ቅ/ሲኖዶስ: ለአማሳኞቹ ቀኖናዊ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ወሰነ፤ ፓትርያርኩ ‹‹ልዩ ጸሐፊዬን ከምታነሡ እኔን አውርዱኝ፤ ጥዬ እሔዳለኹ፤ ገዳሜ እገባለኹ›› ሲሉ ለንቡረ እድ ኤልያስ ተከላከሉ

  • ውሳኔው በዋናነት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስንና መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃን ይመለከታል
  • በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር በተቀጡበት ድርጊታቸው ከተገኙ ክህነታቸው እንዲያዝ ተወስኗል
  • ፓትርያርኩ ‹‹አጀንዳው መያዙን አላውቅም›› በሚል ውይይት እንዳይካሔድ ተቃውመው ነበር

*          *         *

  • ‹‹እምነት አለው ለማለት ይከብዳል፤ የሙስና አባትና የሰላም ጠንቅ ነው፤›› የተባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ የነበሩትም ያሉትም ፓትርያርኮች ችግር ዋነኛ መንሥኤ እንደኾኑ ተሠምሮበታል
  • በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሾም የበሸቁትና በቀኖናዊ ውሳኔው የተደናገጡት እነሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ይኼ ይዞ ሟች፤ለሸዋ አሳልፎ ሰጠን›› እያሉ ፓትርያርኩን ሲዘልፏቸው ዋሉ

*           *         *

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥረኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ‹‹በሌብነት ላይ ተሠማርተው ቤተ ክርስቲያኗን እያወደሙ ነው›› ባላቸው ኹለት የአማሳኙ ቡድን መሪዎችና ግብረ አበሮቻቸው ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ስለሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር የተወያየው ምልአተ ጉባኤው÷ ‹‹ቤተ ክርስቲያኗን አዋርደዋል›› ባላቸው የአማሳኞች መሪዎች ላይ ባሳለፈው ውሳኔ፣ ቀኖናዊ ቅጣት እንዲፈጸምባቸውና ከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

the heavily corrupt Haile Abreha barking on the multitude of the<br />
participants of the 33rd gen assembly” width=”600″ height=”430″ /></a></strong><span style=ቀኖናዊ ቅጣቱና ከባድ ማስጠንቀቂያው በተለይ የአማሳኞቹን ቡድን እንቅስቃሴን በመደገፍ፣ በማስተባበርና በመምራት ተጠቃሽ በኾኑት የሲ.ኤም.ሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ እና የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ ላይ ተፈጻሚ እንደሚኾን ታውቋል፡፡

ኹለቱን የአማሳኞች መሪዎች እንደ አቀባባይ ደላሎች በመጠቀም ቀድሞም የነበራቸውን የምዝበራ ሰንሰለት አጠናክረው በቀጠሉት የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጉዳይ ምልአተ ጉባኤው የተነጋገረ ቢኾንም ፓትርያርኩ ‹‹የእኔ የግሌ ጸሐፊ ነው›› በሚል ተከላክለውለታል፡፡

‹‹እርሱን ብታነሡ ጦር ያማዝዛል›› በማለት ብፁዓን አባቶችን ፈገግ ያሰኙት ፓትርያርኩ፣ ልዩ ጸሐፊአቸው ከሓላፊነት ከሚነሡ ይልቅ የእርሳቸው ከፓትርያርክነት መነሣት እንደሚቀል በመናገር የምልአተ ጉባኤውን አባላት አስደምመዋል፡፡