የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስትያን ሲኖዶስ ዛሬ ሚያዝያ 13/2007 ባወጣው ባለ9 ነጥብ መግለጫ፡- በሊቢያ ውስጥ በተደረገው አሰቃቂ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንኒቱ እጅግ ያዘነች መሆኗን ገልጾ በዚህ ግድያ ውስጥ ግን ሟቾቹ ሰማዕት በመሆን የተጠቀሙ ጀግኖች እንጂ ተጐጂዎች እንዳልሆኑም ጭምር ማሰብ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የሚገኙ ገዳማት እና አድባራት በአጠቃላይ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት ጸሎተ ፍትሐት እንዲያደርሱ ጥሪ አስተላለፏል፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ከሚያዚያ 14 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ምህላ እንዲያረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አያይዞ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ አክሎም ለሟቾቹ የሰማዕትነት ክብርን በቀኖናው መሠረት መስጠት እንዲቻል ቤተሰቦቻቸውን የሚያውቁ ምዕመናን ፎቶአቸውንና ስማቸውን አሰባስባው ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ አዝዟል፡፡ ሙሉ የሲኖዶስን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ከሥር ካለው ምስል ያንብቡ ወይም እዚህ ጋር በመጫን (link) ዳውንሎድ ያድርጉ፡፡ *********** — More from Horn Affairs AmharicSendek | የጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ 29 ሰዎች በሽበርተኝነት ተከሰሱETV | የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን ተይዞ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷልማዕተብም መስቀልም በግለሰቦች ነፃነት ውስጥ የሚካተት ነው – ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያምየዩኒቨርስቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስ ደንብን በመቃወም በሽብር የተሳተፉ ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉሕገ-መንግስት እንዲያከብሩ ሲመከሩ – በሃይማኖታችን ጣልቃ ተገባ ይላሉ (ሚ/ር እውነቱ ብላታ)ማዕተብ ከሂጃብ

http://www.eaglewingss.com/
እስከመቼ ነው?
ዛሬ ውስጤን የሚያናውጠው ማዕበል፡ ከጥቂት ግለሰቦች በስተቀር የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ አእምሮ እንደ ትንሽ ታንኳ እያናጋ፡ አንዴ ከራሱ ምናብ የሃሳብ ቋጥኝ ጋር፡ አንዴም ከአምላክ ምስጢራዊ ፈቃድ ዓለት ጋር እያጋጨው እንዳለ ይገባኛል። ታዲያ፥ ስሜት በቀላሉ ሰብረው በማያመልጡት የምሬት ሠራዊት ሲከበብ፣ ተስፋ በድቅድቅ የሞት ጭጋግ ውስጥ ሲደበቅ፣ ለነፍስና – ለስጋ፡ ለአእምሮና – ለእጅ፡ እንደ መፃፍ ያለ ከባድ ህመም የለም። ልብ ብርቱ በሆነ የሀዘን ጦር ሲቆፈር፡ ጉልበትን ሰብስቦ ሃሳብን አምጦ መውለድ አይደለም፡ እውነታንም ቁጭ ብሎ መታዘብ ይከብዳል። ያኔ፥ እፅፋለሁ ላለ ጣት፡ ብዕር እንደ ብረት ለሽክም ይከብዳል። ቢሆንም ግን፡ የቆሰለው አእምሮዪ በተደጋጋሚ አንድ ጥያቄ ይጠይቀኛልና፡ በዝምታ ከማስታምመው – ይኸው ተንፍሼ ልገላገለው ሞከርኩ።

የማከብርህ ኢትዮጵያዊ ወገኔ፥ ተፈጥሮ ሳትሰስት፡ ከዓለም ሁሉ አብልጣና አድልታ የሰጠችንን የዘፍጥረት እና የስልጣኔ ብኩርና፡ እንደ ኤሳው ለሆዳችን – ለምስር ወጥ – ሸጠን፡ እስከመቼ ነው እንደ ዝቃጭ እንደ አተላ፡ ህይወታችን ክብር፣ ሞታችን ዝክር የሚያጣው? እስከመቼ ነው ዘረኞች የዘሩልንን አዝመራ ስናጭድ – ስንውቃ ውለን፡ ሲመሽ ምርት ሳይሆን ምሬት ሰብስበን ወደ ቤታችን የምንገባው? እስከመቼ ነው ሰሜን ጫፍ ተቀምጠው፡ ከደቡብ ጫፍ የተወረወረ ጠጠር ሊስታቸው እስከሚሳነው ድረስ እየሰፉ እና እየሰቡ ያሉት የፖለቲካ መሪዎቻችን፡ ከአፍንጫችን በላይ ያንጠለጠሉልንን የነፃነት ካሮት ላንደርስበት-ላንበላው አህያ ሆነን ስንጋልብ እና ስን’ጋለብ ዘመን የሚያልፈው? እስከመቼስ ነው ምስኪኑ ወገናችን ደረቱ ላይ ተደግኖ የተተኮሰበት የመሳሪያ ጥይት እስኪስተው ድረስ በየሰከንዱ-በየደቂቃው በረሃብ እየከሳ እና እያነሰ፡ በየበራሃው በኖ ተኖ፣ በየባህሩ ዝሎ ሰጥሞ የሚያልቀው?

በወንደሞችህ የግፍ ሞት ልብህ የተሰበረው ኢትዮጵያዊ ወገኔየነፃነት ትግል እኮ ዓላማ እንጂ ባህል አይደለም። ተጀምሮ ማለቅ፤ መነሻ አምድ፣ መደምደሚያ ግብ ሊኖረው ይገባል። የባርነት ሰንሰለት አልበጠስ ብሎ ከከረረ፡ አልቋጭ ብሎ ከረዘመ፡ እንደ ወግ-ባህል ከዘመን ዘመን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከተሻገረ፡ ቆም ብሎ ማስተዋል፤ መሪ ተመሪን መቃኘት ግድ ይላል።

ዛሬ በኣራቱም የዓለም ማዕዘናት ህዝባችን እየቆጠረ ላለው ፍዳና ሰቆቃ መነሻ ምክንያቱ ፖቲካዊ እንጂ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አንዳልሆነ ለመረዳት፡ ማንም የርዕዮተ ዓለም ፈላስፋ አሊያም የምጣኔ ሃብት ሊቅ መሆን አይጠበቅበትም። ፖለቲካዊ ችግር ደግሞ ከምንም በላይ ፖለቲካዊ መፍትሔን ይሻልና፡ ፖለቲካችን እንዴት እና ወዴት ነው? ዜጎቻችን ትላንት- ሳውድ ዓረቢያ፡ ዛሬ- የመንደቡብ ኣፍሪካሊቢያ ላይ እየተጋቱ ያሉትን መከራ ከምንጩ ለማድረቅ፣ ነገም ተመሳሳይ ጥፋት ካይሮ ላይ ከመከሰቱ በፊት ችግሩን ከችካሉ ለመንቀል ልምን ተሳነን? ጉድለታችን የመሪ? የተመሪ? ወይንስ አጠቃላይ የድርጀታዊ መዋቅር እንከን ነው የሚለውን መጠየቅ እና በአፋጣኝ መመለስ ወቅቱ ይመስለኛል። እርግጥ ነው ዛሬም ቢሆን፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶች ከብሉይ ኪዳን የመማፀኛ ግንብ በተለየ መልኩ መዋቀርና ተቀዳሚ ዓላማቸው ተገዳዩን ማትረፍ እንጂ ገዳዩን ማቀፍ መሆን የለበትም ብዪ አምናለሁ። ዘራፊው ዘርፎ፣ ገዳዩም ገድሎ እጁ ሲዝል እና ሲደከም፡ ሀጢያቱን ለማስተሰረይ፣ ከህዝብ ለመታረቅ ዘሎ የሚቀላቀለው እና የሚያንቀላፋበት ጎራ – እንደ እኔ ግለሰባዊ እምነት- ወህኒ-ቤት እንጂ አንድነት፣ መድረክ፣ ሸንጎ ወይንም ግንቦት ሰባት መሆን ያለበት አይመስለኝም።

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነርሱ የሚወስደውን መንገድ ታዘጋጃለህ … (ኦሪት ዘዳግም / ምዕራፍ 19 : 2)

ላለፉት በርካታ አመታት እንደታዘብነው ግን፦ ሀገር እንደ ቡሄ ሙልሙል ገምሶ፣ ህዝብ እንደ አክርማ ቀጭቶ፣ ዘርፎ እና አዘርፎ የበቃው ባለስልጣን መሽሽጊያው አንድም ቤተ-መቅደስ ኣለበለዚያም የተቃዋሚው ድርጅት ነው። ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች፡ ወንጀለኞች ሰይጣናዊ ባህሪያቸውን በሃይማኖታዊ ጠበል አርጥበው፣ በተቃዋሚ ፎጣ አድርቀው በአዲስ ካባ ብቅ ሲሉ እንደ ቅዱስ መላዕክት የሚሰገድላቸው የአይሁዳውያኑ የመማፀኛ ቅጥር መሆናቸው እስካላበቃ ድረስ፡ የነፃነት ኣላማችን ዕውን የሚሆነው፣ የመከራችን ቋጠሮ በዘላቂነት የሚፈታው – በዕድል እንጂ በትግል እንዳልሆነ መጠርጠር የለብንም።

ከረሃብ ወደ ስድብና ውርደት ተመሳሌነት ያሻገሩህ ኢትዮጵያዊ ወገኔ፥ ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት ዛሬም እንደ ትላንቱ የማሰምርበት እውነት ቢኖር፦ ህዝባችን ከእንሰሳ ባነሰ ክብር በየመንገዱ ተቀጥቅጦ ሲገደል ዝም ብሎ ከማየት የከፋ የወገን በደል የለምና፡ እንደ ዜጋ የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግ የተረፉትን ለመታደግ፣ የረገፉትንም ቤተሰቦች ለማፅናናት ዛሬ! አሁን! ቃል ብቻ ሳይሆን ከትግሉም መሃል መግባት ይኖርብናል።

መፈራረሳችን፣ ስድባችን፣ መዋረድና መታረዳችን ዓላማቸው ብቻ ሳይሆን አለማቸውም ለሆነው ጎጠኞች፡ የሃዘን ሲቃችን ብሔራዊም ባይሆን ጎሳዊ መዝሙራቸው ነው። የድረሱልን ለቅሶና ጩኸታችን፡ “አከርካሪውን ሰበርነው – ጥርሱን አወለቅነው” ብለው ለተሳለቁብን ዘረኞች፡ የዓላማቸውን መሳካት የሚያበስር ደወል፣ የግባቸውን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ቃጭል ከመሆን ባሻገር ፋይዳ እንደሌለው ተረድተን፤ ራሰን፣ ወገንን እና ሃገርን የማዳን ዘመቻውን ከራሳችን በራሳችን መጀመር ብልህነት ነው። የዓባይን ውሃ ለኣባዮቹ ትተን፡ የወገናችንን፣ የአዛውንት እናትና አባቶቻችንን የኣይን ፍሳሽ- ዕንባ – ለመገደብ፡ የትግል ቦንድ (ውህደት) መፍጠሩ ከመቼውም በላይ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ደርሰናልና ወንድ – ሴት፣ እስላም – ክርስቲያን ሳንል በተግባር በስነ-ምግባር እንተባበር።

ኤግል-ዊንግስ-ሶሳይቲ በደቡብ ኣፍሪካ፣ በየመን፡ አንዲሁም በሊቢያ ህይወታቸው ለጠፋው ዜጎቻችን የተሰማንን ከፈተኛ ሃዘን ስንገልፅ፡ ለቤተሰቦቻቸውም አምላካዊ መፅናናትን እየተመኘን ነው። ችግሩ ከመሠረቱ አልተወገደምና፤ በኣሁኑ ወቅትም በአደጋ ወስጥ ላሉት ወንድሞችና እህቶቻችን፡ ከበረከታችን ሳንሰስት በጉልበት፣ በዕውቀትና በገንዘብ የምንችለውን ሁሉ ከማደረግ ባሻገር ትግሉ ለመከራው ዘለቄታዊ መፍትሔ እስኪያመጣ ድረስ፡ የአምላክ ሰፊ መዳፍ የመጠለያ ድንኳን እንዲሆናቸሁ ምኞትና ፀሎታችን ነው።


የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ባወጣው ባለ ዘጠኝ ዐንቀጽ መግለጫ ለሰማዕታቱ ተገቢውን ቀኖናዊ ክብር እንደሚሰጥ ገልጧል፡፡ ለዚህም የሰማዕታቱን ቤተሰቦች የመረጃ ትብብር ጠይቋል፡፡ ‹‹የጀግና እናት አታለቅስም›› ያለው መግለጫው የሰማዕታቱ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ሰማዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ስላለው በዚህ እንዲጽናኑ አደራ ብሏል፡፡ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ከመንግሥት ጋር አብሮ የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ እንደሚያቋቁምም ገልጧል፡፡
መግለጫውን ቀጥሎ ያንብቡት
በተያያዘ ዜና ዛሬ ከሰዓት ዐሥር ሰዓት ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ ሰማዕታቱ ቤተሰቦች በመሄድ ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚያጽናኑ ተነግሯል፡፡  
ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ሲሠራ ‹ሲኖዶስ ሲኖዶስ› ይላል፡፡

click here for pdf

ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከፖኤቲክ ጃዝ አባላትና ከሌሎች የኪነ ጥበብ ሰዎች ጋር ወደ ቂርቆስ ሄጄ ነበር፡፡ ያቺ ሳቂታዋና ተጫዋቿ ቂርቆስ ኀዘን ወርሯታል፡፡ የቂርቆስን ልጆች አውቃቸዋለሁ፡፡ ማልታ፣ ግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ስዊዘርላንድ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ መሳቅ ነው፣ መጨዋት ነው፡፡ መቀለድ ነው፡፡ ችግር እነርሱ ጋር የለም፡፡ ካገኙ ተካፍለው ካጡ ተሳስቀው ያልፉታል፡፡ መተዛዘን፣ መረዳዳት፣ ነገር ማቅለል ማን ይችላቸዋል፡፡ እንግሊዝ ሀገር የደረሱት በመንገድ ያለቁትን የሚያስቡበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀን አላቸው፡፡
ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ
ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ
ይላሉ የማልታ ልጆች፡፡

ዛሬ ያ ሁሉ ሳቅና ጨዋታ በኀዘን ተቀይሯል፡፡ የልጆቻቸውን መሞት በቪዲዮ በተመለከቱ ወላጆች፣ ማንነታቸውን ከቪዲዮው ለመለየት አቅቷቸው በሰቀቀን ውስጥ በሚገኙ ወላጆች፣ የልጆቻቸውን መረጃ ፈልገው መልስ ባጡ ወላጆች ቂርቆስ ተሞልታለች፡፡ ትጠይቃለች፤ መልስ ግን አላገኘችም፡፡ እንዴት ያለው ትምህርት፣ እንዴት ያለው ጥበብ፣ እንዴት ያለው ብልሃት እንደሚያጽናናት እንጃ፡፡  
እኔ በልቅሶ ቤት ሄጄ ብዙም አላለቅስም፡፡ ዛሬ ግን አለቀስኩ፡፡ በተለይ የባልቻ እናት ‹ፍቅር እስከ መቃብር› እያሉ ሲያለቅሱ ስሰማ ዕንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ኢያሱና ባልቻ ሲበሉም፣ ሲጠጡም፣ ሲሄዱም፣ ሲቀመጡም የማይለያዩ አብሮ አደጎች ናቸው፡፡ ሲሰደዱም አብረው ነው የተሰደዱት፤ መሥዋዕት የሆኑትም አብረው ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹ፍቅር እስከ መቃብር› የሚሉት የባልቻ እናት፡፡ እናቱን ሊረዳ እንደሄደ፣ ድሮም በእምነቱ ቀልድ እንደማያውቅ፣ ብዙ ተስፋ ሰጥቷቸው እንደነበረ እያነሡ ያለቅሳሉ፡፡ ‹‹እኔ ሲሞት እንዳላየው ብሎ አንገቱን ዘንበል አደረገ››  ይላሉ፡፡
 አያሌ የከተማው ሕዝብ ለእግር መቆሚያ እስኪጠብ ድረስ ሠፈሩን አጨናንቆታል፡፡ ኡኡታ፣ እሪታ፣ ሰቆቃ፣ ቁጭት፣ ሰቀቀን፣ ይነበባል፡፡ የባልቻ እናት ከልጃቸው ሞት በላይ አሁንም በሊቢያ የሚገኙ ሌሎች ወገኖቻችን ያሳስቧቸዋል፡፡ ስለ እነርሱም ያለቅሳሉ፣ ይወዘወዛሉ፡፡ አይ ኢትዮጵያዊት እናት፡፡  

ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ እና የሌላ ሀገር ተወላጅነት ባላቸዉ ንፁሀን ዜጉች ላይ በተፈፀመዉ አሰቃቄ የግድያ ወንጀል አዝነን ሳናበቃ ፦ ዛሬ ደግሞ በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን እጅግ አሳዛኝ ፤ አረመኔያዊ ተግባር ስይና ስንሰማ የተሰማኝን ሐዘን ለመግለፅ ቃላትም ሆነ ቋንቋ ያጥረኛል። እንኳን የኔ በሚሉት የራስ ወገን ይቅርና ክቡር በሆነዉ […]

ሰበር ዜና አሁን የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ከተማ ውስጥ ማን እንደበተነው ያልታወቀ ነገ የስራ ማቆም አድማ እና ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ወረቀት ተበትኗል! በየታክሲውና ከተማ ውስጥም መነጋገሪያ እንደሆነ ታውቋል። ፖሊስ ሰልፈኛው ወደ ሜክሲኮ እንዳይሄድ ለማገት ቢጥርም ህዝቡ ግን አንቆምም ብሎዋል ሰልፉ አዲስ አበባን ሲዞር ሊውል ነው! አሁን ሰልፈኛው ወደ ከቄራ ወደ ሜክሲኮ እየዞረ ነው! ፖሊስ ምንም […]

በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችኋል፤ በስሜም ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ሰዎችም እርስ በርሳቸው ይጣላሉ፡፡ ብዙ ሃሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤ ከክፋት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች፡፡ እስከ መጨረሻ በትዕግስት የሚጸና ግን ይድናል፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ ምሥክር እንዲሆን ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል […]

ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ በግፍ የተሠው ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን መኾናቸውን አረጋገጠ፤ ‹‹የልጆቻችን ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚኽ ከሐዘናችኹ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡›› ነገ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንት፣ ካህናት የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እንዲኹም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው …

በሊቢያ፣ በየመን እና በሌሎችም ክርስቲያኖች ለጥቃት በተጋለጡባቸውና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ በሚገኙባቸው አገሮች ከተጨማሪ ጉዳት ለመታደግ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል በአዲስ አበባ እና በአህጉረ ስብከት የሰማዕታት ቤተ ሰዎችን እያፈላለጉ የማጽናናት እና የመደገፍ መርሐ ግብር ይካሔዳል ከሊቢያው የግፍ ተግባር ጋራ በተያያዘ ባሉ ኹኔታዎች ላይ በየዕለቱ እየተሰበሰበ በመምከር መልእክት ለማስተላለፍ የወሰነው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም መግለጫ ይሰጣል

ሊቢያ ላይ በአይ ኤስ አይ ኤስ በተገደሉት ኢትዮጵያውያን መንግስት ትኩረት አለመስጠቱን ተከትሎ በርካታ ህዝብ በተቃውሞ ወደ ቤተ መንግስት እያቀና ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ ከሟቾቼ ቤተሰቦች ተነስቶ በመስቀል አደባባይ አልፎ አሁን ውጭ ጉዳይ ላይ ደርሷል:: የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በቦታው ተገኝቶ እየዘገበ ይገኛል፡፡Filed under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Addis Ababa University, Africa, African Commission on Human and Peoples’ […]

ደጋግመን መፈክር ስላሰገርንና፣ ደጋግመን በቃል ቃል ስለገባን ግባችንን በተግባር እንመታለን ማለት አይደለም፡፡ የምንጓዘው ዓላማችንን አንጥረንና አነጣጥረን መሆን አለበት፡፡ ተግባሩን እንጂ ተደጋጋሚ ወሬውን እንተው፡፡ቃል ስንገባ በስሜታዊነት አይሁን! ቃል ስንገባ በአድር-ባይነት አይሁን! ቃል ስንገባ ለይስሙላ አይሁን! ቃል ስንገባ በእርግጥ አደርገዋለሁ ወይ? ብለን ከልባችን ጠይቀን፣ በአዎንታዊነት እራሳችንን አሳምነን፣ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን […]

(ይሄን መልእክት እና ሌሎች ተመሳሳይ መልእክቶችን ያሰራጩ። ሕዝቡ መረጃ እንዲደርሰውና የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆን የድርሻዎትን ይወጡ) ሐሙስ በመላው አገሪቷ፣ በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ደብር ብርሃን፣ ደሴ አርባ ምንጭ አዋሳ …የሥራ ማቆም አድማዎችን ያካተቱ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ። ታክሲዎች አይንቀሳቀሱም። ሰራተኞች፣ ተማሪዎች ፣ አስተማሪዎች ሐሙስ ቀን ወደ ስራችሁ እና ወደ ትምህርት ቤታችሁ እንዳትሄዱ። ሐሙስ […]

በሊቢያ ምድር እምነታቸው ወንጀል ሆኖባቸው በአይሲስ የተሠዉትን ሰማዕታተ ሊቢያ በተመለከተ መንግሥታዊና የሃይማኖት ተቋማት ሊያደርጉ ስለሚገባው ነገር ስንለው ስንለው ቆየን፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡
እነዚህ ወገኖቻችን ስማቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን የምታውቁ ንገሩን፡፡ በባሕላችን መሠረት ልቅሶ እንድረሳቸው፡፡ ኀዘናቸው እነርሱ ብቻ አለመሆኑን እንንገራቸው፤ መከራቸውን እንካፈላቸው፡፡ እንደ ባሕሉ ማድረግ ያለብንን እናድርግ፡፡ ይኼ ከዘወትሩ ኀዘን ይለያል፡፡ የተሠዉበት ምክንያት፣ የተሠዉበት ሁኔታ፣ ለመሥዋዕትነት ያቀረቧቸው አሸባሪዎች ማንነት ከዘወትሩ ይለያቸዋል፡፡ ኀዘኑ የወላጅ፣ የዘመድ የመንደር፣ የዕድር ብቻ አይደለም፡፡ ከፕሬዚዳንቱ እስከ እኔ ላለነው ሁሉ ኀዘን ነው፡፡ ስለዚህም እንደየአመቺነቱ ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ በየደረጃው ያለን እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ልቅሶ እንድረስ፤ ሰውነታችንን፣ ለዜጎቻችን ያለብንን ኃላፊነት፣ ለቤተሰቦቹ ያለንን የመጽናናት ምኞት በመግለጫ ብቻ ሳይሆን በባሕሉ መሠረት እንግለጠው፡፡ ፖለቲካዊ ዲስኩሩን፣ ነጥብ ለማስቆጠር መጨቃጨቁን፣ የተለመደ ቢሮክራሲያዊ አሠራሩን ትተን ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡ ባሕል የሌለን እምነት የሌለን አንምሰል፡፡ ለእንደዚህ ያለ ወቅት የሚሆን ወግና ሥርዓት አለን፡፡  ያለ ወግ የመየጣውን ዕዳ በወግ እንክፈለው፡፡

ታዋቂ ሰዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት መሪዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሞያ ማኅበራት መሪዎች፣ ባለ ሀብቶች፣ በባሕሉ መሠረት ወደ ቤተሰቦቹ ሄደን ኀዘናችንን እንግለጥ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ኀዘናችንን እንካፈለው፡፡ ልዩነታችንን ኀዘን አንድ ሊያደርገው ካልቻለ ከእንግዲህ ምን አንድ ያደርገዋል፡፡
እንደ እምነታችን ለሰማዕታቱ ተገቢውን ሥፍራ እንስጥ፤ የጸሎት ሥነ ሥርዓት በየአጥቢያው ይዘጋጅ፤ ፎቶዎቻቸው በየአጥቢያው ይለጠፉ፤ የተሠዉበት ክቡር ዓላማ ይነገር፤ በየአጥቢያው የሚዘመረው መዝሙር፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ምዕዳን ነገሩን ያገናዘበ ይሁን፤ ቢቻል በየ ቤተ እምነቱ ልዩ መርሐ ግብር ይዘጋጅ፡፡ ስለ ሰማዕታቱ የሚያወሳ፣ሽብርና ሽብርተኛነትን የሚያወግዝ፣ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር፤ በሐሳብ፣ በርእዮተ ዓለም፣ በአካሄድ ብንለያይም በሀገራዊ ጉዳይ አንድ መሆናችንን የሚያበሥር፣ የሰማዕታቱን ሰማያዊ ዋጋ የሚዘክር፤ ነገ ተመሳሳይ ነገር እንዳይደገም  መንገድ የሚቀይስ፣ ጉባኤ ይዘጋጅ፡፡
ይሄንን ነገር ያደረጉት አሸባሪዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር ያደረጉት ኢሰብአውያን በመሆናቸው እንጂ ሙስሊም በመሆናቸው አይደለም፡፡ አንዱም ፍላጎታቸው እንዲህ ስሜት በሚነኩ ድርጊቶች ልዩነታችንን ማስፋት ነው፡፡ እኔ የብዙ ሙስሊም ወገኖቼን ስልክ ዛሬ ስቀበል ነበር፡፡ እጅግ ያዘኑ፣ የተነኩ፣ በእስልምና ስም በተፈጸመው ድርጊት ልባቸው የበገነ ሙስሊሞች፤ አማኞች እንጂ አሸባሪዎች ያልሆኑ፡፡ ሰው በእምነቱ የተነሣ መገደሉን በምንም መልኩ የማይቀበሉ ሙስሊሞች ኀዘናቸውን ሲገልጡ ነበር፡፡
ይኼንን ሰማዕታቱ የሰጡንን ዕድል ለአንድ ዓላማ ለመቆም እንጠቀምበት፤ የሰማዕታት ዓላማ ማስታረቅ ነው፤ ማግባባት ነው፡፡ ይኼንን የኢትዮጵያዊ መተዛዘንና መረዳዳት ጉዳይ ሙስሊም ወገኖቼ በእምነታቸውና በባሕላቸው አጉልተው ያሳዩናል ብዬ አምናለሁ፡፡ አንዳችን በሌላችን የኀዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተን ከእኩዩ ተግባር በተቃራኒ በጋራ መቆማችንን እናሳይ፡፡  
ያ ከሆነ የደሙ ልቦች ይድናሉ፣ የተጎዱ ቤተሰቦች ከልብ ይጽናናሉ፤ አራጆቻችንም የፈለጉትን ማግኘት እንዳልቻሉ ያያሉ፡፡ አሸባሪዎቹ በሰማዕትነት እንዳከበሩን ሁሉ እኛ ደግሞ የሰማዕታቱን ዓላማ በማጽናት እናዋርዳቸዋለን፡፡ ማን ያውቃል፣ የሰማዕታቱ ደም አልግባባ ላለው ልዩነታችን ሥርየት ይሆነን ይሆናል፡፡

ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ሳምንቱን በሀዘን ተውጠው አሳልፈዋል። በየመን የተጀመረው የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ጩኸት በደቡብ አፍሪካ እና በሊቢያ ተሰምቷል። 30 ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ በአይ ኤስ ወታደሮች የተገደሉበት ዜና መላውን አለም እያነጋገረ ነው። ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ከመግለጽ በተጨማሪ ምን እናድርግ እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው። በፌስቡክ እና በማህበራዊ ድረገጾች የፖለቲካ እምነታቸውም ሆነ ሃይማኖታዊ …

ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 12 ፣ 2007ዓም ኡራኤል አካባቢ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤንዚን በራሱ ላይ አርከፍክፎ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ ከተቃጠለ በሁዋላ በህዝብና በፖሊስ እርዳታ ሊተርፍ ችሎአል። የአይን እማኞች ግለሰቡ ሙሉ ልብስ የለበሰ እና ጥሩ የሰውነት ቁመና  ያለው መሆኑን ተናግረዋል።  ፖሊሶችም ግለሰቡን ወደ ስድሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል ዘግይቶ በመጣው መረጃ ደግሞ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

በሊቢያ እስላማዊ መንግሥት የተሰኘው አክራሪ ድርጅት 30 ኢትዮጵያውያንን በጥይትና በመቀላት የገደለበት የጭካኔ ተግባር ፣ እንዲሁም፣ በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች አንፃር በቀጠለው ሁከት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የኃይል ተግባር በኢትዮጵያ ተወገዘ።

በሜድትሬንየን ባህር ከሊቢያ የባህር ዳርቻ ወደ ኢጣልያ በመጓዝ ላይ የነበረች መርከብ ከትናንት ወዲያ ባጋጠማት የመስመጥ አደጋ 950 ያህል ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ።

በሊቢያ የአይሲስ ታጣቂ ቡድን የተገደሉት 30 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ማረጋገጡን አስታወቀ። ግድያው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። የአውሮጳ ህብረት፤የአፍሪቃ ህብረትና ዩ.ኤስ አሜሪካ የታጣቂ ቡድኑን ድርጊት በጽኑ ኮንነዋል።

ከሊቢያ ወደብ ተነስታ የሜድትራኒያንን ባህር በማቋረጥ ወደ ጣሊያን በማምራት ላይ የነበረች መርከብ በመስጠሟ ከ900 ሰዎች በላይ ሳይሞቱ አልቀረም። በመርከቧ ከተሳፈሩ ሰዎች መካከል 28 ስደተኞች ብቻ ተርፈዋል።

ማህሌት ፋንታሁን 
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ደስታ በዋናነት
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – በተያዝኩባቸው ቀናት በሙሉ (በተለይ ሚያዝያ 18 በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በሰፊው) 

የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ቢሮ ላይ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት

– በጠበቃ እና በቤተሰብ የመጎብኘት መብቴ ተጥሷል፡፡ ከተጎበኘሁም 10ደቂቃ ለማይሞላ ጊዜ በፓሊስ ተከብቤ ነበር፡፡

– በተደጋጋሚ በምርመራ ወቅት አመጽ ለማነሳሳት እነደጸፍሽ እመኚ እየተባልኩ በጥፊ እና በካልቶ ተደብድቤያለሁ፡፡

– በምርመራ ወቅት ልብሴን አስወልቀው አንድቀመጥ በማድረግ አይኔ ተሸፍኖ በምሽት ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡

– ሙሉ ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ ራቄቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፓርት አንድሰራ እገደድ ነበር ፡፡ “ሴትነትሽ አንዲህ ከሚዋረድ አመጽ እንዳነሳሳሽ እመኚ ተብያሁ”

– በሌሊት ግርፋት የሚፈጸምበት ክፍል ውስጥ ገብቼ ጫማሽን አውልቂ ተብዬ ጫማዬን አውልቄ ከቆምኩ በኋላ ውስጥ እግርሽን ከምትገረፊ አመጽ ማነሳሳትሽን አምነሽ ፈርሚ ተብያለሁ፡፡

– ሰጠሁት የተባለው ቃል ሰዎች በሚቀጥለው ክፍል እየተደበደቡ የጩኀት ድምጻቸው እየተሰማ ፈርሚ ተብዬ የተባልኩት ቦታ ላይ ሳላነብ በፍርሃት ፈርሜያለሁ።

– በተለያዬ ምርመራ ወቅቶች “ለነጭ አገሪትዋን የሸጥሽ ሸርሙጣ ውሻ ባንዳ…” አንዲሁም ለመጸፍ የሚከብዱ አፀያፈ ስድቦች በየቀኑ እሰደብ ነበር ፡፡

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው […]

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

ብዙ ሰዎች የሚፀዳድት አይነ ምድር ቀለም ከበሽታ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ብለው መጠየቅ የተለመደ ነው በመሠረቱ ስጋት ውስጥ ሊከቱን የሚችሉ የአይነ ምድር ቀለም ለውጦች ቢኖሩም ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ግን የአይነ ምድር ቀለም ትክክለኛው ቀለም ላይሆን ይችላል።
አይነ ምድር በአብዛኛው ቢሊሩቢን በሚባል ቁስ ነገር ምክንያት ነጣ ያለ ቡናማ ወይም ቢጫ ቀለም ይኖረዋል። ይህ ቢሊሩቢን…

click here for pdf


የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡ 

ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?
እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?
‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?
ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች  ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡
እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡

ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?

ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡

የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?

ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?

ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡

እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡


የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ በአሸባሪው አይሲስ እጅ በሰማዕትነት የተሠውትን ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ዛሬ ጠዋት 5፡30 ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከውጭ ሀገር ጉዞ ቀርተው በመንበረ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሌሎች የእምነት ተቋማትም ተመሳሳይ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
 መግለጫውን ተመልከቱት፡፡ 

በፍቃዱ ሃይሉ

ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎች ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ 
-መርማሪ ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም ) 
– መርማሪ ጽጌ 
-መርማሪ ብቂላ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 22 ( ከምሽቱ 2 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 23 ከጠዋቱ 4 ሰአት፣ ግንቦት 6( ከምሽቱ 3 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 24 ከጠዋቱ 4 ሰአት እና ከሚያዝያ 22 እስከ ግንቦት 6/2006 ድረስ ባሉት ቀናት ከእሁድ በስተቀር

የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 35 ፣ 27 እና ቁጥሩን በማላስታውሰው የቃለ መጠይቅ ቦታ

ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– ማአከላዊ ምርመራ በቆየሁባቸው ቀናት ከእሁድ በስተቀር ጠዋት ከሰአት ማታ እየተጠራሁ በዛቻ በአጸያፌ ስድብ ጭካኔ የተሞላበት ግርፌያ ጥፌና እርግጫ አንዲሁም ከአቅሜ በላይ የሆነ ስፓርት እየሰራሁ ቃሌን እንድሰጥ ተገድጃለሁ፡፡የተያዝክበትን ድብቅ አጀንዳ ንገረን በማለት ራሴን እንድወነጅል ተገድጃለሁ፡፡

– መርማሪው በመጀመሪያ ቀን ምርመራ በጥፌ መምታት የጀመረ ሲሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ከጠየቀኝ በኋላ በጥፌ ይመታኝ ነበር፡፡ የዞን9 አላማ ጠይቆኝ ስነግረው ድብቁን አውጣ በማለት መሬት ላይ አንድቀመጥ እና ያደረኩትን ነጠላ ጫማ እነዳወልቅ አዞኝ በኮምፒውተር ገመድ እግሬን መግረፍ ጀመረ፡፡ በተጨማሪም በሆዴ አንድተኛ በማዘዝ እና እግሬን አጥፌ ከፍ አንዳደርገው በማድረግ ውስጥ እግሬን ገርፎኛል፡፡ ድብቄ አጀንዳህን ካልተናገርክ ነገ እዘለዝልሃለሁ በሚል አስፈራርቶኛል፡፡ ግርፌያው ውስጥ እግሬን ሲለበልበኝ ነበር ፡፡

– ድምጽ እንዲያፍን ሆኖ ወደተሰራው የስብሰባ አዳራሽ ተወስጄ በጥፌ እየደበደቡኝ የዞን አላማ ተናገር ተብዬ ተደብድቤያለሁ፡፡ ስቃዬ ሲበዛብኝም የፈጠራ ታሪክ አንዳወራ ተገድጃለሁ፡፡ እኔ የምጽፈው ኢትዬጲያ ውስጥ አብዬት ለማስነሳት ነው ብዬ እንድፈርምም አስገድደውኛል

– በምርመራ ወቅት እጄ በካቴና እነደታሰረ ለሰአታት ቁጭ ብድግ አንድል ተገድጃለሁ፡፡

– መርማሪው በአንድ ወቅት አራት የዞን9 አባላት ሆናችሁ ስለአላማው የተወያያችሁትን በቃል መስጫው ክስ ላይ ልጽፍ ነው ሲለኝ አንደዛ አይነት ውይይት ማድረጋችንን አላስታውስም ስለው እንዴት አታስታውስም ብሎ በጥፌ መማታት ጀመረ፡። በተደጋጋሚ ከመደብደብም በላይ እስክስታስታውስ እዚሁ ታድራታለህ በማለት ድብደባው በመቀጠሉ አስታውሳለሁ ብዬ ተገላገልኩ ፡፡ የሰጠሁት ቃል ላይም እንደፈለገው አድርጎ ጻፈው፡፡ እኔም በድብደባ ብዛት ፈርሜያለሁ፡፡

– ዞን9 ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሌለው ከሆነ ይህንን ህዝብ አንዴት ነው ነጻ የምታወጡት በሚል ሲጠይቁኝ የነጻ አውጪነት ሚና የለንም ስላቸው ከወንበሬ አንድነሳ አዘዙኝ፡። ከዚያም በቆምኩበት ግራ ብብቴን እና እጄን በአንድ እጁ አንዳልወድቅ ወጥሮ ይዞ በእግሩ ጭኔን በሃይል ደበደበኝ ፡፡ ከድብደባው በማስከተል ደግሞ እግሬ መሃል እግሩን በማስገባት ወደግራ እና ወደቀኝ በመምታት ተዘርጥጬ እንድቆይ በማድረግ እጄን ወደላይ አድርጌ እግሬ ግራና ቀኝ ተዘርጥጦ ( በተለምዶ ስፕሊት በሚባለው) በግራ እና ከቀኝ በመደብደብ እጄን ወደላይ አድርጌ እነድመረመር ተደርጌያለሁ፡፡ከዚህ ምርመራ በኋላ ለሁለት ቀን እያነከሰኩ ነበር፡፡

– በጥቅሉ ምርመራው በተከናወነባቸው ቀናት ከእሁድ በስተቀር ሳልደበደብ ቢያንስ በጥፌ ሳልመታ የቀረሁበት ቀን የለም፡፡ ድበደባዎቹ አብዛኛው ድብቅ አጀንዳችሁን ተናገር የሚሉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በጣም ጥቃቅን በመሆኑ ምክንያቶች ነው ፡፡ መልስህ ንቀት አለበት ለምን አላስታወስክም በሚሉ ምክንያቶች ስደበደብ ነበር ፡፡

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ እስልማና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት አሸባሪው የአይ ኤስ ቡድን በሊቢያ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አወዘገ።

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሙሃመድ አወል ኡመር ጀማል፥ የአይ ኤስ ታጣቂዎች ሃይማኖትን ጭምብል ያደረጉ ፀረ ሃይማኖተኛ ናቸው ብለዋል።

በእስልምና እምነት የሰው ልጅ ከየትኛውም ፍጡር የከበረ ነው ያሉት ሼህ ሙሃመድ፥ ይህ አረመኒያዊ ተግባር እስልምናን አይወክልም ብለዋል።

ምክር ቤቱ ይህን ፀረ እስልምና እንቅስቃሴ እንደሚያወግዝ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥  ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህ አክራሪ ቡድን በሌሎች ሀገራት እያደረገ ያለውን ተግባር ወደ ኢትዮጵያ እንዳያስፋፋ ከመንግስትና ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በንቃት እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል።

የሀገራችንን ሰላም ለመጠበቅ እምነታችን አይለያየንም ነው ያሉት ሼህ ሙሃመድ።

የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታ በበኩላቸው  ኢትዮጵያ ዜጎቿ  ቀዳዳውን አጥብበውት እንጂ  ለበርካታ ጊዜ የሞት ድግስ ተደግሶላት እንደነበር ተናግረዋል።

ትናንት በኢትዮጵያዊያኑ ላይ የደረሰው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ አክራሪዎች ለሺህ ዘመናት ተዋዶ እና ተከባብሮ በመኖር ለአለም ተምሳሌት በሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ክፉ ዘርን ለመዝራት ታልሞ የተደረገ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ድኤታው የገለጹት።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያውን ለዘመናት የኖረው ተቻችሎ እና ተዋዶ የመኖር ልምድ ልዩነትን አያበቅልም ብለዋል።

የነዚህ ንፁሃን ደም ኢትዮጵያውያንን ከፀረ አክራሪነት ትግሉ ስንዝር ወደ ኋላ እንደማይጎትታቸውም ነው ያረጋገጡት።

ሀገሪቱ የፀረ ሽብር ህግ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተውን አዋጅ አውጥታ ወደ ተግባር ባትገባ ኑሮ አክራሪዎች ኢትዮጵያን እንደ ሊቢያ፣ ሶርያ፣ የመን እና ኢራቅ የፈራረሰች ባድማና የደም መሬት ባደረጓት ነበርም ብለዋል።

የትናንቱ ድርጊት የፀረ ሽብር እና ፀረ ፅንፈኝነት ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።

አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ትናንት በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ኢትዮጵያውያን ያላቸው 28 ንፀሃን 16ቱን በስለት ተቀልተው ደማቸው በባህር ዳርቻ ሲፈስ 12 ጭንቃላታቸው በጥይት ተመትቶ በበረሃ ሲወድቁ አሳይቷል።

አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን አለም አቀፉ ፅንፈኛ ቡድን አይ አይ ኤስ አል ፉቅራን ባለው ድረ ገፁ የለቀቀውን ዘግናኝ ምስል ተቀባብለውታል።

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬውዳን ሁሴንም በግፍ የተገደሉት ንፀሃን ሁሉም ኢትዮጵያን ስለመሆናቸው እያጣራን ነው ብለዋል።

በሊብያ፣ በደቡብ አፍሪካም ሆነ በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ከፈለጉ የፈቀዱትን ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አቶ ሬድዋን ገልጸዋል።

በዳዊት መስፍን

Subscribe to SodereMovies YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡

ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?

ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡

የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?

ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?

ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡

እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡

“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ…ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር… በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት። አስሩን ህጻናት […]

– እነ BBC፣ CNN የተገደሉት ኢትዮጵያዉያን ናቸው ሲሉ ወያኔዎች ማረጋገጫ የለንም አሉ። – ኢቢሲ የሊቢያውን ጭፍጨፋ የዘገበው እንደተራ ዜና በሶስተኝንት ነው። አል ጃዚራ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያንን አይሰስ፣ በሊቢያ ኢሰብአዊና ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እንዳረዳቸው ዘግቧል። CNN “ISIS operatives have beheaded two groups of prisoners, believed to be Ethiopian Christians, in Libya” ሲል፣ BBC ደግሞ “ISIS releases […]

እራሱን «እስላማዊ መንግስት» እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ሊቢያ ውስጥ ዛሬ በአሰቃቂ ኹኔታ መግደሉን የሚያሳይ ቪዲዮ ማሰራጨቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

Islamischer Staat Video Christen Libyen 29 ደቂቃ የሚፈጀው ቪዲዮ «ከጠላቲቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመስቀሉ ተከታዮች» የሚል ርእስ እንደያዘ እና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ታጣቂዎች በሁለት ምድብ ኢትዮጵያውያኑን በተርታ ይዘው እንደሚያሳይ ተገልጿል። ሽጉጥ የያዘ አንድ ታጣቂ፤ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ወደ እስልምና እስካልቀየሩ ድረስ ቡድኑ እንደሚዋጋቸው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዝቷልም ተብሏል። በመቀጠል ቪዲዮው ውስጥ 12 ሰዎች ያሉበት ቡድን አንገታቸው በካራ ሲቆረጥ፤ ሌሎች ቢያንስ 16 ሰዎች ደግሞ በጥይት ሲገደሉ እንደሚያሳይ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሬድዋን ሁሴን በ«እስላማዊ መንግስት» የተገደሉት 30 ሰዎች ማንነት ማጣራት አለመቻላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ቃል አቀባዩ አክለው ሲናገሩ «ቪዲዮውን ተመልክተነዋል፤ ሆኖም የተገደሉት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ካይሮ የሚገኘው ኤምባሲያችን ማረጋገጥ አልቻለም» ማለታቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ተናግሯል። ቃል አቀባዩ «እንዲያም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ይኽን አሰቃቂ ድርጊት ያወግዛል» ብለዋል። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ሊቢያ ውስጥ ኤምባሲ ባይኖራትም ከሊቢያ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ዝግጁ ናት ማለታቸውም ተዘግቧል። ቀደም ሲል ይኽ እራሱን «እስላማዊ መንግስት» እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን 21 የግብጽ ኮፕት ክርስቲያኖችን አንገት የሊቢያ ባሕር ዳርቻ ላይ በስለት መቁረጡ ይታወሳል።

አይሲስ በሊቢያ በሚገኙ ስደተኞች ላይ ፈፅሜዋለሁ ያለውን ግድያ መንግስት አወገዘ

አይሲስ የተባለው አለምዓቀፍ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ፈፅሜያዋለሁ በሚል በቪዲዮ ያሰራጨውን ዘግናኝ የግድያ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያወግዘው አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሀፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን እንደገለፁት አሸባሪዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙትን ይህን መሰል የጭካኔ ተግባር ኢትዮጵያ በፅኑ የምታወግዘውን ያህል ቀደም ሲል ጀምሮ ዜጎቿንም ከሽብርና አሸባሪዎች ጥቃት ለመታደግ የሚያስችላትን አስፈላጊውን ዝግጁነት ተግባራዊ በማድረግ የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት በአስተማማኝ ማረጋገጥ ችላለች ፡፡

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11፣2007 የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይሲስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድኑ ለህልፈት የዳረጋቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ባይሆኑም መንግስት በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ይህን መሰል አፀያፊና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት አጥብቆ ይኮንናል ብለዋል፡፡

በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ከሆነም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡በመሆኑም ከሊቢያ ወደ ሀገር ተመላሽ ፈላጊ ስደተኞች በግብፅ ካይሮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ግኑኝነት እንዲፈጥሩም የኢትዮጵያ መንግስት አሳስቧል ሲል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሀፈት ቤት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በላው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ዛሬ የዓለም መገናኛ ብዙኃን የ30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በኢስላሚክ ስቴት በሰማዕትነት መገደል ሲዘግቡ ነበር፡፡ ሰው በእምነቱ ብቻ ሰማዕትነት የሚከፍልበት ዘመነ ሰማዕታት አንደገና ታድሶ እየተነሣ ነው፡፡ ትናንት ግብጻውያን ምእመናን የከፈሉትን ሰማዕትነት ዛሬ ኢትዮጵያውያኑ ከፍለውታል፡፡ ክርስቲያን መሆን ወንጀል ሆኖ፡፡ ሰማዕታቱስ ወደሚወዱት ጌታ ሄደዋል፡፡ ይህ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የሚፈተኑበት ጊዜ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥትና የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለግብጽ ሰማዕታት ያደረጉትን በቅርብ ዓይተናል፡፡ የኛዎቹ በሚዛን የሚመዘኑበት ወይ ቀልለው ወይም ከብደው የሚገኙበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ እግዚአብሔር ከሰማዕታቱ በረከት ይክፈለን፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በ  [ሰንደቅ ]

ፍቅር፣ ትዝታ፣ ፀፀት፣ ያደረ ስህተትና ይቅር ባይነት የሚፈራረቁበት ፊልም ነው፤ በበኃይሉ ዋሴ ተፅፎ፣ በፍቅረየሱስ ድንበሩ ዳይሬክት የተደረገው “ሰኔ 30”። በኩል ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ፊልም በአይረሴዎቹ “አይራቅ”፣ “አምራን” እና “እኔና አንቺ” በተሰኙ ፊልሞቹ ልምድ ያለው ዳይሬክተር የሰራው የፍቅር ፊልም ነው።…