በአንታርስ ሮኬት መቃጠል የወደመችው ሲግነስ የጠፈር መንኩራኩር

 

የዩናይትድ ስቴትስ የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር – ናሳ የጠፈር ምልልሱን ሥራ ለግል ኩባንያዎች ኮንትራት እየሰጠ ነው፡፡

ከእነዚህ የግል ኩባንያዎች አንዱ ዋና መሥሪያ ቤቱ ቨርጂንያ የሆነው ኦርቢታል ሳይንስስ ኮርፐሬሽን በሚያንቀሳቅሰው የ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ኮንትራት ኅዋ ውስጥ ለሚገኘው ዓለምአቀፍ ጣቢያ ስንቅና ቁሳቁስ እየላከ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ተልዕኮዎች አንዱ ከትናንት በስተያ ተስተጓጉሏል፡፡

በአንታርስ ሮኬት ከቨርጂንያው ማስወንጨፊያ ከሁለት ቶን በላይ ውኃ፣ ምግብና የምርምር ቁሣቁስ ይዛ የተነሣችው መንኩራኩር ከተተኮሰች ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ፈንድታለች፡፡

በሰው ላይ ምንም ጉዳት አይድረስ እንጂ መላው ጭነት በፍንዳታውና በእሳቱ ወድሟል፡፡

የማስወንጨፊያው ማማ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

በናሳ…