ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት
ዛሬ የዓለም መገናኛ ብዙኃን የ30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በኢስላሚክ ስቴት በሰማዕትነት መገደል ሲዘግቡ ነበር፡፡ ሰው በእምነቱ ብቻ ሰማዕትነት የሚከፍልበት ዘመነ ሰማዕታት አንደገና ታድሶ እየተነሣ ነው፡፡ ትናንት ግብጻውያን ምእመናን የከፈሉትን ሰማዕትነት ዛሬ ኢትዮጵያውያኑ ከፍለውታል፡፡ ክርስቲያን መሆን ወንጀል ሆኖ፡፡ ሰማዕታቱስ ወደሚወዱት ጌታ ሄደዋል፡፡ ይህ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የሚፈተኑበት ጊዜ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥትና የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለግብጽ ሰማዕታት ያደረጉትን በቅርብ ዓይተናል፡፡ የኛዎቹ በሚዛን የሚመዘኑበት ወይ ቀልለው ወይም ከብደው የሚገኙበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ እግዚአብሔር ከሰማዕታቱ በረከት ይክፈለን፡፡