ቤል ተዋረደ፣ ናባው ተሰባበረ

ዳዊት ፋንታ

በአንድ ወቅት ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም “ይህ አዲስ አበባ አይደለም፣ ይህ የገጠር ቀበሌ ነው” የተሰኘ መጣጥፍ ፅፎ ነበር። እናም በዚያች “ሥርዓት አልበኝነት” በነገሰባት የገጠር ቀበሌ ውስጥ የሂሳብ መምህሩ ከመቅፅበት ተነስተው የስዕል መምህር ሲሆኑ ይታያል። በርግጥም የሕግ የበላይነት ባልሰፈነባት በዚያች የገጠር መንደር የሂሳብ መምህሩ የስዕል መምህር መሆን ሳያንሳቸው ተማሪዎቻቸውን ሲያሰቃዩ ይስተዋላል።