ቅዱስ ሲኖዶስ: ጸሎተ ምሕላ ያውጃል፤ በሊቢያ በግፍ ለተሠውት ክርስቲያኖች ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፤ የመታሰቢያ ሥያሜም ይሰጣል
- በሊቢያ፣ በየመን እና በሌሎችም ክርስቲያኖች ለጥቃት በተጋለጡባቸውና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ በሚገኙባቸው አገሮች ከተጨማሪ ጉዳት ለመታደግ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል
በደቡባዊ ሊቢያ በርሓ ከተሠውት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አንዱ የኾነውና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ አጥቢያ የሚገኙት የኢያሱ ይኵኖ አምላክ ቤተ ሰዎች እና ወዳጆች
- በአዲስ አበባ እና በአህጉረ ስብከት የሰማዕታት ቤተ ሰዎችን እያፈላለጉ የማጽናናት እና የመደገፍ መርሐ ግብር ይካሔዳል
- ከሊቢያው የግፍ ተግባር ጋራ በተያያዘ ባሉ ኹኔታዎች ላይ በየዕለቱ እየተሰበሰበ በመምከር መልእክት ለማስተላለፍ የወሰነው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም መግለጫ ይሰጣል

