ሰላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ በጉዲፈቻ የወሰዷቸውን ጨምሮ የሰባት ልጆች ወላጆች – “ይቻላል” ይላሉ
ሶፊያ አለማየሁ
የግል ህይወት ለማሸነፍ በምንጣጣርበት በዚህ የውድድር ዘመን አንዳንድ ሰዎች ከራሣቸው አልፈው፤ ካላቸው አካፍለው ለሌሎች ህይወት እና ተስፋ፣ ለብዙኃን ተምሣሌት ይሆናሉ፡፡
ወጣት ሠላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ ከነዚህ ግብረ ሠናይ ሰዎች መሀል ናቸው፡፡ ሰባት ልጆች አሏቸው፡፡ ከነዚህም አምስቱ በጉዲፈቻ የወሰዷቸው ናቸው፡፡ ከዓመት በፊት፣ ወደ ካሊፎርንያ ከመምጣታቸው በፊት የሚኖሩት አምስት ልጆቻቸውን ባገኙበት በኢትዮጵያ፣ ናዝሬት ከተማ ነበር፡፡
“ሠላም ገና እጮኛዬ ሆና ለመጋባት ያስቀመጠችልኝ ቅድመ ሁኔታ፤ ‘ከተጋባን ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን እንረዳለን፤ ድጋፍህ እንደማይለየኝ ቃል ግባልኝ’ የሚል ነበር” ይላል ሙሉጌታ፡፡ ጥያቄዋን በእሺታ የተቀበለው ሙሉጌታ ‘ወደፊት ትተወዋለች’ የሚል ግምት እንደነበረው ይናገራል፤ ነገር ግን ሠላም ይህንን …