የሚቀጥለው ሳምንት ምርጫ ነው። ከምርጫው የሚጠበቅ ለዉጥ ባይኖርም መድረክ እና ሰማያዊ( የአንድነት ሰዎች በብዛት በምርጫው እንቅስቃሴ ለማድረግ ስለገቡ) በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ዉስጥም ሆነ ሕዝቡን ለማንቀሳቀስ ጥረት እያደረጉ ነው። በተለይም መድረክ በኦሮሚያና በትግራይ ብዙ ድጋፍ እያገኘ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።

መድረክን እና ሰማያዊ ወክለው ለፓርላማ ከሚወዳደሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል እኝህ አባት ይገኙበታል። በሞያቸው ጠበቃ ናቸው። የመልካም ሴት ባላቤትና የተባረኩ ልጆች አባት ናቸው። ከእኝህ አባት ሴት ልጆች መካከል አንዷ አስተማሪ ሆና ነበር። ከደሞዟ ብዙ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ትረዳና ትደግፍ ነበር። እንደ ዜጋ ሕግ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ጻፈች፣ አስተያየቷን ሰጠች።
እነርሱ መስማትና ማንበብ ከሚፈለጉት ዉጭ እንዲጻፍና እንዲነገር የማይፈልጉት ገዢዎች፣ የአስተሳሰብ ድሆች በመሆናቸው፣ ብእሯን መመከት አልቻሉም። ወደ ጡንቻ ሄዱ። አሰሯት። በዉሸት ክስ ሽብርተኛ ናት ብለው ከሰሷት። ጠበቃ አባቷ ተከራከሩ። ሆኖም ፍርድ ቤቶች የፍትህ አካላት ሳይሆን የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆናቸው፣ ፍትህ ሊገኝ አልቻለም። ይች ወጣት ለአመታት በቃሊቲ ትሰቃያለች። ይች ወጣት ርዮት አለሙ ትባላለች። በዘመናችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬና ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ !!!!

ጠበቃ አባቷ፣ ምን ያህል የሕግ ስርዓት እንደሌለ በመረዳታቸው፣ ፍትህ ከፍርድ ቤት እንደማይገኝ በማወቃቸው ለዚህ ደግሞ በዋናነት ምክንያቱ የተበላሻዉና የበሰበሰው የፖለትካ ስርዓቱ በመሆኑ፣ ይሄንን ስርዓት ለመለወጥ በቀድሞ ወረዳ አራት የመድረክ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።እኝህ አባት ጠበቃ አለሙ ጎቤቦ ይባላሉ።

ትግል የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል። ጠበቃ አለሙ በጥብቅና ሞያቸው ቀጥለው፣ ፍትህ ቢጓደልም “ ምን አገባኝ” ብለው መቀመጥ ይችሉ ነበር። ሆኖም ከራስ አልፎ ለሌላ መቆም ትልቅነት ስለሆነ፣ እኝህን አባትም ትልቅ አባት ስለሆኑ፣ ዝምታን አልመረጡም። ፖለቲካዉን ተቀላቅለው አምባገነንነትን ለመታገል ተነሱ።

የርዮት አለሙን አባት፣ የኛም የነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ አባት የሆኑትን፣ አቶ አለሙን እንምረጥ !!!!! አገዛዙ ከአምስት አመታት በፊት እንዳደረጉት ድምጽ እንዳይሰርቁም፣ ድምጹ እስኪቆጠር ድረስ፣ ሕዝቡ በየምርጫ ጣቢያ ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ራሱ ማስቆጠር አለበት። 3፣ 4 አጋዚ፣ ፌዴራልና ካድሬ ፣ ሺሆችን አስፈራርተው የሕዝብ ድምጽ እንዲሰርቁ ሊፈቅድላቸው አይገባም።

የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ። በጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል። ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ ሲደኸይ ማየት አልፈለጉም። በቢሯቸው፣ በቤታቸው፣ ሴቶቹ በቦርሳቸው፣ ወንዶቹ ደግሞ በኪሳቸው ቦምብ ወይም ፈንጂ አልተገኘባቸው። በድብቅ የዶለቱት ወይንም የሰሩት ነገር የለም። የጻፉትና የተናገሩት ሁሉም በግልጽና በአደባባይ ነው። የተወሰኑቱ አርቲክል ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው። እነዚህ ወገኖች የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ( bloggers) ናቸው።

አርቲክል ዘጠኝ እንደ አይሰስ፣ ወይም አልካይዳ ያለ ደርጅት አይደለም። የአርቲክል 19 ድርጅት አመጣጥ እንደዚህ ነው። የተባበሩት መንግስታት የሰባአዊ መብት ድንጋጌ (THE UNIVERSAL DECLARATION OF HUMAN RIGHTS የሚባል አለ። የዚህ ድንጋጌ አንቀጽ 19 ( አርቲክል 19) «Everyone has the right to freedom of opinion and expression; this right includes freedom to hold opinions without interference and to seek, receive and impart information and ideas through any media and regardless of frontiers.» ይላል።

በዚህ አንቀጽ ላይ የተጻፈው ነጻነት በአለም ዙሪያ ሁሉ እንዲከበር ለመርዳት (አድቮኬት ለማድረግ) የተቋቋመ የሲቪክ ማህበር ነው፣ አርቲክል ዘጠኝ። ይህ ማህበር አርቲክል 19 የሚል ስያሜ ይዞ፣ በአሜሪካ፣ በአዉሮፓ ባሉ በርካታ አገሮች፣ በኬንያ፣ በቱኒዚያ ፣ በባንግላዲሽ ሳይቀር እውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ነው። በአገራችን ዉስጥ በኢሕአዴግ መንግስት ተጋብዞ በምርጫ ዙሪያ ስልጠናዎች የሰጠ ድርጅት ነው።

ይህ የተባበሩት መንግስታት አንቀጽ 19 ድንጋጌ በኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 29፣ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ በግልጽ ተቀምቷል። «Everyone shall have the right to hold opinions without any interference.Everyone shall have the right to freedom of expression without interference. This right shall include freedom to seek, receive and impart information and ideas of all kinds, regardless of frontiers, either orally, in writing or in print, in the form of art, or through other media of his choice.» ይላል የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29።

በተባበሩት መንግስታት የሰባአዊ መብት ድንጋጌ አንቀጽ ( አርቲክል 19) ወይንም የኢትዮጵያ መንግስት አንቀጽ 29፣ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጽፉ፣ የተደራጁ ሰላማዊ ዜጎች ናቸው። ለሕገ መንግስቱ ፣ ለሕግ ከበሬታ ያላቸው ናቸው።

ነገር ግን ከዘመናዊነት ፍጹም የራቁ፣ በሚድል ኤጅ ይኖሩ ከነበሩ በአስተሳሰብ የማይተናነሱ፣ አዲስ አበባ ያሉ ገዢዎች ግን፣ ራሳቸው ያወጡትን ሕገ መንግስት ረጋግጠው ፣ ሽብርተኞች ናቸው በሚል ክስ ከሰዋቸው ከፍተኛ መከራና እንግልት እየፈጸሙባቸው ነው። ይኸው ለአሥራ ሰባተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ገና ጠፋተኛ ነኝ አይደለሉም የሚል ቃል አልሰጡም። አሥራ ሰባት ጊዜ ፍርድ ቤት ሄደዋል ? አዎን 17 ጊዜ።

እንግዲህ ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ አሳዛኝና አሳፋሪ ግፎች የሚፈጸምባት አገር መሆኗን ነው። ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ገነት፣ በአሥር ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጆቿ ሲኦል የሆነች እንደሆነች ነው። ይሄን ለመቀየር ሕጋዊ በሆነ መልኩ እንቅስቃሴ ተደረገ። ይሄን ለመቀየር እነ ጆን ኬሪ ጠየቁ። ነገር ግን የሕወሃት ሽፍቶች ሊሰሙ አልቻሉም። እነርሱ ማሰር እንጂ መፍታት፣ መደብደብ እንጂ የወቀደን ማንሳት፣ ዜጎችን እንዲፈናቀሉና እንዲሰደዱ እንጂ ዜጎችን ማሰባሰብ አያወቁም። ጨካኞች ናቸው። ስብእና አይሰማቸው።

በመሆኑም እንደ አገር እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን እነዚህ ሰዎችን እነርሱ ካሰመሩት መስመር አልፈን መሄድ መቻል አለብን። የነርሱ ጭካኔ ሊያስፈራራን አይገባም። እነርሱ የፈለገ ጭራቅ ቢሆንም፣ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን። በያዙት ጠመንጃ፣ አሁን እንደ ንስር ትልቅ ቢመስሉንም ፣ እኛ ሁላችንም ከተነሳም እንደ ዝንብ እናጠፋቸዋለን።

ነገ ቀኑ ጥር 19 ቀን ነው። ሕወሃት አንድ አዋጅ በምርጫ ቦርድ በኩል ያስተላልፋል። ወይ የአንድነትን ፓርቲ ኦፌሴላዊ በሆነ መንገድ በማገድ ፣ የድርጅቱን ሰርተፊኬትና ወረቀት (እውቅና ) ጠፍጥፎ ላደራጃቸው ተለጣፊዎች ይሰጣል። አሊያም በምርጫው መወዳደር እንደማይችሉ ያስታወቃል። የአንድነት ፓርት በአገሪቱ ጠንካራ ድርጅት …

ይች መልእክት ለሕወሃት የመጨረሻ ልትሆን ትችላለች – ግርማ ካሳ Read more »

ወደ አስራ አንድ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች አንድ ኮሚቴ አዋቀሩ። ይህ ኮሚቴ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ዶር ሰለሞን ተርፋና ዶር ስብሐት የሚመራ ነበር። ይህ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የነበረው አለመረጋጋት አገሪቷን ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይወስዳት፣ በወቅቱ ይገዛ ከነበረው ከኢሰፓ/ደርግ እንዲሁም ከሽምቅ ተዋጊዎች (ሻእቢያና ወያኔ) የተወጣጣ ፣ የሽማግሌ ጊዚያዊ መንግስት እንዲቋቋም የሚጠይቅ ነበር። “ይቅር ለ እግዚአብሄር “ በሚል መንፈስ መቀባበል እንዲመጣ ነበር ምሁራኑ የጠየቁት። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ወያኔ ከትግራይ ፣ ሻእቢያ ደግሞ ከከረን አላለፉም ነበር። ያ ማለት ወታደራዊ የበላይነት የነበረው ደርግ ነበር ማለት ነው። ምሁራኑ ይሄንን የእርቅ ሐሳብ ሲያቀርቡ የሽምቅ ተዋጊዎችን ጥንካሬ በማየት ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ደርግ በሕዝብ እየተተፋ መምጣቱን በማየታቸው፣ አገሪቷም እንደ ላይቤሪያና ሶማሊያ እንዳትሆን በመፍራት ነበር።

አርብ ከሰዓት በኋላ ነው። መስሪያ ቤቶች የተዘጉ ይመስላል። ሁሉም በየቤቱ ገብቷል። ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ለሕዝብ ንግግር ሊያደርጉ ነው። በፊታቸው ለነርሱም መዉጭ መንገድ፣ ለሽምቅ ተዋጊዎችም እንደዚሁ የሚበጅ፣ የመፍቴሄ ሀሳብ ቀርቧል። “ኮሎኔሉ ለዚህ ቀና ሐሳብ ምን ይመልሱ ይሆን?” ብለን መጠባበቅ ጀመርን። አራት ሰዓት ሙሉ ተናገሩ። “የአገር ጉዳይ የባልና የሚስት ጉዳይ አይደለም፣ በይቅር ለእግዚአብሄር የሚፈታው” ብለው እነ ፕሮፌሰር መስፍንን ወረፏቸው። አንድ የብነመር ሰው የሰጠኝ ብለው አንድ ጊራጌ መዘዙና አሳዩን። አይ ፉከራ !. አይ ጀብደኝነት !!!!!

ብዙም አልቆየም፣ ሰራዊቱ እየተከፋፈለ፣ እየከዳቸው ፣ ሽምቅ ተዋጊዎችም ተዋግተው ሳይሆን እንደ ማራቶን እየሮጡ፣ ጎንደር፣ ወሎ …እያሉ አዲስ አበባ አካባቢ ደረሱ። እንደ አጼ ቴዎድሮስ እስከመጨረሻው ጥይት ጠጥቼ እሞታለሁ ያሉት ኮሎኔሉ ፈረጠጡ። “ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት” ብለው ራሳቸውን የጠሩት ወያኔዎችም፣ ስኳር እየቃሙ በጢቢጢቢ ጫማ፣ አዲስ አበባን ተቆጣጠሩ። የኢሰፓና የደርግ አመራሮች ከያሉበት እንደ ጥንቸል ታድነው ተያዙ። የነበራቸውን ነገር በሙሉ አጡ። ወደ ወህኒ ተወረወሩ።፡አይወድቁ አወዳደቅ ወደቁ።

አሁን ሕወሃቶች፣ ተመሳሳይ ጀብደኝነት እያሳዩ ናቸው። ህዝብ እየተፋቸው ነው። ሕዝብ በደርግ ላይ ከነበረው የበለጠ ጥላቻ በነርሱ ላይ እያደረበት ነው። ብዙ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች አገዛዙ ወደ ብሄራዊ መግባባት እንዲመጣ እየመከሩና እየተማጸኑ ነው። ሆኖም ሕወሃቶች ልባቸው በጣም አብጧል። ማሰብ ተሰኗቸዋል። የትላንትናዉን ረስተዋል። ኢትዮጵያዉያን ወደ አመጽና ጦርነት እየገፋፏቸው ነው። “እስቲ ወንድ ከሆናችሁ ኑና በጦርነት ግጠሙን” እያሉ ነው። የሰላም በሮችን በሙሉ እየዘጉ ነው። ከነርሱ የተለያ ሐሳብ ያላቸው በሚቆጣጠሩት ሜዲያ፣ ትላንት ደርግ የፍየ ወጠጤ እያለ ሲፊከርና ሲያስፈራራ እንደነበረው፣ ዶኩመንተሪ ምጥርቅሾ እያሉ፣ እያስፈራሩ ነው። ዜጎች በአገራቸው ተሸማቀው እንዲኖሩ እያደረጉ ነው። በአጭሩ አባባል ዳግማዊ ግራዚያኒ እየሆኑ ነው።

በአገር ዉስጥ በምርጫ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ህዝቡ የፈለገውን እንዲሽርና እንዲሾም የሚደረግበት ሲስተም ከሌለ፣ ሌላው አማራጭ ጦርነትና አመጽ ነው። “የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ” እንዳለው አብርሃ ደስታ። በአገር ቤት ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ፓርቲ በማገድ፣ የፓርቲዉን ሕጋዊ ሰርተፊኬት፣ እነርሱ ራሳቸው ላደራጁት ተለጣፊ አንድነት ለመስጠት ወስነዋል የሚል መረጃ አለ። የአንድነት ፓርቲም ይሄን በመቃወም ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ እሁድ ሰልፍ ጠርቷል። ለአስተዳደሩ አሳዉቋል። ሆኖ አገዛዙ በሜዲያ መዛቱን ቀጥሏል። አንድነቶ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስዱም፣ ዳኞች ፈርተው ጉዳዩን ለማያተ ፍቃደኛ አልሆኑም።

እንግዲህ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚደረገው ትግል ጫፍ ላይ ደርሷል። ሕወሃት ተጠንቆ እርምጃ እንዲወስድ እመክራለሁ። በአንድነት ፓርቲ ላይ ማናቸዉንም አይነት ሕግ ወጥና አምባገነናዊ እርምጃ ቢወስድ፣ አመራር አባላቱ ቢታሰሩ፣ በአገራች ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዳከተመ፣ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የመታገል በር ሙሉ በሙሉ እንደተዘጋ የሚገልጽ አዋጅ እንዳወጀ ነው የሚቆጠረው።

ወያኔዎች አዲስ አበባ ሲቆጣጠሩ «ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት» ነበር ያሉት። ልክ እንደያኔውም ብሶት፣ የግፍ ቀንበር፣ ጭቃና፣ ባርነት እጅግ በጣም ብዙ ሰራዊቶችን ይፍጥራል። ስለዚህ ረጋ ብለው እንዲያስቡ የኮሎኔል መንግስቱ አይነት ስህተትን እንዳይሰሩ እመክራለሁ። ጀብደኝነት ለማንም አይጠቅምም። እነርሱም ጥብቆ እንደታጠቁት ሌላው ጥብቆ ታጥቋል። ለሁላችንም ሰላምና መግባባት ይበጀናል። እሁድ የአንድነት ሰልፍ በሰላም ተጠናቆ (ለምን ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ነውና) ምርጫ ቦርድም በአንድነት ላይ የከፈተውን ዘመቻ አቁሞ፣ ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን ሥራ ይጀመር። አለበለዚያ ግን እነርሱ ራሳቸው በለኮሱት እሳት መጥፊያችውን እንዳወጁ ይወቁ።

“አቶ በላይ በዝረራ ነው የጣለኝን ፣ ጨብጬም ስሜዋለሁ” ትግስቱ አወል

ይህ በአቶ ትግስቱና በአንድ የአንድነት ደጋፊ መካከል ከተደረገ ልዉውጥ የተወሰደ ነው። በዚህ ልዉውጥ አቶ ትግስቱ ለፕሬዘዳንትነት ሲወዳደሩ ፣ በምክር ቤቱ አንድ ድምጽ ብቻ በማግነት (እርሱም የርሳቸው ብቻ ድምጽ) በተሸነፉበት ጊዜ ስለ አቶ በላይ ፍቃዱ የተናገሩት ይገኝበታል።

ደጋፊ

“ቃለ መሐላ ሲያደርጉ የሚይሳይ ፎቶ አየሁ። የአንድነት ሊቀመንበር ነኝ ብለው እየተናገሩ ነው። ስልጣን የሚወዱ ሰው እንደሆኑ ብዙዎች ይናገሩ ነበር። የምርጫ ቦርድ ያሰናከለዉን የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት ቢሳካ ኖሮ፣ ዉህዱን ፓርቲ በፕሬዘዳንትነት ለመምራት ራስዎትን እጩ አደረጉ። ዉህደቱ እንደማይሆን ሲታወቅ ኢንጂነር ግዛቸው እንደገና ካቢኔያቸውን ሲያዋቅሩ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ። ለጊዜው የስልጣን ጥሞትን ትንሽ አረኩ። ዉች ካሉ ደጋፊዎችም ጋር መገናኘት ጀመሩ። ኢንጂነር ግዛቸው ከሃላፊነት ሲለቁ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴያቸውን በተኑ። ለጥቂት ሳምንታት ያገኙት ስልጣን በማጣትዎት ተከፉ። በምክር ቤቱ በሕጉ መሰረት አዲስ ሊቀመነበር መመረጥ ስላለበት፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እጩዎች ቀረቡ። እርስዎም እንደጋና እጩ ሆነው ቀረቡ። ከምክር ቤት አባላት አንድ ሰው ለርስዎ ድምጹን ሳይሰጠ ቀረ። አንድ ድምጽ ብቻ እርሱም እርስዎ ለራስዎት የሰጡትን ድምጽ ብቻ አገኙ። በአባላት ባለመመረጥዎት የተነሳ ራስዎትን መጠየቅ ሲገባዎት አኮረፉ። በዉስጥዎት በአንድነት ፓርቲ ላይ ቂም ቋጠሩ። አንድነት ደንቡን በማሻሻል የኮረም ቁጥር ማስገባት አለበት የሚል ሕገ ወጥ ጥያቄ ባቀረቡበት ጊዜ፣ አንድነት በትንሽ ነገር ግብግብ አያስፈልግም በሚል፣ ለአባላት ስልጠና ለመስጠት በማሰብ የጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ። እርስዎም በጉባኤ ተገኝተው ፣ እርስዎ አንድ ድምጽ ሲያገኙ 26 ድምጽ፡ያገኙትን የአቶ በላይን አመራር ተቃዉመው ጠቅላላ ጉባዔው አመራሩን እንዲመርጥ ጠየቁ። ጠቅላላ ጉባኤ በርስዎ ፊት ምክር ቤቱ በደንቡ መሰረት ሊቀመነበሩን መምረጡን ትክክል እንደሆነ አረጋገጠ። በድጋሚም የአቶ በላይን ምርጫ አጸደቀ። እርስዎም አፈሩ። በዲሞክራሲና በሐሳብ ተሸነፉ።”የተማሩ ኖት። የማስተርስ ዲግሪ አልዎት። እንደ አዋቂ ቢያስቡና ቢያስተዉሉ ኖሮ ፣ ሌላ ጊዜ የአባላትን ድጋፍ በማግኘት ወደ ስልጣን ለመምጣት ይሰሩ ነበር። ሆኖም እልህ ተሞሉ። ህዝብን እያሸበረ ካለ ቡድን፣ ጋር ከሕወሃት ጋር አበሩ። “

አቶ ትግስቱ

ተወዳድረህ ሰው አልመረጠህም ያልከኝ፤ እውነት ነው፤ በዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚጠበቅ ነው ። በመሆኑም እኮራለሁ እንጂ አላፍርበትም፡፡ በእለቱም በዝረራ የጣለኝን አቶ በላይ ፈቃዱን ጨብጬ ስሜዋለሁ ምርጫው ዴሞክራሲዊ እንደሆነ ገልጬ መልካም ምኞቴን ገልጫለሁ፡፡ በመቀጠልም በበላይ ክብኔ ስር ምክትል ሃላፊ ሆኜ እስከ ታህሳስ 3ቀን 2007 ጉባኤ እስከተደረገበት ድረስ አብሬ ነበር፡፡ እኔ ከፓርቲው ሳይሆን በሃሳብ ከነበላይ የተለየሁት በጉባኤው ወቅት ይህ ዛሬ በምርጫ ቦርድ የቀረበው ጥያቄ እንዳይመጣ በማሰብና ፓርቲዬን ለማዳን ያቀረብኩትን ደንባዊ አስተያዬት በእውቀት ሳይሆን በስሜት በ……… ጩኸት ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በጩኸት የሚደረግ ውሳኔ ዴሞክራሲያዊ ተደርጎ በየዋሆች ሊወሰድ ስለሚችል፡፡ በድምፅ ተቃወምኩት፡፡ ከጉባኤው በኃላ በ ………… ፊታውራሪነት አንድነት የአባላቱ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች አክሲዮን በሚመስል መልኩ አመራሩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ስገነዘብና በተለይ ……………. የፓርቲውን አባላት በንቀት ሲመለከትና የአመራሩ መታበይ ምክንያት የእነ አቶ አየለ ስሜነህን ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ትግል ተቀላቀልኩ፡፡”

እንግዲ እዚህ ላይ አቶ ትግስቱ ሐሳባቸውን ጠቅላላ ጉባኤው እንዳልተቀበለው አስቀምጠዋል። በአቶ በላይ በዝረራ እንደተሸነፉ ይናገራሉ። በዲሞክራሲ እንደሚያምኑም ጽፈዋል። አድንነትን ከምርጫ ቦርድ ከሚመጣ ችግር ለማዳን ስል፣ አቶ አየለ ስሜነህ የሚመሩትን ቡድን እንደተቀላቀሉ ይናገራሉ።

አቶ አየለ ስሜነህ በምርጫ ቦርድ የሚደረገው ደባ ስላልተመቻቸው በምርጫ ቦርድ በኩል በሕወሃት የሚደረገውን በሜዲያ በይፋ አጋልጠዋል። አቶ ትግስቱ ግን በምርጫ ቦርድ ገጸ በረከት የአንድነት ስርተፊኬት ለመቀበል፣ በምርጫ ያላገኙትን በምርጫ ቦርድ ስጦታ ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው። አንድነትን ከምርጫ ቦርድ ለማዳን ሳይሆን የምርጫ ቦርድ መሳሪያና “ሰራተኛ” ሆነው አቶ ትእግስቱ ትልቅ ታሪካዊ ስሀተት እየሰሩ ነው።

በአዲስ አበባ፣ በጂንካ፣ በደብረ ማርቆስ ፣ በሸዋ ሮቢት እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ለመብትና ለነጻነት ሰልፍ ተጠርቷል። የብዙዎቻችን ትእግስትና ዝምታ እንደ ፍርህታ በመቁጠር ጥቂቶች ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ነው። ምናልባትም በያዙት መሳሪያና ባሏቸው ትቂት ሰራዊቶች ይመኩ ይሆናል። ሆኖም እኛ ግን ሚሊዮኖች ነን !!!! የሚሊዮኖች ኃይል ምን እንደሆነ የምናሳይበት ጊዜ ነው። ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ […]

The post አሁን ካልተነሳን መቼ እንነሳለን – ግርማ ካ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ጥያቄዉ አሁን ምርጫዉን ቦይኮት የማድረግ እና ያለማድረግ አይደለም። የአንድነት ፓርቲ ምርጫዉን እንደሚወዳደር ይፋ በማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ነበር። ብዙዎች “አንድነት እንዴት ምርጫዉን እወዳደራለሁ ይላል” የሚል ትችት አቅርበው ነበር። የአንድነት አመራሮች ግን ፣  አንድነት በምርጫዉ የሚሳተፈው በምርጫ ቦርድ ተማምኖ ሳይሆን በሕዝቡ ተማምኖ እንደሆነ በመገልጽ፣ አንድነት ከምርጫው ቢወጣ ደስ የሚሰኘዉና የሚጠቀመው ገዢው ፓርቲ ብቻ እንደሆነ  በመግለጽ ገለጹ። በአንድነት […]

የአንድነት ፓርቲ ዛሬ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤዉን ያደርጋል።  ምርጫ ቢቦርድ ከሕግ ዉጭ አንድነት ፓርቲ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክት አልሰጥም በሚል፣ አንድነትን ከምርጫዉ ለማስወጣት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአንድነት ፓርቲ ግን ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን መሰናክል ለማለፍና ለምርጫ ቦርድ ቀዳዳዎችን ሁሉ ለመዝጋት በሚል ነው ስብሰባው የተጠራው። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ እንዲገኝ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም ሌሎች ግለሰቦች […]

“አንድነትን ለመታደግ ከየአቅጣጫው እየተመመ ያለው የአንድነት የሰላማዊ ትግል ሰራዊት፣ በጊዜ በዋናው ጽ/ቤት ከትመዋል፤ ይሄው ታሪክ ሊሰራ፣ የምርጫ ቦርዱ አሳፋሪነት፣ የስርዓቱ ሽፍትነት ሊመሰክር፤ ይህን የአንድነት ልጆች ተጋድሎ ለልጅ ልጅ ሊነግር ታድመዋል። ይህ ትልቅ ታሪክ ሲፈፀም በቦታው ተገኝቼ ለመመልከት በመቻል ኩራት ነው የሚሰማኝ”  ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት የአንድነት ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ አስራት አብራሃ፣   ነገ እሁድ […]

እዉነቱ እዚህ ምርጫ ቦርዱ የሚለፍፈው እዚያ ፣ እዉነቱን ይረዱ
=====================================
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ገብረግዚአብሄር በፋና ራዲዮ እንዲሁም ሃላፊው ፕሮፌሰር መርጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ መኢአድ እና አንድነት ችግር እንዳለባቸው በመገልጽ በስድስት ቀናት ዉስጥ ፓርቲዎቹ “ችግሮቻቸውን” ካልፈቱ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰደባቸዋል ሲል አስጠንቅቀዋል። ምርጫ ቦርድ የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንደሆነ ይነገርለታል።

የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሕጉ መሰረት የሚንቀሳቀሱ ሳይሆን የፖለቲካ ዉሳኔ የሚያስፈጸሙ እንደሆኑ በሚያደርጓቸው ኢሕገ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች እያሳዩ እንደሆነ የሚገልጹት የመኢአድ እና የአንድነት አመራር አባላት የተደቀነባቸውን እንቅፋት ከህዝብ ጋር ሆነው እንደሻገሩትን በሙሉ መተማመን እየገለጹ ናቸው።

የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በአባላት ደረጃ እንደተዋሃዱ፣ አብረዉ እየተሳሩ፣ እየደሙ እንዳለ የገለጹት አመራር አባላቱ መኢአድ እና አንድነት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። መኢአድ በ354 ወረዳዎች አንድነት ደግሞ ከ450 ወረዳዎች በላይ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የገለጹት አመራሮቹ፣ አገዛዙ በምርጫ ቦርድ በኩል በድርጅቶቹ ላይ እየፈጸመ ያለው ነገር ፣ ድርጅቶቹ በሕዝብ ተቀባይነት እንዳላቸው በመረዳቱ ነው ሲሉ፣ ከህዝብ ጋር ሆነው የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቋቋም ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።

የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ያዳምጡ
https://www.youtube.com/watch?v=M0OfiIh … e=youtu.be

ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ኢ-ሕገመንግስታዊ ተግባራት ዙሪያ የአንድነት አመራር አባል የሆኑት አቶ አለነ ማጸንቱ ለኢሳት ማብራሪይ ሰጥተዋል።

አቶ አለነ፣ በጎጃም ክፍለ ሀገር አገው ምድር አውራጃ ሲሆን የተወለደው፣ የ28 አመት ወጣት ነው። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1999 በሶሻል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ2004 ደግሞ ሁለተኛውን ድግሬ ተቀብሏል።

በተለያዩ የግል ኮሌጆች ዲን እና አስተማሪ በመሆን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ርዕሠ- መምህር በመሆን አገልግሏል። አሁን ደግሞ በሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሥቴር የጥናትና ምርምር ቡድን አስተባባሪ በመሆን የተለያዩ መመሪያዎች፣ ፕሮግራሞች እና መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የአሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

በ1997 የመኢአድ(ቅንጅት) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የወጣቶች አደራጅ፤ ከ2001 እስከ 2002 በአዊ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ እና የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ፣ ከ2003 እስከ 2005 በአንድነት ፓርቲ በጥናትና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ከ2006 ወዲህ ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።

አቶ አለነ ከኢሳት ጋር ያደረገዉን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።
https://www.youtube.com/watch?v=x5DzqIK … e=youtu.be

ምርጫ ቦርድ ማንም ይዘዘው ማንም ወይም በግል ተነሳሽነት እያደረገ ያለው ነገር የኢትዮጵያን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከምን ጊዜውም በለይ ወደኋላ ለመመለስ እንደሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረዳው ይገባል፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እንዲያሰተዳድር በተሰጠው ኃላፊነት የፓርቲዎች አስተዳደሪ ለመሆን እየቃጣው ያለ ተቋም ነው፡፡ ስናከብረው ለመከበር ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለዚህ ተቋም መጠናክር የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለን የተነሳን ፓርቲዎችን ጭምር እየገፉ አለቆቹን ለማስደሰት ደም ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን የሚያደርጉትን ሰዎች ደግሞ በህዝብ ፊት ለብይን እንዲቀርቡ በግልፅ ማጋለጥ ይኖርብናል፡፡

ትላንትና ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ ቀርቦ የተናገረው በምንም መልኩ አንድነትን አይመጥንም፡፡ የተቀሩት የቦርድ አባላትም ይመጥነናል ካሉ ትዝብት ላይ ይወድቃሉ፡፡ የምርጫ ቦርድ አባላት ሳያገባቸው እንፈትፍት ሲሉ መፈተፍቱን ለእኛ ተዉልን ነው ያልናቸው፡፡ ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ የቦረድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል ብሎ ካቀረበ በኋላ ዛሬ ታህሳስ 28 2007 ቦርድ ተሰብስቦ ውሳኔ ሰጥቶዋል፡፡ ይህን ውሳኔ እንገራችሁ ብለው በስልክ ከጠሩን በኋላ የአንድነት ፓርቲ የወረዳ አባላት የሆኑትንም በተመሳሳይ መልክ ጠርተው ነበር፡፡ ለነገሩ ይህ አካሄድ አንድነትን ስለማይመጥን በፅሁፍ እንዲገልፁልን ነግረናቸው ተመልሰናል፡፡ ለማንኛውም ዶ/ር አዲሱ የሰጠው መግለጫ ይህ መግለጫ እንዲሰጥ የወሰኑትን ጨምሮ ለተቀሩት የቦርድ አባላት ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ቦርዱ ተሰብሰቦ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ውሳኔውን ሚዛን የሚያሳጣ መግለጫ ለመስጠት ምን እንዳጣደፋቸው መገመት ቀላል ነው፡፡ በልባቸው የሚደግፉትን ፓርቲ ለማንገስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡

ልክ የዛሬ አምስት ዓመት አንድነት ላይ ተመሳሳይ ግብ ግብ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የዚህ ተልዕኮ ፈፃሚዎች ዛሬ ላይ ሆነው ምን እንደተጠቀሙ ሲያሰላስሉ ምን እንደሚሰማቸው ባላውቅም ዛሬ በዚህ ተግባር ላይ የተሰለፉት አባላት ደግሞ ምን እንደሚያደርጉ መጠበቅ ነው፡፡ ለመማር ያልተፈጠረን ሁሉ ምንም ማድረግ ይቻላል? ማንም ተላላኪና ላኪ ሆኖ ቢያገለግልም ዛሬ የተሰማኝ ነገር አንድነት በምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን እንደዚህ ዓይነት ተቋማት በምን ያህል ደረጃ ለመዋረድ ዝግጁ እንደሆኑ ለመረዳት የሚያስችል ነው፡፡ አሁንም ትግሉ መራራ፣ የሚያስከፍለው መስዋህትነትም ውድ ሊሆን እንኳን ቢችል የአንድነት አባላት በድል እንደሚወጡት ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ እሩቅ እንደሆነ አውቀን ለጀመርነው ትግል አቋራጭ እንደማንፈልግ መግለፅ ይኖርብናል፡፡

ውድ የአንድነት አባላት ለቀጣይ አንድነት ከምርጫ ቦርድ አሻጥር ለማላቀቅ ለምናደርገው ትግል ቀበቶ ጠበቅ ነው፡፡ ከሰማይ በታች አንድነት ለመፍታት የማይችለው ፈታኝ ነገር ምርጫ ቦርድም ሆነ በውሰጥችን ያሉት ዙንቢዎች ሊያቀርቡ አይችሉም፡፡ ጎበዝ ጠንከር ነው፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ጥቂት ፓርቲዎች አንድነት አንዱ ነው፡፡ እናም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ና እውነተኛ ፍትህ ለማምጣት የአንድነት መኖር ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ ፓርቲው የአንድነት ፓርቲ አባላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሣይሆን የራሳችን አቋምና መስመር ይዘን በሌላ ፓርቲ ያለን ሰዎች እንኳ አንድነት እንዲኖር አጥብቀን እንፈልጋለን፡፡ ወደፊት አንድነትም እኛም ቤታችን እያፅዳን መንገድ ላይ መገናኘት አለብን፡፡

ያኔ ብቻ ነው ኢትዮጵያን የምናድናት፡፡ እንዳንራመድ ቀይዶ የያዘን ገመድ እየበጣጠስን፤ ፀረ-ለውጥና አድሃሪ አቋምን እየመከትንና እያፀዳን የዴሞክራሲ እና የሉዓላዊነት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል ፡፡ አንድነቶች አሁን ነው የፖለቲካ ፅናታቸው በጥበብ ማሳየት ያለባቸው፡፡ ወንድሞቻችን በርቱ!!!

አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡

በዚህ ሂደት ላይ ሰፊ እዉነታ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከምርጫዉ ቦርድ መጋረጃ ካሉት ወገኖች ጋር በሃሳብ እየተሸነፈ ግን ተሳትፎዉ ያለተቋረጠ አንድ ከፍተኛ አመራር እንዳለ እናዉቃለን፡፡ሁሉን ነገር በደንብና በመርህ የምንሰራዉ ለኢህኣዲግ/ምርጫ ቦርድ ካለን ፍርሃት ሳይሆን ለወደፊቱ ለምናስተዳድረዉ ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ፖለቲካ ክብር ስንል ነዉ፡፡እናም ከደንብ ወጥተን የሰራነዉ ክዋኔም በግፍ የገፋነዉ አመራርም፤አባልም የለም፡፡በመቻቻል መንፈስ ዲሰፒሊን ተጥሶም እንዲጓተት ተደርጓል፡፡ይህንንም የኢህኣዴግ ተባባሪነት ለታሪክ አስቀምጠነዋል፡፡

ምርጫ ቅንጦት ሆኖብን፤የተከበሩ እየተባሉ ለመጠራት ሳይሆን እፊታችን ላይ ያለ እድልና ስልትም ስለሆነ አንድነት ፓርቲ መጪዉን ምርጫ የምር እንዲሆን ወስኗል፡፡ ኢህኣዴግ ደግሞ ማበላሸቱን ተያያይዞትል፡፡ምርጫ በአምባገነን ቡድኖች ለሚገዙ አገራት ለለዉጥ እንዱ ስልት እንጂ ብቸኛዉ አለመሆኑ ይታመናል፡፡ፓርቲያችን ለለዉጥ ተደራጅም ይላል፡፡እዉነተኛ ፓርቲዎች ከምርጫዉ ባሻገር ላለዉ ግብ እንዲዋሃዱና እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርቧል፤ስልቶችን ለማቀራረብም እየጣረም ነዉ፡፡የአንድነት ኣባላት በያለንበት ድርብ ሃላፊነት አለብን፡፡ለአንድነት ሃይሎች ስልቶቻችን ሁሉ በማቀራረብ የተጀመረዉ የስልጣን ሃይሎችን እያራገፉ ትግሉን በሰለጠነና አንድነቱን በጠበቀ መልኩ የማስቀጠልና ልዩነቶችን በማቻቻል ሰፊ መሰረት የማንበር ሃለፊነት አለብን፡፡ ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ፤ፊታችንን ወደ ዋናዉ ግብ እናድርግ፤ከሃዲዱ አንወርድም!

ሕዝብን ያላስከተለ ትግል ዉጤት አያመጣም – ግርማ ካሳ

“ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል።በምርጫው ልንሳተፍም ሆነ ላንሳተፍ ውሳኔ የምናሳልፈው እኛ ሳንሆን ሂደቱ ነው” ብለዋል። ” እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው” ሲሉ ደግሞ አቶ ግርማ በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ፣ ቀደም ሲል ለምርጫው ቅድመ ሁኔታ አላቀመጥንም የሚለው ለማሻሻል ሞክረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የትብብሩ አመራሮች መልስ ለመስጠት የተቸገሩ፣ እርስ በርሳቸዉም አንድ አቋም ያልያዙ መሰለኝ። አቶ ዮናትን ቅድመ ሁኔታ ለምርጫው አስቀምጥናል እያሉ፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ ለምርጫው ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጥንም የሚሉ ከሆነ የቱ ነው ትክክለኛ የትብብሩ አቋም ? ? ? አቶ ዮናትን ወይስ አቶ ግርማ በቀለ ያሉት። በዚህ ጥያቄ ላይ “Honesty is the best policy” ይላሉ ፈረንጆች። ሰማያዊም ሆነ ትብብር በዚህ ረገድ አቋማችሁን በግልጽ ማስቀመጥ አለባችሁ። መቃረን የለባችሁም።

ሌላው ወደ ምርጫ ለመግባት ሂደቱ ይወስነዋል ይላሉ አቶ ዮናታን። ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። አንዱ ቅድመ ሁኔታ ይመስለኛል የምርጫ ቦርድ ነጻ መሆን አለበት የሚል ነው። በዚህ ረገድ አሁን ባለው ሁኔታ ገዢው ፓርቲ ፈቀቅ ያለበት ሁኔታ የለም። ካልተገደደ በቀር አሁን ያለው ምርጫ ቦርድ ነው የሚቀጥለው።

ትዝ ይለኛል ከምርጫ ቦርድ ሰብሰባ ሰማያዎች ረግጠው ወጥተው ነበር …ምርጫ ቦርድ ግን ኢግኖር ነው ያደረጋቸው። ስራዉንም ቀጥሏል። የአንድ ወር መርሃ ግብር ብለዉም ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ፥ ብዙዎች ለሁለት ሶስት ቀናት ታሰሩ። አሁንም ምንም ለዉጥ የለም በምርጫ ቦርድ አካባቢ።

ሁለት ሶስት መቶ ሰዎች ይዞ ሰልፍ መዉጣት አገዛዙን አያስገድድም። ይልቅ መቶ ሺሆች፣ ሚሊዮን ሕዝብ እንዲወጣና ለመብቱ እንዲጮህ ነው ማድረግ የሚያስፈለገው። ለዚህም በጋራና በትብብር መስራት ያስፈልጋል። ጠንካራ ከሚባሉ ድርጅቶች ጋር ከነ አንድነት፣ መድረክ ጋር አብራችሁ ሰላማዊ ሰልፎችን ሰማያዎች ቢጠሩ፣ አብረው መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ቢያነሱ ብስለትና እውቀት ባለበት መልኩ ቢንቀሳቀሱ፣ ትልቅ ቫይብሬሽን መፍጠር ይቻል ነበር።

እርግጥ ነው እዚህ በዉጭ ያሉ እንዳንድ ጽንፈኞቹ ከረን አፌር ክፍል ያሉ ሰማያዎችን ፣ ሆይ ሆይ እያሏቸው ነው። ምናልባት ሁለት፣ ሶስት ቀናት በመታሰራችሁ “ጀግኖች፣ አንበሶች” ሲሏቸው፣ ያለ እነርሱ ሰው የሌለ ሊመስላቸው ይችላል።

ሆኖም ግን እዚህ በዉጭ ያሉ ጽንፈኖች ችግር ዉስጥ ነው ሰማያዎዎችን የሚከቷችሁ። አዎ ከዉጭ ድጋፍ ማግኘት ጥሩ ነው። ዉጭ ያለው ወገን የትግሉም አካል ነው። ሆኖም ዉጭ ያለው ማህበረሰብ የሚፈልገውን ሳይሆን በአገር ቤት ያለው ሕዝብ የሚፈለገውን በማዳመጥ ነው መንቀሳቀስ የሚገባው። የሰላማዊ ትግል የራሱ የሆነ ሰራዊት አለው። እርሱም ሕዝብ ነው። ሕዝብን ያላሰለፈና ያላንቀሳቀሰ ትግል ዋጋ አይኖረዉም።

አንድ ነገር ብዬህ ላቁም። ከአንድ አመት በፊት ሰማያዊ ሰልፍ ሲጠራ ወደ 70 ሺህ ሕዝብ ተገኝቶ ነበር። ከሶስት ወራት በኋላ ሰልፍ አንድነት ሲጠራ አብረው አእንዲያደረጉ ትልቅ ተማጽኖ ቢቀርብላቸውም፣ እምቢ ብለው፣ ተሽቀዳድመው ሰልፍ ጠሩ። ሰልፉ ጃን ሜዳ ነበር ግን መስቀል አደባባይ መሄድ አለብን ሲሉ ከፖሊስ ጋር ዉዝግብ ፈጠሩ። ጥቂት ፖሊሶች አፈኗችሁ።

ስድስት ወራት በኋላ፣ ሚያዚያ ላይ አንድነት ሰልፍ ጠርቶ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋገረ ባለበት ጊዜ ፣ እንደ ጎህ ዝንብ ጣልቃ ገብተው፣ ሰልፍ ጠሩ። ለአንድነት አይሆንም በተባለ ቀን፣ እውቅና አገኙ። ለሰልፉም ቅስቀሳ አደረጉ። የተገኘላችሁ ሰው ሶስት መቶ አካባቢ ብቻ ነበር። ከሰባ ሺህ ወደ ሶስት መቶ መዉረድ ማለት ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ የሰማያዊን ስትራቴጂ እንደማያደገፍ ሰልፉ ላይ ባለመገኘት ገለጸ።

ለምንድን ነው ይሄ የሆነው ብለው መጠየቅ አልቻሉም። አሁን በአንድ ወር መርሃ ግብር እንቅስቃሴያቸውም የተለየ ነገር አላየንም። እንደ ኢሳት ባሉ ሜዲያዎች ሁሉ ሳይቀር ለሌለ ማንም ድርጅት ያልተደረገ ትልቅ ቅስቀሳ ተደረገላቸው። በሶሻል ሜዲያዉም እንደዚሁም። ከአምስት ሚሊዮን የአዲስ አበባ ህዝብ፣ መቶ አይሞላም የወጣላቸው። ለምን የአዲስ አበባ ህዝብ ጥሪያቸዉን ሰምቶ እንቅስቃሴያቸዉን አልተቀላቀለም ? ይሄ መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ ነው።

ገዢው ፓርቲን ማስገደድ የሚቻለው ህዝቡ በነቂስ ሲወጣ ብቻ ነው። ሰማያዊቾ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ የነበረባቸው ሕዝቡ እንዲወጣ ማድረግ የሚቻልበትን ስትራቴጂ በመንደፍ ላይ መሆን ነበረበት። ደግሜ እላለሁ ….ሰማያዊች የያዙት መስመር በጣም አደገኛና ትግሉን የሚጎዳ ነው። አላስፈላጊ ኮንፍሮንቴሽን አስወግደው፣ ሕዝቡን በማደራጀት ላይ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ላይ ቢያተኩሩ ጥሩ የሚሆን ይመስለኛል። አለበለዚያ የሁለተኛ መርሃ ግብር ብለዉም የሚያወጡት ከአንደኛው የሚለይ አይሆንም።

የአንድነት ፓርቲ በፖለቲካ ፕሮግራም ተመሳሳይነት ካላቸው ጋር ፣ ሰማያዊን ጨምሮ፣ ያለ አንዳንች ቅድመ ሁኔታ በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ እየገለጸ ነው። ሆኖም የሰማያዊ አመራሮች ከአንድነት ጋር ለመስራት አለርጂክ ለምን እንደሆነባቸው ደጋፊዎቻቸው መጠየቅ ያለባቸው መስለኝ።

የሰማያዊ አቅጣጫ ስህተትና የማይጠቅም ነው – ግርማ ካሳ

አቶ እያስፔድ ተስፋዬ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ናቸው። “አቧራን ለማጥራት – ነጻነት ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ነው” በሚል ርእስ አንጹ ጽሁፍ አቅርበዋል። በሚከተለው ሊንክ ያገኙታል። የእኝህ ወጣት አቀራረብ በጣም ተመችቶኛል። በነጻነት ነጥባቸውን በማስቀመጥ ለምርጫ ከመገባቱ በፊት መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ እንዳለ ይከራከራሉ።

viewtopic.php?f=2&t=90558

የድርጅት አባል ባልሆነም፣ የምደገፈው ድርጅት አለ። እርሱም የአንድነት ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለምርጫ እንደሚሳተፍ በይፋ ለህዝብ አሳዉቆ፣ «2007 ለለውጥ»፣ «ተደራጅ ለምርጫ» በሚል መርህዎች በአገሪቷ ሁሉ መጠነ ሰፊ የምርጫ እንቅስቃሴ ጀመሯል።

የአንድነት አቋም ለምን ትክክለኛ እንደሆነ፣ በአንጻሩም ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አቋም ለምን የወቅቱን ሁኔታ ያላመዛዘነ የተሳሳተና በ እወቀት ሳይሆን በስሜት ላይ የተመሰረተ አቋም እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ። የአንድነት አባል እንዳለመሆኔ፣ ከዚህ በታች የምጽፈው የግል አስተያየቴ እንደሆነ ከወዲሁ ለአንባቢያን አሳውቃለሁ።

ብዙዎቻችን በምርጫ በመግባትና ባለመግባት ዙሪያ የሚደረገው ዉይይት አካል ሆነን ሐሳቦችን ሰንዝረናል። አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ መገባት የለበትም የሚሉ ወገኖች ፣ ከምን ተነስተው እንደዚያ እንደሚሉ እረዳለሁ። ሆኖም የነርሱን አቋም ተቃዉሜ ስጽፍ፣ ምርጫ ባለመግባት የሚገኝን ጥቅም ሊያሳዩን ባለመቻላቸው ነው።

እዚህ ዉጭ አገር ያሉ አንዳንድ በጠመንጃ ትግል እናምናለን የሚሉ ቡድኖች፣ ምርጫ እንዲገባ አይፈልጉም። (እነርሱ ዉጊያቸውን ትተው ለምን በሰላማዊ ታጋዮች ዙሪያ እንደሚጨነቁ ባይገባኝም) ምናልባት ምርጫ ከተደረገና አንጻራዊ መሻሻል ከመጣ የነርሱ ፖለቲካ ዜሮ ስለሚገባ ሊሆን ይችላል ምርጫዉን የሚቃወሙት። በመሆኑም ከነዚህ ቡድኖች በምርጫ ዘመቻ ላይ ተቃውሞ ቢሰማ ልንገረም አይገባም።

አገር ቤት በሰላም የሚታገሉ ወገኖች ግን ፣ ምርጫዉን ቦይኮት ሲያደርጉ ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ደርጅታቸውን ወይንም ሕዝቡን የሚጠቅም መሆኑን በማስላት መወሰን ያለባቸው መሰለኝ። ይሄን ካደረጉ የቦይኮት ጥሪው ችግር ይኖረዋል ብዬ አላስብም። ነገር ግን ትንሽ ያልተመቸኝ ፣ እነ አቶ እስያስፔድ እንዲያስረዱን የምፈልገው ፣ ቦይኮት ማድረጉ ምን ጥቅም ለትግሉም ሆነ ለሰማያዊ ፓርቲ እንደሚያስገኝ ነው። ቦይኮት ተደረገ፤ ከዚያስ ? ? ትልቅ መመለስ ያለበት ጥያቄ።

እስከሚገባኝ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ሆነ ትብብር በቀዳሚነት አቋማቸው በግልጽ አይታወቅም። አንዳንድ አመራሮች ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫው እንገባለን ይላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃራኒዉን ይናገራሉ። ስለዚህ በቅድሚያ የሰማያዊም ሆነ ትብብሩ አቋም ግልጽ መሆን አለበት። አንድ የአመራር አባል ፌስ ቡክ ላይ በመጻፉ ሳይሆን፣ ደርጅቶቹ በኦፊሴል ለሕዝብ አቋማቸዉን ግልጽ ማድረግ አለባቸው።

ለዉይይት ያህል.፣ ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ ወደ ምርጫው አይገባም ከተባለ፣ ቀጣዩ ጥያቄ የሚሆነው ቅድመ ሁኔታዎቹ ምንድን ናቸው የሚል ነው። ከዚያ ገዚው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ ምን እየተደረገ ነው ? የተደረገውስ ምን ዉጤት አመጣ ? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

የሰማያዊ ፓርቲ አገዛዙ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ፣ ጫና ለማድረግ የአንድ ወር መርሃ ግብር አጠናቋል። ዉጤቱን ሁላችንም የምናወቀው ነው። ካለፈው የአንድ ወር መርሃ ግብር የተለየ ነገር በሚቀጥሉት መርሃ ግብሮች ምን ሊፈጠር እንደሚችል በርግጠኝነት መናገር ቢያስቸግረም፣ መገመቱ ግን ይከበዳል ብዬ አላስብም።

የሰማያዊ ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟሉም ብሎ ከምርጫው ቢወጣ፣ ገዢው ፓርቲ የሚፈራው ወይም የሚጎዳበት ሁኔታ የሚፈጥር ቢሆን ኖሮ «ቦይኮት አደርጋለሁ» በሚል ማስፈራራትና ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጥ ያስኬዳል ብዬ ልቀበል እችል ነበር። ሆኖም ያደረች ባቄላ እንደሚባል፣ ገዢው ፓርቲ ሰማያዊ ምርጫ ዉስጥ ገባ፣ አልገባ ግድ አይሰጠዉም። የሰማያዊ ምርጫውን አለመሳተፍ ለነርሱ ኢንሲግኒፊካንት ነው። በመሆኑም ምርጫ አንገባም ማለት ፖለቲካ ፋይዳ አይኖረዉም።

ሌላው ቦይኮት በሚደረግበት ጊዜ ፣ ሕዝቡም ቦይኮት እንዲያደርግ ማስተባበር ያስፈልጋል። ህዝቡ ወደ ምርጫ ሄዶ ፣ ሰማያዊ ግን ብቻዋን ቦይኮት ቢያደረግ፣ እንደ ቢራቢሮ አየር ላይ የሚንሳፈፍ ድርጅት ነው የሚሆነው። ድርጅቶች በሙሉ ተባብረው፣ ተነጋግረው፣ በተቀናጀ መልኩ ቦይኮት እንዲደረግ ዘመቻ ቢያደርጉ፣ ህዝቡም የቦይኮቱ አካል እንዲሆን ቢያደራጁ፣ ከቦይኮቱ ጎን ለጎን ሰላማዊ ሰልፎችን የሥራ ማቆም አድማዎችን ቢጠሩ …ቦይኮት ሊሰራ ይችላል። ከዚያ ዉጭ ግን ቦይኮት የሚያመጣዉ አንዳች ፋይዳ አይኖርም። (እስከሚገባኝ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ከነ አንድነት ፓርቲ ጋር አብሮ መስራቱ እንደ አለርጂክ እየሆነበት ነው። ከተመሰረቱ ጊዜ ጀመሮ ከአንድነት ጋር ፉክክር እንጂ የያዙት፣ በቁም ነገር፣ «በአንድ ላይ መሰባሰባች የአገርና የሕዝብ ጥያቄ ነዉ» በሚል ሂሳብ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ አይታዩም)

በመጨረሻ የማነሳው ነጥብ የፕራክቲካሊቲ ነጥብ ነው። ሰማያዊ «አገዛዙ ላይ ጫና አሳድሬ፣ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ አደርጋለሁ» ይላል። በአራት ወራት ጊዜ ዉስጥ ምን ያህ ይሄ ግብ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ? እዉነት እንነጋገርና በአራት ወራት ዉስጥ አገዛዙ ምርጫ ቦርድን ይለውጣልን ? ለነዚህ ጥያቄዎች መልሱ « አይችልም፣ አይሆንም» የሚል ነው።

ምርጫ ቦርድ ላይ በየምርጫ ጣቢያ ጫና ሊያደረግ የሚችለዉን ህዝብ፣ ድምጹን እንዲያስከበር ከማደራጀትና በየሜዳው ሄዶ ከመንቀሳቀስ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖርም። የሰላማዊ ትግል ሰራዊት ሕዝቡ ነው። ወታደሮች ከኋላው ያላሰለፈ ጀነራል የትም እንደማይደርስ፣ ህዝቡን ከበስተኋላ ያላሰፈ የሰላማዊ ትግል መሪም ሆነ ድርጅት ሩጫ ከንቱ ነው።

«አንድነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በምርጫው እሳተፋለሁ» ብሎ መግለጫ መስጠቱን አልቃወምም፡፡ አባላቶቼን ከወዲሁ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳኛል ብሎ ይሆናልና፡፡ ልክ እንደዚሁም ሁሉ ሌላውም የእኛን አቋም እንዲያከብርልን እሻለሁ፡፡» ሲሉም አቶ እያስፔድ ጽሁፋቸውን ያጠቃልላሉ። በመርህ ደረጃ ትክክል ናቸው። ሆኖም በዚህ ወሳኝ ወቅት የሰማያዊና የአንድነት ስትራቴጂዎች የተለያዩ በመሆናቸው ሕዝቡን የማደናገር ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። አንድነት በአንድ በኩል ለምርጫ ተመዝገቡ እያለ ለምርጫ ሲቀሰቀስ፣ ሰማያዊ ደግሞ በሌላ በኩል ቦይኮት ይደረግ እያለ የሚቀሰቅስ ከሆነ፣ በተቃራኒ ወገን ቆሙ ማለት ነው። የግድ አንድነቶች የሰማያዊ አማራጭ ትክክል እንዳለሆነ የማስተማርና የመቀስቀስ፣ በሐሳብ የማሸነፈ ሃላፊነት ይኖርባቸዋል።

ስለዚህ መከባበሩ፣ እንደተጠበቀ፣ ቢቻል ሁለቱም ወደ አንድ አቋም እንዲመጡ ቢነጋገሩና በጋራ ቢሰሩ፣ ካልሆነም ግን የግድ አንዱ ሐሳብ አሸናፊ ሆኖ መውጣት ስላለበት የፖለቲካ ክርክሮቹ በሰለጠነ፣ ከስሜትና ከስድብ በጸዳ መልኩ ቢደረጉ ጥሩ ሊሆን ይችላል።

ከዚህ በፊት እንደጻፍኩት፣ ሰማያዊ የወሰደው ቅድመ ሁኔታ የማስቀመጣ ፖለቲካና አቋም ስህተተ ነው ብዬ ነው የማምነው። አንዳንዶች በምርጫው መሳተፉን «ተለጣፊ» እንደመሆን እና ለአገዛዙ ሌጂቲመሲ(እውቅና) እንደመስጠት አድርገው የሚቆጥሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች አንድነት ወደ ምርጫ በመግባቱ «ተለጣፊ» ሆኗል የሚል አስተሳሰብ ካላቸው፣ መለስ ብለው የሚሊዮኖችን ንቅናቄ እንዲመለከቱ እጋብዛቸዋለው። በአሁኑ ጊዜ የሕዝብን ትርታ የያዘ፣ በሆያ ሆዬ ላይ ሳይሆን፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምድ ፣ በሁሉም ክልሎች መዋቅር ያለው የፖለቲካ ድርጅት አንድነት ብቻ ነው። ሂዱ አርባ ምንጭ፣ ሂዱ ጂንክ፣ ሂዱ ወሊሶ፣ ሂዱ ጊምቢ፣ ሂዲ ጎንደር፣ ሂዱ አሳሶ፣ ሂዱ አዳማ፣ ሂዲ ሶዶ፣ ሂዱ ደሴ …አንድነትን በዚያ ታገኛላችሁ።

ለአገዛዙ ሌጂቲመሲ መስጠት ነው ለሚሉት ደግሞ ሌጂቲመሲ ሰጭው ማን እንደሆነ ቢነገሩን ጥሩ ነበር። በዉጭ ኃይሎች ዘንድ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሌጂቲሚስ ያገኛል የሚል ፍርሃት ከሆነ ያላቸው፣ በጣም የዲፕሎማሲ እወቀት ዴፊሸንሲ አለባቸው ማለት ነው። እነአሜሪካ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች አምባገነን፣ በሕዝብ ያልተመረጡ፣ ድምጽ ሰርቀው ስልጣን ላይ ጠመንጃ ስለያዙ ብቻ፣ እየገደሉና እያሰሩ እንደሚገዙ ያውቃሉ። ሆኖም እውቅና ሰጥተዋቸው ዋይት ሃዉስ ድረስ ጠርተው እያስተናገዷቸው ነው። ለምን ሌላ፣ የተሻለ፣ ጥቅማቸውን የሚያስጤብቅ ኃይል ስለሌለ። እቅጩን እንወቅ፣ ቦይኮት ተደረገም አልተደረገም፣ ምርጫ ተገባም አልተገባም፣ አሜሪካም ሆነ አዉሮፓዉያን በአገዛዙ ላይ ያላቸውን አቋም አይለዉጥም። እነ አሜሪካ የፖሊሲ ለዉጥ የሚያደርጉት፣ ፊታቸውን ከሕወሃት/ኢሕአዴግ የሚያዞሩት፣ ተቃዋሚዎች ምርጫዉን ቦይኮት በማድረጋቸው ሳይሆን፣ ሕዝቡን አደራጅተው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ማነቃነቅ ከጀመሩ ብቻ ነው። ለዚህም ነው ምርጫ ከተገባ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሌጂቲማሲ እንዲያገኝ እናደርገዋለን የሚለው አስተያየት ዉህ የማይቋጥርና በእወቅት ላይ ያልተመሰረተ ነው የምለው።

ለጊዜው አበቃሁ !

አቶ ይድነቃቸው የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ናቸው። አንድነት ፓርቲ ላይ ያነጣጠረ ሁለት ጽሁፎችን በቅርቡ ለቀዋል። እንደ አንድነት ደጋፊ አንድነት ላይ ትችት መቅረቡን አልቃወምም። ሆኖም ትንሽ የመረጃ ክፍተት ሳይኖርባቸው እንደማይቀር በመገመት እንደሚከተለው ምላሽ ስጥቻለሁ፡

ወንድም ይድነቃቸው፡

“እኔም ሆንክ ሌሎቻችን በሰጠነው ትችት እና አስተያየት አንድነት ፓርቲ ጉዳዩን ለማጥረት በዛሬው ዕለት “አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!” በማለት ያዋጣው መግለጨ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው፡፡” ብለ በጻፉት ላይ አስተያየት እንድሰጥ ይፍቀዱልኝ።

ይመስለኛል አንድነት በጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ላይ ያልጠራ ነገር እንደነበረዉና አሁን በመገልጫው እንዳጠራው የሚገልጽ እድምታ ያለው ሐሳብ መሰለኝ ያስቀመጡት። አስተያየቶችን በነጻነት ለመጻፍና ለመናገር መብትዎትን እየተለማመዱ መሆንዎትን አደንቃለሁ፨ ማንም የተቃዋሚ ድርጅት ሆነ የተቃዋሚ መሪዎች ሁልጊዜ ቻሌንጅ ሊደረጉ ይገባል። ቻሌንጂን የሚፈሩ አምባገነን ባህርሪ ያላቸው ብቻ ናቸው ።
ሌላው “ አቶ ግርማ ሰይፉ “……ሁሉ ጊዜ ከመንግስት ጋር “እንትን” የምንለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ፣ ችግር ይፈጥራሉ ብሎ የሚባል ነገር ካለ እኛም የበለጠ ያጋባንል….” ያሉትን ጠቅሰዉ “ይቺ ናት ጨዋታ” ብለዉም ጽፈዋሃል።

ይመስለኛል የሕግ ባለሞያ ሳይሆኑ አይቀሩም። የናንተ የሰማያዎችን አቋምን አላውቅም። አንድነት ግን ጠንካራ ጽረ-ሽብርተኛ አቋም ያለው ድርጀት ነው። እንደ አልካይዳ፣ አልሻባብ የመሳሰሉ ድርጅቶች ለመዋጋት የሚደረገዉን አለም አቀፍ ጥረት ይደጋፍፋል። በተለይም አል ሻባብ የአካባቢያችን ትልቅ ጠንቅና ካንሰር እንደሆነም ያምናል። እንደ አይሳስ፣ ቦኮ ሃራም ያሉትን ይቃወማል። ይህን አቋም መያዝ ከህወሃት/ኢሕአዴግ ጋር መመሳሰል አይደለም።

ስለዚህ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት በአገራችን ሰላምን ለማናጋት የሚሞክሩ ኃይላት ካሉ የአገር ሰላምና ጸጥታ አንድነትን ያገባዋል። ወንድሜ እኔ እስከሚገባኝ የአንድነት አላማና ራእይ ኢትዮጵያን ማዳን ነው። የእንግሊዘኛ አባባልን ልጠቅምና “ Andinet ( UDJ) is not against anyone ; but is FOR Ethiopia”.

ጸረ-ሽብርተኝነትን ሽብርተኛ የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ህጉ የተለይያዩ ነገሮች ናቸው። አንድነትን የምትተቸው ለምን ሽብርተኝነት ላይ ጠንካራ አቋም ያዘ ብለህ ከሆነ ንገረን ? ይሄን ትላለህ ብዬ አላስብም። አንተም እንደ አይሰስ ያሉ ሽብርተኞችን አጥብቀህ የምትቃወም እና የምትኮንን መሆንህን ስለማወቅ።

አንድነትን የሚተቹት የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉን ይደግፋል ብለው ከሆነ ደግሞ መረጃ ያቅርብልን። እኛም ትችትዎትን እንድነጋራ። ግን የሚያቀርቡት መረጃ አይኖርም ለምን የአንድነት ፓርቲ በስራው አቋሙን ያስመሰከረ ነውና። የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ አደራጅቶ በይፋ በአደባባይ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግን ተቃዉሞ ሲንቀሳቀስ ለማየት የሚከተሉትን ፎቶውፖች መመለክቱ ብቻ ይበቃል፡ መቃወም፣ መተቸት መብት ነው። ግን ተቻለ መጠን አገናዝበን መረጃ ይዘን ብናደርገውው ደግሞ የበለጠ ጥሩም ይሆናል።

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች ፣ አሁን ለሕሊና እስረኞች ተቆርቋሪ ነን የሚሉቱ ጡሩምባ ከመንፋታቸው በፊት፣ አሁን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የሚቃወሙ ፊታወራሪዎች ከመነሳታቸው በፊት፣ የአንድነት ፓርቲና አንድነቶች ናቸው ለሕሊና እስረኞች አጋርነት በማሳየት፣ እስረኞች እንዲታሰሩበት ምክንያት የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ በሶሻል ሜዲያዉና ከመገልጫም ባለፈ፣ ህዝብ ጋር በመዉረድ፣ ህዝብን በማስተባበር ሲጮሑ የነበሩት። ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ዉጭ ባሉ ከተሞች በተደረጉ ሰልፎች የነበረዉን በጥቂቱ ይመልከቱ። “የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ሕግ መንግስቱን የጣሰ ነው” ወዘተረፈ የሚሉ መፈክሮችን ያንብቡ። ሐቁ እንግዱህ ይሄ ነው።

ወንድም ይድነቃቸው በርግጥ የጸረ-ሽብተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ ለዉጥ እንዲመጣ. የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱ ፍላጎት ካሉ እድነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሶሻል ሜዲያ ያለፈ ህዝብን የማደራጀት ሥራ እርስዎና ድርጅትዎ ለመስራት ሞከሩ። የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በመቀሌ በመሳሰሉ ጽ/ቤቶችን በአዲስ መልክ አጠናክሮ በየከልሉ ህዝቡ ወርዶ እያደራጀ ነው። በአዲስ አበባ በ23ቱም ወረዳዎች በአሥሩም ክፍለ ከተማው መዋቅሩን ዘርግቶ ወደ ህዝብ እየወረደ ነው። እናንተ እዚያ ላይ በርቱ።

አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛ የተቃዋሚዎች ተወካይ ናቸው። በፓርላማ ዉስጥ ሆነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ ትረታ የሳቡ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎች በመጠየቅ፣ በተስጣቸው ጥቂት ደቂቃዎች የአገዛዙ ባለስልጣናትን ደም ግፊት በየጊዜው እንዲጨመር የሚያደርጉ አንጋፋ ሰው ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ለተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን፣ በፓርላማ የሕዝብ ብቸኛ ድምጽ በመሆን ለሚያበረክቱት አስተዋጾ ያለኝን ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ። ለእኝህ ወዳጄ ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ እገልጻለሁ።

የሕሊና እስረኞችን በተመለከተ ይፋ በሆንው የሚሊዮኖች ድምጽ ለሕሊና እስረኞች የበየነ መረድ ዘመቻን በተመለከተ፣ በአንድነት ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ጊዜ አቶ ግርማ ሰይፉ አንድ ጥያቄ ይጠየቃሉ። የአንድነት ፓርቲ አባል የነበሩና ከነጀነራል መላኩ ተፈራ ጋር፣ ከአምስት አመታት በፊት ስለታሰሩ፣ አቶ መላኩ ስለሚባሉ እሰረኛ የተመለከተ ነው። “አቶ መላኩ የአንድነት አባል ነበሩ። የሕሊና እስረኛ ተደርግው ነው ወይ የሚታዩት ?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። አቶ መላኩ እነ አንዱዋለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ፣ ናትናኤል መኮንን ከመታሰራቸው ሁለት አመታት በፊት የታሰሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ተገደው ይሁን አምነዉበት፣ በኢቲቪ ቀርበው፣ ከግንቦት ሰባት ጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ስንት እስረኛ እያለ፣ የእኝህ ሰው ስም በተናጥል ተጠቅሶ ጥያቄ መቅረቡ በራሱ አጠያያቂ ነው። ሆን ተብሎ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በሚሰጡት መልስ ችግር ዉስጥ እንዲገቡ፣ ታስቦ እንደሆነ መገመት አያቅትም።

አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የታሰረ ሁሉ የሕሊና እስረኛ እንዳልሆነ ገልጸው፣ አንድ ሰው ጥፋት አጥፍቻለሁ ብሎ ካመነ (ወዶም ሆኖ ተገዶ) ፣ አላጠፋም ብለው መከራከር እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሰላምን በማስጠበቅ አንጻር፣ አንድነት ከኢሕአዴግ የበለጠ እንጂ ያላነሰ የጸረ-ሽብርተኝነት አቋም እንዳለውም አቶ ግርማ ሰይፉ አስረድተዋል።

ሆኖም የአቶ ግርማ ሰይፉ መልስ በመለጠጥና በማጦዝ ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ዘመቻ አቶ ግርማ ሰይፉ ላይ እና ፓርቲያቸው አንድነት ላይ ተከፍቷል። የዚህ ዘመቻ አዝማች ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው ደግሞ “የሕዝብ አይን እና ጆሮ ነኝ” የሚለው በሻእቢያ የሚደገፈው ኢሳት ነው።
አቶ ግርማ ሰይፉ አንድነት በሽብርተኝነት ላይ ከኢሕአዴግ የበለጠ እንጂ ያነሰ አቋም እንደሌለው በግልጽ አስቅምጠዋል። ጸረ-ሽብርተኝነት እና ሽብርተኛ የሆነው የጸረ-ሽብርተኘንት ሕጉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የአንድነት ፓርቲ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ ያለው አቋም ግልጽ ነው። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎ እንቅስቃሴዎችን ባደረገ ጊዜ ዋና አጀንዳ አድርጎ አንግቦት የነበረው የጸረ-ሽብርተኝኘት ሕጉ እንዲሰረዝ በማድረጉ ላይ ነበር። በወቅቱ የአንድነት ፓርቲን ወክለው፣ ከነሽመለስ ከማል ጋር በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ዙሪያ ክርክር ያደረጉት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌውም፣ በይፋ ሕጉ እንደማያስፈልግም መግለጻቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ግርማ ሰይፉ ራሳቸው፣ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር በጸረ- ሽብርተኝነት ሕግ ስም መንግስት ህዝቡን እያሸበረ እንደሆነም አስረድተዋል። እንደዉም “ሽብርተኞች” እየተባለ ዜጎችን የማሰሩ ጎጂ ተግባራትን “መንግስታዊ ዉንብድና” ብለው ነው ያቀረቡት። እንደዉም ያለማገናን እንደ አንድነት ፓርቲ ይሄ ዜጎችን እያሸበረ ያለውን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ የታገለ ድርጅት የለም።

ታዲያ ሁኔታው ይሄ ሆኖ እያለ፣ ቅንጣቢ በመያዝ፣ ብዙ ዋጋ በአገር ቤት እየተከፈሉ ያሉ ወገኖች ላይ፣ አሁን ኢሳት እንዳደረገው፣ አክብሮት በጎድለው መልኩ ጠጠር መወርወር የሚያስተዛዝብ ነው። በተለይም ኢሳት አላማው ምን እንደሆነ እንድንገነዘብ እያደረገን ነው። ትግላቸው ጸረ-ወያኔ ነው ቢሉንም ሌሎች ላይም ሳያነጣጥሩ እንዳልቀረም እያየን ነው።

ኢሳቶች በአቶ ግርማ ሰይፉ ላይ ያቀረቡት ከዚህ በፊትም አቶ ሃብታሙ አያሌውም ላይ አቅርበዉት ነበር። “ከአድማጮች የመጡልን ነው” በማለት አቶ ሃብታሙን ወያኔ ነው እስከማለት የተደረሰበትም ሁኔታ እንደነበረም ሁላችንም የምናስታወሰው ነው።

እንደኔ አስተያየት፣ አቶ ግርማ ሰይፉ የተናገሩት ነገር ምንም ስህተት አለው ብዬ አላስብም። ስህትት ሰሩ ቢባልም ደግሞ ብዙ ልንደነቅም አይገባም። ከፖለቲካ መሪዎቻችን ስህተቶች ሲሰሩ፣ ስህተቶችን አርመው፣ ከወደቁበት ተነስተው ጉዞ እንዲጀመሩ መደግፍና ማንሳት እንጂ ማብጠልጠል ነውር ነው። እንዲህ ስል አቶ ግርማም ሆነ ሌላ የፖለቲካ መሪ ተጠያቂ መሆን የለባቸዉም ማለቴ አይደለም። (በቅርቡ የአንድነት መሪ በነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ላይ እና የሰማያዊ መሪ አቶ ይላቃል ላይ ትችቶች እኔም አቅርቤ ነበር) ሆኖም ስንተችና ስንቃወም መረጃ ይዘን መሆን አለበት። ዉይይቶች ከተደረጉ፣ እዉነትን ይዞ፣ ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶ፣ በአክብሮት መሆን አለበት። ኢሳት ለነ ዶር ብርሃኑ ነጋ ሰዓታት በየጊዜው ዓድማጮች እስኪሰለቻቸው ድረስ እንደሚሰጥ፣ ለአንድነቶች ወይም ለአንድነት ድጋፍ ድርጅት መሪዎች በቂ ጊዜ ቢሰጥ፣ ምናልባት ሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ በሚገባ ሊኖረው ይችል ነበር። ኢሳቶች ግን ያንን አላደረጉም።

ሌላው የአንድነት ፓርቲ የአንድ ግለሰብ ፓርቲ እንዳልሆነም መታወቅ አለበት። አቶ ግርማ ሰይፉ አንድ የፓርቲው አንጋፋ ጠንካራ አመራር ናቸው። ሆኖም አንድነት ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ብዙ አባላትና ደጋፊዎች ያሉት ድርጅት ነው። በቅርቡ በመቀሌ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳር፣ በአዋሳ ጽ/ቤቶቹን በአዲስ መልክ ከፍቶ ትልቅ ድርጅታዊ ሥራ እየሰራ ነው። በመጪው ምርጫ እሳተፋለሁ ብሎ በይፋ አዉጆ የምርጫ ዘመቻውን ጀምሯል። ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጋዜጣውን አላትምም በማለቱ፣ የራሱ ማተሚያ ማሽን ገዝቶ፣ በር ሲዘጋ ሌላ በር አስከፍቶ፣ መልእክቶቹን ለሕዝብ እያቀረበ ነው።

ታዲያ ኢሳቶች የአንድነት ፓርቲ እንደ ፓርቲ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ያልዘገቡ፣ አንድ የአንድነት አባል ተሳሳተ ብለው በብዙ ሺህ ዶላር የሚያወጣ የአየር ጊዜ ማጥፋት ምን ይባላል ?

ኢሳቶች አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩት ካሉት በዘለለም አንድነት ለምርጫ እሳተፋለህ ማለቱን እየተቸ በይፋ እየተናገሩ ነው። ኢሳቶችም ሆነ ሌሎች አንድነት ለምርጫ እሳተፋለሁ ማለቱ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸው ላይ ችግር የለኝም። የተሻለ አማራጭ ኖሯቸው፣ በአንድነት ፓርቲ ላይ ተቃዉሞ ቢያሰሙ ለምን ሊባሉ አይገባም። ለምን ሲቃወሙ ሌላ አማራጭ በማቅረባቸው። ነገር ግን ምንም አማራጭ ሳይኖራቸው፣ እነርሱም በባዶ ዉስጥ ሆነው፣ በፈታኝ ሁኔታ ዉስጥ ደፋ ቀና የሚሉት፣ እኔ አቶ ግርማ ሰይፉና አንድነቶች ላይ ጠጠር መወርወር ትንሽ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ረገድ ቆም ብለው እንዲያስቡ እመክራለሁ።

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እምነት ያላችሁ፣ ህዝቡ ከተደራጀና ከተባበረ ለዉጥ ያመጣል የምትሉ፣ የጥላቻና የስሜት፣ የግትርነት ፖለቲካን ሳይሆን የበሰለ፣ የስለጠነ ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያቀፈን ፖለቲካን የምትደገፉ፣ በሁሉም አካባቢዎች ህዝቡ ለፍትህና ለነጻነት ለማንቀሳቀስ ደፋ ቀና እያለ ያለውን ፣ ከሕዝቡ ጋር ያለውን አንድነትን ተቀላቀሉ፣ ደግፉ።

የአንድነት ፓርቲ አንጻራዊ ጥንካሬ ቢኖረውም ብዙ ድክመቶች አሉት። ድክመትን፣ አክብሮት ባለበት መልኩ እየጠቆምን፣ የአመራር አባላቱም ሲሳሳቱ እየገሰጽን፣ ካልሰሙም ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ግፊት እያደረግን፣ ፓርቲው አቅሙን እንዲያጎለበት ማድረግ ነው የሚጠበቅብን። እነ ከበደ ካሳና ኢቲቪ ትንሽ ነገር ባገኙ ቁጥር በአንድነት ልስይ ይጮሃሉ። እነ ሲሳይ አጌናና ኢሳቶች ደግሞ ኢዚያ ትንሽ ነገር ይዘው ብዙ የአየር ሰዓት ፈጅተው፣ አንድነትን በማጥላላት ይፈርጃሉ።

የአንድነት አመራር አባላት ከየአቅጣጫው ቀሥት እንደተመዘዘባቸውም ተርድተው ለነዚህ ቡድኖች ብዙ ቀዳዳ ላለመስጠት እንዲጠነቀቁ አጥብቄ እየመከርኩ፣ “ሥራችሁ ላይ በርቱ” እላቸዋልለሁ: የሚያወራው ፣ የሚተቸው መተቸቱን ዕና ማወራቱን አያቆምምና ለወሬ ቦታ አትስጡ እላለሁ።

በአገር ዉስጥና ከአገር ውጭ ያለን፣ በሚሊዮኖች የምንቆጠር ለዉጥ ፈላጊ ወገኖች፣ በግላችን የድርሻችንን ለመወጣት እንሞክር። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሆን። እኔ አምነት አለኝ እያንዳንዳችን ከተነሳን ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። አንርሳ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደ ዜጋ የድርሻቸዉን በአገር ቤት እየከፈሉ ነው። እኛም የድርሻችንን ለመከፈል እንዘጋጅ።

አቶ ግርማ አገዛዙ አፍንጫ ሥር ሆነው በፓርላማ እያደረጉት ያለው ለማወቅ ይችን ያዳምጡ፡

https://www.youtube.com/watch?v=9HffknkPwYw

ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም መኢአድ እና አንድነት ዉህደት ይፈጽማሉ ተብሎ ተጠብቆ እንደነበረና የሕወሃት ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ አመራር እውቅና አልሰጥም በሚል ዉህደቱን ማጨናገፉ ይታወቃል። ከሁለት አመታት በላይ በአቶ አበባው መሐሪ ከሚመራው መኢአድ ጋር ደብዳቤዎች ሲጻጻፍ የነበረው ምርጫ ቦርድ ፣ አንድም ጊዜ በአመራሩ ላይ ጥያቄ አንስቶ ሳያውቅ፣ ዉህደት ሊደረግ ሲል፣ ሸንካላ ምክንያት በመፍጠር ሆን ብሎ ዉህደቱን ማጨናገፉ፣ ምርጫ ቦርዱ በሕወሃት አመራር ታዞ ያደረገዉ እና ምንም አይነት ገለልተኝነት እንደሌለው ያሳየበት እንደሆነ ብዙዎች ያናግራሉ።

የምርጫ ቦርድን ሕገ ወጥ ጥይቄ ለማሟላት መኢአድ ቅዳሜ ጥቅምት 29 እና እሁድ ጥቅምት 30 ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባኤው ባለመስማማት እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ችለናል።

አርብ ጥቅምት 28 ቀን፣ የመኢአድ ላእላይ ምክር ቤት ተሰብስቦ የመኢአድ አመራር የነበሩና በተለያዩ ችግር የተገለሉ ፣ አቶ ማሙሸት አማረን ያካተተ ፣ 14 ሰዎችን ጉዳይ፣ ጠቅላላ ጉባኤው በነገታው ዉሳኔ እንዲያሳልፍ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ ምንም እንኳን ከአንድንት ጋር ሊደረግ የነበረዉን ዉህደቱ ምርጫ ቦርድ ቢያጨናግፈውም፣ የምርጫ ዘመቻውን ከአንድነት ጋር በተቀናጀ መልኩ ለማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ዉሳኔ ለማስወሰን ታስቦም እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።

ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው በአቶ ሃይሉ ሻዉል መሪነት የተከፈተ ሲሆን፣ ከ335 በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዉም ነበር። እነ አቶ ማሙሸት በርካታ ሰዎች በስብሰባው እንዲገኙ ማድረጋቸዉንም ለማረጋገጥ ችለናል።

በስብሰባው ወቅት በአቶ ኃይሉ ሻዉልና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል ጠንካራ ልዩነቶችና አለመስማማቶች የነበሩ ሲሆን ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ እንዳልተጠናቀቀም ለማውቅ ችለናል። አቶ አበባው፣ ከሁለቱ በስተቀር የሥራ አስፈጻሚ አባላት በሙሉ ለደህንነታቸው ፈርተናል በሚል ስብሰባዉ ጥለው እንደወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከስብሰባው ከወጡት መካከል የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ተስፋሁን አለምነህም ይገኙበታል።

ስብሰባው እሁድ ጥቅምት 30 በቀሩት በአብዛኛው እነ አቶ ማሙሸት የሰበሰቧቸው ተወካዮች ባሉበት አቶ ማሙሸት አማረን የመኢአድ ፕሬዘዳንት አድርገው መርጠዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን የተደረገ እለት የምርጫ ቦርድ ተወካይ እንዳልነበረም የደረሰን ዘገባ ሲያመለክት፣ የምርጫ ቦርድ ተወካይ በሌለበት፣ አብዛኛው የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች አልተገኙም በተባለበት የተደረገ ምርጫ ምን ያህል ሕጋዊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ የሆነ ነገር እንደሌለ ከመኢአድ አባላት የሚደርሱ ዘገባዎች ይገልጻሉ።

ከአራት አመታት በላይ ያልታዩት ኢንጂነር ኃይሉ ሻዉል፣ በዚህ መልኩ ስብሰባው በሰላም እንዲጠናቀቅ አለማድረጋቸው እንዳልተደሰቱ የሚገልጹት አንድ ያነጋገርናቸው የመኢአድ አባል ለመኢአድ አሁን ያለበት ደረጃ በዋናነት ተጠያቂው አቶ ኃይሉ ሻወል እንደሆኑ ይናገራሉ።
በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ሊደረግ ታስቦ የነበረ አብሮ የመስራት ዉሳኔ በነበረው አለመስማምምት አልመሳካቱ ጥሩ እንዳልነበረ የተናገሩት እኝሁ የመኢ፤አድ አባል፣ “አብዛኛው የመኢአድ አባል ከአንድነቶች ጋር እየታሰረ፣ እየተደበደበ፣ እየተገደለ ነው። በተግባር የመኢአድ እና የአንድነት አባላት አንድ ናቸው” ሲሉ በአመራሮች ዘንድ አለመስማማቶች ቢፈጠሩም በሜዳ በየዞኑና በየወረዳው ያለው የመኢአድ ታግይ እንኳን እርስ በርሱ እንደ አንድነቶ ካሉ ሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር አንድ ሆነ እየሰራ እንደሆነም ይገልጻሉ።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ከበርካታ ተወካዮች ጋር ስብሰባዉን ለቀው የወጡት አንድ የመኢአድ ከፍተኛ አመራርር አባል፣ በማንም ድርጅት አለመስማማቶች እንደሚፈጠሩ ገልጸው፣ ብሶት ለመናገር ወደ ኢቲቪ እንደማይሮጡ ገልጸዋል።

በአቶ አማረ ማሙሽት የሚመራው መኢአድ ጽ/ቤቱን ተቆጣጥሮ አዲስ ካቢኔም እንዳዋቀረ ለማወቅ ችለናል። በዚሁ መሰረት አዲስ ካቢኔ የሚከተሉት አባላትን አካቷል፡

1: አቶ ማሙሸት አማረ (ፕሬዝዳንት)
2: ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ (ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት)
3: አቶ እንድርያስ ኤሮ (ምክትል ፕሬዝዳንት)
4: አቶ ተስፋየ መላኩ (ዋና ፅሃፊ)
5: አቶ ሰማሀኝ አብርሃም (የድርጂት ጉዳይ)
6: ኮኔሌር ትርሶት ጉልላት(የህዝብ ግንኙነት)
ገ: ወ/ሮ አለማየሁ ሞገድ (የሴቶች ጉዳይ)
8: አቶ አብርሀም ጌጡ (የውጭ ጉዳይ)
9: አቶ ሀብተማርያም ያንተ(ፋይናንስና አስተዳድር)
10: አቶ ታጠቅ አሰፋ (የወጣቶች ጉዳይ)
11:አቶ ሀይለየሱስ ሚናስ (የምርጫ ጉዳይ)
13:አቶ ተስፋሁን አለምነህ (ትምህርትና ስልጠና አላፊ)
14 : መ/አ አየለ አለ(የህግና ዲስፕሊን አላፊ)
15: አቶ ወርቁ ከበደ (የምሃል ቀጠና ሃላፊ)
16: አቶ አዳነ ጥላሁን(የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
17: አቶ ብሩ ደሲሳ( የምራብ ቀጠና ሃላፊ)
18: አቶ ገለቱ ደጀርሳ (የደቡብ ቀጠና ሃላፊ)
19: አቶ ተፈራ መንግስቴ (የምስራቅ ቀጠና ሃላፊ)\

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሥራ አንደ በመቶ በላይ፣ ለበርካታ አመታት እንዳደገ ይናገራል። በአገሪቷ በተለይም በአዲስ አበባ ግንባታዎች ይታያሉ። መንገዶች ይሰራሉ። ነገር ግን ግንባታዎቹ በአብዛኛው ከዉጭ በልምና በመጣ ገንዘብ የተሰሩ እንደመሆናቸው የኢትዮጵይን ምርታማነትና እድገት አመልካች አይደለም። የብር የመግዛት አቅም ከማሽቆልቆሉ የተነሳ፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መጥቷል።

የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ተመዝግቧል የሚሉት የኢኮኖሚ እድገት በርግጥ እድገት ነው ወይ ? ከሆነስ ስለምን ህዝቡ የእድገቱ ተካፋይ ሊሆን አልቻለም ? ለሚሉት ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በጥናትና በመረጃ ላይ ያተኮረ መልስ ለማግኘት፣ በቃሌ የፓልቶክ ክፍል የቀረበ፣ በአንድነት ደጋፊዎች የተቀናበረና የተዘጋጀ፣ ገለጻ ያዳምጡ።

https://www.youtube.com/watch?v=rxVV-Jx … e=youtu.be

በሽብር ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ላይ የሚገኙት እነ ሀታብሙ አያሌው ልደታ ፍ/ቤት ቀረቡ
**************************************
በማዕከላዊ እስር ቤት ከ115 ቀን እስር በኋላ ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው
****************************

<a href=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg”><img src=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg” alt=”10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n” width=”252″ height=”144″ class=”alignleft size-full wp-image-15235″ /></a>
በትላናው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሊቀርቡ ያልቻሉት የፓርቲ አመራሮች፣ በድብቅ ትላንትናውኑ ልደታ ፍ/ቤት መቅረባቸውንና ዳኛ ባለመሟላቱ ለዛሬ ጠዋት ተቀጠረው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ከታሰሩበት ማዕከላዊ ፍርድ ቤ/ት ፖሊስ አጅቦ ቢያመጣቸውም ከቀኑ በግምት 5፡00 ሰዓት አካባቢ 4ኛ ወንጀል ችሎት ካስገቡዋቸው በኋላ፣ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ወደ መኪናቸው በመመለስ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት እንደሚቀርቡ ለመጣው ታዳሚ ከችሎት አስተናጋጇ በመገለጹ፣ ከሰዓት በ 8፡00 ሠዓት 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ችሎት መግባት ይከለከል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ታዳሚው ችሎት እንዲገባ ተፈቀደ፡፡

በችሎቱ የቀረቡት 10 ተከሳሾች ሲሆኑ እነሱም፡-

1ኛ. ተከሳሽ የአ/አ ዩኒቨርስቲ ማስትሬት ተማሪ የሆነው ወጣት ዘላለም ወርቅአገኘሁ
2ኛ. ሃብታሙ አያሌው
3ኛ. ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ. አብርሃ ደስታ
5ኛ. የሺዋስ አሰፋ
6ኛ. ዮናታን ወልዴ
7ኛ. አብርሃም ሰለሞን
8ኛ. ሰለሞን ግርማ
9ኛ. ባህሩ ደጉ
10ኛ. ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡

በችሎቱ ላይ 3 ዳኞች የተሰየሙ ሲሆን የመሀል ዳኛው የዘገየነው ዳኞች ባለመሟላታቸው መሆኑን ከገለጹ በኋላ ተከሳሾችን ክሱ እንደደረሳቸው ጠየቁ፡፡ ተከሳሶችም ክሱ እንዳልደረሳቸው መለሱ፡፡ ክሱ የቀረበው ጥቅምት 20 ቀን2007 ዓ.ም መሆኑን ዳኛው ከገለጹ በኋላ ክሱ እንዲታደላቸው አደረጉ፡፡

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉት ተከሳሶች አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚንቀሳቀሰው ራሱን ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት አባል በመሆን ከድርጅቱ አባሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አባላት በመመልመል፣ ህጋዊ የፖቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ ሕዝቡ በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ፣ በደቡብ ክልል ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ መግለጫ በመስጠት፣ እንዲሁም ትህዴን ከሚባል ድርጅት ጋር በህቡዕ ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም በዋና የወንጀል ድርጊት ተካፋይ በመሆን የተከሰሱ ሲሆን ከ6ኛ እስከ 10ኛ ድረስ ያለት ተከሳሾች ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ማህበራዊ ተቋማትን ለማፈራረስ የሽብር ድርጊቱን ለመፈጸም በውጭ ሀገር በተማሩት የማህበራዊ ድህረ ገጽ አጠቃቀም የተለያዩ የፌስ ቡክ አካውንቶችን በመጠቀም ለድርጊቱ መፈጸም ሲሰሩ እንደነበር የአቃቤ ህግ ክስ ያመለክታል፡፡

እንደ ቅደም ተከተሉ ክሳቸው ተነቦ ካለቀ በኋላ ዳኛው ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም ትችላላችሁ ወይስ መንግስት ያቁምላችሁ ብለው በጠየቁት መሰረት ከ8ኛው ተከሳሽ በስተቀር ሁሉም ጠበቃ እንደሚያቆሙ ገለጹ፡፡ ነገር ግን እኛ ጠበቃ ብናቆምም ከታሰርንበት ሀምሌ 1 ቀን ጀምሮ ከጠበቆቻችን ጋር መገናኘት አልቻልንም ክቡር ፍ/ቤቱ ልንገናኝ እንድንችል ትዕዛዝ ይስጥልን፣ እስካሁን ከታሰርንበት ማዕከላዊ ወደ ማረሚያ ቤት እንድንሄድ እንዲታዘዝልን በማለት አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍ/ቤቱ ጠይቋል፡፡

አቃቤ ህግ አንቀጽ ጠቅሶ በሽብር የተጠረጠረ የዋስትና መብትን አይፈቅድም ይላል በመሆኑም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ እንደረግ ጠየቀ፡፡

ዳኛውም በዋስትና ላይ ያላችሁን አስተያየት ይዛችሁ ረቡዕ ጥቅምት 26 ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት መልሳችሁን በጽሑፍ ይዛችሁ ቅረቡ ተከሳሾች በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ይደረግ በማለት ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

በቅርቡ፣ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት ፣ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያና የኤርትራ ሞኒተሪንግ ግሩፕ በለቀቀዉ ሪፖርት ዙሪያ አንድ መግለጫ አዉጥቷል። አንዳንድ የተወሰኑ ድህረ ገጾች የግንቦት ሰባትን መግለጫ ለጥፈው፣የተባበሩት መንግስታ ሪፖርትን ግን ሳያያይዙ ቀርተዋል። ይሄን ሰነድ በሚከተለው ሊንክ ልታገኙት ትችላላሁ፡

http://www.un.org/ga/search/view_doc.as … S/2014/727

አስገራሚ መረጃዎችን ያካተተ ሰነድ ነው። ሰነዱ አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥቃቅን ግድፈቶች አሉት። ለምሳሌ ግንቦት ሰባትን የአማራ ድርጅት እንደሆነ የገለጹበት ሁኔታ አለ። ከዚያ ዉጭ ከሞላ ጎደል በሰነዱ የተካተተው ዝርዝር፣ የሚታመን ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ ሪፖርት ላይ በስፋትና በቅርብ ጊዜ ትንታኔ እንሰጥበታለን። ግን ለአሁን በግርድፉ አንብቤ ከሰነዱ ያገኙኋቸውን ጥቂት አንኰ ነጥቦች እንዳስቀመጥ ይፈቀድልኝ፡

1) ኦ.ኤን.ኤል፣ኤፍ ከአልሻባብ ጋር እንደሚሰራና ማእከሉን ከኤርትራ ወደ ሶማሊያ እንደወሰደና አሁን ኤርትራ ከበስተጀርባ ሆና መደገፏን እንደቀጠለች

2) ኦነግ የሚባል ነገር እንደሌለ

3) የግንቦት ሰባት ጦር ከ50 እስከ 70 እንደሆነ

4) ደሚት የሚባለው ድርጅት ትልቁና ጠንካራው እንደሆነ፣ ከሕወሃት ተቃዋሚነት አልፎ የኢሳያስ ክብር ዘበኛና ቅልብ ጦር እንደሆነና ከባባድ መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እየተወሰደ ወደ ደሚት እየተሰጠ እንደሆነ

5) ሻእቢያ ለግንቦት ሰባት ሆነ ለሌሎች ድርጅቶች የሚያደርገው እርዳታ የተባበሩት መንግስታትን ዉሳኔ የሚያፈርስ እንደሆነና ግንቦት ሰባት በተባበሩት መንግስታት ራዳር ዉስጥ እንደወደቀ

በቅርቡ ኢትዮጵያያ ሪቪው የተለያዩ ሪፖርቶች ሲያቀርብ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። የዚህ ሞኒተሪንግ ቡድን ሪፖርት በአብዛኛው ኢትዮጵያ ሪቪው ካቀረበው ጋር የሚዛመድ ነው።

በተያያዘ ዜና ደግሞ በኤርትራ ዉስጥ ከፍተኛ ተቃዉሞ በኢሳያስ አፈርቂ አገዛዝ ላይ እየተነሳ እንደሆነ ነው። ሃርነር አርቢ የሚባለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘ ነው። በጦር ሰራዊቱ ዉስጥ ሁሉ ዘልቆ ስለገባ ፣ ኢሳያስ ፊቷን ወደ ደሚት ለማዞር እስኪገደድ ድረስ።
በ ኤርትራ ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ እያለ የተከበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ ከአሜሪካን አገር ሳይወጡ ለምን የግፈኛው አቶ ኢሳያስ ተሟጋች እንደሆኑ አልገባኝም ? እርሳቸውስ እሺ ሌሎች የግንቦት አባላትና ደጋፊዎች፣ እንደ አበበ ገላው፣ መቼ ይሆን አንድ ግለሰብን ማምለክና መከተል አቁመው ለሕዝቡና ለትግሉ የሚጠቅም ነገር የማያደርጉት ?

የግንቢት ሰባት ንቅናቄ የተሳሳተ መንገዱን በአስቸኳይ መመርመር አለበት። ኢሳያስ ሊገነደስ ጥቂት ጊዜ የቀረው የበሰበሰ ዛፍ ነው። እስከመቼ ነው በበሰበሰ ዛፍ ላይ ተንጠልጥለው ትግሉን ብለው ወደነርሱ የመጡትን ለጋ ኢትዮጵያዉያን የሚያስበሉት ?

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች በስፋት ተደረጉ። ባለስልጣናቱ፣ የሕዝቡ ሰላማዊ ተቃዉሞ አይሎ መምጣቱን ሲያዩ አፈገፈጉ። የተቃዋሚዎች ስብስብ በክልል ምርጫዉ ያገኙትን ምርጫ፣ ተቀበሉ። ሊበራል ዴሞክራቱ ዞራን ጂንጂች የአገሪቷ መዲና የቤል ግሬድ ከንቲባ ሆኑ።

ብዙም አልቆየም፣ በተቃዋሚዎች መካከል ችግር መታየት ጀመረ። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ ፓርቲና በዞራን ጂንጂች በሚመራዉ ፓርቲ መካከል ልዩነቶች ተፈጠሩ። መካረር መጣ። የሕዝብን ጥያቄ አንግቦ በጋራ መቆም ተሳናቸው። በአደባባይ መወጋገዝ ጀመሩ። በአመቱ አገራዊ የፕሬዘዳንት ምርጫ ሲደረግ የሚሎሶቪች የሶሻሊስት ፓርቲ በቀላሉ ስልጣኑን ጨበጠ። የተለፋበት፣ የተደከመበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሸፈ። አምባገነኖች አሸነፉ። በሕዝብ ትግል የተገኙ ዉጤት እንደገና ተቀለበሱ። ዞራን ጂንጂችም ከናካቴዉ ከተመረጡበት የቤልግሬድ ከንቲባነት ተነሱ።

በ1998 በየክልሉ ተማሪዎች «ኦትፖር» ( በሰርቢያን ቋንቋ እምቢተኝነት) በሚል ስም ከታች ወደ ላይ የሆነ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የተከፋፈሉ የፖለቲካ ደርጅቶች በአንድ ላይ እንደገና ተሰባሰቡ። ካለፉት ስህተቶች በመማር፣ ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለሚቀጥለው ምርጫ መዘጋጀት ጀመሩ። ከፍተኛ ጫና እየተደረገም ዝግጅቱ ተጧጧፈ። የገዥዉ ፓርቲ ደጋፊዎችን የመሳብ ሥራ በስፋት ተሰራ። በዚህም ምክንያት በርካታ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ጀመሩ። ኢቫን ስታምቦሊች ፣ የሚሎሶቪች አጋር የነበሩ ፖለቲከኛ ፣ ተቃዋሚዎች በመቀላቀላቸውም በሚሎሶቪሽ የደህንነት ሰራተኞች ታፍነው ተገደሉ።

ሴፕቴምበር 2000 ዓ.ም ምርጫ ተደረገ። የሚሎሶቪች ምርጫ ቦርድ፣ አሁንም የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት ይፋ አደረገ። ያንን አስከትሎ ኦክቶቦር 2000 ዓ.ም ፣ ትልቅ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። ምርጫ ቦርድ የምርጫዉን ዉጤት ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተገደደ። የተቃዋሚዎች እጩ የሆኑት ኮስቶኒሳ እንዳሸነፉ ተገለጸ። የሚሎሶቪች ስልጣን ፍጻሜ ሆነ። የሰርቢያ ሕዝብ የማይቀለበስ ድል ተቀዳጀ።

ይሄንን ያለ ምክንያት አይደለም ያመጣሁት። በሰርቢያ፣ በመጀመሪያዉ ምርጫ የተከሰተው፣ በኢትዮጵያም በምርጫ ዘጠና ሰባት ከተከሰተው ብዙ የሚለይ አይደለም። ያኔ በቅንጅት ጊዜ የሕዝብ ጉልበት አያሎ የወጣበት ወቅት ነበር። ነገር ግን በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠሩ ልዩነቶች፣ በቀላሉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ለመቆየት ቻለ። (በገዢው ፓርቲ የደረሰው ወከባ፣ ግድያ፣ እሥር፣ እንግልትን ጫና ቢኖርም፣ በዋናነት የተቃዋሚዎች ችግር ነው አገዛዙን ያቆየው ብዬ ነዉ የማምነው)

ሰርቦች ጠመንጃ አላነሱም። ሰርቦች ለዉጥ ማምጣት አይቻልም ብለው አላወጁም። ሰርቦች ተስፋ አልቆረጡም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ተስፋ ቆረጥን። ፎጣችንን መሬት ላይ ጥለን፣ አምባገነንነትን አሜን ብሎ የመቀበል አዝማሚያ አሳየን። «ተቃዋሚዎች አይረቡም። ያኔ ደግፈናቸው ጉድ አላደረጉንም እንዴ ? አርፎ መቀመጥ ይሻላል፣ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ….» የሚሉ ጨለምተኛና የሽንፈት አባባሎችን ማሰማት ጀመርን።
የገዢዉ ፓርቲ ሰዎችም፣ ስልጣን ላይ ለመቆት የሚያስችላቸው፣ ይሄዉ የተቃዋሚዎች መከፋፈልና የሕዝቡም ተስፋ መቁረጥ ስለነበረ፣ በሚቆጣጠሯቸው ሜዲያዎች፣ ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ የበለጠ ተስፋ እንዲቆርጥ፣ ከፍተኛና ሲስቴማቲክ፣ ተቃዋሚዎች የማጥላላትን የማሳነስ ዘመቻቸዉን አፋፋሙ። ጠንካራ የሚሏቸውን የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለ ርህራሄ አሰሩ። ብርቱካን ሚደቅሳን አሰቃይተውና ሰባብረው (ለስድስት ወራት ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር ጨለማ ቤት ዉስጥ እንዳስቀመጧት) ለስደት ዳረጓት። «እነርሱን ያየህ ተቀጣ» በሚል፣ በአንዱዋለም አራጌ፣ በእስክንደር ነጋ፣ በርዪት አለሙ፣ በዉብሸት ታዬ፣ በበቀለ ገርባ፣ በአብርሃ ደስታ፣ በሃብታሙ አያሌው፣ በዳነል ሺበሺ፣ በየሺዋስ አሰፋ፣ በተመሰገን ደሳለኝ፣ በዞን ዘጠኞች እንዲሁም በሌሎች ..ሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ፣ በተራ የዉሸት ሽብር ክስ፣ ኢፍትሃዊነትና ኢሰብአዊነት የተሞላበት ግፍ መፈጸማቸዉን ቀጠሉ። በሕዝቡ አይምሮ ዉስጥ፣ እነርሱን ማንም ሊነካቸው የማይችሉ፣ ግዙፎች (ኢንቪሲብል) እንደሆኑ ለመሳል መሞከርና፣ ሕዝቡ እርስ በርስ ተፈራርቶ እንዳይደራጅ፣ እንዳይነጋገር፣ እንዳይተማመን፣ በዘር፣ በኃይማኖት በጥቅም እንዲከፋፈል፣ ማድረጉን ተያያዙት።

ነገር ግን ኢትዮጵያዉያን መንቃት ያለብን ይመስለኛል። ከሰርቦች መማር ያለብን ይመስለኛል። አምባገነኖች ኃይለኛ የሆኑ ይመስላሉ እንጂ ሁልጊዜ ባዶ መሆናቸዉን መረዳት አለብን። ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሕዝብ ድጋፍ የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀ፣ ለሕዝብና ለዜጎች ከበሬታ የማያሳይ፣ ዜጎችን ሽብርተኞች እያለ የሚያሸብር፣ የበሰበሰ ድርጅት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነዉ።

እንግዲህ «ትላንት ወድቀናል ብለን፣ የትናንቱ ጠባሳችንን እያየን ወደፊት ከመራመድ መቆጠብ የለብንም» እላለሁ። ከስህተቶቻችን ተምረን፣ ያለፈው ታሪካችን በአይምሯችን እየፈጠረ ካለው ጎታች ጫና ተላቀን፣ ይሄንን ዘረኛና አምባገነን ስርዓት ለመቀየር በቁርጠኝነት መነሳት የግድ ነዉ። ቁልፉ በእጃችን ነዉ። በርግጥ ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። ጥያቄው «ፍላጎቱ አለን ወይ?» የሚል ነዉ።

እያንዳንዳች ወደ ራሳችን እንመልከት። እራሳችንን እንጠይቅ። «እስከመቼ ነዉ፣ በአገራችን እንደ ባይተዋር ፈርተን እና አንገታችንን ደፍተን የምንቀመጠው ?» ማለት እንጀመር። በየወረዳችን፣ በየአካባቢያችን፣ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶችን እንቀላቀል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ጠንካራና አገር ሰፊ የኢትዮጵያዊትነትና የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነዉ። በመቀሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ አዳማ ፣ አሶሶ …በአገርቷ ክፍሎች ሁሉ ብትሄዱ አንድነት በዚያ አለ። አንድነትን እንቀላቀል። አንድነትን እንደግፍ። የሰማያዊ ፓርቲ ፣ መኢአድ፣ ትብብር ..ሁሉም በፊናቸው የሕዝብን ጥያቄ እያሰተጋቡ ነው። እንቀላቀላቸው። እንደግፋቸው። ልዩነቶቻቸውንም አጣበው ፣ የበለጠ ኃይልና ጉልበት ኖሯቸው ሰላማዊ፣ የኢትዮጵያዊነት የሰለጠነን የፖለቲካ ትግል ይመሩ ዘንድ፣ እንዲሰባሰቡ፣ እንዲዋሃዱ እናበረታታቸው።