የሀገር ጩኸት እና የታሳሪ ልጆች… አውደ-ዓመት
አጀንዳ- ፩
ለምን ይጮኸል?
መልሱ፣ ለምን አይጮኸም ይሆን? …በጠመንጃ አስገዳጅነት፣ ለማይጨበጥ፣ ለማይታይ ‹‹ራዕይ›› ሀገርን፣ ዘመንን፣ ትውልድን፣ እምነትን… ‹‹ገብር›› ሲባል ማን ነው የማይጮኸው? … የመንግስት ሰራተኛው ይጮኸል፣ የግል ተቀጣሪው ይጮኸል፣ ቀጣሪው ይጮኸል፣ ስራ እጡ ይጮኸል፣ ነጋዴው ይጮኸል፣ ሸማቹ ይጮኸል፣ ሰራዊቱ ይጮኸል፣ ሙስሊሙ ይጮኸል፣ ክርስቲያኑ ይጮኸል፣ ጠንቋዩ ይጮኸል፣ እምነት የሌለው ይጮኸል፣ የተደራጀው ይጮኸል፣ ያልተደራጀው ይጮኸል፣ የጠገበው ይጮኸል፣ የራበው ይጮኸል፣ ፍትህ ያጣው ይጮኸል፣ እስረኛው ይጮኸል፣ እስረኛ ጠባቂው ይጮኸል፣ ታሪክ ይጮኸል….ሰሚ አልባ ጩኸት! እሪ በከንቱ!!