መነገር ያለበት ቁጥር አራት ከበልጅግ ዓሊ
ጉዳዩ – እሁድ ጃንዋሪ 13 ጠዋት ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በምገኝበት ወቅት ነው የተከሰተው። የዜጎቻችንን ቁጥር ስለበዛ (አበሻ የሚለውን ቃል መጠቀም ስለሚደብረኝ) ምን ይሆን ምክንያቱ ብዬ አካባቢውን እየቃኘሁ ፓስፖርቴን አሳይቼ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰሌዳው ላይ የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዳለውና መግቢያውም በበር ቁጥር 22 እንደሆነ ይገልፃል። በተጠቀሰው በር […]