ በወንጂ
ስኳር ማስፋፊያ፣ በአዲስ አዳማ የፍጥት መንገድ ግንባታ ላይ
የተሳተፈ ሲሆን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት በፕሬዚዳንት ሙላቱ
ተሾመ የተመረቀውንና ቦሌ አካባቢ የሚገኘውን የኦሮሚያ ልማት
ማኅበር ሕንፃን ገንብቷል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጥቅምት 18/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋኙን ስርዓት በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ አቀረበ፡፡
ImageImage
‹‹የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ ገዥው ፓርቲ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መልኩ አፋኝ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ ገልጾአል፡፡

መግለጫው ለስርዓቱ አፋኝነት በምሳሌነት ካነሳቸው መካከል በአለፈው ክረምት ወራት ጀምሮ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው የግዳጅ ስልጠና የሚገኝበት ሲሆን በስልጠናው ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ እንደተዳፈነ ያሳየ ነው ብሎታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ መሆኑንና ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ መግለጹንም መግለጫው አውስቷል፡፡
ፓርቲው በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የማሳደድ እርምጃ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የተፈጸመው አፈና የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው ብሏል፡፡

‹‹እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ያለው አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመግዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው›› ያለው መግለጫው በተለይ በኦጋዴን በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላም የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እያመራች ለመሆኑ አመላካች ነው ሲል ገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው ‹‹የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስካሁን ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ፣ ከ5 ሺ ያላነሱ ኦሮሞች በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥናቱን ያጠኑት የአምነስቲ የኢትዮጵያ ክፍል ሃላፊ ክሌር ቤስተን መንግስት አገሪቱን ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ  መብት ድርጅቶች እንዲሁም ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ክፍት ቢያደርግ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች  በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል።  መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል። ተመሳሳይ መልእክት የያዙ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ የሚገኙት የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም በምእራብ አፍሪካ የሚታየውን የኢቦላ ወረርሽን ለመዋጋት ቢያንስ 5 ሺ ዶክተሮች የሚያስፈልጉ በመሆኑ ፣ ዶክተሮች ና የጤና ባለሙያዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃዳቸውን እንዲገልጹ ተማጽነዋል። ” በአሁኑ ሰአት ይህን ሁሉ ቁጥር ያለው የህክምና ዶክተር ከየት እንደምናገኝ ሳስብ እጨነቃለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ …

የስዊድን ጋዜጠኞች ማኅበርና የተለያዩ ለፕረስ ነጻነት የሚቆረቆሩ ወገኖች በትናንቱ ዕለት ፣ ኤርትራ ውስጥ ባለፉት 13 ዓመታት በአሥራት ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅን አስበውት ዋሉ ። በትውልድ ኤርትራዊ በዜግነት ስዊድናዊ የሆነው ዳዊት ጉዳይ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች