መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ
“ነፍስ ካለ፣ መፍጨርጨር አይቀርም!”
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በሐምሌ 1955ዓ.ም የወጣው መነን መጽሔት፣ (7ኛ ዓመት፣ ቁ.10 ዕትም፣ በገጽ 27) ላይ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፤ “እኚህ የ33 ዓመት ወጣት በአባታቸው ጎንደሬ፣ በእናታቸውም ይፋቴ ሲሆኑ፣ በአማርኛ የበሰሉ በመሆናቸው የመናገርና የማስረዳት ስጦታ ያላቸው ትሁት ወጣት ናቸው፤” ሲል ይገለጻቸዋል። ለጥቆም የወጣቱን መስፍን ወልደ ማርያም ሦስት ሐሳቦች እንደሚከተለው አስፍሮት ይገኛል። “ማናችንም በዘመኑ የምንገኝ ትውልዶች በምናውቀውና በተማርነው ችሎታችን ተሽለን ተገኝተን፣ የዚህ ዕድል ተሣታፊ ለመሆን የሚጓጉ ወንድሞቻችንን ለመርዳት የምንቦዝንበት ትርፍ ጊዜ እንዲኖረን አያሻም።