የወያኔው ቀኝ እጅ የአጋአዚ ጦር ሊበተን ይችላል ::

ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።
Minilik Salsawi Via ፍሰሃ ደስታ
በመከላከያ ሚኒስተር ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ምንጮቼ እንደላኩልኝ የወያኔ መንግሰስት ቀኝ እጁን አጥተዋል። በዘመነ አቶ መለስ አድርግ የተባለውን ያለማወላወል የሚያደርግ : በ97 በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት የፈፀመው የኢህአዲግ ታማኙና ፈጥኖ ደራሹ የአጋአዚ ክፍለሰራዊት ከወያኔ መንግስት ጋር የነበረው ቆይታውን በፍቺ ሊፈፅመው መሆኑ ምንጮቼ ገልፀዋል።
እንደ ፍሰሃ ምንጮች ገለፃ በአጋአዚ ክ /ሰራዊት የሚገኙ ሀይሎች ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከቤተ መንግሰት ወጥተው ወደ ሱማሊና ደቡብ ሱዳን ጸጥታ ለማስከበር በሚል እንደተሰማሩ የሚታወቅ ነው። ከሀገር ውጭ እስከሁለት ዓመት ያክል ቆይተው ሲመለሱ ሊከፈላቸው የጠበቁት: ገንዘብ በተባበሩት መንግስታት ስኬል በመሆኑ ከፍ ያለ ነበር የተሰጣቸው ግን ሀምሳ ሽህ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው። ለምን ብለው የጠየቁት ደግሞ የርግጫ የምንትሴ እየተባለ ተቆርጦ እንደቀረ ተገልፆላቸዋል።
ተቆርጦ ተገምዶ ሊያገኙ ከጠበቁት ሩቡን እንኩዋ አላገኙም።በዚህም ምክንያት የክፍለ ሰራዊቱ አባላት መንግስት ላይ ኩፍኛ አንዳኮረፉና በተለይ የሁለት ሀይሎች አብዛኛው አባላት መልቀቅያ እንዳስገቡ: መልቀቅያቸው እንዲቀዱ የተለያየ ተስፋ ቢሰጣቸውም: ለመዓርግ እድገት ቢታጩም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም። ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።በነገራችን ላይ የአጋአዚ ሰራዊት ከውትድርና ውጭ ሌላ ሂወት የለንም ሲሉ እንደነበር ይነገራል ታድያ አሁን ከውትድርና ሂወት ወጥተው ምን ሊሆኑ ነው? ግንቦት ሰባት ጥሪ ሊያደርግላቸው ይችላል የሚል እርግጠኛ ያልሆነ ጥርጣሬ አለኝ።#ምንሊክሳልሳዊ